text stringlengths 4 267 |
|---|
እውነት ነው፣ ቅዱሳን መጻሕፍት አንዳንዶች እጥፍ ክብር ሊሰጣቸው እንደሚገባ ይናገራሉ። |
እነዚህ ክርስቲያኖች ክብር ሊሰጣቸው የሚገባው ግን ቅቡዓን ስለሆኑ ሳይሆን በመልካም ሁኔታ የሚያስተዳድሩ እንዲሁም በመናገርና በማስተማር ተግተው የሚሠሩ በመሆናቸው ነው። |
ሰማያዊ ጥሪ ያላቸው ክርስቲያኖች፣ ሌሎች አላስፈላጊ አድናቆት ወይም ትኩረት የሚሰጧቸው ከሆነ ይጨንቃቸዋል። |
ከዚህ የባሰው ደግሞ እንዲህ ያለው ለየት ያለ ትኩረት፣ ትሑት መሆን እንዲከብዳቸው ሊያደርግ ይችላል። |
ማናችንም ብንሆን ለክርስቶስ ወንድሞች ማሰናከያ መሆን አንፈልግም!—፤ |
ቅቡዓን በዚህ መንገድ በመንፈስ ቅዱስ መቀባታቸው፣ እንደ ቀብድ አሊያም ወደፊት ለሚመጣው ነገር እንደ ዋስትና ወይም መያዣ ነው። |
አንድ ቅቡዕ ክርስቲያን ይህን ማረጋገጫ ስላገኘ መቀባቱን ይተማመናል። |
ግለሰቡ ጥሪውን እንደተቀበለ እርግጠኛ ነው። |
ሆኖም በሰማይ ሽልማቱን ማግኘት አለማግኘቱ የተመካው ለጥሪው ታማኝ ሆኖ በመገኘቱ ላይ ነው። |
ጴጥሮስ ነጥቡን እንዲህ በማለት ገልጾታል፦ በመሆኑም ወንድሞች፣ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን አስተማማኝ ለማድረግ ከበፊቱ ይበልጥ ትጉ፤ እነዚህን ነገሮች የምታደርጉ ከሆነ ፈጽሞ አትወድቁምና። |
እንዲያውም በእጅጉ ትባረካላችሁ፤ ጌታችንና አዳኛችን ወደሆነው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ መንግሥትም ትገባላችሁ። |
እንግዲያው እያንዳንዱ ቅቡዕ ክርስቲያን ታማኝነቱን ለመጠበቅ መታገል አለበት። |
ታማኝ ካልሆነ ግን ሰማያዊ ጥሪ ወይም ግብዣ ማግኘቱ ምንም አይጠቅመውም። |
በአንድ ወቅት በይሖዋ ፊት ጥሩ አቋም ነበረው። |
ይሁንና ይህ መንፈሳዊ ፍጡር፣ ሰዎች እንዲያመልኩት መመኘት ጀመረ። |
ይህን ተገቢ ያልሆነ ምኞት ከማስወገድ ይልቅ ስላሰላሰለበትና እንዲያድግ ስለፈቀደለት ምኞቱ ኃጢአትን ወለደ። |
እያወራን ያለነው በእውነት ውስጥ ጸንቶ ስላልቆመው ስለ ሰይጣን እንደሆነ የታወቀ ነው። |
ሰይጣን በይሖዋ ላይ ያመፀ ከመሆኑም ሌላ የውሸት አባት ሆነ። |
ሰይጣን ካመፀበት ጊዜ ጀምሮ የይሖዋ ቀንደኛ ጠላት እንደሆነ ታይቷል፤ የሰው ልጆች ወዳጅ ሆኖ እንደማያውቅም ግልጽ ነው። |
ለሰይጣን የተሰጡት መጠሪያዎች ምን ያህል በክፋት እንደተዘፈቀ ይጠቁማሉ። |
ሰይጣን የሚለው ቃል ተቃዋሚ ማለት ሲሆን ይህ ክፉ መንፈሳዊ ፍጡር የአምላክን ሉዓላዊነት እንደማይደግፍ ያሳያል፤ እንዲያውም የይሖዋን ሉዓላዊ ገዢነት የሚጠላ ከመሆኑም ሌላ አጥብቆ ይቃወመዋል። |
ሰይጣን ከምንም በላይ የሚፈልገው ነገር የይሖዋ ሉዓላዊ ገዢነት ሲያበቃ ማየት ነው። |
ወንድሞችን በመንፈሳዊ እንዲያድጉ በመርዳት ረገድ የተዋጣላቸው አንዳንድ ሽማግሌዎች ሌሎችን ለማሠልጠን ምን ዓይነት ዘዴዎችን እንደተጠቀሙ በቅርቡ ተጠይቀው ነበር። |
እነዚህ ሽማግሌዎች ያሉበት ሁኔታ በእጅጉ የተለያየ ቢሆንም የሰጡት ምክር በሚያስገርም ሁኔታ ይመሳሰላል። |
