text stringlengths 4 267 |
|---|
ይሖዋ ሆይ፣ የማዳን ሥራህን ተስፋ አደርጋለሁ፤ትእዛዛትህንም እፈጽማለሁ። |
ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ፤ደግሞም እጅግ እወዳቸዋለሁ። |
መመሪያዎችህንና ማሳሰቢያዎችህን እጠብቃለሁ፤የማደርገውን ነገር ሁሉ ታውቃለህና። |
ይሖዋ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት የማሰማው ጩኸት ወደ አንተ ይድረስ። እንደ ቃልህ ማስተዋል ስጠኝ። |
ሞገስ ለማግኘት የማቀርበው ልመና ወደ አንተ ይድረስ። ቃል በገባኸው መሠረት አድነኝ። |
ሥርዓትህን ስለምታስተምረኝከንፈሮቼ ውዳሴን ያፍልቁ። |
አንደበቴ ስለተናገርከው ቃል ይዘምር፤ትእዛዛትህ ሁሉ ጽድቅ ናቸውና። |
መመሪያዎችህን ለመታዘዝ ስለምመርጥ፣እጅህ እኔን ለመርዳት ዝግጁ ይሁን። |
ይሖዋ ሆይ፣ ማዳንህን እናፍቃለሁ፤ሕግህንም እወዳለሁ። |
አወድስህ ዘንድ በሕይወት ልኑር፤አንተ ያወጣሃቸው ፍርዶች ይርዱኝ። |
እንደጠፋ በግ ተቅበዘበዝኩ። አገልጋይህን ፈልገው፤ትእዛዛትህን አልረሳሁምና። |
አምላክ ሆይ፣ እንደ ታማኝ ፍቅርህ መጠን ሞገስ አሳየኝ። እንደ ታላቅ ምሕረትህ መተላለፌን ደምስስ። |
ከበደሌ ሙሉ በሙሉ እጠበኝ፤ከኃጢአቴም አንጻኝ። |
መተላለፌን በሚገባ አውቃለሁና፤ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነው። |
አንተን፣ አዎ ከማንም በላይ አንተን በደልኩ፤በአንተ ዓይን ክፉ የሆነውን ነገር ፈጸምኩ። ስለዚህ አንተ በምትናገርበት ጊዜ ጻድቅ ነህ፤በምትፈርድበት ጊዜም ትክክል ነህ። |
እነሆ፣ በደለኛ ሆኜ ተወለድኩ፤እናቴም በኃጢአት ፀነሰችኝ። |
ከልብ የመነጨ እውነት ደስ ያሰኝሃል፤ልቤን እውነተኛ ጥበብ አስተምረው። |
ንጹሕ እሆን ዘንድ በሂሶጵ ከኃጢአቴ አንጻኝ፤ከበረዶም የበለጠ እነጣ ዘንድ እጠበኝ። |
ያደቀቅካቸው አጥንቶች ደስ እንዲላቸው፣የደስታንና የሐሴትን ድምፅ አሰማኝ። |
ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ፤የፈጸምኳቸውንም ስህተቶች ሁሉ አስወግድ። |
አምላክ ሆይ፣ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤በውስጤም ጽኑ የሆነ አዲስ መንፈስ አኑር። |
ከፊትህ አትጣለኝ፤ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ አትውሰድ። |
የአንተ ማዳን የሚያስገኘውን ደስታ መልስልኝ፤አንተን የመታዘዝ ፍላጎት በውስጤ እንዲቀሰቀስ አድርግ። |
ኃጢአተኞች ወደ አንተ እንዲመለሱ፣ለሕግ ተላላፊዎች መንገድህን አስተምራለሁ። |
አምላክ ሆይ፣ የመዳኔ አምላክ፣ አንደበቴ ጽድቅህን በደስታ ያስታውቅ ዘንድየደም ባለዕዳ ከመሆን አድነኝ። |
ይሖዋ ሆይ፣ አፌ ምስጋናህን እንዲያውጅከንፈሮቼን ክፈት። |
መሥዋዕት እንዲቀርብልህ አትፈልግምና፤ ቢሆንማ ኖሮ ባቀረብኩልህ ነበር፤ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አያስደስትህም። |
አምላክን የሚያስደስተው መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤አምላክ ሆይ፣ የተሰበረንና የተደቆሰን ልብ ችላ አትልም። |
በበጎ ፈቃድህ ለጽዮን መልካም ነገር አድርግላት፤የኢየሩሳሌምን ግንቦች ገንባ። |
በዚያን ጊዜ የጽድቅ መሥዋዕቶች፣የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችና ሙሉ በሙሉ የሚቀርቡ መባዎች ደስ ያሰኙሃል፤በዚያን ጊዜ ኮርማዎች በመሠዊያህ ላይ ይቀርባሉ። |
የበቀል አምላክ፣ ይሖዋ ሆይ፣የበቀል አምላክ ሆይ፣ ብርሃንህን አብራ! |
የምድር ፈራጅ ሆይ፣ ተነስ። ለትዕቢተኞች የሚገባቸውን ብድራት ክፈላቸው። |
