text stringlengths 4 267 |
|---|
ክርስቲያን ወላጆች እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ካስተዋሉ፣ ልጆቻቸው እውነትን አጥብቀው እስኪይዙ ድረስ ልጆቹ በደንብ በሚረዱት ቋንቋ ወደሚመራ ጉባኤ ለመመለስ ሊወስኑ ይችላሉ። |
አምላክን ለበርካታ ዓመታት ያገለገለ ክርስቲያንም እንኳ በሥጋዊ ነገሮች ላይ ማተኮር ሊጀምር ይችላል። |
ጳውሎስ ይህን ማስጠንቀቂያ ሲሰጥ ስለ ምግብ፣ ስለ ሥራ፣ ስለ መዝናኛ እንዲሁም ስለ ፍቅር ግንኙነት ጨርሶ ማሰብ እንደሌለብን መግለጹ አልነበረም። |
ማንኛውም የአምላክ አገልጋይ በሕይወቱ ውስጥ ስለ እነዚህ ነገሮች ማሰቡ አይቀርም። |
ኢየሱስ በምግብ ይደሰት የነበረ ሲሆን ሌሎችንም መግቧል። |
መዝናኛም ቢሆን አስፈላጊ መሆኑን ያውቅ ነበር። |
ጳውሎስም በትዳር ውስጥ ፍቅርን መግለጽ ተገቢ መሆኑን በደብዳቤው ላይ ገልጿል። |
ጳውሎስ የተጠቀመበት የግሪክኛ ቃል አእምሮን ወይም ልብን በአንድ ነገር ላይ ማሳረፍ፣ የታሰበበት ግብ ለማውጣት የማመዛዘን ችሎታን መጠቀም የሚል ትርጉም አለው። |
እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ ሰዎች የኃጢአት ዝንባሌዎቻቸው ሕይወታቸውን እንዲመሩት ይፈቅዳሉ። |
አንድ ምሁር ላይ ስለተጠቀሱት ሰዎች ሲናገሩ ትኩረታቸውን የሚስበው ማለትም ከምንም በላይ የሚማርካቸው፣ አዘውትረው የሚያወሩትና የሚሠሩት እንዲሁም የሚያስደስታቸው ሥጋዊ ነገር ነው ብለዋል። |
ማንኛውም ሰው ለጊዜውም ቢሆን በሥጋዊ ምኞቶች ከተሸነፈ ከልኩ አልፎ ሊሄድ ይችላል። |
ለራስ ክብር እንደ መፈለግ፣ ቅናትና ግልፍተኝነት ያሉት ባሕርያት በርካታ ሰዎችን የእብሪት ድርጊት ወደ መፈጸም መርተዋቸዋል። |
እንደ አቢሴሎም፣ ዖዝያና ናቡከደነጾር ያሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሰዎች እንዲህ ባሉት የሥጋ ሥራዎች የተሸነፉ ሲሆን ይሖዋም የእብሪት ድርጊት በመፈጸማቸው እንዲዋረዱ አድርጓል። |
ይሁንና አንድ ሰው ልኩን እንደማያውቅ የሚያሳይ ድርጊት እንዲፈጽም የሚያደርጉት ሌሎች ምክንያቶችም አሉ። |
እስቲ ላይ የሚገኙትን የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች እንደ ምሳሌ እንመልከት። |
አቢሜሌክ እና ጴጥሮስ የፈጸሙት ድርጊት እብሪተኛ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው? |
ወይስ በዘገባው ላይ የተጠቀሰውን ድርጊት የፈጸሙት ስለ ጉዳዩ ሙሉ መረጃ ስላልነበራቸው አሊያም ስለተዘናጉ ይሆን? |
ማናችንም ብንሆን የሰውን ልብ ማንበብ አንችልም፤ በመሆኑም ሰዎች አንድን ነገር ለማድረግ የተነሳሱበትን ውስጣዊ ግፊት በተመለከተ ፍርድ ከመስጠት መቆጠባችን ጥበብ ከመሆኑም ሌላ ለእነዚህ ሰዎች ፍቅር እንዳለን ያሳያል። |
