text
stringlengths
4
267
በተጨማሪም ጎረቤቶቻችን አሊያም አብረውን የሚሠሩ ወይም የሚማሩ ሰዎች ከእኛ የተለየ ዜግነት፣ ዘርና የቆዳ ቀለም ያላቸውን ሰዎች የሚያንቋሽሽ ነገር ሲናገሩ እንሰማ ይሆናል።
ላይ የተዘረዘሩት ታማኝ የአምላክ አገልጋዮች በሞት ያንቀላፉት፣ ተስፋ የተሰጠበት ዘር ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ ሕይወት ለማግኘት የሚያስችል መንገድ ከመክፈቱ በፊት ነው።
ያም ቢሆን ከሞት ተነስተው ገነት በሆነች ምድር ላይ ለዘላለም ይኖራሉ፤ በዚያም ፍጹም ሕይወት ያገኛሉ።
በቅድመ ክርስትና ዘመን ስለኖሩ አንዳንድ የአምላክ አገልጋዮች ሲናገር እንዲህ ይላል፦ እነዚህ ሁሉ የተስፋውን ቃል ፍጻሜ ባያዩም እምነታቸውን እንደጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከሩቅ አይተው በደስታ ተቀበሉት።
ከእነዚህ መካከል አንዱ አብርሃም ነው።
ይሁንና አብርሃም፣ ተስፋ የተሰጠበት ዘር በሚያመጣው አዲስ ዓለም ውስጥ የሚኖረው አስደሳች ሕይወት በአእምሮው ቁልጭ ብሎ ይታየው ነበር?
ኢየሱስ ለተቃዋሚዎቹ የተናገረው ሐሳብ ለዚህ ጥያቄ ግልጽ መልስ ይሰጠናል፤ አባታችሁ አብርሃም ቀኔን እንደሚያይ ተስፋ በማድረግ እጅግ ተደሰተ፤ አይቶትም ደስ ተሰኘ ብሎ ነበር።
ሣራ፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብና ሌሎች በርካታ የአምላክ አገልጋዮችም አምላክ ንድፍ ያወጣላትንና የገነባትን ከተማ ይኸውም ወደፊት የሚቋቋመውን የአምላክ መንግሥት በጉጉት ይጠባበቁ ነበር።
ኖኅና ሦስቱ ወንዶች ልጆቹ ከአንድ በላይ ባያገቡም በጥንት ዘመን ብዙ ሚስቶችን ማግባት የተለመደ ነበር።
በብዙ ባሕሎች ውስጥ የፆታ ብልግና በጣም የተስፋፋ ከመሆንም አልፎ በአንዳንድ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ውስጥ እንኳ ተካትቶ ነበር።
አብራም አብርሃም እና ሚስቱ ሦራ ሣራ አምላክ በሰጣቸው መመሪያ መሠረት ወደ ከነዓን በሄዱበት ወቅት የጋብቻ ዝግጅትን የሚያቃልሉ ልማዶች በዚያ አካባቢ ተስፋፍተው ነበር።
የሰዶምና የገሞራ ነዋሪዎች ልቅ የሆነ የፆታ ብልግና ይፈጽሙ ወይም እንዲህ ያለውን ድርጊት በቸልታ ያልፉ ስለነበር ይሖዋ እነዚህ ከተሞች እንዲጠፉ ወሰነ።
አብርሃም በቤተሰቡ ላይ የራስነት ሥልጣኑን በአግባቡ ይጠቀምበት የነበረ ሲሆን ሣራም ለባሏ በመገዛት ረገድ ግሩም ምሳሌ ነች።
አብርሃም፣ ልጁ ይስሐቅ ይሖዋን የምታመልክ ሴት እንዲያገባ አድርጓል።
ይስሐቅም ለልጁ ለያዕቆብ እንዲህ ያደረገ ሲሆን ከጊዜ በኋላ 12ቱ የእስራኤል ነገዶች የተገኙት ከያዕቆብ ወንዶች ልጆች ነው።
እንላለን።
እስራኤላውያን ከግብፅ ባርነት በተአምራዊ መንገድ ነፃ ከወጡ ብዙም ሳይቆይ አማሌቃውያን ጥቃት ሰነዘሩባቸው።
ደፋር የሆነው ኢያሱ የሙሴን አመራር በመከተል እስራኤላውያንን እየመራ ለጦርነት ዘመተ።
በዚህ ጊዜ ሙሴ፣ ከአሮንና ከሁር ጋር በመሆን በአቅራቢያው ወደሚገኝና ጦር ሜዳውን ለማየት ወደሚያስችል ኮረብታ ወጣ።
ሙሴ ይህን ያደረገው እስራኤላውያን ድል እንዲቀዳጁ የሚያስችላቸውን ስልት ለመጠቀም ስላሰበ ነው።
በመሆኑም ሙሴ የእውነተኛውን አምላክ በትር በእጆቹ ወደ ላይ ከፍ አድርጎ ያዘ።
እሱ እጆቹን እስካላወረደ ድረስ እስራኤላውያን በአማሌቃውያን ላይ እንዲያይሉና ድል እንዲያደርጓቸው ይሖዋ ይረዳቸው ነበር።
