text stringlengths 4 267 |
|---|
ደራሽ ውኃ ጠርጎ እንዲወስደኝ አትፍቀድ፤ጥልቁም አይዋጠኝ፤የጉድጓዱም አፍ በእኔ ላይ አይዘጋ። |
ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ጥሩ ስለሆነ መልስልኝ። እንደ ምሕረትህ ብዛት ወደ እኔ ተመልከት፤ |
ፊትህንም ከአገልጋይህ አትሰውር። ጭንቅ ውስጥ ነኝና በፍጥነት መልስልኝ። |
ወደ እኔ ቀርበህ ታደገኝ፤ከጠላቶቼ የተነሳ ዋጀኝ። |
የደረሰብኝን ነቀፋ፣ ኀፍረትና ውርደት ታውቃለህ። ጠላቶቼን በሙሉ ታያለህ። |
የተሰነዘረብኝ ነቀፋ ልቤን ሰብሮታል፤ ቁስሉም የሚድን ዓይነት አይደለም። የሚያዝንልኝ ሰው ለማግኘት ተመኝቼ ነበር፤ ሆኖም አንድም ሰው አልነበረም፤የሚያጽናናኝ ሰውም ለማግኘት ስጠባበቅ ነበር፤ ሆኖም አንድም ሰው አላገኘሁም። |
ይልቁንም መርዝ እንድበላ ሰጡኝ፤በጠማኝ ጊዜም ኮምጣጤ እንድጠጣ ሰጡኝ። |
ማዕዳቸው ወጥመድ፣ብልጽግናቸውም አሽክላ ይሁንባቸው። |
ዓይኖቻቸው ማየት እንዳይችሉ ይጨልሙ፤ሰውነታቸውም ምንጊዜም እንዲንቀጠቀጥ አድርግ። |
ቁጣህን አውርድባቸው፤የሚነደው ቁጣህም ድንገት ይምጣባቸው። |
ሰፈራቸው ወና ይሁን፤በድንኳኖቻቸው የሚኖር ሰው አይገኝ። |
አንተ የመታኸውን አሳደዋልና፤ደግሞም አንተ ያቆሰልካቸውን ሰዎች ሥቃይ ሁልጊዜ ያወራሉ። |
በበደላቸው ላይ በደል ጨምርባቸው፤ከአንተም ጽድቅ ምንም ድርሻ አይኑራቸው። |
ከሕያዋን መጽሐፍ ይደምሰሱ፤በጻድቃንም መካከል አይመዝገቡ። |
እኔ ግን በጭንቅና በሥቃይ ላይ ነኝ። አምላክ ሆይ፣ የማዳን ኃይልህ ይጠብቀኝ። |
ለአምላክ ስም የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ፤እሱንም በምስጋና ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ። |
ይህ ከበሬ ይበልጥ ይሖዋን ያስደስተዋል፤ቀንድና ሰኮና ካለው ወይፈን ይበልጥ ደስ ያሰኘዋል። |
የዋሆች ይህን ያያሉ፤ ሐሴትም ያደርጋሉ። እናንተ አምላክን የምትፈልጉ፣ ልባችሁ ይነቃቃ። |
ይሖዋ ድሆችን ይሰማልና፤በምርኮ ላይ ያለውን ሕዝቡንም አይንቅም። |
ሰማይና ምድር፣ባሕርና በውስጡ የሚንቀሳቀሱ ሁሉ ያወድሱት። |
አምላክ ጽዮንን ያድናታልና፤የይሁዳንም ከተሞች መልሶ ይገነባል፤እነሱም በዚያ ይኖራሉ፤ ደግሞም ይወርሷታል። |
የአገልጋዮቹ ዘሮች ይወርሷታል፤ስሙን የሚወዱም በእሷ ላይ ይኖራሉ። |
ያህን አወድሱ! እናንተ የይሖዋ አገልጋዮች፣ ውዳሴ አቅርቡ፤የይሖዋን ስም አወድሱ። |
ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም፣የይሖዋ ስም ይወደስ። |
ከፀሐይ መውጫ አንስቶ እስከ መግቢያው ድረስየይሖዋ ስም ይወደስ። |
ይሖዋ ከብሔራት ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ነው፤ክብሩም ከሰማያት በላይ ነው። |
ከፍ ባለ ቦታ እንደሚኖረውእንደ አምላካችን እንደ ይሖዋ ያለ ማን ነው? |
