text
stringlengths
4
267
አታላይ ከሆኑ ሰዎች ጋር አልቀራረብም፤ማንነታቸውን ከሚደብቁም እርቃለሁ።
ከክፉ ሰዎች ጋር መሆን እጠላለሁ፤ከክፉዎችም ጋር መቀራረብ አልፈልግም።
ንጹሕ መሆኔን ለማሳየት እጆቼን እታጠባለሁ፤ይሖዋ ሆይ፣ መሠዊያህን እዞራለሁ፤
ይህም የምስጋናን ድምፅ አሰማ ዘንድ፣ድንቅ ሥራዎችህንም ሁሉ አውጅ ዘንድ ነው።
ይሖዋ ሆይ፣ የምትኖርበትን ቤት፣የክብርህንም ማደሪያ ቦታ እወዳለሁ።
ከኃጢአተኞች ጋር አታጥፋኝ፤ሕይወቴንም ከዓመፀኞች ጋር አታስወግድ፤
እጆቻቸው አሳፋሪ ድርጊት ይፈጽማሉ፤ቀኝ እጃቸውም በጉቦ የተሞላ ነው።
እኔ ግን ንጹሕ አቋሜን ጠብቄ እመላለሳለሁ። ታደገኝ፤ ሞገስም አሳየኝ።
እግሬ በደልዳላ ስፍራ ቆሟል፤በታላቅ ጉባኤ መካከል ይሖዋን አወድሳለሁ።
በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣በኃጢአተኞች መንገድ የማይቆም፣በፌዘኞችም ወንበር የማይቀመጥ ሰው ደስተኛ ነው።
ይልቁንም በይሖዋ ሕግ ደስ ይለዋል፤ሕጉንም በቀንና በሌሊት በለሆሳስ ያነበዋል።
በጅረቶች ዳር እንደተተከለ፣ፍሬውን በወቅቱ እንደሚሰጥ፣ቅጠሉም እንደማይጠወልግ ዛፍ ይሆናል። የሚሠራውም ሁሉ ይሳካለታል።
ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፤ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው።
ከዚህም የተነሳ ክፉዎች በፍርድ ፊት ለዘለቄታው አይቆሙም፤ኃጢአተኞችም በጻድቃን ጉባኤ ጸንተው አይቆሙም።
ይሖዋ የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፤የክፉዎች መንገድ ግን ይጠፋል።
የአምላክ ከተማ የተመሠረተችው በተቀደሱት ተራሮች ላይ ነው።
ይሖዋ ከያዕቆብ ድንኳኖች ሁሉ ይበልጥየጽዮንን በሮች ይወዳል።
የእውነተኛው አምላክ ከተማ ሆይ፣ ስለ አንቺ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች እየተነገሩ ነው። (ሴላ)
እኔን ከሚያውቁኝ መካከል ረዓብንና ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤ኢትዮጵያን ጨምሮ ፍልስጤምና ጢሮስም ይገኙበታል። እንዲህም ይባላል፦ “ይህ በዚያ የተወለደ ነው።”
ስለ ጽዮን ደግሞ እንዲህ ይባላል፦ “ይሄኛውም ሆነ ያኛው የተወለደው በእሷ ውስጥ ነው።” ልዑሉ አምላክም አጽንቶ ይመሠርታታል።
ይሖዋ ሕዝቡን ሲመዘግብ “ይህ በዚያ የተወለደ ነው” ብሎ ያስታውቃል። (ሴላ)
ዘማሪዎችና ጨፋሪዎች “ምንጮቼ ሁሉ በአንቺ ውስጥ ይገኛሉ” ይላሉ።
አምላክ ሆይ፣ ሟች የሆነ ሰው ጥቃት እየሰነዘረብኝ ስለሆነ ሞገስ አሳየኝ። ቀኑን ሙሉ ይዋጉኛል፤ ደግሞም ያስጨንቁኛል።
ጠላቶቼ ቀኑን ሙሉ እኔን ለመንከስ ይሞክራሉ፤ብዙዎች በእብሪት ተነሳስተው ይዋጉኛል።
ፍርሃት በሚሰማኝ ጊዜ በአንተ እታመናለሁ።
ቃሉን በማወድሰው አምላክ፣አዎ፣ በአምላክ እታመናለሁ፤ አልፈራም። ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
ቀኑን ሙሉ የእኔን ጉዳይ ለማበላሸት ይጥራሉ፤ሐሳባቸው እኔን መጉዳት ብቻ ነው።
እኔን ለማጥቃት ራሳቸውን ይሰውራሉ፤ሕይወቴን ለማጥፋት በመሻትእርምጃዬን አንድ በአንድ ይከታተላሉ።
ከክፋታቸው የተነሳ አስወግዳቸው። አምላክ ሆይ፣ ብሔራትን በቁጣህ አጥፋቸው።
ከቦታ ቦታ ስንከራተት አንድ በአንድ ትከታተላለህ። እንባዬን በአቁማዳህ አጠራቅም። ደግሞስ በመጽሐፍህ ውስጥ ሰፍሮ የለም?
