text
stringlengths
4
267
ይሁንና ኃጢአቱን የምትደብቅለት ከሆነ ለአምላክ ያለህን ታማኝነት እያጓደልክ ነው።
ከማንም በላይ ታማኝ መሆን ያለብህ ለይሖዋ እንደሆነ ጥያቄ የለውም።
ደግ ሆኖም ደፋር ልትሆን ይገባል።
ጓደኛህ ወይም ዘመድህ የሽማግሌዎችን እርዳታ እንዲጠይቅ አበረታታው።
በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ይህን ካላደረገ ግን ለአምላክ ያለህ ታማኝነት፣ ጉዳዩን ለሽማግሌዎች እንድታሳውቅ ሊያነሳሳህ ይገባል።
እንዲህ ስታደርግ ለይሖዋ ታማኝነት፣ ለወዳጅህ ወይም ለዘመድህ ደግሞ ደግነት ታሳያለህ፤ ምክንያቱም ክርስቲያን ሽማግሌዎች እንዲህ ያለውን ሰው በገርነት ለማስተካከል ይጥራሉ።
ታማኝ የይሖዋ አገልጋዮች የተዉት ምሳሌ ለመጽናት የሚያስፈልገንን ጥበብና ብርታት ይሰጠናል።
ለምሳሌ ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ የባቢሎንን መንግሥት የሚወክለውን ምስል ለማምለክ ፈቃደኞች አልሆኑም።
በዛሬው ጊዜ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች እነዚህ ወጣቶች ስለወሰዱት ቆራጥ እርምጃ በማንበባቸው፣ ለሚኖሩበት አገር ባንዲራ አምልኮ አናቀርብም ለማለት የሚያስችላቸውን ድፍረት አግኝተዋል።
ኢየሱስም ቢሆን በዓለም ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ግጭቶች ውስጥ ፈጽሞ ጣልቃ አልገባም።
የእሱ ምሳሌ ሌሎችን ሊጠቅም እንደሚችል ስለተገነዘበ ደቀ መዛሙርቱን አይዟችሁ! ብሏቸዋል።
በጉባኤህ ያሉ ወንድሞችና እህቶችም ድጋፍ ሊሰጡህ ይችላሉ።
የጉባኤው አባላት የሚያጋጥሙህን ተፈታታኝ ሁኔታዎች ካወቁ ሊያበረታቱህ ይችላሉ።
ስለ አንተ እንዲጸልዩ ጠይቃቸው።
እርግጥ ነው፣ ወንድሞቻችን እንዲያበረታቱንና እንዲጸልዩልን የምንፈልግ ከሆነ እኛም ለእነሱ እንዲሁ ልናደርግላቸው ይገባል።
ዮፍታሔ ስለ እስራኤላውያን ታሪክ በሚገባ ማወቁ፣ በይሖዋ ዓይን ትክክል ስለሆነውና ስህተት ስለሆነው ነገር ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረው አድርጓል።
በሙሴ ሕግ ውስጥ የሚገኙት አምላክ ያወጣቸው መሠረታዊ ሥርዓቶች በዮፍታሔ አስተሳሰብና ስሜት ላይ ተጽዕኖ አሳድረዋል።
ይሖዋ ቂም መያዝን ይጠላል፤ ሕዝቦቹም እርስ በርስ እንዲዋደዱ ይፈልጋል፤ ዮፍታሔ ይህን ያውቅ ነበር።
በተጨማሪም አንድ ሰው የሚጠሉት ሰዎች እንኳ ችግር ላይ ሲወድቁ ዝም ብሎ ማለፉ ተገቢ አለመሆኑን ሕጉ እንደሚያስተምር ያውቃል።
እንደ ዮሴፍ ያሉ የእምነት ምሳሌዎችም በዮፍታሔ አመለካከት ላይ ተጽዕኖ ሳያሳድሩ አልቀሩም፤ ዮሴፍ ወንድሞቹ ቢጠሉትም ምሕረት አሳይቷቸዋል።
ዮፍታሔ እንዲህ ያሉ ሰዎች በተዉት ምሳሌ ላይ ማሰላሰሉ፣ ይሖዋን የሚያስደስት እርምጃ እንዲወስድ ረድቶታል።
ወንድሞቹ ያደረጉት ነገር በጣም እንደጎዳው ግልጽ ነው፤ ይሁንና ይህ ሁኔታ ይሖዋንና ሕዝቦቹን ከማገልገል ወደኋላ እንዲል አላደረገውም።