ይሖዋ አስቀድሞ ስለወደደን እኛም እንወደዋለን። |
ይሖዋ ለታማኝ አገልጋዮቹ ጥልቅ ፍቅር እንዳለው የሚያሳይበት አንዱ መንገድ የሚባርካቸው መሆኑ ነው። |
ለይሖዋ ያለን ፍቅር እያደገ በሄደ መጠን አምላክ መኖሩንና ለሚወዳቸው ወሮታ ከፋይ መሆኑን ይበልጥ እርግጠኛ ስለምንሆን እምነታችን እየጠነከረ ይሄዳል። |
ወሮታ ከፋይ መሆን የይሖዋ ማንነትና የመንገዶቹ አቢይ ገጽታ ነው። |
አምላክ ከልብ ለሚፈልጉት ወሮታ ከፋይ መሆኑን እርግጠኞች ካልሆንን እምነታችን ሙሉ ሊሆን አይችልም፤ ምክንያቱም እምነት ተስፋ የተደረጉትን ነገሮች በእርግጠኝነት መጠበቅ ማለት ነው። |
በእርግጥም እምነት ማለት ይሖዋ ቃል የገባቸው በረከቶች መፈጸማቸው እንደማይቀር ሙሉ በሙሉ መተማመን ነው። |
በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ እንደተገለጸው ይሖዋ የእሱን በረከት እንድናገኝ ግብዣ አቅርቦልናል። |
ይሖዋ እንድንፈትነው ያቀረበውን ግብዣ በመቀበል አድናቆታችንንና አመስጋኝነታችንን እናሳያለን። |
ጥንት የነበሩ እውነተኛ የአምላክ አገልጋዮች እንዳደረጉት እኛም በምንታመምበት ጊዜ መጽናኛ፣ ጥበብና ድጋፍ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ዞር ማለት እንችላለን። |
እርግጥ ነው፣ ዳዊት ይህን ሲል በዚያ ዘመን የኖረ ለተቸገረ የሚያስብ አንድ ሰው፣ ሞትን ፈጽሞ አያይም ማለቱ እንዳልነበረ እናውቃለን። |
በመሆኑም ዳዊት፣ በዕለቱ ጥቅስ ላይ ያለውን ሐሳብ ሲጽፍ ለተቸገረ የሚያስብ ሰው በተአምራዊ ሁኔታ ሕይወቱ እንደሚቀጥልና ለዘላለም እንደሚኖር መናገሩ አይደለም። |
በመንፈስ መሪነት የተጻፈው ይህ ሐሳብ አምላክ፣ ታማኝና ለሌሎች አሳቢ የሆኑ ሰዎችን እንደሚረዳ የሚጠቁም ነው። |
የሚረዳቸው እንዴት ነው? |
ዳዊት ይህን ሲያብራራ ታሞ በአልጋ ላይ ተኝቶ ሳለ ይሖዋ ይደግፈዋል፤ በታመመበት ወቅት መኝታውን ሙሉ በሙሉ ትቀይርለታለህ ብሏል። |
ለተቸገረ አሳቢነት ያሳየ ሰው፣ አምላክ እሱንም ሆነ የታማኝነት አካሄዱን እንደማይረሳ እርግጠኛ መሆን ይችላል። |
በተጨማሪም አምላክ፣ ሰውነታችን ራሱን በራሱ የመጠገን ችሎታ እንዲኖረው አድርጎ ስለፈጠረን ግለሰቡ ከበሽታው ሊያገግም ይችላል። |
አንድን ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ለማስጠናት ስንዘጋጅ የምናሰላስልበት ጊዜ ያስፈልገናል። |
እያንዳንዱን ተማሪ በአእምሯችን በመያዝ የምንዘጋጅ ከሆነ ተማሪው እድገት እንዲያደርግ ለመርዳት ምን ዓይነት የአመለካከት ጥያቄ ብንጠይቀው ወይም የትኛውን ምሳሌ ብንጠቀም የተሻለ እንደሆነ ልናስብ እንችላለን። |
እንዲህ በማድረግ የምናሳልፈው ጊዜ አስደሳች ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም በእነዚህ ነገሮች ላይ ማሰላሰላችን የእኛን እምነት ያጠናክራል፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪያችንን ይበልጥ ውጤታማ በሆነ መንገድና በቅንዓት ለማስጠናት ያስችለናል። |