ይህ ምን ይጠቁማል? |
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተው ለተማሪዎች የሚሰጠው ይህ ሥልጠና በሐዋርያው ጳውሎስ ዘመን ብቻ ሳይሆን ዛሬም በሁሉም ስፍራ በሚገኙ ጉባኤዎች ውስጥ ይሠራል። |
አስተማሪዎች ለሥልጠና አመቺ ሁኔታ መፍጠር ይኖርባቸዋል። |
አንድ ገበሬ ዘር ከመዝራቱ በፊት መሬቱን ማለስለስ እንዳለበት ሁሉ አንድ አስተማሪም ተማሪውን ማሠልጠን ከመጀመሩ በፊት የተማሪውን ልብ ማዘጋጀት ይኖርበታል። |
ታዲያ አስተማሪዎች ሌሎችን ለማሠልጠን አመቺ ሁኔታ መፍጠር የሚችሉት እንዴት ነው? |
ሳሙኤል፣ ሳኦል የእስራኤልን ሕዝብ እንዲመራ ሲያዘጋጀው የተጠቀመውን ዘዴ በመከተል ነው። |
የሕዝበ ክርስትና ቀሳውስት ስለ አምላክ መንግሥት እየሰበኩ አይደሉም። |
ስለ መንግሥቱ ቢናገሩ እንኳ ብዙዎቹ፣ በክርስቲያኖች ልብ ውስጥ ያለ ስሜት ወይም ሁኔታ እንደሆነ አድርገው ይገልጹታል። |
የአምላክ መንግሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥ ሆኖ የተሾመበት በሰማይ የሚገኝ መስተዳድር እንደሆነ፣ ለሰው ልጆች ችግሮች በሙሉ መፍትሔ እንደሚያመጣ እንዲሁም በቅርቡ ክፋትን ሁሉ ከምድር እንደሚያስወግድ ሰዎች እንዲገነዘቡ አያደርጉም። |
ከዚህ ይልቅ ኢየሱስን የሚያስታውሱት በገና እና በፋሲካ በዓል ወቅት ነው። |
ኢየሱስ የምድር ንጉሥ ሲሆን ምን እንደሚያከናውን የሚያውቁት ነገር ያለ አይመስልም። |
እነዚህ ቀሳውስት የስብከቱን ሥራ እንዲያከናውኑ የሚያነሳሳቸው ምክንያት ምን ሊሆን እንደሚገባም አያውቁም። |
ዓላማው ገንዘብ መሰብሰብና የተንቆጠቆጡ ሕንፃዎችን መገንባት መሆን የለበትም። |
በአምላክ ቃል ሊነገድ አይገባም። |
ግርጌ መልእክቱን የሚሰብኩ ሰዎች ከሚያከናውኑት ሥራ የግል ጥቅም ለማግኘት መሞከር የለባቸውም። |
አንድ ልብስ መልበስ ፈለጋችሁ እንበል፤ ልብሱ የጉባኤውን አባላት ቅር የሚያሰኝ ሊሆን ይችል ይሆናል። |
ሆኖም ይህን ልብስ እንዳትለብሱ የሚከለክል ቀጥተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ሕግ እንደሌለ ታውቃላችሁ። |
ታዲያ ይሖዋ በዚህ ረገድ ያለውን አመለካከት ማወቅ የምትችሉት እንዴት ነው? |
ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት የሚከተለውን ምክር ሰጥቷል፦ ሴቶች ፀጉር በመሸረብና በወርቅ ወይም በዕንቁ ወይም ደግሞ በጣም ውድ በሆነ ልብስ ሳይሆን በልከኝነትና በማስተዋል ተገቢ በሆነ ልብስ ራሳቸውን ያስውቡ፤ ለአምላክ ያደርን ነን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉት እንደሚገባ በመልካም ሥራ ይዋቡ። |
ይህ መሠረታዊ ሥርዓት ለክርስቲያን ወንዶችም በእኩል ደረጃ ይሠራል። |
ለይሖዋ ያደርን እንደመሆናችን መጠን የራሳችን ምርጫ ብቻ ሳይሆን አለባበሳችንና አጋጌጣችን በሌሎች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖም ያሳስበናል። |
