text
stringlengths
4
267
ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው ሰዎች በንቀት ያፌዙብኛል፤በእኔ ላይ ጥርሳቸውን ያፋጫሉ።
ይሖዋ ሆይ፣ ዝም ብለህ የምታየው እስከ መቼ ነው? ከሚሰነዝሩብኝ ጥቃት ታደገኝ፤ውድ ሕይወቴን ከደቦል አንበሶች አድናት።
ያን ጊዜ በታላቅ ጉባኤ መካከል አመሰግንሃለሁ፤በብዙ ሕዝብ መካከል አወድስሃለሁ።
ያላንዳች ምክንያት ጠላቶቼ የሆኑ እኔን አይተው እንዲፈነድቁ፣ያለምክንያት የሚጠሉኝ በተንኮል እንዲጠቃቀሱብኝ አትፍቀድ።
የሰላም ቃል ከአፋቸው አይወጣምና፤ከዚህ ይልቅ በምድሪቱ በሰላም በሚኖሩት ላይ ተንኮል ይሸርባሉ።
እኔን ለመወንጀል አፋቸውን ይከፍታሉ፤“እሰይ! እሰይ! ዓይናችን ይህን አየ” ይላሉ።
ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ተመልክተሃል። ዝም አትበል። ይሖዋ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።
ለእኔ ጥብቅና ለመቆም ንቃ፤ ተነሳም፤ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ተሟገትልኝ።
ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ እንደ ጽድቅህ ፍረድልኝ፤በእኔ እንዲፈነድቁ አትፍቀድ።
በልባቸው “እሰይ! የተመኘነውን አገኘን” አይበሉ። ደግሞም “ዋጥነው” አይበሉ።
እኔ ላይ በደረሰው ጉዳት የሚፈነድቁ ሁሉይፈሩ፣ ይዋረዱም። በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ።
በእኔ ጽድቅ የሚደሰቱ ግን እልል ይበሉ፤ሁልጊዜም እንዲህ ይበሉ፦ “በአገልጋዩ ሰላም የሚደሰተው ይሖዋ ከፍ ከፍ ይበል።”
በዚህ ጊዜ ምላሴ ስለ ጽድቅህ ይናገራል፤ቀኑን ሙሉም ያወድስሃል።
ይሖዋን የሚፈሩ፣በመንገዱም የሚሄዱ ሁሉ ደስተኞች ናቸው።
በእጅህ ደክመህ ያፈራኸውን ትበላለህ። ደስተኛ ትሆናለህ፤ ደግሞም ትበለጽጋለህ።
ሚስትህ በቤትህ ውስጥ፣ ፍሬ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤ወንዶች ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ዛፍ ቡቃያዎች ይሆናሉ።
እነሆ፣ ይሖዋን የሚፈራ ሰውእንደዚህ የተባረከ ይሆናል።
ይሖዋ ከጽዮን ይባርክሃል። በሕይወት ዘመንህ ሁሉ የኢየሩሳሌምን ብልጽግና ለማየት ያብቃህ፤
ደግሞም የልጅ ልጅ ለማየት ያብቃህ። በእስራኤል ሰላም ይስፈን።
አምላክ በይሁዳ የታወቀ ነው፤ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።
መጠለያው በሳሌም ነው፤መኖሪያውም በጽዮን ነው።
በዚያም የሚንበለበሉትን ፍላጻዎች፣ጋሻን፣ ሰይፍንና የጦር መሣሪያዎችን ሰባበረ። (ሴላ)
አንተ ደምቀህ ታበራለህ፤አዳኝ አራዊት ከሚኖሩባቸው ተራሮች ይልቅ ታላቅ ግርማ ተጎናጽፈሃል።
ልበ ሙሉ የሆኑት ሰዎች ተዘርፈዋል። እንቅልፍ ጥሏቸዋል፤ተዋጊዎቹ በሙሉ መከላከል የሚችሉበት ኃይል አልነበራቸውም።
የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ከተግሣጽህ የተነሳባለ ሠረገላውም ሆነ ፈረሱ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷቸዋል።
አንተ ብቻ እጅግ የምትፈራ ነህ። ኃይለኛ ቁጣህን ማን ሊቋቋም ይችላል?