ይሁንና ሙሴ እጆቹ ሲዝሉ ወደ ታች ያወርዳቸው ነበር፤ በዚህ ጊዜ አማሌቃውያን ያይሉባቸዋል።
አሮንና ሁር ይህን ሲመለከቱ ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ ድንጋይ ወስደው ከሙሴ ሥር አስቀመጡለት፤ እሱም በድንጋዩ ላይ ተቀመጠ።
ከዚያም አሮንና ሁር አንዱ በአንደኛው በኩል፣ ሌላው ደግሞ በሌላኛው በኩል ሆነው እጆቹን ደገፉለት፤ በመሆኑም ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ እጆቹ ባሉበት ጸኑ።
እስራኤላውያን፣ አምላክ በኃያል እጁ ስለደገፋቸው በውጊያው ድል አደረጉ።
ይህን ልመና ስናቀርብ የዕለት ምግቤን ብቻ ሳይሆን የዕለት ምግባችንን ማለት እንዳለብን ልብ በል።
በአፍሪካ የሚያገለግል ቪክቶር የተባለ የወረዳ የበላይ ተመልካች ስለዚህ ጉዳይ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ እኔና ባለቤቴ የምንበላውን ምግብ ከየት እንደምናገኝ ወይም የቤት ኪራይ ማን እንደሚከፍልልን መጨነቅ ስለማያስፈልገን ይሖዋን ብዙ ጊዜ ከልቤ አመሰግነዋለሁ።
ወንድሞቻችን የሚያስፈልገንን ነገር በየዕለቱ በደግነት ይሰጡናል።
በሌላ በኩል ደግሞ እኛን የሚንከባከቡን ወንድሞች የሚያጋጥሟቸውን የኢኮኖሚ ችግሮች መቋቋም እንዲችሉ ይሖዋ እንዲረዳቸው እጸልያለሁ።
እኛም ለብዙ ቀን የሚሆን ምግብ ይኖረን ይሆናል፤ ያም ቢሆን ድሃ የሆኑ ወይም አደጋ በደረሰበት አካባቢ የሚኖሩ ወንድሞቻችንን ማሰብ አለብን።
ስለ እነሱ ከመጸለይም አልፈን ከጸሎታችን ጋር የሚስማማ እርምጃ መውሰድ ይኖርብናል።
ለምሳሌ፣ ያለንን ነገር እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የእምነት ባልንጀሮቻችን ማካፈል እንችላለን።
በተጨማሪም ለዓለም አቀፉ ሥራ የምናደርገው መዋጮ እንደማይባክን እርግጠኛ በመሆን አዘውትረን የገንዘብ መዋጮ የማድረግ አጋጣሚ አለን።
እኛም እንደ ጳውሎስ በስብከቱ ሥራ ከተጠመድን ይሖዋ የሚያስፈልጉንን ሌሎች ነገሮች በሙሉ እንደሚሰጠን መተማመን እንችላለን።
የመንግሥቱ ሰባኪዎች እንደመሆናችን መጠን ምሥራቹን በአደራ ተቀብለናል፤ እንዲሁም ይሖዋ ከእሱ ጋር አብረን የምንሠራ እንደሆንን አድርጎ ይመለከተናል።
በአምላክ ሥራ በተቻለን መጠን ንቁ ተሳትፎ ማድረጋችን ችግሮቻችን እስኪቃለሉ ድረስ መጠበቅ ቀላል እንዲሆንልን ያደርጋል።
እንግዲያው የቀረውን ጊዜ ከአምላክ ጋር ያለንን ዝምድና ለማጠናከር እንጠቀምበት።
የሚያስጨንቀን ሁኔታ ሲያጋጥመን ይህን ወደ ይሖዋ ይበልጥ ለመቅረብ እንደሚያስችል አጋጣሚ አድርገን እንመልከተው።
በእርግጥም፣ የአምላክን ቃል በጥልቀት የምናጠና፣ አዘውትረን የምንጸልይ እንዲሁም በመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች የምንጠመድ ከሆነ ይሖዋ አሁን ያሉብንንም ሆነ ወደፊት ሊያጋጥሙን የሚችሉትን ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንድንወጣ ሊረዳን እንደሚችልና ይህንንም እንደሚያደርግ መተማመን እንችላለን።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ ለመላው የሰው ዘር የላከውን መልእክት የያዘ መሆኑን እንደምታምን ጥርጥር የለውም።
ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ፣ አንተ በግልህ ወደ ይሖዋ እንዴት መቅረብ እንደምትችል የሚገልጽ ሐሳብስ ይዟል?
