text
stringlengths
4
267
ክፉዎች ግን ይጠፋሉ፤የይሖዋ ጠላቶች እንደ መስክ ውበት ይከስማሉ፤እንደ ጭስ ይበናሉ።
ክፉ ሰው ይበደራል፤ መልሶም አይከፍልም፤ጻድቅ ሰው ግን ለጋስ ነው፤ ደግሞም ይሰጣል።
አምላክ የባረካቸው ምድርን ይወርሳሉ፤እሱ የረገማቸው ግን ይጠፋሉ።
ይሖዋ በሰው መንገድ ደስ ሲሰኝ፣አካሄዱን ይመራለታል።
ቢወድቅም እንኳ አይዘረርም፤ይሖዋ እጁን ይዞ ይደግፈዋልና።
በአንድ ወቅት ወጣት ነበርኩ፤ አሁን ግን አርጅቻለሁ፤ይሁንና ጻድቅ ሰው ሲጣል፣ልጆቹም ምግብ ሲለምኑ አላየሁም።
ሁልጊዜ ሳይሰስት ያበድራል፤ልጆቹም በረከት ያገኛሉ።
ከክፉ ራቅ፤ መልካሙንም አድርግ፤ለዘላለምም ትኖራለህ።
ይሖዋ ፍትሕን ይወዳልና፤ታማኝ አገልጋዮቹንም አይተዋቸውም። ע [አይን] ምንጊዜም ጥበቃ ያገኛሉ፤የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።
የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤ምላሱም ስለ ፍትሕ ያወራል።
የአምላኩ ሕግ በልቡ አለ፤በሚሄድበት ጊዜም እግሮቹ አይብረከረኩም።
ክፉ ሰው ጻድቁን ለመግደልበዓይነ ቁራኛ ይከታተለዋል።
ይሖዋ ግን በክፉው እጅ አይጥለውም፤ወይም ለፍርድ በሚቀርብበት ጊዜ ጥፋት አያገኝበትም።
ይሖዋን ተስፋ አድርግ፤ መንገዱንም ተከተል፤እሱም ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ምድርንም ትወርሳለህ። ክፉዎች ሲጠፉ ታያለህ።
ጨካኝ የሆነውን ክፉ ሰው፣በበቀለበት መሬት ላይ እንደለመለመ ዛፍ ተንሰራፍቶ አየሁት።
ይሁንና ሕይወቱ በድንገት አለፈ፤ በቦታውም አልነበረም፤አጥብቄ ፈለግኩት፤ ላገኘው ግን አልቻልኩም።
ነቀፋ የሌለበትን ሰው ልብ በል፤ቀና የሆነውንም ሰው በትኩረት ተመልከት፤የዚህ ሰው የወደፊት ሕይወት ሰላማዊ ይሆናልና።
ኃጢአተኞች ሁሉ ግን ይጠፋሉ፤ክፉዎች ምንም ተስፋ አይኖራቸውም።
ጻድቃን መዳን የሚያገኙት ከይሖዋ ነው፤በጭንቅ ጊዜ መሸሸጊያቸው እሱ ነው።
ይሖዋ ይረዳቸዋል፤ ይታደጋቸዋልም። እሱን መጠጊያ ስላደረጉ፣ከክፉዎች ይታደጋቸዋል፤ ደግሞም ያድናቸዋል።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መኖሪያችን ሆነሃል።
ተራሮች ሳይወለዱ፣ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣ከዘላለም እስከ ዘላለም አንተ አምላክ ነህ።
ሟች የሆነ ሰው ወደ አፈር እንዲመለስ ታደርጋለህ፤“የሰው ልጆች ሆይ፣ ወደ አፈር ተመለሱ” ትላለህ።
በአንተ ዘንድ ሺህ ዓመት፣ እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣እንደ አንድ ክፍለ ሌሊትም ነው።
ጠራርገህ ታስወግዳቸዋለህ፤ እንደ ሕልም ይጠፋሉ፤በማለዳ ሲታዩ እንደሚለመልም ሣር ናቸው።
ጠዋት ላይ ሣሩ ያቆጠቁጣል፤ ደግሞም ይለመልማል፤ምሽት ላይ ግን ጠውልጎ ይደርቃል።
በቁጣህ አልቀናልና፤ከታላቅ ቁጣህም የተነሳ ተሸብረናል።
በደላችንን በፊትህ ታኖራለህ፤የደበቅናቸው ነገሮች በፊትህ ብርሃን ተጋልጠዋል።
ከኃይለኛ ቁጣህ የተነሳ ዘመናችን ይመናመናል፤ዕድሜያችንም ሽው ብሎ ያልፋል።
የዕድሜያችን ርዝማኔ 70 ዓመት ነው፤ለየት ያለ ጥንካሬ ካለን ደግሞ 80 ዓመት ቢሆን ነው። ይህም በችግርና በሐዘን የተሞላ ነው፤ፈጥኖ ይነጉዳል፤ እኛም እናልፋለን።
የቁጣህን ኃይል መረዳት የሚችል ማን ነው? ቁጣህ፣ አንተ መፈራት የሚገባህን ያህል ታላቅ ነው።
ጥበበኛ ልብ ማግኘት እንችል ዘንድ፣ዕድሜያችንን እንዴት መቁጠር እንዳለብን አስተምረን።
ይሖዋ ሆይ፣ ተመለስ! ይህ ሁኔታ የሚቀጥለው እስከ መቼ ነው? ለአገልጋዮችህ ራራላቸው።
በሕይወት ዘመናችን ሁሉ እልል እንድንልና ሐሴት እንድናደርግ፣በማለዳ ታማኝ ፍቅርህን አጥግበን።
ባጎሳቆልከን ዘመን ልክ፣መከራም ባየንባቸው ዓመታት መጠን ሐሴት እንዲሰማን አድርገን።
አገልጋዮችህ ሥራህን ይዩ፤ልጆቻቸውም ግርማህን ይመልከቱ።
