text
stringlengths
4
267
ማስተዋልንና እውቀትን አስተምረኝ፤በትእዛዛትህ ታምኛለሁና።
መከራ ላይ ከመውደቄ በፊት፣ መንገድ ስቼ እሄድ ነበር፤አሁን ግን የተናገርከውን እጠብቃለሁ።
አንተ ጥሩ ነህ፤ ሥራህም ጥሩ ነው። ሥርዓትህን አስተምረኝ።
እብሪተኞች በውሸት ስሜን ያጎድፋሉ፤እኔ ግን በሙሉ ልቤ መመሪያዎችህን እጠብቃለሁ።
ልባቸው ደንዝዟል፤እኔ ግን ሕግህን እወዳለሁ።
ሥርዓትህን እማር ዘንድበመከራ ውስጥ ማለፌ ጥሩ ሆነልኝ።
አንተ ያወጅከው ሕግ ጠቅሞኛል፤ለእኔ ከብዙ ወርቅና ብር እጅግ የተሻለ ነው።
እጆችህ ሠሩኝ፤ ደግሞም አበጁኝ። ትእዛዛትህን እማር ዘንድማስተዋል ስጠኝ።
አንተን የሚፈሩ ሰዎች እኔን አይተው ሐሴት ያደርጋሉ፤ቃልህ ተስፋዬ ነውና።
ይሖዋ ሆይ፣ ፍርዶችህ በጽድቅ ላይ የተመሠረቱ እንደሆኑናከታማኝነትህ የተነሳ እንደቀጣኸኝ አውቃለሁ።
ለአገልጋይህ በገባኸው ቃል መሠረት፣እባክህ፣ ታማኝ ፍቅርህ ያጽናናኝ።
በሕይወት መኖሬን እንድቀጥል ምሕረት አሳየኝ፤ሕግህን እወዳለሁና።
እብሪተኞች ኀፍረት ይከናነቡ፤ያላንዳች ምክንያት በድለውኛልና። እኔ ግን በመመሪያዎችህ ላይ አሰላስላለሁ።
አንተን የሚፈሩ፣ ማሳሰቢያዎችህንም የሚያውቁ፣ወደ እኔ ይመለሱ።
ለኀፍረት እንዳልዳረግ፣ልቤ ነቀፋ በሌለበት መንገድ ሥርዓትህን ይከተል።
ማዳንህን እናፍቃለሁ፤ቃልህ ተስፋዬ ነውና።
አንተ የተናገርከው ቃል ሲፈጸም ለማየት ዓይኖቼ ይጓጓሉ፤“የምታጽናናኝ መቼ ነው?” እያልኩ እጠይቃለሁ።
ጭስ እንዳደረቀው አቁማዳ ሆኛለሁና፤ሆኖም ሥርዓትህን አልረሳም።
ባሪያህ በሕይወት የሚቆየው እስከ መቼ ነው? ስደት በሚያደርሱብኝ ላይ የምትፈርደው መቼ ነው?
ሕግህን የሚጥሱእብሪተኛ ሰዎች እኔን ለማጥመድ ጉድጓድ ይቆፍራሉ።
ትእዛዛትህ ሁሉ አስተማማኝ ናቸው። ሰዎች ያለምክንያት ያሳድዱኛል፤ አቤቱ እርዳኝ!
ከምድር ገጽ ሊያጠፉኝ ምንም ያህል አልቀራቸውም ነበር፤እኔ ግን መመሪያዎችህን አልተውኩም።
የተናገርካቸውን ማሳሰቢያዎች እጠብቅ ዘንድ፣ከታማኝ ፍቅርህ የተነሳ በሕይወት አቆየኝ።
ይሖዋ ሆይ፣ ቃልህ በሰማያት፣ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
ታማኝነትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው። ምድር ለዘለቄታው እንድትኖር በጽኑ መሠረትካት።
በፍርዶችህ መሠረት እስከ ዛሬ ጸንተው ኖረዋል፤ሁሉም አገልጋዮችህ ናቸውና።
ሕግህን ባልወድ ኖሮ፣በደረሰብኝ ጉስቁልና በጠፋሁ ነበር።
መመሪያዎችህን ፈጽሞ አልረሳም፤ምክንያቱም በእነሱ አማካኝነት በሕይወት አቆይተኸኛል።
እኔ የአንተ ነኝ፤መመሪያዎችህን ፈልጌአለሁና አድነኝ።
ክፉዎች እኔን ለማጥፋት ያደባሉ፤እኔ ግን ለማሳሰቢያዎችህ ትኩረት እሰጣለሁ።
ፍጽምና ሁሉ ገደብ እንዳለው አይቻለሁ።ትእዛዝህ ግን ገደብ የለውም።
ሕግህን ምንኛ ወደድኩ! ቀኑን ሙሉ አሰላስለዋለሁ።
ትእዛዝህ ለዘላለም ስለማይለየኝ፣ከጠላቶቼ ይበልጥ ጥበበኛ ያደርገኛል።
በማሳሰቢያዎችህ ላይ ስለማሰላስል፣ከአስተማሪዎቼ ሁሉ የበለጠ ጥልቅ ማስተዋል አለኝ።
መመሪያዎችህን ስለማከብር፣ከሽማግሌዎች ይበልጥ በማስተዋል እመላለሳለሁ።
ቃልህን እጠብቅ ዘንድ፣በየትኛውም ክፉ መንገድ ከመሄድ እቆጠባለሁ።
አንተ አስተምረኸኛልና፣ከፍርዶችህ ፈቀቅ አልልም።
የተናገርከው ነገር ለምላሴ እጅግ ጣፋጭ ነው፤ለአፌም ከማር የበለጠ ይጥማል!
