text stringlengths 4 267 |
|---|
አመንኩ ስለዚህም ተናገርኩ፤እጅግ ተጎሳቁዬ ነበር። |
በጣም ደንግጬ “ሰው ሁሉ ውሸታም ነው” አልኩ። |
ላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉለይሖዋ ምን እመልስለታለሁ? |
የማዳንን ጽዋ አነሳለሁ፤የይሖዋንም ስም እጠራለሁ። |
በሕዝቡ ሁሉ ፊትስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ። |
የታማኝ አገልጋዮቹ ሞትበይሖዋ ዓይን ከባድ ነገር ነው። |
ይሖዋ ሆይ፣እኔ አገልጋይህ ስለሆንኩ እለምንሃለሁ። እኔ የሴት ባሪያህ ልጅ፣ አገልጋይህ ነኝ። አንተ ከእስራቴ ነፃ አውጥተኸኛል። |
ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ፤የይሖዋን ስም እጠራለሁ። |
በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ስእለቴን ለይሖዋ እፈጽማለሁ፤ |
በይሖዋ ቤት ቅጥር ግቢዎች፣በኢየሩሳሌም መካከል ስእለቴን አቀርባለሁ። ያህን አወድሱ! |
ያህን አወድሱ! ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤በታማኝ አገልጋዮች ጉባኤ መካከል አወድሱት። |
እስራኤል በታላቅ ሠሪው ሐሴት ያድርግ፤የጽዮን ልጆች በንጉሣቸው ደስ ይበላቸው። |
ስሙን በሽብሸባ ያወድሱ፤በአታሞና በበገና የውዳሴ መዝሙር ይዘምሩለት። |
ይሖዋ በሕዝቡ ደስ ይሰኛልና። እሱ የዋሆችን በማዳን ውበት ያጎናጽፋቸዋል። |
ታማኝ አገልጋዮቹ በክብር ሐሴት ያድርጉ፤በመኝታቸው ላይ ሆነው እልል ይበሉ። |
አንደበታቸው አምላክን የሚያወድስ መዝሙር ይዘምር፤እጃቸውም በሁለቱም በኩል የተሳለ ሰይፍ ይያዝ፤ |
ይህም በብሔራት ላይ የበቀል እርምጃ እንዲወስዱ፣ሕዝቦችንም እንዲቀጡ፣ |
ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣በመካከላቸው ያሉትን ታላላቅ ሰዎችም በእግር ብረት እንዲያስሩ፣ |
ደግሞም በእነሱ ላይ የተላለፈውን በጽሑፍ የሰፈረ ፍርድ እንዲፈጽሙ ነው። ታማኝ አገልጋዮቹ ሁሉ ይህ ክብር ይገባቸዋል። ያህን አወድሱ! |
ያህን አወድሱ! አምላክን በተቀደሰ ስፍራው አወድሱት። ብርታቱን በሚያሳየው ጠፈር አወድሱት። |
ስለ ብርቱ ሥራዎቹ አወድሱት። ወደር የለሽ ስለሆነው ታላቅነቱ አወድሱት። |
በቀንደ መለከት ድምፅ አወድሱት። በባለ አውታር መሣሪያና በበገና አወድሱት። |
በአታሞና በሽብሸባ አወድሱት። በባለ አውታር መሣሪያና በዋሽንት አወድሱት። |
በሚያስተጋባ ሲምባል አወድሱት። ኃይለኛ ድምፅ በሚያወጣ ሲምባል አወድሱት። |
እስትንፋስ ያለው ሁሉ ያህን ያወድስ። ያህን አወድሱ! |
“ወደ ይሖዋ ቤት እንሂድ” ባሉኝ ጊዜ እጅግ ደስ አለኝ። |
ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አሁን በበሮችሽ ገብተንከውስጥ ቆመናል። |
ኢየሩሳሌም አንድ ወጥ ሆናእንደተገነባች ከተማ ናት። |
ለእስራኤል በተሰጠው ማሳሰቢያ መሠረት፣ነገዶቹ ይኸውም የያህ ነገዶች፣ለይሖዋ ስም ምስጋና ለማቅረብወደዚያ ወጥተዋል። |