የአምላካችን የይሖዋ ሞገስ በእኛ ላይ ይሁን፤የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን። አዎ፣ የእጆቻችንን ሥራ ፍሬያማ አድርግልን።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተን እጣራለሁ። እኔን ለመርዳት ፈጥነህ ድረስልኝ። አንተን ስጣራ በትኩረት ስማኝ።
ጸሎቴ በአንተ ፊት እንደተዘጋጀ ዕጣን ይሁን፤የተዘረጉት እጆቼ ምሽት ላይ እንደሚቀርብ የእህል መባ ይሁኑ።
ይሖዋ ሆይ፣ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤በከንፈሮቼም በር ላይ ዘበኛ አቁም።
ከክፉ ሰዎች ጋር መጥፎ ድርጊት እንዳልፈጽም፣ልቤ ወደ ክፉ ነገር እንዲያዘነብል አትፍቀድ፤ጣፋጭ ከሆነው ምግባቸው አልቋደስ።
ጻድቅ ቢመታኝ፣ የታማኝ ፍቅር መግለጫ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፤ቢወቅሰኝ በራስ ላይ እንደሚፈስ ዘይት አድርጌ አየዋለሁ፤ራሴም ይህን ፈጽሞ እንቢ አይልም። መከራ በገጠማቸው ወቅትም እንኳ መጸለዬን እቀጥላለሁ።
ፈራጆቻቸው ከገደል አፋፍ ቢጣሉም፣ሕዝቡ ለምናገራቸው ቃላት ትኩረት ይሰጣል፤ ደስ የሚያሰኙ ናቸውና።
ሰው ሲያርስና ጓል ሲከሰክስ አፈሩ እንደሚበታተን ሁሉ፣አጥንቶቻችንም በመቃብር አፍ ላይ ተበታተኑ።
ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ። አንተን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ። ሕይወቴን አትውሰድ።
ከዘረጉብኝ ወጥመድ፣ክፉ አድራጊዎች ካስቀመጡብኝ አሽክላም ጠብቀኝ።
ክፉዎች አንድ ላይ የገዛ ወጥመዳቸው ውስጥ ይወድቃሉ፤እኔ ግን አንድም ነገር ሳይነካኝ አልፋለሁ።
ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
እስራኤል እንዲህ ይበል፦ “ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”
ከአሮን ቤት የሆኑ እንዲህ ይበሉ፦ “ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”
ይሖዋን የሚፈሩ እንዲህ ይበሉ፦ “ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።”
በተጨነቅኩ ጊዜ ያህን ተጣራሁ፤ያህም መለሰልኝ፤ ደህንነት ወደማገኝበት ስፍራም አመጣኝ።
ይሖዋ ከጎኔ ነው፤ አልፈራም። ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
ይሖዋ ረዳቴ ሆኖ ከጎኔ አለ፤የሚጠሉኝን ሰዎች በድል አድራጊነት እመለከታለሁ።
በሰው ከመታመን ይልቅ፣ይሖዋን መጠጊያ ማድረግ ይሻላል።
በመኳንንት ከመታመን ይልቅ፣ይሖዋን መጠጊያ ማድረግ ይሻላል።
ብሔራት ሁሉ ከበቡኝ፤እኔ ግን በይሖዋ ስምመከትኳቸው።
ከበቡኝ፤ አዎ፣ ዙሪያዬን ከበቡኝ፤እኔ ግን በይሖዋ ስምመከትኳቸው።
እንደ ንብ ከበቡኝ፤ሆኖም በእሳት እንደተያያዘ ቁጥቋጦ ወዲያውኑ ጠፉ። እኔም በይሖዋ ስምመከትኳቸው።
እወድቅ ዘንድ በኃይል ተገፋሁ፤ይሖዋ ግን ረዳኝ።
ያህ መጠለያዬና ብርታቴ ነው፤አዳኝም ሆኖልኛል።
በጻድቃን ድንኳኖች ውስጥ፣የሐሴትና የመዳን ድምፅ ይሰማል። የይሖዋ ቀኝ እጅ ኃይሉን ያሳያል።
የይሖዋ ቀኝ እጅ ከፍ ከፍ አለ፤የይሖዋ ቀኝ እጅ ኃይሉን ያሳያል።
የያህን ሥራዎች አስታውቅ ዘንድበሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም።
ያህ ጠንከር ያለ ተግሣጽ ሰጥቶኛል፤ሆኖም ለሞት አሳልፎ አልሰጠኝም።
የጽድቅን በሮች ክፈቱልኝ፤በዚያ ገብቼ ያህን አወድሳለሁ።
ይህ የይሖዋ በር ነው። ጻድቃን በዚያ በኩል ይገባሉ።
መልስ ስለሰጠኸኝናአዳኝ ስለሆንከኝ አወድስሃለሁ።
ግንበኞች የናቁት ድንጋይየማዕዘን ራስ ድንጋይ ሆነ።
ይህ የይሖዋ ሥራ ነው፤ለዓይናችንም ድንቅ ነው።
ይህ ይሖዋ የሠራው ቀን ነው፤በዚህ ቀን እንደሰታለን፤ ሐሴትም እናደርጋለን።
ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ እንድታድነን እንለምንሃለን! ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ድል አቀዳጀን!