ከመመሪያዎችህ የተነሳ በማስተዋል እመላለሳለሁ። ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ እጠላለሁ።
ቃልህ ለእግሬ መብራት፣ለመንገዴም ብርሃን ነው።
የጽድቅ ፍርዶችህን ለመጠበቅ ምያለሁ፤ደግሞም እፈጽመዋለሁ።
ከፍተኛ ጉስቁልና ደርሶብኛል። ይሖዋ ሆይ፣ በቃልህ መሠረት በሕይወት አቆየኝ።
ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ በፈቃደኝነት የማቀርበውን የውዳሴ መባ በደስታ ተቀበል፤ፍርዶችህንም አስተምረኝ።
ሕይወቴ ሁልጊዜ አደጋ ላይ ናት፤እኔ ግን ሕግህን አልረሳሁም።
ክፉዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤እኔ ግን ከመመሪያዎችህ ዝንፍ አላልኩም።
ማሳሰቢያዎችህ ልቤን ደስ ስለሚያሰኙ፣ቋሚ ንብረቴ አደርጋቸዋለሁ።
ሥርዓትህን በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣እስከ መጨረሻው ለመጠበቅ ቆርጫለሁ።
በግማሽ ልብ የሚመላለሱትን እጠላለሁ፤ሕግህን ግን እወዳለሁ።
አንተ መጠለያዬና ጋሻዬ ነህ፤ቃልህ ተስፋዬ ነውና።
እናንተ ክፉዎች፣የአምላኬን ትእዛዛት መጠበቅ እንድችል ከእኔ ራቁ።
በሕይወት እንድቀጥልቃል በገባኸው መሠረት ደግፈኝ፤ተስፋዬ ሳይፈጸም ቀርቶ እንዳዝን አትፍቀድ።
እድን ዘንድ ደግፈኝ፤ያን ጊዜ ለሥርዓትህ ዘወትር ትኩረት እሰጣለሁ።
ከሥርዓትህ የሚርቁትን ሁሉ ገሸሽ ታደርጋቸዋለህ፤ውሸታሞችና አታላዮች ናቸውና።
በምድር ላይ ያሉ ክፉዎችን ሁሉ ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ ታስወግዳቸዋለህ። ስለዚህ ማሳሰቢያዎችህን እወዳለሁ።
አንተን እጅግ ከመፍራቴ የተነሳ ሰውነቴ ይንቀጠቀጣል፤ፍርዶችህን እፈራለሁ።
ትክክልና ጽድቅ የሆነውን አድርጌአለሁ። ለሚጨቁኑኝ አሳልፈህ አትስጠኝ!
ለአገልጋይህ ደህንነት ዋስትና ስጥ፤እብሪተኞች እንዲጨቁኑኝ አትፍቀድ።
ዓይኖቼ ማዳንህንናየገባኸውን የጽድቅ ቃል በመጠባበቅ ደከሙ።
ለአገልጋይህ ታማኝ ፍቅርህን አሳየው፤ሥርዓትህንም አስተምረኝ።
እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ማሳሰቢያዎችህን እንዳውቅ ማስተዋል ስጠኝ።
ይሖዋ ሆይ፣ እርምጃ የምትወስድበት ጊዜ ደርሷል፤ሰዎች ሕግህን ጥሰዋልና።
ስለዚህ እኔ ትእዛዛትህን ከወርቅ፣ምርጥ ከሆነ ወርቅ ይበልጥ እወዳለሁ።
በመሆኑም የምታስተምረው ትምህርት በሙሉ ትክክል እንደሆነ አምናለሁ፤የሐሰትን መንገድ ሁሉ እጠላለሁ።
ማሳሰቢያዎችህ ድንቅ ናቸው። ስለዚህ እጠብቃቸዋለሁ።
አንተ የምትገልጣቸው ቃላት ብርሃን ይፈነጥቃሉ፤ተሞክሮ የሌላቸውን አስተዋዮች ያደርጋሉ።
ትእዛዛትህን ለመስማት ከመጓጓቴ የተነሳአፌን ከፍቼ በረጅሙ እተነፍሳለሁ።
ስምህን ለሚወዱ ሰዎች ከምትሰጠው ፍርድ ጋር በሚስማማ መንገድ፣ወደ እኔ ተመለስ፤ ሞገስም አሳየኝ።
በቃልህ መሠረት አካሄዴን በሰላም ምራ፤ማንኛውም ክፉ ነገር በእኔ ላይ አይሠልጥን።