የአምላክ ሕዝቦች የመናገር ይኸውም በቋንቋ የመጠቀም ችሎታቸውን ምንጊዜም ይሖዋን ለማወደስና ፈቃዱን ለሰዎች ለማሳወቅ ያውሉታል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ በቋንቋ አማካኝነት ንጹሑን አምልኮ ማስፋፋት የተቻለበት ዋነኛ መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ነው።
በሺዎች የሚቆጠሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ቢኖሩም በበኩረ ጽሑፉ ላይ የሚገኘውን መልእክት በታማኝነት የሚያስተላልፉት ግን ሁሉም አይደሉም።
በ1940ዎቹ ዓመታት የአዲስ ዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ኮሚቴ ለመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መሠረት ሆነው የሚያገለግሉ መመሪያዎችን አዘጋጀ፤ እነዚህን መመሪያዎች ከ130 በሚበልጡ ቋንቋዎች ተግባራዊ አድርገናል።
መመሪያዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦ ትክክለኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም 1 የአምላክ ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቀድሞ በነበረበት ትክክለኛ ቦታ ላይ መልሶ እንዲገባ በማድረግ የአምላክን ስም ያስቀድሳል።
2 የቋንቋው ሥርዓት እስከፈቀደለት ድረስ መጽሐፍ ቅዱስ መጀመሪያ በተጻፈበት ቋንቋ ውስጥ ለሚገኘው ሐሳብ ቀጥተኛ ፍቺ ይሰጣል፤ ቃል በቃል መተርጎም ሊተላለፍ የተፈለገውን መልእክት የሚያዛባ ከሆነ ግን የቃሉን ወይም የሐረጉን ትክክለኛ መንፈስ ለማስተላለፍ ይጥራል።
3 ለማንበብ የሚማርክና ለመረዳት የማያስቸግር ቋንቋ ይጠቀማል።
አምላክ ለሰው ልጆች ፍቅር ባይኖረው የወደፊት ሕይወታችን ምን ሊመስል እንደሚችል እስቲ አስበው።
ሰይጣን ዲያብሎስ አምላክ የሆነለት ብሎም በሰብዓዊ አገዛዝ የሚመራው ይህ ዓለም ያስመዘገበውን አሰቃቂ ታሪክ መመልከቱ ብቻ በቂ ነው፤ ሰይጣን ፍቅር የሌለው ከመሆኑም ሌላ በቁጣ ተሞልቷል።
አፍቃሪ የሆነው አምላክ አመራር ባይኖር ኖሮ በጽንፈ ዓለም ውስጥ ያሉ ፍጥረታት የወደፊት ሕይወት ምን ያህል አስከፊ ሊሆን እንደሚችል ከዚህ መረዳት ይቻላል።
ዲያብሎስ በይሖዋ አገዛዝ ላይ ባመፀበት ጊዜ የአምላክ ጽንፈ ዓለማዊ አገዛዝ ትክክለኛና ጽድቅ የሰፈነበት ስለመሆኑ ጥያቄ አንስቷል።
በሌላ አባባል ሰይጣን የእሱ አገዛዝ ከፈጣሪ አገዛዝ የተሻለ እንደሚሆን መናገሩ ነበር።
ሰይጣን ያነሳው ጥያቄ ትክክል መሆኑን ለማሳየት እንዲሞክር ይሖዋ ጊዜ የሰጠው ቢሆንም ይህ ጊዜ ገደብ አለው።
ይሖዋ ከእሱ በቀር ሌሎች አገዛዞች በሙሉ ብቃት እንደሌላቸው በማያሻማ መንገድ መረጋገጥ እንዲችል በቂ ጊዜ በመስጠት ታላቅ ጥበቡን አሳይቷል።
አሳዛኝ የሆነው የሰው ዘር ታሪክ እንደሚያሳየው የሰው ልጆችም ሆኑ ሰይጣን መልካም አገዛዝ እንዲሰፍን ማድረግ አይችሉም።
እንደ ወንድማማች እንዋደዳለን ሲባል ምን ማለት ነው?