በዚያ የፍርድ ዙፋኖች፣የዳዊት ቤት ዙፋኖች ተቀምጠዋልና። |
ለኢየሩሳሌም ሰላም ጸልዩ። አንቺ ከተማ ሆይ፣ አንቺን የሚወዱ ከስጋት ነፃ ይሆናሉ። |
በመከላከያ ግንቦችሽ ውስጥ ሰላም ለዘለቄታው ይኑር፤በማይደፈሩ ማማዎችሽ ውስጥ የተረጋጋ ሁኔታ ይስፈን። |
እንግዲህ ለወንድሞቼና ለወዳጆቼ ስል “በውስጥሽ ሰላም ይስፈን” እላለሁ። |
ለአምላካችን ለይሖዋ ቤት ስልለአንቺ መልካም ነገር እሻለሁ። |
በሰማያት ዙፋን ላይ የተቀመጥክ ሆይ፣ዓይኖቼን ወደ አንተ አነሳለሁ። |
የአገልጋዮች ዓይን ወደ ጌታቸው እጅ፣የሴት አገልጋይም ዓይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደሚመለከት ሁሉ፣የእኛም ዓይኖች ሞገስ እስኪያሳየን ድረስወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመለከታሉ። |
ንቀት እጅግ በዝቶብናልና፣ሞገስ አሳየን፤ ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ አሳየን። |
ከልክ በላይ በራሳቸው የሚተማመኑ ሰዎችን ፌዝ፣የእብሪተኞችንም ንቀት ጠግበናል። |
አምላክ ሆይ፣ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ዘወትር እጠባበቃለሁ። አንተን ተጠማሁ። ውኃ በሌለበት ደረቅና የተጠማ ምድርአንተን ከመናፈቄ የተነሳ እጅግ ዝያለሁ። |
ስለዚህ በቅዱሱ ስፍራ አንተን ተመለከትኩ፤ብርታትህንና ክብርህን አየሁ። |
ታማኝ ፍቅርህ ከሕይወት ስለሚሻልየገዛ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል። |
በመሆኑም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አወድስሃለሁ፤በአንተም ስም እጆቼን ወደ ላይ አነሳለሁ። |
ምርጥ የሆነውንና ስቡን በልቼ ጠገብኩ፤ስለዚህ በከንፈሬ እልልታ አፌ ያወድስሃል። |
መኝታዬ ላይ ሆኜ አንተን አስታውሳለሁ፤ሌሊት ስለ አንተ አሰላስላለሁ። |
አንተ ረዳቴ ነህና፤በክንፎችህም ጥላ ሥር ሆኜ እልል እላለሁ። |
አንተን የሙጥኝ እላለሁ፤ቀኝ እጅህ አጥብቆ ይይዘኛል። |
ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ሰዎች ግንወደ ምድር ጥልቅ ይወርዳሉ። |
ለሰይፍ ስለት አልፈው ይሰጣሉ፤የቀበሮዎችም ምግብ ይሆናሉ። |
ንጉሡ ግን በአምላክ ሐሴት ያደርጋል። በእሱ የሚምል ሰው ሁሉ ይደሰታል፤ሐሰትን የሚናገሩ ሰዎች አፍ ይዘጋልና። |
አምላክ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤ምሕረት እንድታደርግልኝ የማቀርበውንም ልመና ቸል አትበል። |
ትኩረት ስጠኝ፤ መልስልኝም። ያሳሰበኝ ጉዳይ እረፍት ነስቶኛል፤ደግሞም በጣም ተጨንቄአለሁ፤ |
ይህም ጠላት ከሚናገረው ቃል፣ክፉውም ሰው ከሚያሳድረው ጫና የተነሳ ነው። እነሱ በእኔ ላይ መከራ ይከምራሉና፤በቁጣም ተሞልተው በጥላቻ ዓይን ያዩኛል። |
ልቤ በውስጤ በጣም ተጨነቀ፤የሞት ፍርሃትም ዋጠኝ። |
ፍርሃት አደረብኝ፤ ደግሞም ተንቀጠቀጥኩ፤ብርክም ያዘኝ። |