እርዳታ ለማግኘት በምጣራበት ቀን ጠላቶቼ ያፈገፍጋሉ። አምላክ ከጎኔ እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ።
ቃሉን በማወድሰው አምላክ፣ቃሉን በማወድሰው በይሖዋ፣
አዎ፣ በአምላክ እታመናለሁ፤ አልፈራም። ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
አምላክ ሆይ፣ ለአንተ በተሳልኳቸው ስእለቶች የተነሳ ግዴታ ውስጥ ገብቻለሁ፤ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ።
አንተ ከሞት ታድገኸኛልና፤እግሮቼንም ከእንቅፋት አድነሃል፤ይህም በሕያዋን ብርሃን በአምላክ ፊት እመላለስ ዘንድ ነው።
ይሖዋን አመስግኑ፤ ስሙን ጥሩ፤ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!
ለእሱ ዘምሩ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩለት፤አስደናቂ በሆኑት ሥራዎቹ ሁሉ ላይ አሰላስሉ።
በቅዱስ ስሙ ተኩራሩ። ይሖዋን የሚፈልጉ ሰዎች፣ ልባቸው ሐሴት ያድርግ።
ይሖዋንና ብርታቱን ፈልጉ። ፊቱን ሁልጊዜ እሹ።
ያከናወናቸውን አስደናቂ ሥራዎች፣ተአምራቱንና የተናገረውን ፍርድ አስታውሱ፤
እናንተ የአገልጋዩ የአብርሃም ዘሮች፣እሱ የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች፣ ይህን አስታውሱ።
እሱ ይሖዋ አምላካችን ነው። ፍርዱ በመላው ምድር ላይ ነው።
ቃል ኪዳኑን ለዘላለም፣የገባውን ቃል እስከ ሺህ ትውልድ ያስታውሳል፤
ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣ለይስሐቅም በመሐላ የገባውን ቃል አይረሳም፤
ቃሉን ለያዕቆብ ድንጋጌ፣ለእስራኤልም ዘላቂ ቃል ኪዳን አድርጎ አቋቋመ፤
“የከነአንን ምድርርስትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ” አለ።
ይህን የተናገረው በቁጥር ጥቂት፣አዎ፣ በጣም ጥቂት በነበሩ ጊዜ ነው፤ በምድሪቱም ላይ የባዕድ አገር ሰዎች ነበሩ።
እነሱም ከአንዱ ብሔር ወደ ሌላው ብሔር፣ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው ሕዝብ ተንከራተቱ።
ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቀደም፤ይልቁንም ለእነሱ ሲል ነገሥታትን ገሠጸ፤
“የቀባኋቸውን አገልጋዮቼን አትንኩ፤በነቢያቴም ላይ አንዳች ክፉ ነገር አታድርጉ” አላቸው።
በምድሪቱ ላይ ረሃብን ጠራ፤የምግብ አቅርቦታቸው እንዲቋረጥ አደረገ።
ባሪያ እንዲሆን የተሸጠውን ሰው፣ ዮሴፍንከእነሱ አስቀድሞ ላከው።
እግሮቹን በእግር ብረት አሰሩ፤አንገቱም ብረት ውስጥ ገባ፤
የይሖዋ ቃል አጠራው፤ይህም የሆነው የተናገረው ቃል እስኪፈጸም ድረስ ነው።
ንጉሡ ልኮ አስፈታው፤የሕዝቦቹም ገዢ ነፃ አወጣው።
የቤቱ ጌታ አድርጎ ሾመው፤የንብረቱ ሁሉ ገዢ አደረገው፤
ይህም ደስ ባሰኘው መንገድ በመኳንንቱ ላይ እንዲሠለጥን፣ሽማግሌዎቹንም ጥበብ እንዲያስተምር ነው።
ከዚያም እስራኤል ወደ ግብፅ መጣ፤ያዕቆብም በካም ምድር የባዕድ አገር ሰው ሆኖ ኖረ።
አምላክ ሕዝቡ እየተባዛ እንዲሄድ አደረገ፤ከጠላቶቻቸው ይበልጥ ኃያላን አደረጋቸው፤
ሕዝቡን ይጠሉ ዘንድ፣በአገልጋዮቹም ላይ ያሴሩ ዘንድ የጠላቶቻቸው ልብ እንዲለወጥ ፈቀደ።
አገልጋዩን ሙሴን፣የመረጠውንም አሮንን ላከ።
እነሱም ምልክቶቹን በመካከላቸው፣ተአምራቱን በካም ምድር አደረጉ።
ጨለማን ላከ፤ ምድሪቱም ጨለመች፤እነሱ በቃሉ ላይ አላመፁም።
ውኃዎቻቸውን ወደ ደም ለወጠ፤ዓሣዎቻቸውንም ገደለ።
ምድራቸው፣ የነገሥታታቸውም እልፍኞች እንኳ ሳይቀሩበእንቁራሪቶች ተጥለቀለቁ።
ተናካሽ ዝንቦች እንዲወሯቸው፣ትንኞችም በግዛቶቻቸው ሁሉ እንዲርመሰመሱ አዘዘ።
