text stringlengths 4 267 |
|---|
ጻድቅ ግን እንደ ዘንባባ ዛፍ ይለመልማል፤እንደ አርዘ ሊባኖስም ትልቅ ይሆናል። |
በይሖዋ ቤት፣ ተተክለዋል፤በአምላካችን ቅጥር ግቢዎች ያብባሉ። |
ባረጁ ጊዜም እንኳ ማበባቸውን ይቀጥላሉ፤እንደበረቱና እንደጠነከሩ ይኖራሉ፤ |
ይሖዋ ትክክለኛ እንደሆነ እያወጁ ይኖራሉ። እሱ ዓለቴ ነው፤ በእሱም ዘንድ ክፋት የለም። |
አምላክ ሆይ፣ ዝም አትበል፤አምላክ ሆይ፣ ጸጥ አትበል፤ ደግሞም ጭጭ አትበል። |
እነሆ፣ ጠላቶችህ እየደነፉ ነውና፤አንተን የሚጠሉ በእብሪት ይመላለሳሉ። |
በስውር በሕዝቦችህ ላይ የተንኮል ሴራ ይሸርባሉ፤በውድ አገልጋዮችህ ላይ ይዶልታሉ። |
“የእስራኤል ስም ተረስቶ እንዲቀር፣ኑ፣ ሕዝቡን እንደምስስ” ይላሉ። |
የጋራ ዕቅድ ይነድፋሉ፤በአንተ ላይ ግንባር ፈጥረዋል፤ |
የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣ ሞዓብና አጋራውያን፣ |
ጌባል፣ አሞንና አማሌቅ፣እንዲሁም ፍልስጤም ከጢሮስ ነዋሪዎች ጋር አበሩ። |
አሦርም ከእነሱ ጋር ተባብሯል፤ለሎጥ ልጆችምድጋፍ ይሰጣሉ። (ሴላ) |
በምድያም እንዳደረግከው፣በቂሾንም ጅረት በሲሳራና በያቢን ላይ እንዳደረግከው አድርግባቸው። |
እነሱ በኤንዶር ተደመሰሱ፤ለምድርም ፍግ ሆኑ። |
በመካከላቸው ያሉትን ታላላቅ ሰዎች እንደ ኦሬብና ዜብ፣አለቆቻቸውንም እንደ ዘባህና ጻልሙና አድርጋቸው፤ |
እነሱ “አምላክ የሚኖርባቸውን ቦታዎች እንውረስ” ብለዋልና። |
አምላኬ ሆይ፣ ነፋስ እያሽከረከረ እንደሚወስደው ኮሸሽላ፣ነፋስ እንደሚጠርገው ገለባ አድርጋቸው። |
ጫካን እንደሚያቃጥል እሳት፣ተራሮችን እንደሚያነድ ነበልባል፣ |
አንተም እንዲሁ በሞገድህ አሳዳቸው፤በአውሎ ነፋስህም አሸብራቸው። |
ይሖዋ ሆይ፣ ስምህን ይሹ ዘንድ፣ፊታቸውን በኀፍረት ሸፍን። |
ለዘላለም ይፈሩ፣ ይሸበሩም፤ውርደት ይከናነቡ፤ ደግሞም ይጥፉ፤ |
ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣አዎ፣ አንተ ብቻ በመላው ምድር ላይ ልዑል እንደሆንክ ሰዎች ይወቁ። |
አንተ ኃያል፣ መጥፎ በሆነው ተግባርህ የምትኩራራው ለምንድን ነው? የአምላክ ታማኝ ፍቅር ዘላቂ እንደሆነ አታውቅም? |
ምላስህ እንደ ምላጭ የተሳለ ነው፤ጥፋትን ይሸርባል፤ ተንኮልንም ያቀነባብራል። |
መልካም ከሆነው ነገር ይልቅ ክፋትን፣ትክክል የሆነውን ነገር ከመናገር ይልቅ ሐሰትን ትወዳለህ። (ሴላ) |
አንተ አታላይ ምላስ!ጎጂ ቃልን ሁሉ ትወዳለህ። |
በመሆኑም አምላክ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያንኮታኩትሃል፤መንጭቆ ይወስድሃል፤ ከድንኳንህም ጎትቶ ያወጣሃል፤ከሕያዋን ምድር ይነቅልሃል። (ሴላ) |
ጻድቃንም ይህን አይተው በፍርሃት ይዋጣሉ፤በእሱም ላይ ይስቃሉ። |