ክፉዎች እስከ መቼ፣ ይሖዋ ሆይ፣ክፉዎች እስከ መቼ ድረስ ይፈነጥዛሉ? |
ይለፈልፋሉ፤ በእብሪት ይናገራሉ፤ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ስለ ራሳቸው ጉራ ይነዛሉ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን ያደቃሉ፤ርስትህንም ይጨቁናሉ። |
መበለቲቱንና ባዕዱን ሰው ይገድላሉ፤አባት የሌላቸውንም ልጆች ሕይወት ያጠፋሉ። |
“ያህ አያይም፤የያዕቆብ አምላክ አያስተውለውም” ይላሉ። |
እናንተ ማመዛዘን የጎደላችሁ ሰዎች፣ ይህን ልብ በሉ፤እናንተ ሞኞች፣ አስተዋዮች የምትሆኑት መቼ ነው? |
ጆሮን ያበጀው እሱ መስማት አይችልም? ወይስ ዓይንን የሠራው እሱ ማየት አይችልም? |
ብሔራትን የሚያርመው እሱ መውቀስ አይችልም? ለሰዎች እውቀት የሚሰጠው እሱ ነው! |
ይሖዋ የሰዎችን ሐሳብ ያውቃል፤ከንቱ እንደሆነም ይረዳል። |
ያህ ሆይ፣ አንተ የምታርመው፣ከሕግህ ላይ የምታስተምረው ሰው ደስተኛ ነው፤ |
ይህም ለክፉዎች ጉድጓድ እስኪቆፈር ድረስ፣በመከራ ወቅት ለእሱ ሰላም ትሰጠው ዘንድ ነው። |
ይሖዋ ሕዝቡን አይጥልምና፤ርስቱንም አይተውም። |
ፍርድ፣ ዳግመኛ ጽድቅ የሚንጸባረቅበት ይሆናልና፤ልበ ቅን የሆኑ ሰዎችም ሁሉ ይከተሉታል። |
ከክፉዎች ጋር የሚሟገትልኝ ማን ነው? ክፉ አድራጊዎችን በመቃወም ከጎኔ የሚቆም ማን ነው? |
ይሖዋ ረዳቴ ባይሆን ኖሮ፣በአጭር ጊዜ ውስጥ በጠፋሁ ነበር። |
“እግሬ አዳለጠኝ” ባልኩ ጊዜ፣ ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ደገፈኝ። |
በጭንቀት በተዋጥኩ ጊዜ፣አጽናናኸኝ፤ ደግሞም አረጋጋኸኝ። |
ምግባረ ብልሹ ገዢዎች በሕግ ስም ችግር ለመፍጠር እያሴሩ፣የአንተ ተባባሪ ሊሆኑ ይችላሉ? |
በጻድቁ ላይ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ይሰነዝራሉ፤በንጹሕ ሰው ላይ ሞት ይፈርዳሉ። |
ለእኔ ግን ይሖዋ አስተማማኝ መጠጊያ ይሆንልኛል፤አምላኬ መጠጊያ ዓለቴ ነው። |
ክፉ ሥራቸውን በላያቸው ይመልሳል፤ በገዛ ክፋታቸው ያጠፋቸዋል። ይሖዋ አምላካችን ያጠፋቸዋል። |
ያህን አወድሱ! ሁለንተናዬ ይሖዋን ያወድስ። |
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይሖዋን አወድሳለሁ። በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ። |
በመኳንንትም ሆነማዳን በማይችሉ ሰዎች አትታመኑ። |
መንፈሱ ትወጣለች፤ ወደ መሬት ይመለሳል፤በዚያው ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል። |
የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ፣በአምላኩ በይሖዋ ተስፋ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው፤ |
እሱ የሰማይ፣ የምድር፣የባሕርና በውስጣቸው ያሉት ነገሮች ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ደግሞም ለዘላለም ታማኝ ነው፤ |
ግፍ ለተፈጸመባቸው ፍትሕ ያሰፍናል፤ለተራቡት ምግብ ይሰጣል። ይሖዋ እስረኞችን ነፃ ያወጣል። |
ይሖዋ የዓይነ ስውራንን ዓይን ያበራል፤ይሖዋ ያጎነበሱትን ቀና ያደርጋል፤ይሖዋ ጻድቃንን ይወዳል። |
ይሖዋ የባዕድ አገር ሰዎችን ይጠብቃል፤አባት የሌለውን ልጅና መበለቲቱን ይደግፋል፤የክፉዎችን ዕቅድ ግን ያጨናግፋል። |
ይሖዋ ለዘላለም ይነግሣል፤ጽዮን ሆይ፣ አምላክሽ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይገዛል። ያህን አወድሱ! |
አምላክ ሆይ፣ በስምህ አድነኝ፤በኃይልህም ደግፈኝ። |