እኔም እንዲህ እላለሁ፦ “ምነው እንደ ርግብ ክንፍ በኖረኝ! በርሬ ሄጄ ያለስጋት በኖርኩ ነበር። |
እነሆ፣ ወደ ሩቅ ቦታ በበረርኩ፣ በምድረ በዳም በቆየሁ ነበር። (ሴላ) |
ከአውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼመጠለያ ወደማገኝበት ቦታ ፈጥኜ በሄድኩ ነበር።” |
ይሖዋ ሆይ፣ ግራ አጋባቸው፤ ዕቅዳቸውንም አጨናግፍ፤በከተማዋ ውስጥ ዓመፅና ብጥብጥ አይቻለሁና። |
ቅጥሮቿ ላይ ወጥተው ቀንና ሌሊት ይዞራሉ፤በውስጧም ተንኮልና መከራ አለ። |
ጥፋት በመካከሏ አለ፤ጭቆናና ማታለል ከአደባባይዋ ፈጽሞ አይጠፉም። |
የሚዘልፈኝ ጠላት አይደለምና፤ቢሆንማ ኖሮ በቻልኩት ነበር። በእኔ ላይ የተነሳው ባላጋራ አይደለም፤ቢሆንማ ኖሮ ከእሱ በተሸሸግኩ ነበር። |
ነገር ግን ይህን ያደረግከው እንደ እኔው ሰው የሆንከው አንተ ነህ፤በሚገባ የማውቅህ የገዛ ጓደኛዬ ነህ። |
በመካከላችን የጠበቀ ወዳጅነት ነበር፤ከብዙ ሕዝብ ጋር ወደ አምላክ ቤት አብረን እንሄድ ነበር። |
ጥፋት በድንገት ይምጣባቸው! በሕይወት ሳሉ ወደ መቃብር ይውረዱ፤ክፋት በመካከላቸውና በውስጣቸው ያድራልና። |
እኔ በበኩሌ አምላክን እጣራለሁ፤ይሖዋም ያድነኛል። |
በማታ፣ በጠዋትና በቀትር እጨነቃለሁ፤ ደግሞም እቃትታለሁ፤እሱም ድምፄን ይሰማል። |
በእኔ ላይ ጦርነት ከከፈቱ ሰዎች ይታደገኛል፤ ሰላም እንዳገኝም ያደርጋል፤እጅግ ብዙ ሰዎች በእኔ ላይ ተነስተዋልና። |
ከጥንት ጀምሮ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው አምላክ ይሰማል፤ምላሽም ይሰጣቸዋል። (ሴላ) አምላክን የማይፈሩት እነዚህ ሰዎችለመለወጥ ፈቃደኞች አይደሉም። |
ከእሱ ጋር ሰላም በነበራቸው ሰዎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል፤የገባውን ቃል ኪዳን አፍርሷል። |
የሚናገራቸው ቃላት ከቅቤ ይልቅ የለሰለሱ ናቸው፤በልቡ ውስጥ ግን ጠብ አለ። ቃሎቹ ከዘይት ይልቅ የለሰለሱ ቢሆኑምእንደተመዘዘ ሰይፍ ናቸው። |
ሸክምህን በይሖዋ ላይ ጣል፤እሱም ይደግፍሃል። ጻድቁ እንዲወድቅ ፈጽሞ አይፈቅድም። |
አምላክ ሆይ፣ አንተ ግን ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ታወርዳቸዋለህ። የደም ዕዳ ያለባቸውና አታላይ የሆኑ ሰዎች የዕድሜያቸውን ግማሽ እንኳ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ንጉሡ በአንተ ብርታት ደስ ይለዋል፤በማዳን ሥራህ እጅግ ሐሴት ያደርጋል! |
የልቡን ፍላጎት አሟልተህለታል፤የከንፈሩንም ልመና አልከለከልከውም። (ሴላ) |
የተትረፈረፉ በረከቶች ይዘህ ተቀበልከው፤ምርጥ ከሆነ ወርቅ የተሠራ አክሊልም በራሱ ላይ ደፋህለት። |
ሕይወትን ለመነህ፤አንተም ረጅም ዕድሜ ብሎም የዘላለም ሕይወት ሰጠኸው። |
የማዳን ሥራህ ታላቅ ክብር ያስገኝለታል። ሞገስና ግርማ አጎናጸፍከው። |
ለዘላለም እንዲባረክ አደረግከው፤ከእሱ ጋር እንዳለህ ሲያውቅ በጣም ደስ ይለዋል። |
ንጉሡ በይሖዋ ይተማመናልና፤በልዑሉ አምላክ ታማኝ ፍቅር የተነሳ ፈጽሞ አይናወጥም። |
እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ይይዛቸዋል፤ቀኝ እጅህም የሚጠሉህን ይይዛቸዋል። |
በተወሰነው ጊዜ ትኩረትህን በእነሱ ላይ ስታደርግ እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ። ይሖዋ በቁጣው ይውጣቸዋል፤ እሳትም ይበላቸዋል። |
የሆዳቸውን ፍሬ ከምድር ገጽ፣ዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ። |
በአንተ ላይ ክፉ ለመሥራት አስበዋልና፤ሊሳካ የማይችል ሴራ ጠንስሰዋል። |
ቀስትህን በእነሱ ላይ በማነጣጠርእንዲያፈገፍጉ ታደርጋለህና። |
ይሖዋ ሆይ፣ በብርታትህ ተነስ። ለኃያልነትህ የውዳሴ መዝሙር እንዘምራለን። |
ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶቼ እንዲህ የበዙት ለምንድን ነው? ብዙ ሰዎች በእኔ ላይ የተነሱትስ ለምንድን ነው? |
ብዙዎች “አምላክ አያድነውም” እያሉ ስለ እኔ ይናገራሉ። (ሴላ) |
ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን በዙሪያዬ ያለህ ጋሻ ነህ፤አንተ ክብሬና ራሴን ቀና የምታደርግ ነህ። |
ድምፄን ከፍ አድርጌ ይሖዋን እጣራለሁ፤እሱም ከተቀደሰ ተራራው ይመልስልኛል። (ሴላ) |
እተኛለሁ፣ አንቀላፋለሁም፤ይሖዋም ዘወትር ስለሚደግፈኝበሰላም እነቃለሁ። |
በየአቅጣጫው የተሰለፉብኝንበአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አልፈራም። |
ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ! አምላኬ ሆይ፣ አድነኝ! የጠላቶቼን ሁሉ መንጋጋ ትመታለህና፤የክፉዎችን ጥርስ ትሰባብራለህ። |
ማዳን የይሖዋ ነው። በረከትህ በሕዝብህ ላይ ነው። (ሴላ) |
ይሖዋ ሆይ፣ ወደ ላይ ስላነሳኸኝ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ጠላቶቼ በእኔ ሥቃይ እንዲደሰቱ አልፈቀድክም። |
ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እርዳታ ለማግኘት ወደ አንተ ጮኽኩ፤ አንተም ፈወስከኝ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ከመቃብር አውጥተኸኛል። በሕይወት አቆይተኸኛል፤ ወደ ጉድጓድ ከመውረድ አድነኸኛል። |
እናንተ የእሱ ታማኝ አገልጋዮች፣ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ለቅዱስ ስሙ ምስጋና አቅርቡ፤ |
ምክንያቱም የሚቆጣው ለአጭር ጊዜ ነው፤ሞገስ የሚያሳየው ግን ለዕድሜ ልክ ነው። ማታ ለቅሶ ቢሆንም ጠዋት ግን እልልታ ይሆናል። |
በተረጋጋሁ ጊዜ “ፈጽሞ አልናወጥም” አልኩ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ሞገስ ባሳየኸኝ ጊዜ እንደ ተራራ አጠነከርከኝ። ፊትህን በሰወርክ ጊዜ ግን ተሸበርኩ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.