ወደ መስክ አገልግሎት ለመውጣት ልባችንን በምናዘጋጅበት ጊዜም ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ይኖርብናል። |
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከሆነው ከሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ አንድ ምዕራፍ ማንበባችን ለአገልግሎት ያለን ቅንዓት እንዲቀጣጠል ያደርጋል። |
በዚያን ዕለት ልንጠቀምበት ባሰብነው ጥቅስና ጽሑፍ ላይ ማሰላሰላችን አገልግሎታችንን በቅንዓት እንድናከናውን ይረዳናል። |
በክልልህ ስላሉ ሰዎችና ፍላጎታቸውን ለመቀስቀስ ማድረግ ስለምትችለው ነገር አስብ። |
እንዲህ ያለ ዝግጅት ማድረጋችን ከአምላክ ቃል በሚገኘው መንፈስና ኃይል ተጠቅመን ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድንሰብክ ያነሳሳናል። |
ራሳችሁን እንዲህ እያላችሁ ጠይቁ፦ ልጄ የብልግና ምስሎችና ጽሑፎች ለማየት እንዲፈተን የሚያደርገው ምን ሊሆን ይችላል? |
እነዚህ ነገሮች በጣም አደገኛ የሆኑበትን ምክንያት ያውቃል? |
እንዲህ ዓይነት ነገሮችን ለማየት ቢፈተን መጥቶ ሊያነጋግረኝ እንዲችል በቀላሉ የምቀረብ ነኝ? |
ልጆቻችሁ ገና ትናንሽ እያሉም እንኳ እንዲህ ልትሏቸው ትችላላችሁ፦ ሳታስበው የብልግና ድረ ገጽ ብትከፍትና ለማየት ብትፈተን መጥተህ ንገረኝ። |
ፈጽሞ ልታፍር አይገባም። |
የእኔ ፍላጎት አንተን መርዳት ነው። |
አስተዋይ መሆናችሁ የራሳችሁን መዝናኛም በጥንቃቄ ለመምረጥ ያስችላችኋል። |
ፕራናስ የተባለ አንድ አባት እንዲህ ብሏል፦ እኛ ወላጆች ከሙዚቃ፣ ከፊልሞች ወይም ከመጻሕፍት ጋር በተያያዘ የምናደርገው ምርጫ ለቤተሰባችን ምሳሌ ይሆናል። |
ስለተለያዩ ነገሮች ለልጆቻችሁ ብዙ ነገር ትነግሯቸው ይሆናል፤ ልጆቻችሁ የሚያደርጉት ግን እናንተ ስታደርጉ የሚያዩትን ነው። |
እናንተ ተጠንቅቃችሁ ጥሩ መዝናኛ ስትመርጡ ልጆቻችሁ ካዩ እነሱም ተመሳሳይ ምርጫ ያደርጉ ይሆናል። |
የአምላክን ፈቃድ ግምት ውስጥ ሳናስገባ ውሳኔ የምናደርግ ከሆነ ፍቅርና እምነት እንደሚጎድለን ያሳያል። |
በሳሙኤል ዘመን በአንድ ወቅት እስራኤላውያን ከፍልስጥኤማውያን ጋር ባደረጉት ውጊያ ከባድ ሽንፈት ደርሶባቸው ነበር። |
በዚህ ጊዜ አምላክ እንዲረዳቸውና እንዲጠብቃቸው ፈልገው ነበር። |
ታዲያ ምን አደረጉ? |
አብሮን እንዲሆንና ከጠላቶቻችን እጅ እንዲያድነን የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት ከሴሎ ይዘነው እንሂድ አሉ። |
ውጤቱስ ምን ሆነ? |
በጣም ብዙ ሕዝብ አለቀ፤ ከእስራኤላውያንም ወገን 30,000 እግረኛ ወታደር ሞተ። |