ጳውሎስ የተጠቀመበት ፊላደልፊያ የሚለው የግሪክኛ ቃል ቀጥተኛ ፍቺ፣ አንድ ሰው ለወንድሙ ያለውን ፍቅር ያመለክታል።
የወንድማማች መዋደድ የሚለው አገላለጽ ለቤተሰባችን አባል ወይም ለቅርብ ወዳጃችን የሚኖረንን ዓይነት ጠንካራ፣ የጠበቀና ጥልቅ ፍቅር ያመለክታል።
እንዲህ ዓይነት ፍቅር እናሳያለን ሲባል ወንድማማችና እህትማማች መስለን ለመታየት እንሞክራለን ማለት አይደለም፤ ወንድማማችና እህትማማች ነን።
የሚከተለው ጥቅስ በመካከላችን ያለውን የጠበቀ ወዳጅነት በሚገባ ይገልጸዋል፦ በወንድማማች ፍቅር እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ።
አንዳችሁ ሌላውን ለማክበር ቀዳሚ ሁኑ።
በመሠረታዊ ሥርዓት በሚመራው አጋፔ በተባለው ፍቅር ላይ የወንድማማች መዋደድ ሲጨመር በአምላክ ሕዝቦች መካከል የጠበቀ ወዳጅነት እንዲኖር ያደርጋል።
ለክርስቲያኖች ዜግነት ለውጥ አያመጣም፤ ሁሉም አማኞች ወንድማማች ናቸው።
ወንድማማች እንደመሆናችን መጠን ይሖዋ አንዳችን ለሌላው የወንድማማች ፍቅር እንዲኖረን አስተምሮናል።
ለኢየሱስ ያለን ፍቅር በስብከቱና ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ በሙሉ ነፍሳችን እንድንካፈል ሊያነሳሳን ይገባል።
በመታሰቢያው በዓል ወቅት በረዳት አቅኚነት በማገልገል በስብከቱ ሥራ 30 ወይም 50 ሰዓት ለማሳለፍ አጋጣሚ እናገኛለን።
አንተስ ሁኔታህን አመቻችተህ እንዲህ ማድረግ ትችላለህ?
ባለቤታቸውን በሞት ያጡ አንድ የ84 ዓመት አረጋዊ፣ ዕድሜያቸውና ጤናቸው በረዳት አቅኚነት ለማገልገል እንደማይፈቅድላቸው ተሰምቷቸው ነበር።
ይሁንና በአካባቢው የሚገኙ አቅኚዎች እኚህን ወንድም ለመርዳት ፈለጉ።
አቅኚዎቹ እኚህን ወንድም በመኪና ይወስዷቸው የነበረ ሲሆን እሳቸው ሊያገለግሉበት የሚችሉ ጥሩ ክልል መረጡላቸው፤ በመሆኑም ወንድም የ30 ሰዓት ግባቸው ላይ መድረስ ቻሉ።
አንተስ አንድ ክርስቲያን በመታሰቢያው በዓል ሰሞን ረዳት አቅኚ ሆኖ በማገልገል የሚገኘውን ደስታ እንዲያጣጥም ልታግዘው ትችላለህ?