አንተ ከሰማይ ፍርድ ተናገርክ፤ምድር ፈርታ ዝም አለች፤
ይህም የሆነው አምላክ በምድር ላይ የሚኖሩትን የዋሆች ሁሉ ለማዳንፍርድ ሊያስፈጽም በተነሳበት ጊዜ ነው። (ሴላ)
የሰው ቁጣ ለአንተ ውዳሴ ያመጣልና፤በቀረው ቁጣቸው ራስህን ታስጌጣለህ።
ለአምላካችሁ ለይሖዋ ተሳሉ፤ ስእለታችሁንም ፈጽሙ፤በዙሪያው ያሉ ሁሉ በፍርሃት ስጦታቸውን ያምጡ።
እሱ የመሪዎችን ኩራት ያስወግዳል፤በምድር ነገሥታት ላይ ፍርሃት ያሳድራል።
አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ አድርገኸናል፤ መከላከያዎቻችንን ጥሰህ አልፈሃል። ተቆጥተኸናል፤ አሁን ግን መልሰህ ተቀበለን!
ምድርን አናወጥካት፤ ሰነጣጠቅካት። እየፈራረሰች ነውና ስንጥቆቿን ጠግን።
ሕዝብህ መከራ እንዲደርስበት አደረግክ። የወይን ጠጅ እንድንጠጣና እንድንንገዳገድ አደረግከን።
አንተን የሚፈሩ ከቀስት መሸሽና ማምለጥ እንዲችሉምልክት አቁምላቸው። (ሴላ)
የምትወዳቸው ሰዎች እንዲድኑበቀኝ እጅህ ታደገን፤ ደግሞም መልስ ስጠን።
አምላክ በቅድስናው እንዲህ ብሏል፦ “ሐሴት አደርጋለሁ፤ ሴኬምን ርስት አድርጌ እሰጣለሁ፤የሱኮትንም ሸለቆ አከፋፍላለሁ።
ጊልያድም ሆነ ምናሴ የእኔ ናቸው፤ኤፍሬምም የራስ ቁሬ ነው፤ይሁዳ በትረ መንግሥቴ ነው።
ሞዓብ መታጠቢያ ገንዳዬ ነው። በኤዶም ላይ ጫማዬን እጥላለሁ። በፍልስጤም ላይ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።”
ወደተከበበችው ከተማ ማን ይወስደኛል? እስከ ኤዶም ድረስ ማን ይመራኛል?
አምላክ ሆይ፣ ገሸሽ ያደረግከን አንተ አይደለህም?አምላካችን ሆይ፣ ከሠራዊታችን ጋር አብረህ አትወጣም።
ከጭንቅ እንድንገላገል እርዳን፤የሰው ማዳን ከንቱ ነውና።
አምላክ ኃይል ይሰጠናል፤ጠላቶቻችንንም ይረጋግጣቸዋል።
ይሖዋን ሁልጊዜ አወድሰዋለሁ፤ውዳሴው ምንጊዜም ከአፌ አይለይም።
በይሖዋ እኩራራለሁ፤የዋሆች ሰምተው ሐሴት ያደርጋሉ።
ይሖዋን ከእኔ ጋር አወድሱት፤በኅብረት ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።
ይሖዋን ጠየቅኩት፤ እሱም መለሰልኝ። ከምፈራው ነገር ሁሉ ታደገኝ።
እሱን ተስፋ ያደረጉ በደስታ ፈኩ፤ፊታቸው ፈጽሞ ለኀፍረት አይዳረግም።
ይህ ችግረኛ ተጣራ፤ ይሖዋም ሰማው። ከጭንቀቱ ሁሉ ገላገለው።
የይሖዋ መልአክ አምላክን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፤ደግሞም ይታደጋቸዋል።
ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም፤እሱን መጠጊያ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው።
ቅዱሳን አገልጋዮቹ ሁሉ፣ ይሖዋን ፍሩ፤እሱን የሚፈሩ የሚያጡት ነገር የለምና።
ብርቱ ደቦል አንበሶች እንኳ የሚበሉት አጥተው ይራባሉ፤ይሖዋን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጎድልባቸውም።
ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፣ አዳምጡኝ፤ይሖዋን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
ከእናንተ መካከል በሕይወት የሚደሰት፣ብዙ መልካም ዘመን ማየት የሚወድስ ማን ነው?