“እንዲህ ያለ ሰው አምላክን መጠጊያው አያደርግም፤ይልቁንም በታላቅ ሀብቱ ይታመናል፤ራሱ በሚጠነስሰውም ሴራ ይመካል።” |
እኔ ግን በአምላክ ቤት እንዳለ የለመለመ የወይራ ዛፍ እሆናለሁ፤ለዘላለም በአምላክ ታማኝ ፍቅር እታመናለሁ። |
እርምጃ ስለወሰድክ ለዘላለም አወድስሃለሁ፤መልካም ነውና፣ በታማኝ አገልጋዮችህ ፊትበስምህ ተስፋ አደርጋለሁ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ዳዊትን፣የደረሰበትንም መከራ ሁሉ አስታውስ፤ |
ለይሖዋ እንዴት እንደማለ፣ኃያል ለሆነው ለያዕቆብ አምላክ እንዴት እንደተሳለ አስብ፦ |
“ወደ ድንኳኔ፣ ወደ ቤቴ አልገባም። ወደ መኝታዬ፣ ወደ አልጋዬ አልወጣም፤ |
ዓይኖቼ እንዲያንቀላፉ፣ሽፋሽፍቶቼም እንዲያሸልቡ አልፈቅድም፤ |
ይህም ለይሖዋ ስፍራ፣ኃያል ለሆነው የያዕቆብ አምላክም ያማረ መኖሪያ እስከማገኝ ድረስ ነው።” |
እነሆ፣ በኤፍራታ ስለ እሷ ሰማን፤በጫካ በተሞላው ምድር አገኘናት። |
ወደ መኖሪያው እንግባ፤በእግሩ ማሳረፊያ ፊት እንስገድ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ፤አንተና የብርታትህ ታቦት፣ ወደ ማረፊያ ስፍራህ ሂዱ። |
ካህናትህ ጽድቅን ይልበሱ፤ታማኝ አገልጋዮችህም እልል ይበሉ። |
ለአገልጋይህ ለዳዊት ስትል፣የቀባኸውን ሰው ገሸሽ አታድርግ። |
ይሖዋ ለዳዊት ምሏል፤የገባውን ቃል ፈጽሞ አያጥፍም፦ “ከዘሮችህ መካከል አንዱንበዙፋንህ ላይ አስቀምጣለሁ። |
ወንዶች ልጆችህ ቃል ኪዳኔንናየማስተምራቸውን ማሳሰቢያዎች ቢጠብቁ፣የእነሱም ልጆችለዘላለም በዙፋንህ ላይ ይቀመጣሉ።” |
ይሖዋ ጽዮንን መርጧታልና፤የራሱ መኖሪያ እንድትሆን ፈልጓል፤ እንዲህም ብሏል፦ |
“ይህች ለዘላለም ማረፊያ ስፍራዬ ነች፤በእሷ እኖራለሁ፤ ይህ ምኞቴ ነውና። |
የተትረፈረፈ የምግብ አቅርቦት እንዲኖራት በማድረግ እባርካታለሁ፤ድሆቿን እህል አጠግባለሁ። |
ካህናቷ መዳንን እንዲለብሱ አደርጋለሁ፤ታማኝ ሕዝቦቿም እልል ይላሉ። |
በዚያ የዳዊትን ብርታት እጨምራለሁ። ለቀባሁት አገልጋዬ መብራት አዘጋጅቻለሁ። |
ጠላቶቹን ኀፍረት አከናንባለሁ፤በራሱ ላይ ያለው አክሊል ግን ያብባል።” |
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣ በዚያ ተቀምጠን ነበር። ጽዮንን ባስታወስናት ጊዜ አለቀስን። |
በመካከሏ በሚገኙ የአኻያ ዛፎች ላይበገናዎቻችንን ሰቀልን። |
የማረኩን ሰዎች በዚያ እንድንዘምርላቸው ጠየቁን፤የሚያፌዙብን ሰዎች በመዝሙር እንድናዝናናቸው “ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ዘምሩልን” አሉን። |
የይሖዋን መዝሙርበባዕድ ምድር እንዴት ልንዘምር እንችላለን? |
ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አንቺን ብረሳ፣ቀኝ እጄ ትክዳኝ። |