የአምላክም ታቦት ተማረከ። |
እስራኤላውያን ታቦቱን ይዘው መሄዳቸው ይሖዋ እንዲረዳቸው የፈለጉ ሊመስል ይችላል። |
እንደ እውነቱ ከሆነ ግን የይሖዋን መመሪያ ለማግኘት ጥረት አላደረጉም፤ ከዚህ ይልቅ በራሳቸው አመለካከት በመመራታቸው ለከፋ ጥፋት ተዳርገዋል። |
ጠንካራ እምነት ለመገንባትና ጠብቀህ ለማቆየት ማድረግ የምትችለው ነገር ምንድን ነው? |
እስክትጠመቅ ድረስ ባገኘኸው እውቀት ረክተህ አትኑር። |
ፍጻሜያቸውን ስላገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች መማርህን ቀጥል፤ ምክንያቱም እነዚህ ትንቢቶች እምነትህን እንድትገነባ የሚያስችሉ በቂ ማስረጃዎች እንድታገኝ ያደርጉሃል። |
ከዚህ በተጨማሪ ጠንካራ እምነት ካላቸው ሰዎች መካከል የሚያስቆጥረን እምነት ያለህ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ የአምላክን ቃል እንደ መለኪያ አድርገህ መጠቀም ትችላለህ። |
ሐዋርያው ጳውሎስ የእምነት ባልንጀሮቹን ‘እኔ በእናንተ እምነት እናንተም በእኔ እምነት እርስ በርሳችን እንበረታታ ብሏቸው ነበር። |
ከእምነት ባልንጀሮቻችን፣ በተለይ ደግሞ ተፈትኖ የተረጋገጠ እምነት እንዳላቸው ካሳዩ ወንድሞቻችን ጋር ስንሆን አንዳችን የሌላውን እምነት መገንባት እንችላለን። |
መጥፎ ባልንጀርነት እምነት ያጠፋል፤ በአንጻሩ ግን ጥሩ ባልንጀርነት እምነት ይገነባል። |
መሰብሰባችንን ቸል እንዳንል ከዚህ ይልቅ እርስ በርስ እንድንበረታታ የተመከርንበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው። |
የይሖዋ አገልጋዮች ሕሊናቸውን ለማሠልጠን ጥረት ያደርጋሉ። |
ሕሊናቸው የሚነግራቸው ነገር የአምላክ ቃል ትክክልና ስህተት እንዲሁም ጥሩና መጥፎ የሆነውን በተመለከተ ከያዘው መሥፈርት ጋር የሚስማማ እንዲሆን ይፈልጋሉ። |
በአግባቡ የሠለጠነ ሕሊና በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል። |
ይሁንና ክርስቲያናዊ ሕሊናን ማሠልጠንና በዚያ መጠቀም አእምሮን የማሠራት ጉዳይ ብቻ አይደለም። |
መጽሐፍ ቅዱስ ጥሩ ሕሊናን ከእምነትና ከፍቅር ጋር ያያይዘዋል። |
ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ የዚህ ትእዛዝ ዓላማ ከንጹሕ ልብ፣ ከጥሩ ሕሊናና ግብዝነት ከሌለበት እምነት የሚመነጭ ፍቅር እንዲኖረን ነው። |
ሕሊናችንን ካሠለጠንነውና የሚነግረንን ነገር ከሰማን ለይሖዋ ያለን ፍቅር እያደገ ይሄዳል፤ እምነታችንም ይጠናከራል። |
ደግሞም ሕሊናችንን የምንጠቀምበት መንገድ የመንፈሳዊነታችንን ጥልቀት፣ የልባችንን ጥሩነትና ይሖዋን ለማስደሰት ያለንን ብርቱ ፍላጎት ያሳያል። |
በእርግጥም ሕሊናችን የሚያሰማው ድምፅ እውነተኛ ማንነታችንን በሚገባ ያሳያል። |
ይሖዋ የሰው ልጆች ሁሉ ፈጣሪ ነው። |
