text stringlengths 4 267 |
|---|
ይሖዋ ሆይ፣ ወደ አንተ ደጋግሜ ተጣራሁ፤ሞገስ ለማግኘትም ይሖዋን አብዝቼ ተማጸንኩ። |
መሞቴና ወደ ጉድጓድ መውረዴ ምን የሚያስገኘው ጥቅም አለ? አፈር ያወድስሃል? የአንተንስ ታማኝነት ይናገራል? |
ይሖዋ ሆይ፣ ስማኝ፤ ሞገስም አሳየኝ። ይሖዋ ሆይ፣ ረዳቴ ሁን። |
ሐዘኔን ወደ ጭፈራ ለወጥክ፤ማቄን አውልቀህ ደስታን አለበስከኝ፤ |
ይህም እኔ ዝም ከማለት ይልቅ ለአንተ የውዳሴ መዝሙር እዘምር ዘንድ ነው። ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ለዘላለም አወድስሃለሁ። |
ይሖዋ ቤትን ካልገነባ፣ግንበኞቹ የሚደክሙት በከንቱ ነው። ይሖዋ ከተማን ካልጠበቀ፣ጠባቂው ንቁ ሆኖ መጠበቁ ከንቱ ድካም ነው። |
በማለዳ መነሳታችሁ፣እስከ ምሽት ድረስ መሥራታችሁ፣እንዲሁም የዕለት ጉርሳችሁን ለማግኘት መልፋታችሁ ከንቱ ነው፤ምክንያቱም አምላክ የሚወዳቸውን ሰዎች ይንከባከባቸዋል፤ እንቅልፍም ይሰጣቸዋል። |
እነሆ፣ ልጆች ከይሖዋ የተገኙ ውርሻ ናቸው፤የማህፀንም ፍሬ ከእሱ የሚገኝ ስጦታ ነው። |
አንድ ሰው በወጣትነቱ የወለዳቸው ወንዶች ልጆች፣በኃያል ሰው እጅ እንዳሉ ፍላጻዎች ናቸው። |
ኮሮጆውን በእነዚህ የሞላ ሰው ደስተኛ ነው። እነሱ ፈጽሞ አያፍሩም፤በከተማዋ በር ከጠላቶቻቸው ጋር ይነጋገራሉና። |
ይሖዋ ሆይ፣ በሙሉ ልቤ አወድስሃለሁ፤ስለ ድንቅ ሥራዎችህ ሁሉ እናገራለሁ። |
በአንተ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ፤ልዑል አምላክ ሆይ፣ ለስምህ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ። |
ጠላቶቼ ወደ ኋላ ሲያፈገፍጉተሰናክለው ከፊትህ ይጠፋሉ። |
ለማቀርበው ትክክለኛ ክስ ትሟገትልኛለህና፤በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ በጽድቅ ትፈርዳለህ። |
ብሔራትን ገሠጽክ፤ ክፉውንም አጠፋህ፤ስማቸውን ለዘላለም ደመሰስክ። |
ጠላቶች ለዘላለም ጠፍተዋል፤ከተሞቻቸውን አፈራርሰሃል፤መታሰቢያቸውም ሁሉ ይደመሰሳል። |
ይሖዋ ግን በዙፋኑ ላይ ለዘላለም ተቀምጧል፤ዙፋኑንም ለፍትሕ ሲል አጽንቷል። |
ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤ለብሔራት ትክክለኛ የፍርድ ውሳኔዎች ያስተላልፋል። |
ይሖዋ ለተጨቆኑ አስተማማኝ መጠጊያ ይሆናል፤በመከራ ጊዜ አስተማማኝ መጠጊያ ነው። |
ስምህን የሚያውቁ በአንተ ይታመናሉ፤ይሖዋ ሆይ፣ አንተን የሚሹትን ፈጽሞ አትተዋቸውም። |
በጽዮን ለሚኖረው ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤ሥራውንም በሕዝቦች መካከል አስታውቁ። |
ደማቸውን የሚበቀለው እሱ ያስታውሳቸዋልና፤የተጎሳቆሉ ሰዎች የሚያሰሙትን ጩኸት አይረሳም። |
ይሖዋ ሆይ፣ ቸርነት አሳየኝ፤ከሞት ደጆች የምታነሳኝ አምላክ ሆይ፣ የሚጠሉኝ ሰዎች የሚያደርሱብኝን እንግልት ተመልከት፤ |