ሰማይንና ምድርን ለማየት ወደ ታች ያጎነብሳል፤ |
ችግረኛውን ከአፈር ያነሳል። ድሃውን ከአመድ ቁልል ላይ ብድግ ያደርገዋል፤ |
ይህም ከታላላቅ ሰዎች፣ይኸውም በሕዝቡ መካከል ካሉ ታላላቅ ሰዎች ጋር ያስቀምጠው ዘንድ ነው። |
መሃኒቱ ሴት፣ ደስተኛ የልጆች እናት ሆና እንድትኖርቤት ይሰጣታል። ያህን አወድሱ! |
የይሖዋ ታማኝ ፍቅር ስለተገለጠባቸው መንገዶች ለዘላለም እዘምራለሁ። ታማኝነትህን ለትውልዶች በሙሉ በአፌ አስታውቃለሁ። |
እንዲህ በማለት ተናግሬአለሁና፦ “ታማኝ ፍቅር ለዘላለም ይገነባል፤ታማኝነትህንም በሰማያት አጽንተህ መሥርተሃል።” |
አንተም እንዲህ ብለሃል፦ “ከመረጥኩት ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ፤ለአገልጋዬ ለዳዊት ምያለሁ፦ |
‘ዘርህ ለዘላለም ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ፤ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’” (ሴላ) |
ይሖዋ ሆይ፣ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣አዎ፣ በቅዱሳን ጉባኤ ታማኝነትህን ያወድሳሉ። |
በሰማያት ከይሖዋ ጋር ማን ሊወዳደር ይችላል? ከአምላክ ልጆች መካከል እንደ ይሖዋ ያለ ማን ነው? |
አምላክ በቅዱሳን ጉባኤ መካከል እጅግ የተፈራ ነው፤በዙሪያው ባሉት ሁሉ መካከል ታላቅና እጅግ የሚከበር ነው። |
የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ኃያል ነህ፤ያህ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አንተ በሁሉም ነገር ታማኝ መሆንህን ታሳያለህ። |
የባሕሩን ሞገድ ትቆጣጠራለህ፤ማዕበሉም ሲነሳ አንተ ራስህ ጸጥ ታሰኘዋለህ። |
አንተ ረዓብን እንደተገደለ ሰው አደቀቅከው። በብርቱ ክንድህ ጠላቶችህን በታተንካቸው። |
ሰማያት የአንተ ናቸው፤ ምድርም የአንተ ናት፤ፍሬያማ የሆነችውን ምድርና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ የሠራኸው አንተ ነህ። |
ሰሜንንና ደቡብን የፈጠርክ አንተ ነህ፤ታቦርና ሄርሞን ስምህን በደስታ ያወድሳሉ። |
ክንድህ ኃያል ነው፤እጅህ ብርቱ ነው፤ቀኝ እጅህም ከፍ ከፍ ያለ ነው። |
ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረት ናቸው፤ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት በፊትህ ናቸው። |
እልልታ የሚያውቁ ሰዎች ደስተኞች ናቸው። ይሖዋ ሆይ፣ እንዲህ ያሉ ሰዎች በፊትህ ብርሃን ይመላለሳሉ። |
በስምህ ቀኑን ሙሉ ሐሴት ያደርጋሉ፤በጽድቅህም ከፍ ከፍ ይላሉ። |
አንተ የብርታታቸው ክብር ነህና፤በሞገስህም ብርታታችን ከፍ ከፍ ብሏል። |
ጋሻችን ከይሖዋ ነውና፤ንጉሣችን ከእስራኤል ቅዱስ ነው። |
