text stringlengths 4 267 |
|---|
አምላክ ሆይ፣ መንገዶችህ ቅዱስ ናቸው። አምላክ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ ማን ነው? |
አንተ ድንቅ ነገሮችን የምታከናውን እውነተኛ አምላክ ነህ። ብርታትህን ለሕዝቦች ገልጠሃል። |
በኃይልህ ሕዝብህን ይኸውምየያዕቆብንና የዮሴፍን ልጆች ታድገሃል። (ሴላ) |
አምላክ ሆይ፣ ውኃዎቹ አዩህ፤ውኃዎቹ ሲያዩህ ተረበሹ። ጥልቅ ውኃዎቹም ተናወጡ። |
ደመናት ውኃ አዘነቡ። በደመና የተሸፈኑት ሰማያት አንጎደጎዱ፤ፍላጻዎችህም እዚህም እዚያም ተወነጨፉ። |
የነጎድጓድህ ድምፅ እንደ ሠረገላ ድምፅ ነበር፤የመብረቅ ብልጭታዎች በዓለም ላይ አበሩ፤ምድር ተናወጠች፤ ደግሞም ተንቀጠቀጠች። |
መንገድህ በባሕር ውስጥ ነበር፤ጎዳናህም በብዙ ውኃዎች ውስጥ ነበር፤ይሁንና የእግርህ ዱካ ሊገኝ አልቻለም። |
ሕዝብህን በሙሴና በአሮን እጅእንደ መንጋ መራህ። |
አምላክ ሆይ፣ የማቀርበውን ልመና ስማ። ጠላት ከሚሰነዝርብኝ አስፈሪ ጥቃት ሕይወቴን ታደግ። |
ከክፉ ሰዎች ስውር ሴራ፣ከክፉ አድራጊዎች ሸንጎ ጠብቀኝ፤ |
እነሱ ምላሳቸውን እንደ ሰይፍ ይስላሉ፤መርዘኛ ቃላቸውን እንደ ቀስት ያነጣጥራሉ፤ |
ይህን የሚያደርጉት ከተደበቁበት ቦታ ሆነው ንጹሑን ሰው ለመምታት ነው፤ያላንዳች ፍርሃት በድንገት ይመቱታል። |
ክፉ ዓላማቸውን ከመፈጸም ወደኋላ አይሉም፤በስውር እንዴት ወጥመድ እንደሚዘረጉ ይነጋገራሉ። “ማን ያየዋል?” ይላሉ። |
ክፉ ነገር ለመሥራት አዳዲስ መንገዶች ይቀይሳሉ፤የረቀቀ ሴራቸውን በስውር ይሸርባሉ፤በእያንዳንዳቸው ልብ ውስጥ ያለው ሐሳብ አይደረስበትም። |
ሆኖም አምላክ ይመታቸዋል፤እነሱም በድንገት በቀስት ይቆስላሉ። |
የገዛ ምላሳቸው ለውድቀት ይዳርጋቸዋል፤ይህን የሚመለከቱ ሁሉ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ። |
በዚህ ጊዜ ሰዎች ሁሉ ይፈራሉ፤አምላክ ያደረገውንም ነገር ያውጃሉ፤ሥራውንም በሚገባ ያስተውላሉ። |
ጻድቅ ሰው በይሖዋ ሐሴት ያደርጋል፤ እሱንም መጠጊያው ያደርጋል፤ቀና ልብ ያላቸውም ሁሉ ይደሰታሉ። |
ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤እሱ አስደናቂ ነገሮች አድርጓልና። ቀኝ እጁ፣ አዎ ቅዱስ ክንዱ መዳን አስገኝቷል። |
ይሖዋ ማዳኑ እንዲታወቅ አድርጓል፤በብሔራት ፊት ጽድቁን ገልጧል። |
ለእስራኤል ቤት ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ለማሳየት የገባውን ቃል አስታውሷል። የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን አይተዋል። |
ምድር ሁሉ፣ ለይሖዋ በድል አድራጊነት እልል በሉ። ደስ ይበላችሁ፤ ደግሞም እልል በሉ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩ። |
ለይሖዋ በበገና የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤በበገናና ደስ በሚል ዜማ ዘምሩለት። |
በእምቢልታና በቀንደ መለከት ድምፅበንጉሡ በይሖዋ ፊት በድል አድራጊነት እልል በሉ። |
ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ፣መሬትና በላይዋ የሚኖር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰሙ። |
ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፤ተራሮችም በአንድነት በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ፤ |
እሱ በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነውና። በዓለም ላይ በጽድቅ፣በሕዝቦችም ላይ በትክክል ይፈርዳል። |
ዓይኖቼን ወደ ተራሮች አነሳለሁ። እርዳታ የማገኘው ከየት ነው? |
እኔን የሚረዳኝሰማይንና ምድርን የሠራው ይሖዋ ነው። |
እሱ እግርህ እንዲንሸራተት ፈጽሞ አይፈቅድም። ጠባቂህ በጭራሽ አያንቀላፋም። |
እነሆ፣ እስራኤልን የሚጠብቀው፣ፈጽሞ አያንቀላፋም፤ ደግሞም አይተኛም። |
ይሖዋ ይጠብቅሃል። ይሖዋ በቀኝህ ሆኖ ይጋርድሃል። |
ቀን ፀሐይ አይመታህም፤ሌሊትም ጨረቃ አይጎዳህም። |
ይሖዋ ከማንኛውም ጉዳት ይጠብቅሃል። እሱ ሕይወትህን ይጠብቃል። |
ይሖዋ ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣በምታደርገው ነገር ሁሉ ይጠብቅሃል። |
ተስፋዬን ሙሉ በሙሉ በይሖዋ ላይ ጣልኩ፤እሱም ጆሮውን ወደ እኔ አዘነበለ፤ ለእርዳታ ያሰማሁትንም ጩኸት ሰማ። |
የሚያስገመግም ድምፅ ካለበት ጉድጓድ፣ከሚያዘቅጥ ማጥም አወጣኝ። እግሮቼንም በዓለት ላይ አቆመ፤አረማመዴንም አጸና። |
ከዚያም በአፌ ላይ አዲስ መዝሙር፣ለአምላካችን የሚቀርብ ውዳሴ አኖረ። ብዙዎች በፍርሃት ተውጠው ይመለከታሉ፤በይሖዋም ይታመናሉ። |
በይሖዋ የሚታመን፣ እንቢተኛ ወደሆኑት ወይምሐሰት ወደሆኑት ፊቱን ያላዞረ ሰው ደስተኛ ነው። |
ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ያደረግካቸው ድንቅ ሥራዎች፣ለእኛ ያሰብካቸው ነገሮችም ብዙ ናቸው። ከአንተ ጋር ሊወዳደር የሚችል ማንም የለም፤ስለ እነዚህ ነገሮች ላውራ፣ ልናገር ብል፣ዘርዝሬ ልጨርሳቸው አልችልም! |
መሥዋዕትንና መባን አልፈለግክም፤ከዚህ ይልቅ እንድሰማ ጆሮዎቼን ከፈትክልኝ። የሚቃጠል መባና የኃጢአት መባ እንዲቀርብልህ አልጠየቅክም። |
በዚህ ጊዜ እንዲህ አልኩ፦ “እነሆ፣ መጥቻለሁ። ስለ እኔ በመጽሐፍ ጥቅልል ተጽፏል። |
አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህን ማድረግ ያስደስተኛል፤ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው። |
በታላቅ ጉባኤ መካከል የጽድቅን ምሥራች አውጃለሁ። ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ራስህ በሚገባ እንደምታውቀው፣እነሆ፣ ከንፈሮቼን አልከለክልም። |
ጽድቅህን በልቤ ውስጥ አልሸሽግም። ታማኝነትህንና ማዳንህን አውጃለሁ። በታላቅ ጉባኤ መካከል ታማኝ ፍቅርህንና እውነትህን አልደብቅም።” |
ይሖዋ ሆይ፣ ምሕረትህን አትንፈገኝ። ታማኝ ፍቅርህና እውነትህ ምንጊዜም ይጠብቁኝ። |
ለመቁጠር እንኳ የሚያታክት መከራ ከቦኛል። የፈጸምኳቸው በርካታ ስህተቶች ስለዋጡኝ መንገዴን ማየት ተስኖኛል፤በራሴ ላይ ካሉት ፀጉሮች እጅግ ይበዛሉ፤ደግሞም ተስፋ ቆረጥኩ። |
ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለማዳን እባክህ ፈቃደኛ ሁን። ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን። |
ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹ ሁሉ፣ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ። በእኔ ላይ በደረሰው ጉዳት ደስ የሚሰኙአፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ። |