ያን ጊዜ የሚያስመሰግኑ ተግባሮችህን በጽዮን ሴት ልጅ ደጆች አውጃለሁ፤በማዳን ሥራህም ሐሴት አደርጋለሁ። |
ብሔራት፣ ራሳቸው በቆፈሩት ጉድጓድ ውስጥ ገቡ፤የገዛ እግራቸው በስውር ባስቀመጡት መረብ ተያዘ። |
ይሖዋ በሚወስደው የፍርድ እርምጃ ይታወቃል። ክፉ ሰው በገዛ እጁ በሠራው ነገር ተጠመደ። ሂጋዮን። (ሴላ) |
ክፉ ሰው፣ አምላክን የሚረሱ ብሔራትም ሁሉወደ መቃብር ይሄዳሉ። |
ድሃ ግን ለዘላለም ተረስቶ አይቀርም፤የየዋሆችም ተስፋ ፈጽሞ ከንቱ ሆኖ አይቀርም። |
ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ! ሟች የሆነ ሰው እንዲያይል አትፍቀድ። ብሔራት በፊትህ ይፈረድባቸው። |
ይሖዋ ሆይ፣ ፍርሃት ልቀቅባቸው፤ሕዝቦች ሟች መሆናቸውን ይወቁ። (ሴላ) |
የማወድስህ አምላክ ሆይ፣ ዝም አትበል። |
ክፉዎችና አታላዮች በእኔ ላይ አፋቸውን ይከፍታሉና። ስለ እኔ በሐሰተኛ አንደበት ይናገራሉ፤ |
በዙሪያዬም ሆነው የጥላቻ ቃላት ይሰነዝሩብኛል፤ያለምክንያት ያጠቁኛል። |
ፍቅር ሳሳያቸው በምላሹ ይቃወሙኛል፤እኔ ግን መጸለዬን እቀጥላለሁ። |
ለመልካም ነገር ክፋትን፣ላሳየኋቸው ፍቅር ጥላቻን ይመልሱልኛል። |
በእሱ ላይ ክፉ ሰው እዘዝበት፤በቀኙም ተቃዋሚ ይቁም። |
ፍርድ ፊት ሲቆም በደለኛ ሆኖ ይገኝ፤ጸሎቱም እንኳ እንደ ኃጢአት ይቆጠርበት። |
የሕይወት ዘመኑ አጭር ይሁን፤የበላይ ተመልካችነት ሹመቱን ሌላ ሰው ይውሰደው። |
ልጆቹ ያለአባት ይቅሩ፤ሚስቱም መበለት ትሁን። |
ልጆቹ በየቦታው የሚቅበዘበዙ ለማኞች ይሁኑ፤ከፈራረሰው መኖሪያቸው ወጥተው ምግብ ፍለጋ ይንከራተቱ። |
ያበደረው ሰው ያለውን ነገር ሁሉ ይውሰድበት፤ባዕድ ሰዎችም ንብረቱን ይዝረፉት። |
ደግነት የሚያሳየው ሰው ከቶ አይኑር፤ያለአባት ለቀሩት ልጆቹ የሚራራ አንድም ሰው አይገኝ። |
ዘሩ ይጥፋ፤ስማቸው በአንድ ትውልድ ውስጥ ይደምሰስ። |
አባቶቹ የሠሩትን በደል ይሖዋ አይርሳ፤የእናቱም ኃጢአት አይደምሰስ። |
ይሖዋ የሠሩትን ነገር ምንጊዜም ያስብ፤መታሰቢያቸውንም ከምድር ገጽ ያጥፋ። |
ክፉው ሰው ደግነት ለማሳየት አላሰበምና፤ይልቁንም የተጨቆነውን፣ ድሃውንና ልቡ በሐዘን የተደቆሰውን ሰውለመግደል ሲያሳድድ ነበር። |
ሌሎችን መርገም ወደደ፤ በመሆኑም እርግማኑ በእሱ ላይ ደረሰበት፤ሌሎችን ለመባረክ ፍላጎት አልነበረውም፤ ስለዚህ ምንም በረከት አላገኘም። |
እርግማንን እንደ ልብስ ለበሰ። እንደ ውኃም ሰውነቱ ውስጥ ፈሰሰ፤እንደ ዘይት ወደ አጥንቶቹ ዘለቀ። |
እርግማኑ እንደሚከናነበው ልብስ፣ሁልጊዜ እንደሚታጠቀውም ቀበቶ ይሁንለት። |
እኔን የሚቃወመኝ ሰው፣በእኔም ላይ ክፉ ነገር የሚናገሩ ሰዎች ከይሖዋ የሚያገኙት ዋጋ ይህ ነው። |
አንተ ግን ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ለስምህ ስትል እርዳኝ። ታማኝ ፍቅርህ ጥሩ ስለሆነ ታደገኝ። |