ሳላስታውስሽ ብቀር፣ኢየሩሳሌምን ለደስታዬ ምክንያትከሆኑት ነገሮች በላይ ባላደርግ፣ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ትጣበቅ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀንኤዶማውያን ያሉትን አስታውስ፤ “አፍርሷት! ከሥረ መሠረቷ አፍርሷት!” ብለው ነበር። |
በቅርቡ የምትጠፊው አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣በእኛ ላይ በፈጸምሽው በዚያው ድርጊትብድራትሽን የሚመልስ ደስተኛ ይሆናል። |
ልጆችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጥደስተኛ ይሆናል። |
ይሖዋን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ። ታዲያ እንዴት እንዲህ ትሉኛላችሁ? “እንደ ወፍ ወደ ተራራህ ብረር! |
ክፉዎች ደጋናቸውን እንዴት እንደወጠሩ ተመልከት፤በጨለማ፣ ልበ ቀና የሆኑትን ለመውጋት፣ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል። |
መሠረቶቹ ከተናዱ፣ጻድቁ ሰው ምን ማድረግ ይችላል?” |
ይሖዋ ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደሱ ውስጥ ነው። የይሖዋ ዙፋን በሰማያት ነው። የገዛ ዓይኖቹ ይመለከታሉ፤ ንቁ የሆኑት ዓይኖቹ የሰው ልጆችን ይመረምራሉ። |
ይሖዋ ጻድቁንም ሆነ ክፉውን ይመረምራል፤ዓመፅን የሚወድን ማንኛውንም ሰው ይጠላል። |
በክፉዎች ላይ ወጥመድ ያዘንባል፤እሳትና ድኝ እንዲሁም የሚለበልብ ነፋስ ጽዋቸው ይሆናል። |
ይሖዋ ጻድቅ ነውና፤ የጽድቅ ሥራዎችን ይወዳል። ቅን የሆኑ ሰዎች ፊቱን ያያሉ። |
በልዑል አምላክ ሚስጥራዊ ቦታ የሚኖር ሰውሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ጥላ ሥር ይቀመጣል። |
ይሖዋን “አንተ መጠጊያዬና ምሽጌ፣የምታመንብህም አምላኬ ነህ” እለዋለሁ። |
እሱ ከወፍ አዳኙ ወጥመድ፣ከአውዳሚ ቸነፈርም ይታደግሃልና። |
በላባዎቹ ይከልልሃል፤በክንፎቹም ሥር መጠጊያ ታገኛለህ። ታማኝነቱ ትልቅ ጋሻና መከላከያ ቅጥር ይሆንልሃል። |
በሌሊት የሚያሸብሩ ነገሮችን፣በቀንም የሚወነጨፍ ፍላጻን አትፈራም፤ |
በጨለማ የሚያደባ ቸነፈርም ሆነበቀትር የሚረፈርፍ ጥፋት አያስፈራህም። |
በአጠገብህ ሺህ፣በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃሉ፤ወደ አንተ ግን አይደርስም። |
በክፉዎች ላይ የሚደርሰውን ቅጣት ትመለከታለህ፤በዓይንህ ብቻ ታየዋለህ። |
ምክንያቱም “ይሖዋ መጠጊያዬ ነው” ብለሃል፤ ልዑሉን አምላክ መኖሪያህ አድርገኸዋል፤ |
ምንም ዓይነት አደጋ አይደርስብህም፤አንዳችም መቅሰፍት ወደ ድንኳንህ አይጠጋም። |