በዝናባቸው ፋንታ በረዶ አወረደባቸው፤በምድራቸውም ላይ መብረቅ ላከ።
ወይናቸውንና የበለስ ዛፋቸውን መታ፤በግዛታቸው ውስጥ ያሉትንም ዛፎች አወደመ።
አንበጦች፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኩብኩባዎችምእንዲወሯቸው አዘዘ።
እነሱ በአገሪቱ የሚገኘውን አትክልት ሁሉ በሉ፤የምድሪቱንም ምርት ፈጁ።
ከዚያም በአገራቸው ያሉትን በኩራት ሁሉ፣የፍሬያቸው መጀመሪያ የሆኑትን መታ።
ሕዝቡ ብርና ወርቅ ይዞ እንዲወጣ አደረገ፤ከነገዶቹም መካከል የተሰናከለ አልነበረም።
በወጡ ጊዜ ግብፅ ሐሴት አደረገ፤እስራኤላውያንን እጅግ ፈርተዋቸው ነበርና።
እነሱን ለመሸፈን ደመናን ዘረጋ፤ በሌሊትም ብርሃን እንዲሰጥ እሳትን ላከ።
ሥጋ እንዲሰጣቸው በጠየቁት ጊዜ ድርጭት ላከላቸው፤ከሰማይም ምግብ እያወረደ ያጠግባቸው ነበር።
ዓለትን ሰነጠቀ፤ ውኃም ተንዶለዶለ፤በበረሃ እንደ ወንዝ ፈሰሰ።
ለአገልጋዩ ለአብርሃም የገባውን ቅዱስ ቃል አስታውሷልና።
ስለዚህ ሕዝቡን በታላቅ ደስታ፣የተመረጡ አገልጋዮቹንም በእልልታ አወጣቸው።
የሌሎችን ብሔራት ምድር ሰጣቸው፤እነሱም ሌሎች ሕዝቦች ለፍተው ያፈሩትን ወረሱ፤
ይህን ያደረገው ድንጋጌዎቹን እንዲጠብቁ፣ሕጎቹንም እንዲያከብሩ ነው። ያህን አወድሱ!
ይሖዋ ሆይ፣ ለምድርህ ሞገስ አሳይተሃል፤የተማረኩትን የያዕቆብ ልጆች መልሰሃል።
የሕዝብህን በደል ተውክ፤ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይቅር አልክ። (ሴላ)
ንዴትህን ሁሉ ገታህ፤ከብርቱ ቁጣህም ተመለስክ።
የመዳናችን አምላክ ሆይ፣ ወደ ቀድሞ ሁኔታችን መልሰን፤በእኛ የተነሳ ያደረብህን ቁጣም መልስ።
በእኛ ላይ የምትቆጣው ለዘላለም ነው? ቁጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ይዘልቃል?
ሕዝቦችህ በአንተ ሐሴት እንዲያደርጉ፣ዳግመኛ እንድናንሰራራ አታደርገንም?
ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህን አሳየን፤ማዳንህንም ለግሰን።
እውነተኛው አምላክ ይሖዋ የሚናገረውን እሰማለሁ፤እሱ ለሕዝቡና ለታማኝ አገልጋዮቹ ስለ ሰላም ይናገራልና፤ብቻ እንደቀድሞው በራሳቸው ከልክ በላይ አይተማመኑ።
ክብሩ በምድራችን እንዲኖር፣እሱን ለሚፈሩት ማዳኑ በእርግጥ ቅርብ ነው።
ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ይገናኛሉ፤ጽድቅና ሰላም ይሳሳማሉ።
ታማኝነት ከምድር ትበቅላለች፤ጽድቅም ከሰማያት ወደ ታች ይመለከታል።
አዎ፣ ይሖዋ መልካም ነገር ይሰጣል፤ምድራችንም ምርቷን ትሰጣለች።
ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤ለእርምጃውም መንገድ ያዘጋጃል።
ኃጢአት፣ ክፉውን ሰው በልቡ ውስጥ ሆኖ ያናግረዋል፤በዓይኖቹ ፊት አምላክን መፍራት የሚባል ነገር የለም።
ስህተቱ ምን እንደሆነ ተረድቶ የሠራውን ነገር እንዳይጠላው፣ለራሱ ባለው አመለካከት ራሱን እጅግ ይሸነግላልና።
ከአፉ የሚወጣው የክፋትና የሽንገላ ቃል ነው፤መልካም ነገር ለማድረግ ማስተዋል የለውም።
በአልጋው ላይ ሆኖ እንኳ ክፋትን ያውጠነጥናል። ጥሩ ባልሆነ መንገድ ላይ ይቆማል፤መጥፎ የሆነውን ነገር ገሸሽ አያደርግም።
ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ እስከ ሰማያት፣ታማኝነትህ እስከ ደመናት ይደርሳል።
ጽድቅህ ግርማ እንደተላበሱ ተራሮች ነው፤ፍርዶችህ እንደ ጥልቅ ባሕር ናቸው። ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ሰውንና እንስሳን ትጠብቃለህ።
አምላክ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ምንኛ ክቡር ነው! የሰው ልጆችበክንፎችህ ጥላ ሥር ይሸሸጋሉ።