እንግዲያው ምላስህን ከክፉ ነገር ጠብቅ፤በከንፈሮችህም ከማታለል ተቆጠብ።
ክፉ ከሆነ ነገር ራቅ፤ መልካም የሆነውንም አድርግ፤ሰላምን ፈልግ፤ ተከተለውም።
የይሖዋ ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉ፤ጆሮዎቹም እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትን ጩኸት ይሰማሉ።
ሆኖም የክፉዎችን መታሰቢያ ሁሉ ከምድር ለማጥፋት፣የይሖዋ ፊት በእነሱ ላይ ነው።
ጻድቃን ጮኹ፤ ይሖዋም ሰማቸው፤ከጭንቀታቸውም ሁሉ ገላገላቸው።
ይሖዋ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤መንፈሳቸው የተደቆሰባቸውንም ያድናል።
የጻድቅ ሰው መከራ ብዙ ነው፤ይሖዋ ግን ከመከራው ሁሉ ይታደገዋል።
አጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤አንዳቸውም ቢሆኑ አልተሰበሩም።
ክፉ ሰው በአደጋ ይሞታል፤ጻድቁን የሚጠሉ ሰዎችም ይፈረድባቸዋል።
ይሖዋ የአገልጋዮቹን ሕይወት ይዋጃል፤እሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ አይፈረድባቸውም።
ይሖዋ ሆይ፣ በቁጣህ አትውቀሰኝ፤በታላቅ ቁጣህም አታርመኝ።
ይሖዋ ሆይ፣ ዝያለሁና ሞገስ አሳየኝ። ይሖዋ ሆይ፣ አጥንቶቼ ተንቀጥቅጠዋልና ፈውሰኝ።
አዎ፣ እጅግ ተረብሻለሁ፤ይሖዋ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ድረስ ነው? ብዬ እጠይቅሃለሁ።
ይሖዋ ሆይ፣ ተመለስ፤ ደግሞም ታደገኝ፤ለታማኝ ፍቅርህ ስትል አድነኝ።
ሙታን አንተን አያነሱም፤በመቃብር ማን ያወድስሃል?
ከመቃተቴ የተነሳ ዝያለሁ፤ሌሊቱን ሙሉ መኝታዬን በእንባ አርሳለሁ፤በለቅሶ አልጋዬን አጥለቀልቃለሁ።
በሐዘኔ ምክንያት ዓይኔ ደክሟል፤ከሚያጠቁኝ ሰዎች ሁሉ የተነሳ ዓይኔ ፈዟል።
እናንተ መጥፎ ምግባር ያላችሁ ሁሉ ከእኔ ራቁ፤ይሖዋ የለቅሶዬን ድምፅ ይሰማልና።
ይሖዋ ሞገስ እንዲያሳየኝ የማቀርበውን ልመና ይሰማል፤ይሖዋ ጸሎቴን ይቀበላል።
ጠላቶቼ በሙሉ ያፍራሉ፤ ደግሞም እጅግ ይደነግጣሉ፤በድንገት ውርደት ተከናንበው ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ።
አምላክ ሆይ፣ በጽዮን ውዳሴ ይቀርብልሃል፤የተሳልነውን ለአንተ እንሰጣለን።
ጸሎት ሰሚ የሆንከው አምላክ ሆይ፣ ሁሉም ዓይነት ሰው ወደ አንተ ይመጣል።
የፈጸምኳቸው በደሎች አሸንፈውኛል፤አንተ ግን መተላለፋችንን ይቅር አልክ።
በቅጥር ግቢዎችህ ይኖር ዘንድየመረጥከውና ያቀረብከው ሰው ደስተኛ ነው። እኛም በቤትህ፣ቅዱስ በሆነው ቤተ መቅደስህ ውስጥ ባሉ ጥሩ ነገሮች እንረካለን።