በመንገድህ ሁሉ እንዲጠብቁህመላእክቱን ስለ አንተ ያዛልና። |
እግርህን እንቅፋት እንዳይመታውበእጃቸው ያነሱሃል። |
የአንበሳውን ግልገልና ጉበናውን ትረግጣለህ፤ደቦል አንበሳውንና ትልቁን እባብ ከእግርህ ሥር ትጨፈልቃለህ። |
አምላክ እንዲህ ብሏል፦ “ስለወደደኝ፣ እታደገዋለሁ። ስሜን ስለሚያውቅ እጠብቀዋለሁ። |
ይጠራኛል፤ እኔም እመልስለታለሁ። በተጨነቀ ጊዜ ከእሱ ጋር እሆናለሁ። እታደገዋለሁ እንዲሁም አከብረዋለሁ። |
ረጅም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤የማዳን ሥራዎቼንም እንዲያይ አደርገዋለሁ።” |
በክፉዎች አትበሳጭ፤ወይም በክፉ አድራጊዎች አትቅና። |
እንደ ሣር በፍጥነት ይደርቃሉ፤እንደለመለመ ተክልም ይጠወልጋሉ። |
በይሖዋ ታመን፤ መልካም የሆነውንም አድርግ፤በምድር ላይ ኑር፤ ለሰዎችም ታማኝ ሁን። |
በይሖዋ ሐሴት አድርግ፤እሱም የልብህን መሻት ይሰጥሃል። |
መንገድህን ለይሖዋ አደራ ስጥ፤በእሱ ታመን፤ እሱም ለአንተ ሲል እርምጃ ይወስዳል። |
ጽድቅህን እንደ ንጋት ብርሃን፣የአንተንም ፍትሕ እንደ ቀትር ፀሐይ ያበራዋል። |
በይሖዋ ፊት ዝም በል፤እሱንም በተስፋ ተጠባበቅ። የጠነሰሰውን ሴራበተሳካ ሁኔታ እየፈጸመ ባለ ሰው አትበሳጭ። |
ከቁጣ ተቆጠብ፤ ንዴትንም ተው፤ተበሳጭተህ ክፉ ነገር አትሥራ። |
ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፤ይሖዋን ተስፋ የሚያደርጉ ግን ምድርን ይወርሳሉ። |
ለጥቂት ጊዜ ነው እንጂ ክፉዎች አይኖሩም፤በቀድሞ ቦታቸው ትፈልጋቸዋለህ፤እነሱ ግን በዚያ አይገኙም። |
የዋሆች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤በብዙ ሰላምም እጅግ ደስ ይላቸዋል። |
ክፉ ሰው በጻድቁ ላይ ያሴራል፤በእሱ ላይ ጥርሱን ያፋጫል። |
ይሖዋ ግን ይስቅበታል፤የሚጠፋበት ቀን እንደሚደርስ ያውቃልና። |
ክፉዎች የተጨቆነውንና ድሃውን ለመጣል፣እንዲሁም ቀና የሆነውን መንገድ የሚከተሉትን ለማረድሰይፋቸውን ይመዛሉ፤ ደጋናቸውንም ይወጥራሉ። |
ሆኖም ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤ደጋኖቻቸው ይሰበራሉ። |
ብዙ ክፉ ሰዎች ካላቸው የተትረፈረፈ ሀብት ይልቅጻድቅ ሰው ያለው ጥቂት ነገር ይሻላል። |
የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፤ይሖዋ ግን ጻድቃንን ይደግፋል። |
ይሖዋ ነቀፋ የሌለባቸውን ሰዎች የሕይወት ጎዳና ያውቃል፤ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል። |
በአደጋ ወቅት ለኀፍረት አይዳረጉም፤በረሃብ ዘመን የተትረፈረፈ ምግብ ይኖራቸዋል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.