ልከኛ ከሆንንና ለሰዎች ፍቅር ካለን፣ የእምነት ባልንጀሮቻችንን አመለካከት ግምት ውስጥ በማስገባት እነሱን ሊረብሽ ወይም ቅር ሊያሰኝ የሚችል ልብስ ከመልበስ እንቆጠባለን። |
አዳም በፈጣሪው ላይ በማመፁ የልጅነት መብቱን አጣ። |
ይሁንና ባለፉት በርካታ ዘመናት የኖሩ እንደ ታላቅ የምሥክሮች ደመና የሆኑ የአዳም ዘሮች የአምላክን ሉዓላዊነት መደገፍ መርጠዋል። |
እነዚህ ሰዎች ለፈጣሪያቸው በትሕትና በመገዛት፣ ከሰይጣን ይልቅ ይሖዋ እንደ ሸክላ ሠሪ እንዲቀርጻቸው እንዲሁም አባታቸው እንዲሆን እንደሚፈልጉ በተግባር አሳይተዋል። |
ለአምላክ ያላቸው ታማኝነት፣ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን ሐሳብ ያስታውሰናል። |
በዛሬው ጊዜ ይሖዋን በመንፈስና በእውነት የሚያመልኩ ሁሉ እንዲህ ዓይነት የትሕትናና የታዛዥነት መንፈስ ለማሳየት ይጥራሉ። |
ይሖዋን፣ አባታችን ብለው መጥራትና እሱን እንደ ሸክላ ሠሪያቸው ቆጥረው ለእሱ መገዛትን እንደ ታላቅ መብት ይመለከቱታል። |
በቅንዓትና በጥላቻ የተሞሉት የዮፍታሔ ወንድሞች የበኩር ልጅ በመሆኑ ሊያገኝ የሚገባውን መብት በመከልከል ከአባቱ ቤት አባረውታል። |
ይሁንና ዮፍታሔ፣ እንዲረዳቸው ያቀረቡትን ልመና ሰምቶ ረድቷቸዋል። |
ዮፍታሔ ከሌሎች ሰዎች ጋር ከተፈጠረው ግጭት ይልቅ ትልቅ ቦታ የሰጠው የይሖዋን ስም ለማስከበር ሲል ለሚያደርገው ውጊያ ነው። |
ምንጊዜም በይሖዋ ለመታመን ቁርጥ ውሳኔ አድርጎ ነበር፤ ይህ ደግሞ ለእሱም ሆነ ለሌሎች በረከት አምጥቷል። |
ዮፍታሔ ከተወው ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን? |
ምናልባት አንዳንድ ወንድሞች ቅር አሰኝተውን ወይም ተገቢ ያልሆነ ነገር አድርገውብን ይሆናል። |
በዚህ ጊዜ፣ በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ ከመገኘት ወይም ከጉባኤው ጋር ሙሉ በሙሉ ከመተባበርና ይሖዋን ከማገልገል ወደኋላ ማለት አይኖርብንም። |
እኛም እንደ ዮፍታሔ፣ እንዲህ ያሉ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ለማሸነፍና መልካም ነገር ማድረጋችንን ለመቀጠል የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች መከተል ይኖርብናል። |
መጽናት የሚያስፈልገን ለጊዜው ብቻ ሳይሆን እስከ መጨረሻው ነው። |
ይህን በምሳሌ ለማስረዳት፣ አደጋ የደረሰባትን መርከብ እንውሰድ። |
ተሳፋሪዎቹ በሕይወት ለመትረፍ ከፈለጉ እየዋኙ ወደ ዳርቻው መሄድ አለባቸው። |
ወደ ዳርቻው ለመድረስ ጥቂት ሲቀረውም ሆነ ገና መሃል ላይ እያለ ተስፋ የቆረጠ ተሳፋሪ የሚያጋጥማቸው ነገር ተመሳሳይ ነው። |
እኛም ብንሆን ወደ አዲሱ ዓለም እስክንገባ ድረስ ለመጽናት ቆርጠናል። |
ሕይወት ማግኘታችን የተመካው በመጽናታችን ላይ ነው። |