በሚገባ።
እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው?
መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረህ ስታነብና ስታጠና፣ ለመልእክቱ ምን ምላሽ እንደምትሰጥና እንዴት ተግባራዊ እንደምታደርገው ቆም ብለህ አስብ፤ ይህን ማድረግህ ይሖዋ በቃሉ አማካኝነት እንዲያነጋግርህ እንደፈቀድክ ያሳያል።
ይህ ደግሞ ከእሱ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖርህ ያደርጋል።
ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ በምድር ላይ ለራሳችሁ ሀብት አታከማቹ በማለት የሰጠውን ምክር ካነበብክ በኋላ አሰላስልበት።
አሁንም ቢሆን ሕይወትህ ከአምላክ መንግሥት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ከሆነ ይሖዋ እንደሚደሰትብህ ይሰማሃል።
በሌላ በኩል ግን ሕይወትህን ቀላል ማድረግና ከመንግሥቱ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ ይበልጥ ማተኮር እንደሚያስፈልግህ ከተሰማህ፣ ይሖዋ ወደ እሱ መቅረብ እንድትችል በግለሰብ ደረጃ ልትሠራበት የሚገባውን ነገር እንደጠቆመህ አድርገህ ልትወስደው ይገባል።
እንዴት?
ከይሖዋ ጋር ያለንን ዝምድና ከፍ አድርገን የምንመለከት ከሆነ የምናስባቸውን ነገሮች ጨምሮ በመላ ሕይወታችን አምላክን ለማስደሰት ጥረት እናደርጋለን።
አእምሯችን ንጹሕና በጎ በሆኑ እንዲሁም ምስጋና በሚገባቸው ነገሮች ላይ እንዲያተኩር በማድረግ ንጹሕ ልብ እንዲኖረን እንደምንፈልግ እናሳያለን።
ይሖዋ ፍጽምና የሚጎድለን መሆኑን ከግምት እንደሚያስገባ ጥያቄ የለውም።
ተገቢ ያልሆኑ ምኞቶች በቀላሉ ሊያድሩብን እንደሚችሉ ያውቃል።
ያም ቢሆን መጥፎ ሐሳቦችን ለማስወገድ የምንችለውን ያህል ጥረት ከማድረግ ይልቅ የምናሰላስልባቸው ከሆነ ይሖዋ እንደሚያዝን እንገነዘባለን።
በዚህ እውነታ ላይ ማተኮራችን ሐሳባችን ምንጊዜም ንጹሕ እንዲሆን ይበልጥ ጥረት ለማድረግ ያነሳሳናል።
በይሖዋ ሙሉ በሙሉ እንደምንታመን ከምናሳይባቸው መንገዶች አንዱ ርኩስ ሐሳቦችን ለማስወገድ በምናደርገው ትግል እሱ እንዲረዳን መጸለይ ነው።
በጸሎት አማካኝነት ወደ ይሖዋ ስንቀርብ እሱም ወደ እኛ ይቀርባል።
ቅዱስ መንፈሱን በልግስና ስለሚሰጠን የብልግና ሐሳቦችን ለማስወገድና ንጹሕ ሆነን ለመኖር ያደረግነውን ቁርጥ ውሳኔ ያጠናክርልናል።
አምላክ ታማኝ ለሆኑት ቅቡዓን በሰማይ የማይሞት ሕይወት፣ ታማኝ ለሆኑት የኢየሱስ ሌሎች በጎች ደግሞ በምድር ላይ የዘላለም ሕይወት እንደሚሰጣቸው ቃል መግባቱ እንደሚያስደስተን ምንም ጥርጥር የለውም።
በሰማይ የማይሞት ሕይወት የሚሰጣቸውም ሆነ በምድር ላይ ዘላለማዊ ሕይወት የሚያገኙት ሰዎች በዛሬው ጊዜ ያሉት መከራዎች ወደፊት እንደማይደርሱባቸው የታወቀ ነው።