እርግጥ ነው፣ ረዳት አቅኚ ሆነን ማገልገል የምንችለው ሁላችንም አይደለንም።
ያም ቢሆን ያለንን ጊዜና ጉልበት ተጠቅመን ለይሖዋ የምናቀርበውን የውዳሴ መሥዋዕት መጠን ከፍ ማድረግ እንችላለን።
ክርስቶስ ኃይል ያገኘው ከይሖዋ ነው፤ በመሆኑም ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ የተፈጥሮ ኃይሎችን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር እንደሚችል እርግጠኞች ለመሆን የሚያበቃ ምክንያት አለን።
እስቲ አንዳንድ ምሳሌዎች እንመልከት።
ከጥፋት ውኃ በፊት ይሖዋ ከሰባት ቀን በኋላ በምድር ላይ 40 ቀንና 40 ሌሊት ዝናብ አዘንባለሁ ብሎ ነበር።
በተመሳሳይም ይሖዋም ሌሊቱን ሙሉ ኃይለኛ የምሥራቅ ነፋስ በማምጣት ባሕሩ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ ይላል።
ላይ ደግሞ ይሖዋ በባሕሩ ላይ ኃይለኛ ነፋስ አመጣ፤ ከባድ ማዕበል ስለተነሳ መርከቧ ልትሰበር ተቃረበች የሚል ሐሳብ እናገኛለን።
ይሖዋ የተፈጥሮ ኃይሎችን እንደሚቆጣጠር ማወቁ የሚያጽናና ነው።
ከዚህ በግልጽ ማየት እንደሚቻለው የፕላኔታችን የወደፊት ዕጣ አስጊ አይደለም።
የአምላክ ድንኳን ከሰዎች ጋር ስለሚሆን በተፈጥሮ ኃይሎች ምክንያት የሚሞቱ ወይም የአካል ጉዳተኛ የሚሆኑ ሰዎች እንደማይኖሩ ማወቁ እንዴት ያስደስታል! በሺው ዓመት ግዛት ወቅት አምላክ በክርስቶስ በኩል ኃይሉን በመጠቀም የተፈጥሮ ኃይሎችን እንደሚቆጣጠር መተማመን እንችላለን።
ይሖዋ ጽናትንና መጽናኛን የሚሰጥ አምላክ ነው።
የሚያጋጥሙንን ችግሮች ብቻ ሳይሆን ያለንበት ሁኔታ፣ ስሜታችን እንዲሁም ተፈጥሯችን የሚያስከትሉብንን ጫና ሙሉ በሙሉ ሊረዳልን የሚችለው እሱ ብቻ ነው።
በመሆኑም እንድንጸና ከማንም በተሻለ ሊረዳን የሚችለው ይሖዋ ነው።
ታዲያ አምላክ ለመጽናት የሚያስችል ብርታት እንዲሰጠን ስንጸልይ መልስ የሚሰጠን እንዴት ነው?
ይሖዋ የደረሰብንን መከራ መወጣት እንድንችል ስንጠይቀው መውጫ መንገዱን ያዘጋጅልናል።
ይህ ሲባል ይሖዋ ጣልቃ ገብቶ መከራውን ያስወግደዋል ማለት ነው?
አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ ሊያደርግ ይችላል።
ብዙ ጊዜ ግን መውጫ መንገዱን የሚያዘጋጅልን ፈተናውን በጽናት መቋቋም እንድንችል በመርዳት ነው።
ይሖዋ በትዕግሥትና በደስታ ሁሉንም ነገር በጽናት እንድንቋቋም የሚያስፈልገንን ብርታት ይሰጠናል።
ደግሞም ይሖዋ ከአካላችን፣ ከአእምሯችንና ከስሜታችን ጋር በተያያዘ አቅማችን ምን ያህል እንደሆነ በሚገባ ስለሚያውቅ ታማኝነታችንን መጠበቅ እስኪያቅተን ድረስ እንድንፈተን አይፈቅድም።
ለአምላክ መንግሥት በታማኝነት ለመገዛት የገለልተኝነት አቋማችንን መጠበቅ ይኖርብናል።
እንዲህ የማናደርግ ከሆነ ለሰው ልጆች ችግሮች መፍትሔ የሚያመጣው የአምላክ መንግሥት ብቻ እንደሆነ የሚገልጸውን ምሥራች በንጹሕ ሕሊና መስበክ እንዴት እንችላለን?
በሌላ በኩል ደግሞ በፖለቲካ ውስጥ በመግባት ምዕመኖቻቸው እንዲከፋፈሉ ከሚያደርጉት የሐሰት ሃይማኖቶች በተለየ፣ እውነተኛው አምልኮ የገለልተኝነት አቋማችንን እንድንጠብቅ በመርዳት ዓለም አቀፋዊ የወንድማማች ማኅበር እንዲኖረን ያደርጋል።
የሰይጣን ሥርዓት ወደ መጨረሻው እየተቃረበ ሲሄድ የገለልተኝነት አቋምን መጠበቅ ይበልጥ አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል እንጠብቃለን።
የምንኖረው ለመስማማት ፈቃደኞች ያልሆኑ እንዲሁም ግትር የሆኑ ሰዎች በሞሉበት ዓለም ውስጥ በመሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህ ዓለም ይበልጥ እየተከፋፈለ መሄዱ አይቀርም።
በአንዳንድ አገሮች ፖለቲካዊ ሁኔታዎች በፍጥነት በመለዋወጣቸው፣ ወንድሞቻችን ከገለልተኝነት ጋር የተያያዙ ያልተጠበቁ ፈተናዎች አጋጥመዋቸዋል።
እንግዲያው ገለልተኝነታችንን ለመጠበቅ አሁኑኑ አቋማችንን ማጠናከር እንዳለብን አስተዋላችሁ?