ተስፋ አንቆርጥም በማለት ሁለት ጊዜ እንደተናገረው እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ ዓይነት አመለካከት አለን። |
ይሖዋ እስከ መጨረሻው ድረስ መጽናት እንድንችል እንደሚረዳን ፈጽሞ አንጠራጠርም። |
ላይ ጳውሎስ የተናገረውን ሐሳብ እንጋራለን፤ ጥቅሱ እንዲህ ይላል፦ በወደደን በእሱ አማካኝነት እነዚህን ነገሮች ሁሉ ሙሉ በሙሉ በድል አድራጊነት እንወጣለን። |
ምክንያቱም ሞትም ቢሆን፣ ሕይወትም ቢሆን፣ መላእክትም ቢሆኑ፣ መንግሥታትም ቢሆኑ፣ አሁን ያሉት ነገሮችም ቢሆኑ፣ ወደፊት የሚመጡት ነገሮችም ቢሆኑ፣ ማንኛውም ኃይል ቢሆን፣ ከፍታም ቢሆን፣ ዝቅታም ቢሆን፣ ሌላ ማንኛውም ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ከተገለጸው የአምላክ ፍቅር ሊለየን እንደማይችል ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ነኝ። |
ክርስቲያናዊ የገለልተኝነት አቋማችንን እንድናላላ ሊያደርጉ የሚችሉ ሁኔታዎችን ማስተዋልና ማሸነፍ እንድንችል የሚያስፈልገውን ጥበብ እንዲሰጠን ይሖዋን እንጠይቅ። |
ለእውነተኛው አምልኮ ቆራጥ አቋም በመያዛችን ምክንያት ብንታሰር ወይም ሌላ ዓይነት ቅጣት ቢደርስብን ደግሞ እምነታችንን በድፍረት ለማስረዳትና የሚመጣብንን ማንኛውንም ስደት በጽናት ለመቋቋም የሚያስችል ብርታት እንዲሰጠን ወደ ይሖዋ እንጸልይ። |
ይሖዋ በቃሉ አማካኝነት ሊያበረታህ ይችላል። |
ፈተና ሲያጋጥምህ የገለልተኝነት አቋምህን ለመጠበቅ ሊረዱህ በሚችሉ ጥቅሶች ላይ አሰላስል። |
መጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት የማትችልበት አጋጣሚ ቢፈጠር ከእነዚህ ጥቅሶች ማበረታቻ ማግኘት እንድትችል ጥቅሶቹን በቃልህ ለመያዝ ሞክር። |
በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ፣ የአምላክ መንግሥት ወደፊት ስለሚያመጣቸው በረከቶች ያለን ተስፋ እውን ሆኖ እንዲታየን ይረዳናል። |
ስደት ሲደርስብን መጽናት እንድንችል ይህ ተስፋ ያስፈልገናል። |
ስለምትጓጓላቸው በረከቶች በሚገልጹ ጥቅሶች ላይ አሰላስል፤ በገነት ውስጥ እነዚህን በረከቶች ስታገኝ የሚኖረውን ሁኔታ በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል ሞክር። |
በምድር ላይ ያሉ የይሖዋ ታማኝ አገልጋዮችን ወይም ምሥክሮቹን ያቀፈ አንድ ልዩ ድርጅት አለ። |
እርግጥ ነው፣ እነዚህ ሰዎች ፍጽምና የጎደላቸው በመሆናቸው ስህተት ይሠራሉ። |
ያም ሆኖ አምላክ፣ በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት ዓለም አቀፉን ጉባኤ በመባረክ እያደገና እየተጠናከረ እንዲሄድ አድርጓል። |
የዚህ ሥርዓት የመጨረሻ ቀናት በ1914 ሲጀምሩ በምድር ላይ የነበሩት የአምላክ አገልጋዮች በአንጻራዊ ሁኔታ ትንሽ ነበሩ። |
ይሁንና ይሖዋ የስብከቱን ሥራቸውን ባርኮታል። |
በቀጣዮቹ አሥርተ ዓመታት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ተምረው የይሖዋ ምሥክሮች ሆነዋል። |