እኔ ምስኪንና ድሃ ነኝና፤ልቤም በውስጤ ተወግቷል። |
ፀሐይ ስትጠልቅ እንደሚጠፋ ጥላ አልፋለሁ፤እንደ አንበጣ አራግፈው ጣሉኝ። |
ከመጾሜ የተነሳ ጉልበቶቼ ከዱኝ፤ሰውነቴ ከሳ፤ እኔም እየመነመንኩ ሄድኩ። |
የእነሱ መሳለቂያ ሆንኩ። ሲያዩኝ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ። |
ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እርዳኝ፤በታማኝ ፍቅርህ አድነኝ። |
ይህ የአንተ እጅ መሆኑን ይወቁ፤ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ያደረግከው አንተ እንደሆንክ ይገንዘቡ። |
እነሱ ይራገሙ፤ አንተ ግን ባርክ። እነሱ በእኔ ላይ ሲነሱ ለኀፍረት ይዳረጉ፤አገልጋይህ ግን ሐሴት ያድርግ። |
እኔን የሚቃወሙኝ ውርደት ይከናነቡ፤ኀፍረታቸውንም እንደ ልብስ ይጎናጸፉ። |
አንደበቴ ይሖዋን ከልብ ታወድሰዋለች፤በብዙ ሕዝቦች ፊት አወድሰዋለሁ። |
በእሱ ላይ ከሚፈርዱት ሊያድነውበድሃው ቀኝ ይቆማልና። |
ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤ተናደህም አታርመኝ። |
ፍላጻዎችህ እስከ ውስጥ ድረስ ወግተውኛልና፤እጅህም ተጭኖኛል። |
ከቁጣህ የተነሳ መላ ሰውነቴ ታመመ። ከኃጢአቴም የተነሳ አጥንቶቼ ሰላም የላቸውም። |
የፈጸምኳቸው ስህተቶች በራሴ ላይ ያንዣብባሉና፤እንደ ከባድ ሸክም በጣም ከብደውኛል። |
ከሞኝነቴ የተነሳቁስሌ ሸተተ፤ ደግሞም አመረቀዘ። |
በጭንቀት ተዋጥኩ፤ አንገቴንም ደፋሁ፤ቀኑን ሙሉ በሐዘን ተውጬ እመላለሳለሁ። |
ውስጤ ተቃጠለ፤መላ ሰውነቴ ታመመ። |
ደነዘዝኩ፤ ፈጽሞም ደቀቅኩ፤በጭንቀት ከተዋጠው ልቤ የተነሳ እጅግ እቃትታለሁ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ምኞቴ ሁሉ በፊትህ ነው፤የማሰማው ሲቃም ከአንተ የተሰወረ አይደለም። |
ልቤ በኃይል ይመታል፤ ጉልበቴ ከድቶኛል፤የዓይኔም ብርሃን ጠፍቷል። |
ከቁስሌ የተነሳ ወዳጆቼና ጓደኞቼ ሸሹኝ፤በቅርብ የሚያውቁኝ ሰዎችም ከእኔ ራቁ። |
ሕይወቴን የሚሹ ሰዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤እኔን መጉዳት የሚፈልጉም ስለ ጥፋት ያወራሉ፤ቀኑን ሙሉ ተንኮል ሲሸርቡ ይውላሉ። |
እኔ ግን እንደ ደንቆሮ አልሰማቸውም፤እንደ ዱዳም አፌን አልከፍትም። |
መስማት እንደማይችል፣በአፉም የመከላከያ መልስ እንደማይሰጥ ሰው ሆንኩ። |
ይሖዋ ሆይ፣ አንተን በተስፋ ተጠባብቄአለሁና፤ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ አንተም መልስ ሰጥተኸኛል። |
“በእኔ ውድቀት አይፈንድቁ፤ወይም እግሬ ቢንሸራተት በእኔ ላይ አይኩራሩ” ብያለሁና። |
ልወድቅ ምንም አልቀረኝም ነበርና፤ሥቃዬም ከእኔ አልተለየም። |
በደሌን ተናዘዝኩ፤ኃጢአቴም አስጨንቆኝ ነበር። |