ይሖዋ፣ እስራኤላውያን በግብፅ በባርነት እያሉ ሥቃያቸውን እንደተረዳላቸው ሁሉ እኛም የሚያጋጥመንን መከራ በሚገባ ያውቃል።
በእርግጥም ከእስራኤላውያን ጋር በተያያዘ በጭንቃቸው ሁሉ እሱ ተጨነቀ ተብሎ ነበር።
ከዘመናት በኋላ ደግሞ አይሁዳውያን ቤተ መቅደሱን እንደገና ሲገነቡ ጠላቶቻቸው በሰነዘሩባቸው ተቃውሞ የተነሳ ፈርተው ነበር፤ ይሁንና አምላክ እናንተን የሚነካ ሁሉ የዓይኔን ብሌን ይነካል ብሏቸዋል።
አንዲት እናት ለሕፃን ልጇ ጥልቅ ፍቅር እንዳላት ሁሉ ይሖዋም ለሕዝቡ ያለው ፍቅር ለእነሱ ሲል እርምጃ እንዲወስድ ይገፋፋዋል።
በሌላ አባባል ይሖዋ ራሱን በሌሎች ቦታ አድርጎ መመልከት ይችላል፤ ይህንን ችሎታ ለእኛም ሰጥቶናል።
በስብሰባዎቻችን ላይ ታላቁ አስተማሪያችን ይሖዋ፣ በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት መመሪያ ይሰጠናል።
በስብሰባዎቻችን ላይ የሚገኙ የማያምኑ ሰዎች እንኳ አምላክ በእርግጥ በመካከላችሁ ነው የሚል መደምደሚያ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ።
ይሖዋ ስብሰባዎችን በቅዱስ መንፈሱ የሚመራ ሲሆን መንፈሳዊ ትምህርት የሚሰጠን እሱ ነው።
በመሆኑም በስብሰባዎቻችን ላይ የይሖዋን ድምፅ የምንሰማ ከመሆኑም ሌላ ፍቅራዊ እንክብካቤ እንደሚያደርግልን እናስተውላለን።
ይህም ወደ እሱ እንድንቀርብ ያደርገናል።
ኢየሱስ ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እገኛለሁ ብሏል።
ክርስቶስ የጉባኤው ራስ እንደመሆኑ መጠን የአምላክን ሕዝቦች ባቀፉት ጉባኤዎች መካከል ይመላለሳል።
እስቲ አስበው! ይሖዋና ኢየሱስ በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች አማካኝነት ያበረታቱናል።
ነቅቶ የመጠበቅን አስፈላጊነት፣ በጥንት ዘመን ከተሞችን ይጠብቁ ከነበሩ ጠባቂዎች መማር እንችላለን።
በዚያን ዘመን፣ እንደ ኢየሩሳሌም ያሉ በርካታ ትላልቅ ከተሞች ዙሪያቸው በረጅም ቅጥር ይታጠር ነበር።
እንዲህ ያለው ቅጥር ወራሪዎች ከተማዋን እንዳይደፍሯት የሚከላከል ከመሆኑም ሌላ ጠባቂዎቹ ከፍታ ላይ ሆነው አካባቢውን እንዲቃኙ ያስችላቸዋል።
በከተማዎቹ ቅጥሮችና በሮች ላይ ሆነው ቀንና ሌሊት የሚጠብቁ ዘቦች ይመደቡ ነበር።
እነዚህ ጠባቂዎች ከተማዋ ላይ ጥቃት ሊሰነዘር እንደሆነ የሚጠቁም ነገር ከርቀት ከተመለከቱ የከተማዋን ነዋሪዎች ያስጠነቅቃሉ።
ጠባቂዎቹ ንቁ ሆነው አካባቢውን በትኩረት መከታተላቸው የሕይወትና የሞት ጉዳይ ነበር።
አይሁዳዊው ታሪክ ጸሐፊ ጆሴፈስ፣ የሮም ሠራዊት ከኢየሩሳሌም ቅጥር ጋር ተያይዞ የተሠራውን የአንቶኒያን ግንብ በ70 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ሊያውል የቻለው በር ላይ ያሉት ጠባቂዎች ተኝተው ስለነበር እንደሆነ ገልጿል! ሮማውያን በአንቶኒያ ግንብ አልፈው በመግባት ቤተ መቅደሱን በእሳት አጋዩት፤ እንዲሁም ከተማዋን አጠፏት።