ጨቋኝ ከሆኑ ሰዎች ታደገኝ፤እኔም መመሪያዎችህን እጠብቃለሁ።
በአገልጋይህ ላይ ፊትህን አብራ፤ሥርዓትህንም አስተምረኝ።
ሰዎች ሕግህን ስለማያከብሩእንባ ከዓይኖቼ እንደ ውኃ ፈሰሰ።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ጻድቅ ነህ፤ፍርዶችህም ትክክል ናቸው።
የምትሰጣቸው ማሳሰቢያዎች በጽድቅ ላይ የተመሠረቱናሙሉ በሙሉ አስተማማኝ ናቸው።
ጠላቶቼ ቃልህን ስለረሱቅንዓቴ ይበላኛል።
ቃልህ እጅግ የጠራ ነው፤አገልጋይህም ይወደዋል።
እኔ በሌሎች ዘንድ የተናቅኩና የማልረባ ነኝ፤ሆኖም መመሪያዎችህን አልረሳሁም።
ጽድቅህ የዘላለም ጽድቅ ነው፤ሕግህም እውነት ነው።
ጭንቀትና ችግር ቢደርስብኝምትእዛዛትህን ምንጊዜም እወዳለሁ።
ማሳሰቢያህ ለዘላለም ጽድቅ ነው። በሕይወት መኖሬን እንድቀጥል ማስተዋል ስጠኝ።
በሙሉ ልቤ እጣራለሁ። ይሖዋ ሆይ፣ መልስልኝ። ሥርዓትህን እጠብቃለሁ።
አንተን እጣራለሁ፤ አቤቱ አድነኝ! ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ።
ጎህ ሳይቀድ ተነስቼ እርዳታ ለማግኘት እጮኻለሁ፤ቃልህ ተስፋዬ ነውና።
በተናገርከው ቃል ላይ ማሰላሰል እንድችል፣ክፍለ ሌሊቶቹ ከማብቃታቸው በፊት እነቃለሁ።
ከታማኝ ፍቅርህ የተነሳ ድምፄን ስማ። ይሖዋ ሆይ፣ ከአንተ ፍትሕ ጋር በሚስማማ መንገድ በሕይወት አቆየኝ።
አሳፋሪ በሆነ ድርጊት የተጠመዱ ሰዎች ወደ እኔ ቀርበዋል፤ከሕግህም ርቀዋል።
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ቅርብ ነህ፤ትእዛዛትህም ሁሉ እውነት ናቸው።
በቀድሞው ዘመን ስለ ማሳሰቢያዎችህ ተምሬአለሁ፤ለዘላለም ይጸኑ ዘንድ እንደመሠረትካቸው ተረድቻለሁ።
የደረሰብኝን ጉስቁልና ተመልከት፤ ደግሞም ታደገኝ፤ሕግህን አልረሳሁምና።
ተሟገትልኝ፤ ደግሞም ታደገኝ፤በገባኸው ቃል መሠረት በሕይወት አቆየኝ።
ክፉዎች ሥርዓትህን ስላልፈለጉመዳን ከእነሱ ርቋል።
ይሖዋ ሆይ፣ ምሕረትህ ታላቅ ነው። ከአንተ ፍትሕ ጋር በሚስማማ መንገድ በሕይወት አቆየኝ።
አሳዳጆቼና ጠላቶቼ ብዙ ናቸው፤እኔ ግን ከማሳሰቢያዎችህ ፈቀቅ አላልኩም።
ከዳተኛ የሆኑ ሰዎችን ተጸየፍኩ፤ምክንያቱም አንተ የተናገርከውን አይጠብቁም።
መመሪያዎችህን ምን ያህል እንደምወድ ተመልከት! ይሖዋ ሆይ፣ ከታማኝ ፍቅርህ የተነሳ በሕይወት አቆየኝ።
የቃልህ ፍሬ ነገር እውነት ነው፤በጽድቅ ላይ የተመሠረተው ፍርድህ ሁሉ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
መኳንንት ያለምክንያት ያሳድዱኛል፤ልቤ ግን ለቃልህ ጥልቅ አክብሮት አለው።
ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው፣እኔም አንተ በተናገርከው ነገር ሐሴት አደርጋለሁ።
ውሸትን እጠላለሁ፤ ደግሞም እጸየፈዋለሁ፤ሕግህን ግን እወዳለሁ።
በጽድቅ ላይ ከተመሠረቱት ፍርዶችህ የተነሳበቀን ሰባት ጊዜ አወድስሃለሁ።
ሕግህን የሚወዱ ብዙ ሰላም አላቸው፤ሊያደናቅፋቸው የሚችል ምንም ነገር የለም።