ይሖዋ ይህን አስደናቂ እድገት በተመለከተ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን ከተናገረ በኋላ እኔ ይሖዋ፣ ይህን በራሱ ጊዜ አፋጥነዋለሁ ብሏል። |
ይህ ትንቢት በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ፍጻሜውን እንዳገኘ በግልጽ ማየት ይቻላል። |
የይሖዋ ሕዝቦች እንደ አንድ ታላቅ ብሔር ሆነዋል፤ እንዲያውም በአሁኑ ወቅት፣ በምድር ላይ ካሉት የአምላክ ሕዝቦች አጠቃላይ ቁጥር ያነሰ የሕዝብ ብዛት ያላቸው በርካታ አገራት አሉ። |
ኢየሱስ፣ በሰማይ ያለው አባቱ ለወፎች የሚያስፈልጋቸውን ነገር እያሟላ የሰው ልጆችን መሠረታዊ ፍላጎት ችላ ይላል ብሎ ማሰብ ፈጽሞ የማይመስል ነገር እንደሆነ ተሰምቶታል። |
እርግጥ ነው፣ አምላክ ምግቡን አፋችን ላይ አያደርግልንም፤ ምግባችንን ለማግኘት ማረስ አሊያም እህሉን ለመግዛት የሚያስችለንን ገንዘብ ለማግኘት መሥራት ይኖርብናል፤ ይሖዋም የምናደርገውን ጥረት ይባርክልናል። |
ከተቸገርን ደግሞ ሌሎች ያላቸውን እንዲያካፍሉን ሊያነሳሳቸው ይችላል። |
ኢየሱስ የሰማይ ወፎች መጠለያ ስለሚያገኙበት መንገድ ባይጠቅስም ይሖዋ፣ ጎጇቸውን ለመሥራት የሚያስችላቸውን ችሎታና የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ሰጥቷቸዋል። |
ይሖዋ፣ እኛም በተመሳሳይ ቤተሰባችንን የምናስጠልልበት ጎጆ እንድናገኝ ይረዳናል። |
ኢየሱስ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን የተናገረው፣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሕይወቱን ለሰው ልጆች አሳልፎ እንደሚሰጥ በአእምሮው ይዞ መሆን አለበት። |
ጋር አወዳድር። |
ኢየሱስ የሞተው ለሰማይ ወፎች ሳይሆን እኛ የሰው ልጆች የዘላለም ሕይወት እንድናገኝ ነው። |
ሰርዥ እና ባለቤቱ ሚውሪዬል በሌላ ቋንቋ በሚመራ ጉባኤ ውስጥ ከሦስት ዓመት በላይ ካገለገሉ በኋላ፣ የ17 ዓመት ልጃቸው በቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች መካፈል እንደማያስደስተው አስተዋሉ። |
ሰርዥ እንዲህ ብሏል፦ ይህ ሁኔታ ልጃችን መንፈሳዊ እድገት እንዳያደርግ እንቅፋት እንደሆነበት ስናስተውል ወደ ቀድሞ ጉባኤያችን ለመመለስ ወሰንን። |
ወላጆች ወደ ቀድሞ ጉባኤያቸው ለመመለስ እንዲወስኑ የሚያደርጋቸው ምን ሊሆን ይችላል? |
በመጀመሪያ ደረጃ፣ በአንድ በኩል ልጆቻቸው ይሖዋን እንዲወዱ እየረዱ በሌላ በኩል ደግሞ ለልጆቻቸው አዲስ ቋንቋ ለማስተማር የሚያስፈልገው ጊዜና ኃይል ያላቸው መሆኑን መመርመር ይኖርባቸዋል። |
ሁለተኛ፣ ልጆቻቸው ለመንፈሳዊ ነገሮች ያላቸው ጉጉት እንደቀነሰ አሊያም በሌላ ቋንቋ በሚመራ ጉባኤ ውስጥ ለማገልገል ፍላጎት እንደሌላቸው ይገነዘቡ ይሆናል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.