ይህም በአይሁድ ብሔር ላይ የደረሰው ታላቅ መከራ መደምደሚያ ሆነ።
ከፍጥረት መጀመሪያ አንስቶ የዓላማ አንድነት በግልጽ ሲታይ ቆይቷል።
አባትና ልጅ አንድ ላይ በመሥራት ዛሬ የምናያቸውን ልዩ ልዩ ፍጥረታት አስገኝተዋል።
የአምላክ ፍጥረታትም እርስ በርስ ባላቸው የትብብር መንፈስ ይታወቃሉ።
ኖኅና ቤተሰቡ መርከብ ሲሠሩ፣ በምድረ በዳ ይጓዝ የነበረው የአምላክ ሕዝብ የማደሪያውን ድንኳን ሲተክል፣ ሲያፈርስና ከቦታ ቦታ ሲያጓጉዝ አልፎ ተርፎም መዘምራን በይሖዋ ቤተ መቅደስ በሙዚቃ መሣሪያዎች ታጅበው በኅብረት እየዘመሩ እሱን ሲያወድሱ አገልጋዮቹ አንድነት እንዳላቸው ታይቷል።
የእነዚህ ሁሉ ሥራዎች መሳካት በሰዎቹ መተባበር ላይ የተመካ ነበር።
በኢየሱስ ክርስቶስ ራስነት ሥር የነበረው የጥንቱ የክርስቲያን ጉባኤም በኅብረት በመሥራት ይታወቅ ነበር።
ሐዋርያው ጳውሎስ እንደገለጸው ቅቡዓን ክርስቲያኖች በግለሰብ ደረጃ ልዩ ልዩ ስጦታዎች የነበሯቸው ከመሆኑም ሌላ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች እና ልዩ ልዩ ሥራዎች በማከናወን ይሳተፉ ነበር፤ ይሁንና ሁሉም የአንድ አካል ክፍል ነበሩ።
በዕድሜ ትንሽ ሊባል የሚችል ልጅ እንኳ ትክክለኛውን ነገር ማድረግና ራሱን ለፈጣሪው መወሰን ምን ነገሮችን እንደሚያካትት ሊገነዘብ ይችላል።
በመሆኑም አንድ ወጣት በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ከጎለመሰና ራሱን ለይሖዋ ከወሰነ መጠመቁ አስፈላጊ ብሎም ተገቢ እርምጃ ነው።
አንድ ሰው ጎለመሰ ሲባል ምን ማለት ነው?
ጉልምስና ሲባል አካላዊ እድገት ማድረግ ማለት ብቻ አይደለም።
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የጎለመሱ ሰዎች ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር መለየት እንዲችሉ የማስተዋል ችሎታቸውን በማሠራት አሠልጥነዋል።
በመሆኑም የጎለመሱ ሰዎች በይሖዋ ዓይን ትክክል የሆነውን ነገር የሚያውቁ ከመሆኑም በላይ እነዚህን ነገሮች ለመፈጸም ቁርጥ ውሳኔ አድርገዋል።
ስለዚህ ስህተት የሆነውን ነገር ለማድረግ በቀላሉ አይፈተኑም፤ እንዲሁም ትክክል የሆነውን ነገር ለመፈጸም ሁልጊዜ ጉትጎታ አያስፈልጋቸውም።
በእርግጥም አንድ የተጠመቀ ወጣት ወላጆቹ ወይም ሌሎች አዋቂዎች በሌሉበት እንኳ የአምላክን መሥፈርቶች ይጠብቃል ብሎ ማሰቡ ምክንያታዊ ነው።
ይሖዋን የሚያመልከው ለይስሙላ አይደለም።
አንድ ሰው የክርስቶስ ቅቡዕ ወንድም ቢሆንም እንኳ ለዚህ ግለሰብ ልዩ አክብሮት መስጠት ስህተት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ አመራር የሚሰጡትን ክርስቲያን ሽማግሌዎች በእምነታቸው እንድንመስላቸው ያበረታታናል፤ ይሁንና ማንኛውንም ሰው እንደ መሪያችን በማየት ከፍ ከፍ እንድናደርግ ጨርሶ አያዘንም።