አምላክ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤ለአፌም ቃል ትኩረት ስጥ። |
ባዕዳን በእኔ ላይ ተነስተዋልና፤ጨካኝ ሰዎችም ሕይወቴን ይሻሉ። ስለ አምላክ ምንም ግድ የላቸውም። (ሴላ) |
እነሆ፣ አምላክ ረዳቴ ነው፤ይሖዋ እኔን ከሚደግፉ ጋር ነው። |
የገዛ ክፋታቸውን በጠላቶቼ ላይ ይመልስባቸዋል፤በታማኝነትህ አስወግዳቸው። |
ለአንተ በፈቃደኝነት መሥዋዕት አቀርባለሁ። ይሖዋ ሆይ፣ መልካም ነውና፣ ስምህን አወድሳለሁ። |
ከጭንቅ ሁሉ ያድነኛልና፤ጠላቶቼንም በድል አድራጊነት እመለከታለሁ። |
ንጉሡ አምላኬ ሆይ፣ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ለዘላለም ስምህን አወድሳለሁ። |
ቀኑን ሙሉ አወድስሃለሁ፤ለዘላለም ስምህን አወድሳለሁ። |
ይሖዋ ታላቅ ነው፤ እጅግ ሊወደስም ይገባዋል፤ታላቅነቱ አይመረመርም። |
ትውልዶች ሁሉ ሥራህን ያወድሳሉ፤ስላከናወንካቸው ታላላቅ ነገሮች ይናገራሉ። |
ታላቅ ውበት ስለተጎናጸፈው ግርማህ ይናገራሉ፤እኔም ስለ ድንቅ ሥራዎችህ አሰላስላለሁ። |
እጅግ አስደናቂ ስለሆነው ሥራህ ይናገራሉ፤እኔም ስለ ታላቅነትህ አውጃለሁ። |
የጥሩነትህን ብዛት ሲያስታውሱ በስሜት ያወራሉ፤ከጽድቅህም የተነሳ እልል ይላሉ። |
ይሖዋ ሩኅሩኅና መሐሪ፣እንዲሁም ለቁጣ የዘገየ ነው፤ ታማኝ ፍቅሩም ታላቅ ነው። |
ይሖዋ ለሁሉም ጥሩ ነው፤ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ይታያል። |
ይሖዋ ሆይ፣ ሥራዎችህ ሁሉ ከፍ ከፍ ያደርጉሃል፤ታማኝ አገልጋዮችህም ያወድሱሃል። |
የንግሥናህን ክብር ያውጃሉ፤ስለ ኃያልነትህም ይናገራሉ፤ |
ይህም ለሰዎች ታላላቅ ሥራዎችህንናየንግሥናህን ታላቅ ክብር ያስታውቁ ዘንድ ነው። |
ንግሥናህ ዘላለማዊ ነው፤ግዛትህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል። |
ይሖዋ ሊወድቁ የተቃረቡትን ሁሉ ይደግፋል፤ያጎነበሱትንም ሁሉ ቀና ያደርጋል። |
ዓይን ሁሉ አንተን በተስፋ ይመለከታል፤አንተም ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸዋለህ። |
አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታሟላለህ። |
ይሖዋ በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣በሥራውም ሁሉ ታማኝ ነው። |
ይሖዋ ለሚጠሩት ሁሉ፣በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። |
የሚፈሩትን ሰዎች ፍላጎት ያረካል፤እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትንም ጩኸት ይሰማል፤ ደግሞም ይታደጋቸዋል። |
ይሖዋ የሚወዱትን ሁሉ ይጠብቃል፤ክፉዎችን ሁሉ ግን ይደመስሳል። |
አፌ የይሖዋን ውዳሴ ያስታውቃል፤ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ ቅዱስ ስሙን ለዘላለም ያወድሱ። |
ይሖዋ ድምፄን፣እርዳታ ለማግኘት የማቀርበውን ልመና ስለሚሰማ እወደዋለሁ። |
ጆሮውን ወደ እኔ ያዘነብላልና፣በሕይወት እስካለሁ ድረስ እሱን እጣራለሁ። |
የሞት ገመዶች ተተበተቡብኝ፤መቃብር ያዘኝ። በጭንቀትና በሐዘን ተዋጥኩ። |
እኔ ግን የይሖዋን ስም ጠራሁ፦ “ይሖዋ ሆይ፣ ታደገኝ!” |
ይሖዋ ሩኅሩኅና ጻድቅ ነው፤አምላካችን መሐሪ ነው። |
ይሖዋ ተሞክሮ የሌላቸውን ይጠብቃል። ተስፋ ቆርጬ ነበር፤ እሱ ግን አዳነኝ። |
ነፍሴ ዳግመኛ እረፍት ታግኝ፤ይሖዋ ደግነት አሳይቶኛልና። |
እኔን ከሞት፣ ዓይኔን ከእንባ፣እግሬንም ከእንቅፋት ታድገሃል። |
በሕያዋን ምድር በይሖዋ ፊት እሄዳለሁ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.