የመዳናችን አምላክ ሆይ፣ፍርሃት በሚያሳድሩ የጽድቅ ተግባሮች ትመልስልናለህ፤በምድር ዳርቻዎች ሁሉናከባሕሩ ማዶ ርቀው ላሉት መታመኛቸው ነህ።
አንተ በኃይልህ ተራሮችን አጽንተህ መሥርተሃል፤ኃይልንም ለብሰሃል።
አንተ የሚናወጡትን ባሕሮች፣ የሞገዶቻቸውን ድምፅ፣የብሔራትንም ነውጥ ጸጥ ታሰኛለህ።
ርቀው በሚገኙ ስፍራዎች የሚኖሩ ሰዎች ምልክቶችህን አይተው በታላቅ አድናቆት ይዋጣሉ፤ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ ያሉ በደስታ እልል እንዲሉ ታደርጋለህ።
ምድርን እጅግ ፍሬያማ በማድረግናበማበልጸግ ትንከባከባታለህ። የአምላክ ጅረት በውኃ የተሞላ ነው፤ለሰዎች እህል ትሰጣለህ፤ምድርን ያዘጋጀኸው በዚህ መንገድ ነውና።
ትልሞቿን በውኃ ታረሰርሳለህ፤ የታረሰውንም መሬት ትደለድላለህ፤በካፊያ ታለሰልሳታለህ፤ ቡቃያዋንም ትባርካለህ።
ዘመኑ ጥሩነትህን እንደ ዘውድ እንዲጎናጸፍ ታደርጋለህ፤በጎዳናዎችህም ላይ የተትረፈረፉ ነገሮች ይፈስሳሉ።
የምድረ በዳው የግጦሽ መሬቶች ሁልጊዜ እንደረሰረሱ ናቸው፤ኮረብቶቹም ደስታን ተጎናጽፈዋል።
የግጦሽ መሬቶቹ በመንጎች ተሞሉ፤ሸለቆዎቹም በእህል ተሸፈኑ። በድል አድራጊነት እልል ይላሉ፤ አዎ፣ ይዘምራሉ።
ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ አምላክ እጮኻለሁ፤ወደ አምላክ እጮኻለሁ፤ እሱም ይሰማኛል።
በጭንቀት በተዋጥኩ ቀን ይሖዋን እፈልጋለሁ። በሌሊት እጆቼ ያለምንም ፋታ ወደ እሱ እንደተዘረጉ ናቸው፤ ልጽናና አልቻልኩም።
አምላክን ሳስታውስ እቃትታለሁ፤ተጨንቄአለሁ፤ ኃይሌም ከዳኝ። (ሴላ)
የዓይኔ ቆብ እንዳይከደን ያዝከው፤በጣም ተረብሻለሁ፤ መናገርም አልችልም።
የድሮውን ጊዜ መለስ ብዬ አሰብኩ፤የጥንቶቹን ዓመታት አስታወስኩ።
መዝሙሬን በሌሊት አስታውሳለሁ፤በልቤ አወጣለሁ አወርዳለሁ፤በጥሞና እመረምራለሁ።
ይሖዋ ለዘላለም ይጥለናል? ዳግመኛስ ሞገስ አያሳየንም?
ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ተቋርጧል? የተስፋ ቃሉስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ከንቱ ሆኖ ይቀራል?
አምላክ ሞገሱን ማሳየት ረስቷል?ወይስ ቁጣው ምሕረት ከማሳየት እንዲቆጠብ አድርጎታል? (ሴላ)
“እኔን የሚያስጨንቀኝ ይህ ነው፦ ልዑሉ አምላክ ለእኛ ያለውን አመለካከት ለውጧል” እያልኩ ልኖር ነው?
ያህ ያከናወናቸውን ሥራዎች አስታውሳለሁ፤ጥንት የፈጸምካቸውን ድንቅ ተግባሮች አስታውሳለሁ።
በሥራዎችህም ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤ያከናወንካቸውንም ነገሮች አውጠነጥናለሁ።