በይሖዋ ስም የሚመጣው የተባረከ ነው፤በይሖዋ ቤት ሆነን እንባርካችኋለን።
ይሖዋ አምላክ ነው፤ብርሃን ይሰጠናል። ቅርንጫፎች በመያዝ ወደ በዓሉ ከሚጓዙት ጋር ተቀላቅላችሁእስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ ሂዱ።
አንተ አምላኬ ነህ፤ እኔም አወድስሃለሁ፤አምላኬ ሆይ፣ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።
ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
አምላክ ሆይ፣ ፍርዶችህን ለንጉሡ ስጥ፤ጽድቅህንም ለንጉሡ ልጅ አጎናጽፍ።
ስለ ሕዝብህ በጽድቅ ይሟገት፤ለተቸገሩ አገልጋዮችህም ፍትሕ ያስፍን።
ተራሮች ለሕዝቡ ሰላም ያምጡ፤ኮረብቶችም ጽድቅን ያስገኙ።
በሕዝቡ መካከል ላሉት ችግረኞች ጥብቅና ይቁም፤የድሃውን ልጆች ያድን፤ቀማኛውንም ይደምስሰው።
ፀሐይ ብርሃኗን እስከሰጠች፣ጨረቃም በሰማይ ላይ እስካለች ድረስ፣ከትውልድ እስከ ትውልድ አንተን ይፈሩሃል።
እሱ በታጨደ ሣር ላይ እንደሚዘንብ ዝናብ፣ምድርንም እንደሚያጠጣ ካፊያ ይወርዳል።
በእሱ ዘመን ጻድቅ ይለመልማል፤ጨረቃም በምትኖርበት ዘመን ሁሉ ሰላም ይበዛል።
ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፣ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ተገዢዎች ይኖሩታል።
በበረሃ የሚኖሩ ሰዎች በፊቱ ይሰግዳሉ፤ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።
የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ ግብር ያመጣሉ። የሳባና የሴባ ነገሥታት፣ ስጦታ ይሰጣሉ።
ነገሥታትም ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ፤ብሔራትም ሁሉ ያገለግሉታል።
እርዳታ ለማግኘት የሚጮኸውን ድሃ፣እንዲሁም ችግረኛውንና ረዳት የሌለውን ሁሉ ይታደጋልና።
ለችግረኛውና ለድሃው ያዝናል፤የድሆችንም ሕይወት ያድናል።
ከጭቆናና ከግፍ ይታደጋቸዋል፤ደማቸውም በዓይኖቹ ፊት ክቡር ነው።
ረጅም ዘመን ይኑር፤ የሳባም ወርቅ ይሰጠው። ስለ እሱም ሁልጊዜ ጸሎት ይቅረብ፤ቀኑንም ሙሉ ይባረክ።
በምድር ላይ እህል ይትረፈረፋል፤በተራሮችም አናት ላይ በብዛት ይኖራል። የንጉሡም ፍሬ እንደ ሊባኖስ ዛፎች ይንዠረገጋል፤በከተሞቹም ውስጥ ሰዎች በምድር ላይ እንዳሉ ዕፀዋት ያብባሉ።
ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ፀሐይም እስካለች ድረስ ስሙ ይግነን። ሰዎች በእሱ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያግኙ፤ብሔራት ሁሉ ደስተኛ ብለው ይጥሩት።
እሱ ብቻ አስደናቂ ነገሮችን የሚያደርገው፣የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይወደስ።
ክብራማ ስሙ ለዘላለም ይወደስ፤ምድርም ሁሉ በክብሩ ትሞላ። አሜን፣ አሜን።
የእሴይ ልጅ የዳዊት ጸሎቶች እዚህ ላይ አበቁ።
ይሖዋ ሆይ፣ በንጹሕ አቋም ተመላልሻለሁና ፍረድልኝ፤ያለምንም ማወላወል በይሖዋ ታምኛለሁ።
ይሖዋ ሆይ፣ መርምረኝ፤ ፈትነኝም፤በውስጤ ያለውን ሐሳብና ልቤን አጥራልኝ።
ታማኝ ፍቅርህ ምንጊዜም በፊቴ ነውና፤በእውነትህም እመላለሳለሁ።