“እሰይ! እሰይ!” የሚሉኝ በሚደርስባቸው ኀፍረት የተነሳ ክው ይበሉ። |
አንተን የሚፈልጉ ግንበአንተ ይደሰቱ፤ ሐሴትም ያድርጉ። የማዳን ሥራህን የሚወዱ፣ ምንጊዜም “ይሖዋ ታላቅ ይሁን” ይበሉ። |
እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤ይሖዋ ትኩረት ይስጠኝ። አንተ ረዳቴና ታዳጊዬ ነህ፤አምላኬ ሆይ፣ አትዘግይ። |
ምድር ሁሉ፣ በድል አድራጊነት ለይሖዋ እልል በሉ። |
ይሖዋን በደስታ አገልግሉት። በእልልታ ወደ ፊቱ ቅረቡ። |
ይሖዋ፣ አምላክ መሆኑን እወቁ። የሠራን እሱ ነው፤ እኛም የእሱ ንብረት ነን። እኛ ሕዝቡና የማሰማሪያው በጎች ነን። |
በምስጋና ወደ በሮቹ፣በውዳሴም ወደ ቅጥር ግቢዎቹ ግቡ። ምስጋና አቅርቡለት፤ ስሙንም አወድሱ። |
ይሖዋ ጥሩ ነውና፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም፣ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል። |
ይሖዋ ነገሠ። ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ። እሱ ከኪሩቤል በላይ በዙፋን ተቀምጧል። ምድር ትናወጥ። |
ይሖዋ በጽዮን ታላቅ ነው፤ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው። |
ሕዝቦች ታላቅ ስምህን ያወድሱ፤ስምህ እጅግ የሚፈራና ቅዱስ ነውና። |
እሱ ፍትሕን የሚወድ ኃያል ንጉሥ ነው። አንተ ቅን የሆነውን ነገር በጽኑ መሥርተሃል። ፍትሕንና ጽድቅን ለያዕቆብ አስፍነሃል። |
ይሖዋ አምላካችንን ከፍ ከፍ አድርጉት፤ በእግሩ ማሳረፊያ ፊት ስገዱ፤እሱ ቅዱስ ነው። |
ከካህናቱ መካከል ሙሴና አሮን ይገኙበታል፤ስሙን ከሚጠሩ መካከልም ሳሙኤል አንዱ ነው። እነሱ ወደ ይሖዋ ይጣሩ ነበር፤እሱም ይመልስላቸው ነበር። |
በደመና ዓምድ ውስጥ ሆኖ ያነጋግራቸው ነበር። ማሳሰቢያዎቹንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠብቀዋል። |
አምላካችን ይሖዋ ሆይ፣ አንተ መልስ ሰጠሃቸው። ይቅር ባይ አምላክ ሆንክላቸው፤ሆኖም ለሠሯቸው ኃጢአቶች ቀጣሃቸው። |
አምላካችንን ይሖዋን ከፍ ከፍ አድርጉት፤በቅዱስ ተራራውም ፊት ስገዱ፤አምላካችን ይሖዋ ቅዱስ ነውና። |
እናንተ የኃያላን ልጆች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ። |
ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ። ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ ለይሖዋ ስገዱ። |
የይሖዋ ድምፅ ከውኃዎች በላይ ተሰማ፤ክብር የተጎናጸፈው አምላክ አንጎደጎደ። ይሖዋ ከብዙ ውኃዎች በላይ ነው። |
የይሖዋ ድምፅ ኃይለኛ ነው፤የይሖዋ ድምፅ ክብራማ ነው። |
የይሖዋ ድምፅ አርዘ ሊባኖስን ይሰብራል፤አዎ፣ ይሖዋ አርዘ ሊባኖስን ይሰባብራል። |
ሊባኖስን እንደ ጥጃ፣ሲሪዮንንም እንደ ዱር በሬ እንቦሳ እንዲዘሉ ያደርጋል። |
የይሖዋ ድምፅ የእሳት ነበልባል ይረጫል፤ |
የይሖዋ ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፤ይሖዋ የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል። |
የይሖዋ ድምፅ ርኤሞች እንዲርበተበቱና እንዲወልዱ ያደርጋል፤ደኖችንም ያራቁታል። በቤተ መቅደሱም ውስጥ ያሉ ሁሉ “ክብር ለአምላክ!” ይላሉ። |