በዚያን ጊዜ ለታማኝ አገልጋዮችህ በራእይ ተናገርክ፤ እንዲህም አልክ፦ “ለኃያል ሰው ብርታት ሰጠሁ፤ከሕዝቡም መካከል የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግኩ። |
አገልጋዬን ዳዊትን አገኘሁት፤በተቀደሰ ዘይቴም ቀባሁት። |
እጄ ይደግፈዋል፤ክንዴም ያበረታዋል። |
ማንኛውም ጠላት አያስገብረውም፤የትኛውም ክፉ ሰው አይጨቁነውም። |
ባላጋራዎቹን ከፊቱ አደቃቸዋለሁ፤የሚጠሉትንም እመታቸዋለሁ። |
ታማኝነቴና ታማኝ ፍቅሬ ከእሱ ጋር ናቸው፤በስሜም ኃይሉ ከፍ ከፍ ይላል። |
እጁን በባሕሩ ላይ፣ቀኝ እጁንም በወንዞቹ ላይ አደርጋለሁ። |
እሱም ‘አንተ አባቴ ነህ፤አምላኬና አዳኝ ዓለቴ ነህ’ ብሎ ይጠራኛል። |
እኔም በኩር እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ከምድር ነገሥታትም ሁሉ በላይ አስቀምጠዋለሁ። |
ታማኝ ፍቅሬን ለዘላለም አሳየዋለሁ፤ከእሱ ጋር የገባሁት ቃል ኪዳንም ጸንቶ ይኖራል። |
ዘሩን ለዘላለም አጸናለሁ፤ዙፋኑም የሰማያትን ዕድሜ ያህል ጸንቶ እንዲኖር አደርጋለሁ። |
ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣ድንጋጌዎቼንም አክብረው ባይመላለሱ፣ |
ደንቦቼን ቢጥሱናትእዛዛቴን ባይጠብቁ፣ |
ባለመታዘዛቸው በበትር እቀጣቸዋለሁ፤በደል በመፈጸማቸውም እገርፋቸዋለሁ። |
ሆኖም ለእሱ ታማኝ ፍቅር ማሳየቴን አልተውም፤የገባሁትንም ቃል አላጥፍም። |
ቃል ኪዳኔን አላፈርስም፤ከአንደበቴ የወጣውንም ቃል አለውጥም። |
ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁ፤ዳዊትን አልዋሸውም። |
ዘሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ዙፋኑ በፊቴ እንዳለችው ፀሐይ ይጸናል። |
በሰማያት ታማኝ ምሥክር ሆና እንደምትኖረው እንደ ጨረቃ፣ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።” (ሴላ) |
ሆኖም አንተ ራስህ ጣልከው፤ ደግሞም ገሸሽ አደረግከው፤በተቀባው አገልጋይህ ላይ እጅግ ተቆጣህ። |
ከአገልጋይህ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ወደ ጎን ገሸሽ አደረግክ፤አክሊሉን መሬት ላይ በመጣል አረከስከው። |
በድንጋይ የተገነቡትን ቅጥሮቹን ሁሉ አፈረስክ፤ምሽጎቹን የፍርስራሽ ክምር አደረግክ። |
በዚያ የሚያልፉ ሁሉ ዘረፉት፤የጎረቤቶቹም መሳለቂያ ሆነ። |
ባላጋራዎቹ ድል እንዲጎናጸፉ አድርገሃል፤ጠላቶቹ ሁሉ ደስ እንዲላቸው አደረግክ። |
በተጨማሪም ሰይፉን መልሰህበታል፤በጦርነትም እንዲሸነፍ አደረግክ። |
ግርማ ሞገሱ እንዲጠፋ አደረግክ፤ዙፋኑንም መሬት ላይ ጣልከው። |
የወጣትነት ዕድሜውን አሳጠርክበት፤ኀፍረትም አከናነብከው። (ሴላ) |
ይሖዋ ሆይ፣ ራስህን የምትሰውረው እስከ መቼ ነው? ለዘላለም? ቁጣህስ እንደ እሳት ሲነድ ይኖራል? |
ዕድሜዬ ምን ያህል አጭር እንደሆነ አስብ! ሰዎችን ሁሉ የፈጠርከው እንዲያው ለከንቱ ነው? |