ከዚህም የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስ አዳምን የአምላክ ልጅ ብሎ ይጠራዋል፤ ኢየሱስ ደግሞ ተከታዮቹን ወደ አምላክ ሲጸልዩ በሰማያት የምትኖር አባታችን ብለው እንዲጠሩት አስተምሯቸዋል። |
ይሖዋ ሕይወት ሰጪ ስለሆነ አባታችን ነው፤ በእኛና በእሱ መካከል ያለው ዝምድና በአንድ አባትና በልጆቹ መካከል ካለው ዝምድና ጋር ሊመሳሰል ይችላል። |
በአጭር አነጋገር አንድ ጥሩ አባት ልጆቹን እንደሚወድ ሁሉ ይሖዋም እኛን ይወደናል። |
እርግጥ ሰብዓዊ አባቶች ፍጹም አይደሉም። |
የፈለጉትን ያህል ጥረት ቢያደርጉም እንኳ ይሖዋ አባታዊ ፍቅሩን ያሳየበትን መንገድ ሙሉ በሙሉ ማንጸባረቅ አይችሉም። |
እንዲያውም አንዳንዶች ልጅ ሳሉ በቤተሰባቸው ውስጥ ካጋጠማቸው ሁኔታ የተነሳ በስሜታቸው ወይም በአእምሯቸው ላይ የማይሽር ጠባሳ የተወ መጥፎ ትዝታ አላቸው። |
ይህ ስሜታቸውን ጎድቶትና አሳዛኝ ሁኔታ አስከትሎባቸው ሊሆን ይችላል። |
ይሖዋ እንዲህ ዓይነት አባት እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን እንችላለን። |
ይሖዋ ምን ያህል እንደሚወደንና እንዴት እንደሚንከባከበን ማወቃችን ወደ እሱ እንድንቀርብ እንደሚያደርገን የታወቀ ነው። |
ሕዝቅያስ፣ በጣም መጥፎ ከሆኑት የይሁዳ ነገሥታት መካከል የአንዱ ልጅ ቢሆንም በጣም ጥሩ ንጉሥ መሆን ችሏል። |
ሕዝቅያስ አባቱ የፈጸማቸውን መጥፎ ነገሮች ለማስተካከል እርምጃ ወስዷል። |
ይህንንም ያደረገው ቤተ መቅደሱን በማንጻት፣ ለሕዝቡ ኃጢአት ማስተሰረያ በማቅረብ እንዲሁም የአረማውያንን ጣዖታት ለማጥፋት ቅንዓት የተንጸባረቀበት ሰፊ ዘመቻ በማካሄድ ነው። |
ሕዝቅያስ፣ ከባድ ፈተናዎች ባጋጠሙት ጊዜ ለምሳሌ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ለመሰንዘር በሞከረበት ወቅት ታላቅ ድፍረትና እምነት እንዳለው አሳይቷል። |
አምላክ እንደሚያድነው የተማመነ ከመሆኑም ሌላ በንግግሩም ሆነ በድርጊቱ ሕዝቡን አበረታቷል። |
ከጊዜ በኋላ ሕዝቅያስ ልቡ በመታበዩ እርማት ሲሰጠው ራሱን ዝቅ በማድረግ ንስሐ ገብቷል። |
በግልጽ ማየት እንደሚቻለው ሕዝቅያስ፣ ያለፈው ሕይወቱ የአሁኑን ሕይወቱን እንዲያበላሽበት ወይም ጥሩ የወደፊት ሕይወት እንዳይኖረው እንቅፋት እንዲሆንበት አልፈቀደም። |
ከዚህ ይልቅ የይሖዋ ወዳጅ በመሆን እኛም ልንከተለው የሚገባ ጥሩ ምሳሌ ትቷል። |
አንዳንድ ጊዜ ለማን ታማኝ መሆን እንዳለብህ ግራ ስትጋባ ደግነት ሊረዳህ ይችላል። |
ለምሳሌ ያህል፣ አንድ የእምነት ባልንጀራህ ከባድ ኃጢአት እንደሠራ በእርግጠኝነት ታውቃለህ እንበል። |
ይህ ሰው በተለይ የቅርብ ወዳጅህ ወይም ዘመድህ ከሆነ ለእሱ ታማኝ መሆን እንዳለብህ ይሰማህ ይሆናል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.