ይሖዋ ከሚያጥለቀልቁት ውኃዎች በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ይሖዋ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ በዙፋን ላይ ይቀመጣል። |
ይሖዋ ለሕዝቡ ብርታት ይሰጣል። ይሖዋ ሰላም በመስጠት ሕዝቡን ይባርካል። |
ጌታችን ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ በመላው ምድር ላይ ምንኛ የከበረ ነው፤ግርማህ ከሰማያትም በላይ ከፍ ከፍ እንዲል አድርገሃል! |
ከባላጋራዎችህ የተነሳ፣ከልጆችና ከሕፃናት አፍ በሚወጡ ቃላት ብርታትህን አሳየህ፤ይህም ጠላትንና ተበቃይን ዝም ለማሰኘት ነው። |
የጣቶችህን ሥራ ሰማያትን፣አንተ የሠራሃቸውን ጨረቃንና ከዋክብትን ስመለከት፣ |
ታስበው ዘንድ ሟች ሰው ምንድን ነው?ትንከባከበውስ ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? |
ከመላእክት በጥቂቱ አሳነስከው፤የክብርና የግርማ ዘውድም ደፋህለት። |
በእጆችህ ሥራዎች ላይ ሥልጣን ሰጠኸው፤ሁሉንም ነገር ከእግሩ በታች አደረግክለት፦ |
መንጎቹንና ከብቶቹን ሁሉ፣እንዲሁም የዱር አራዊትን፣ |
የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሣዎችን፣በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትን ሁሉ ከእግሩ በታች አደረግክለት። |
ጌታችን ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ በመላው ምድር ላይ ምንኛ የከበረ ነው! |
አምላክ ሆይ፣ ውኃ ሕይወቴን አደጋ ላይ ስለጣላት አድነኝ። |
መቆሚያ ስፍራ በሌለበት ጥልቅ ማጥ ውስጥ ሰምጫለሁ። ጥልቅ ውኃዎች ውስጥ ገባሁ፤ኃይለኛ ጅረትም ጠርጎ ወሰደኝ። |
ከመጮኼ ብዛት የተነሳ ደከምኩ፤ድምፄም ጎረነነ። አምላኬን በመጠባበቅ ዓይኖቼ ፈዘዙ። |
ያለምክንያት የሚጠሉኝከራሴ ፀጉር ይልቅ በዙ። ሊያጠፉኝ የሚፈልጉ፣ተንኮለኛ የሆኑ ጠላቶቼ እጅግ በዝተዋል። ያልሰረቅኩትን ነገር እንድመልስ ተገደድኩ። |
አምላክ ሆይ፣ ሞኝነቴን ታውቃለህ፤ጥፋቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም። |
ሉዓላዊ ጌታ የሆንከው የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣አንተን ተስፋ የሚያደርጉ በእኔ የተነሳ አይፈሩ። የእስራኤል አምላክ ሆይ፣አንተን የሚሹ በእኔ የተነሳ አይዋረዱ። |
በአንተ የተነሳ ነቀፋ ይደርስብኛል፤ኀፍረት ፊቴን ይሸፍነዋል። |
ለወንድሞቼ እንደ እንግዳ፣ለእናቴ ልጆች እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆንኩ። |
ለቤትህ ያለኝ ቅንዓት በልቶኛል፤ሰዎች አንተን ይነቅፉበት የነበረው ነቀፋም በእኔ ላይ ደረሰ። |
በጾም ራሴን ባዋረድኩ ጊዜ፣ነቀፋ ደረሰብኝ። |
ማቅ በለበስኩ ጊዜ፣መቀለጃ አደረጉኝ። |
በከተማዋ መግቢያ የሚቀመጡት የመወያያ ርዕስ አደረጉኝ፤ሰካራሞችም ስለ እኔ ይዘፍናሉ። |
ይሁንና ይሖዋ ሆይ፣ ጸሎቴ ተሰሚነት ሊያገኝ በሚችልበት ጊዜወደ አንተ ይድረስ። አምላክ ሆይ፣ በታማኝ ፍቅርህ ብዛት፣አስተማማኝ በሆነው የማዳን ሥራህም መልስልኝ። |
ከማጡ አውጣኝ፤እንድሰምጥ አትፍቀድ። ከሚጠሉኝ ሰዎችናከጥልቁ ውኃ ታደገኝ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.