ሞትን ጨርሶ ሳያይ በሕይወት ሊኖር የሚችል ሰው ማን ነው? ራሱን ከመቃብር እጅ ማዳን ይችላል? (ሴላ) |
ይሖዋ ሆይ፣ በታማኝነትህ ለዳዊት የማልክለት፣በቀደሙት ዘመናት ያሳየኸው ታማኝ ፍቅር የት አለ? |
ይሖዋ ሆይ፣ በአገልጋዮችህ ላይ የተሰነዘረውን ዘለፋ አስታውስ፤ሰዎች ሁሉ የሰነዘሩብኝን ዘለፋ እንዴት እንደተሸከምኩ አስብ፤ |
ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶችህ ምን ያህል እንደተሳደቡ አስታውስ፤የቀባኸውን ሰው እርምጃ ሁሉ እንዴት እንደነቀፉ አስብ። |
ይሖዋ ለዘላለም ይወደስ። አሜን፣ አሜን። |
አምላክ ሆይ፣ አድነኝ፤ይሖዋ ሆይ፣ እኔን ለመርዳት ፍጠን። |
ሕይወቴን ለማጥፋት የሚሹኀፍረትና ውርደት ይከናነቡ። በእኔ ላይ በደረሰው ጉዳት ደስ የሚሰኙአፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ። |
“እሰይ! እሰይ!” የሚሉ አፍረው ወደ ኋላ ይመለሱ። |
አንተን የሚፈልጉ ግንበአንተ ይደሰቱ፤ ሐሴትም ያድርጉ። የማዳን ሥራህን የሚወዱ፣ ምንጊዜም “አምላክ ታላቅ ይሁን!” ይበሉ። |
እኔ ግን ምስኪንና ድሃ ነኝ፤አምላክ ሆይ፣ ለእኔ ስትል ፈጥነህ እርምጃ ውሰድ። አንተ ረዳቴና ታዳጊዬ ነህ፤ይሖዋ ሆይ፣ አትዘግይ። |
ጠብ እያለ ትልቅ ድግስ ከተደገሰበት ቤት ይልቅሰላም ባለበት ደረቅ የዳቦ ቁራሽ መብላት ይሻላል። |
ጥልቅ ማስተዋል ያለው አገልጋይ አሳፋሪ ድርጊት በሚፈጽም ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤ከወንድማማቾቹ እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል። |
ማቅለጫ ለብር፣ ምድጃ ለወርቅ ነው፤ልብን የሚመረምር ግን ይሖዋ ነው። |
ክፉ ሰው ጎጂ የሆነን ንግግር በትኩረት ያዳምጣል፤አታላይ ሰውም ተንኮለኛ የሆነን አንደበት ያዳምጣል። |
በድሃ የሚያፌዝ ሁሉ ፈጣሪውን ይሳደባል፤በሌላው ሰው ላይ በደረሰው መከራ የሚደሰትም ሁሉ ከቅጣት አያመልጥም። |
የልጅ ልጆች የሽማግሌዎች ዘውድ ናቸው፤አባቶችም ለወንዶች ልጆቻቸው ክብር ናቸው። |
ለሞኝ ሰው ቀና ንግግር አይስማማውም። ለገዢ ደግሞ ሐሰተኛ ንግግር ጨርሶ አይሆነውም! |
ስጦታ ለባለቤቱ እንደከበረ ድንጋይ ነው፤በሄደበት ሁሉ ስኬት ያስገኝለታል። |
በደልን ይቅር የሚል ሁሉ ፍቅርን ይሻል፤አንድን ጉዳይ ደጋግሞ የሚያወራ ግን የልብ ጓደኛሞችን ይለያያል። |
ሞኝን ሰው መቶ ጊዜ ከመግረፍ ይልቅማስተዋል ያለውን ሰው አንድ ጊዜ መገሠጽ የተሻለ ውጤት ያስገኛል። |
ክፉ ሰው የሚሻው ዓመፅን ብቻ ነው፤ሆኖም እሱን እንዲቀጣ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል። |
የቂል ሥራ እየሠራ ካለ ሞኝ ሰው ጋር ከመገናኘት ይልቅግልገሎቿን ካጣች ድብ ጋር መገናኘት ይሻላል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.