ይሁንና ጠላቶቼ ብርቱዎችና ኃያላን ናቸው፤ያላንዳች ምክንያት የሚጠሉኝ ተበራከቱ። |
ላደረግኩት መልካም ነገር ክፉ መለሱልኝ፤መልካም የሆነውን ነገር በመከተሌ ይቃወሙኝ ነበር። |
ይሖዋ ሆይ፣ አትተወኝ። አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ። |
አዳኜ ይሖዋ ሆይ፣እኔን ለመርዳት ፍጠን። |
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ታላቁ የማደሪያ ድንኳንህ ምንኛ ያማረ ነው! |
ሁለንተናዬ የይሖዋን ቅጥር ግቢዎችእጅግ ናፈቀ፤አዎ፣ በጣም ከመጓጓቴ የተነሳ ዛልኩ። ልቤም ሆነ ሥጋዬ ሕያው ለሆነው አምላክ እልል ይላል። |
ንጉሤና አምላኬ የሆንከው የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ታላቁ መሠዊያህ ባለበት አቅራቢያ፣ወፍ እንኳ በዚያ ቤት ታገኛለች፤ወንጭፊትም ጫጩቶቿን የምታሳድግበት ጎጆለራሷ ትሠራለች። |
በቤትህ የሚኖሩ ደስተኞች ናቸው! እነሱ ሁልጊዜ ያወድሱሃል። (ሴላ) |
አንተን የብርታታቸው ምንጭ ያደረጉ፣ወደ ቤትህ የሚወስዱትን መንገዶች የሚናፍቅ ልብ ያላቸው ሰዎች ደስተኞች ናቸው። |
በባካ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ፣ስፍራውን ምንጮች የሚፈልቁበት ቦታ ያደርጉታል፤የመጀመሪያውም ዝናብ በረከት ያለብሰዋል። |
በብርታት ላይ ብርታት እያገኙ ይሄዳሉ፤እያንዳንዳቸውም በጽዮን፣ በአምላክ ፊት ይቀርባሉ። |
የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ አዳምጠኝ። (ሴላ) |
ጋሻችንና አምላካችን ሆይ፣ ተመልከት፤የተቀባውን የአገልጋይህን ፊት እይ። |
በሌላ ቦታ አንድ ሺህ ቀን ከመኖር በቅጥር ግቢዎችህ አንዲት ቀን መዋል ይሻላልና! በክፉዎች ድንኳን ከመኖር፣በአምላኬ ቤት ደጃፍ ላይ መቆም እመርጣለሁ። |
ይሖዋ አምላክ ፀሐይና ጋሻ ነውና፤እሱ ሞገስና ክብር ይሰጣል። ንጹሕ አቋም ይዘው የሚመላለሱትንይሖዋ አንዳች መልካም ነገር አይነፍጋቸውም። |
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣በአንተ የሚታመን ሰው ደስተኛ ነው። |
የአማልክት አምላክ የሆነው ይሖዋ ተናግሯል፤ከፀሐይ መውጫ አንስቶ እስከ መግቢያው ድረስምድርን ይጠራል። |
በውበቷ ፍጹም ከሆነችው ከጽዮን፣ አምላክ ያበራል። |
አምላካችን ይመጣል፤ ፈጽሞም ዝም ሊል አይችልም። በፊቱ የሚባላ እሳት አለ፤በዙሪያውም ሁሉ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ይነፍሳል። |
በሕዝቡ ላይ ለመፍረድ፣በላይ ያሉትን ሰማያትና ምድርን ይጠራል፤ |
“በመሥዋዕት አማካኝነት ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን የሚያደርጉትን፣ታማኝ አገልጋዮቼን ወደ እኔ ሰብስቡ” ይላል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.