ፈታኝ ሁኔታ እስኪፈጠር ድረስ እጃችንን አጣጥፈን የምንጠብቅ ከሆነ አቋማችንን ልናላላና ገለልተኛ ሳንሆን ልንቀር እንችላለን።
በክርስቲያኖች መካከል የሚፈጠሩ አብዛኞቹ አለመግባባቶች በራሳቸው በግለሰቦቹ ብቻ መፈታት ይችላሉ፤ ደግሞም እንዲህ መደረግ አለበት።
ይሁንና ኢየሱስ እንደተናገረው አንዳንድ ጉዳዮችን ለጉባኤው መንገር ሊያስፈልግ ይችላል።
አንድ ግለሰብ የበደለውን ወንድም፣ ምሥክሮችን እንዲሁም ጉባኤውን ለመስማት ፈቃደኛ ባይሆንስ?
ይህ ሰው እንደ አሕዛብና እንደ ቀረጥ ሰብሳቢ መቆጠር ይኖርበታል።
ይህም በዛሬው ጊዜ ውገዳ ብለን የምንጠራው እርምጃ ነው።
እንዲህ ዓይነት ከባድ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑ የተፈጸመው በደል ቀላል አለመግባባት ብቻ እንዳልሆነ ያሳያል።
ከዚህ ይልቅ ጉዳዩ 1 የሚመለከታቸው ግለሰቦች ከተስማሙ እነሱ ራሳቸው ሊፈቱት የሚችሉ 2 ካልፈቱት ግን ለውገዳ የሚያበቃ ከባድ በደል መሆን አለበት።
እንዲህ ያለው በደል፣ ከማጭበርበር ወይም የአንድን ሰው ስም ሆን ብሎ ከማጥፋት ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል።
ኢየሱስ ላይ የጠቀሳቸው ሦስቱም እርምጃዎች ተግባራዊ የሚደረጉት ከላይ ያሉት ሁለት ሁኔታዎች ከተሟሉ ብቻ ነው።
የአምላክ ቃል ለሰብዓዊ መንግሥታት እንድንታዘዝ ያስተምረናል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከሰው ይልቅ አምላክን መታዘዝ እንዳለብን ይገልጻል።
ታዲያ እነዚህ ሐሳቦች እርስ በርስ ይጋጫሉ?
በጭራሽ! በአንጻራዊ ሁኔታ ስለመገዛት የሚገልጸው መሠረታዊ ሥርዓት እነዚህን ትእዛዛት ለመረዳትና ለመፈጸም ያስችለናል።
ኢየሱስ የዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን ሐሳብ ሲናገር ይህን መሠረታዊ ሥርዓት ጠቅለል አድርጎ ገልጾታል።
የምንኖርበት አገር መንግሥት የሚያወጣቸውን ሕጎች በመታዘዝ፣ ባለሥልጣናቱን በማክበር እንዲሁም ቀረጥ በመክፈል ለመንግሥት ሥልጣን እንገዛለን።
ይሁንና የመንግሥት ባለሥልጣናት የአምላክን ትእዛዝ እንድንጥስ ቢያዙን ይህን እንደማናደርግ በአክብሮት እንገልጻለን።
በዚህ ዓለም ፖለቲካዊ ጉዳዮች ረገድ የገለልተኝነት አቋም እንይዛለን።
ሰብዓዊ መንግሥታት ሥልጣን እንዲይዙ የፈቀደላቸው ይሖዋ ስለሆነ አንቃወማቸውም፤ ብሔራዊ ስሜት የሚንጸባረቅባቸው እንቅስቃሴዎችንም አናካሂድም።
በፖለቲካ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር አንሞክርም፤ በምርጫ አንካፈልም ወይም ፖለቲካዊ ሥልጣን አንይዝም፤ አሊያም ደግሞ መንግሥት ለመለወጥ ጥረት አናደርግም።
እያንዳንዳችን የምንወደው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይኖረናል።