text
stringlengths
4
267
ለጋስ ሰው ይበለጽጋል፤ሌሎችን የሚያረካም እሱ ራሱ ይረካል።
እህል ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆነውን ሕዝቡ ይረግመዋል፤የሚሸጠውን ግን ይባርከዋል።
መልካም ነገር ለማድረግ የሚተጋ ሞገስ ለማግኘት ይጥራል፤መጥፎ ነገር ለማድረግ የሚፈልግ ግን ክፋቱ በራሱ ላይ እንደሚመጣ የተረጋገጠ ነው።
በሀብቱ የሚታመን ሰው ይወድቃል፤ጻድቅ ግን እንዳማረ ቅጠል ይለመልማል።
ቤተሰቡ ላይ ችግር የሚያመጣ ሰው ሁሉ ነፋስን ይወርሳል፤ሞኝ ሰውም ጥበበኛ ልብ ላለው ሰው አገልጋይ ይሆናል።
የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ነው፤ነፍሳትንም የሚማርክ ጥበበኛ ነው።
በእርግጥ ጻድቅ በምድር ላይ የሚገባውን ብድራት የሚቀበል ከሆነክፉውና ኃጢአተኛው የሚቀበሉት ብድራትማ ምንኛ የከፋ ይሆን!
በረዶ በበጋ፣ ዝናብም በመከር እንደማያስፈልግ ሁሉክብርም ለሞኝ ሰው አይገባውም።
ወፍ ቱር የምትልበት፣ ወንጭፊትም የምትበርበት ምክንያት እንዳላት ሁሉእርግማንም ያለበቂ ምክንያት አይመጣም።
አለንጋ ለፈረስ፣ ልጓም ለአህያ፣በትርም ለሞኞች ጀርባ ነው።
ለሞኝ እንደ ሞኝነቱ አትመልስለት፤አለዚያ አንተም የእሱ ቢጤ ትሆናለህ።
ጥበበኛ የሆነ እንዳይመስለውለሞኝ እንደ ሞኝነቱ መልስለት።
አንድን ጉዳይ ለሞኝ በአደራ የሚሰጥእግሩን ከሚያሽመደምድና ራሱን ከሚጎዳ ሰው ተለይቶ አይታይም።
በሞኞች አፍ የሚነገር ምሳሌ፣እንደ አንካሳ ሰው እግር ነው።
ለሞኝ ክብር መስጠት፣በወንጭፍ ላይ ድንጋይ እንደ ማሰር ነው።
በሞኞች አፍ የሚነገር ምሳሌበሰካራም እጅ እንዳለ እሾህ ነው።
ሞኝን ወይም አላፊ አግዳሚውን የሚቀጥር፣በነሲብ ያገኘውን ሁሉ እንደሚያቆስል ቀስተኛ ነው።
ውሻ ወደ ትፋቱ እንደሚመለስ፣ሞኝ ሰውም ሞኝነቱን ይደጋግማል።
ጥበበኛ ነኝ ብሎ የሚያስብ ሰው አይተህ ታውቃለህ? ከእሱ ይልቅ ሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው።
ሰነፍ “በመንገድ ላይ ደቦል አንበሳ፣በአደባባይም አንበሳ አለ!” ይላል።
በር በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ሰነፍም በአልጋው ላይ ይገላበጣል።
ሰነፍ እጁን ወደ ሳህን ያጠልቃል፤ወደ አፉ ለመመለስ ግን እጅግ ይታክታል።
ሰነፍ ሰው በማስተዋል መልስ ከሚሰጡ ሰባት ሰዎች ይበልጥጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል።
በሌሎች ጠብ የሚቆጣ መንገደኛየውሻ ጆሮ እንደሚይዝ ሰው ነው።
የሚንበለበሉ ተወንጫፊ መሣሪያዎችን፣ ፍላጻዎችንና ሞትን እንደሚወረውር እብድ፣
ባልንጀራውን አታሎ ሲያበቃ “ቀልዴን እኮ ነው!” የሚል ሰውም እንዲሁ ነው።
እንጨት ከሌለ እሳት ይጠፋል፤ስም አጥፊ ከሌለ ደግሞ ጭቅጭቅ ይበርዳል።
ከሰል ፍምን፣ እንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥልጨቅጫቃ ሰውም ጠብ ይጭራል።
ስም አጥፊ የሚናገረው ቃል ጣፋጭ እንደሆነ ቁራሽ ምግብ ነው፤በፍጥነት ተውጦ በቀጥታ ወደ ሆድ ይገባል።
ከክፉ ልብ የሚወጡ የፍቅር ቃላት፣በቀለጠ ብር እንደተለበጠ የሸክላ ዕቃ ስባሪ ናቸው።
ሌሎችን የሚጠላ ሰው ጥላቻውን በከንፈሩ ይደብቃል፤በውስጡ ግን ተንኮል ይቋጥራል።
አነጋገሩን ቢያሳምርም እንኳ አትመነው፤በልቡ ውስጥ ሰባት አስጸያፊ ነገሮች አሉና።
ጥላቻው በተንኮል ቢሸፈንምክፋቱ በጉባኤ መካከል ይገለጣል።
ጉድጓድ የሚቆፍር እሱ ራሱ እዚያ ውስጥ ይወድቃል፤ድንጋይ የሚያንከባልልም ወደ እሱ ተመልሶ ይመጣበታል።
ውሸታም ምላስ የጎዳቻቸውን ሰዎች ትጠላለች፤የሚሸነግል አንደበትም ጥፋት ያስከትላል።
የእስራኤል ንጉሥ፣ የዳዊት ልጅ የሰለሞን ምሳሌዎች፦
ጥበብንና ተግሣጽን ለመማር፣ጥበብ ያዘሉ አባባሎችን ለመረዳት፣
ጥልቅ ማስተዋል፣ ጽድቅ፣ ጥሩ ፍርድናቅንነት የሚያስገኝ ተግሣጽ ለመቀበል፣
ተሞክሮ ለሌላቸው ብልሃትን፣ለወጣቶች እውቀትንና የማመዛዘን ችሎታን ለመስጠት።
ጥበበኛ ሰው ያዳምጣል፤ ደግሞም ተጨማሪ ትምህርት ይቀስማል፤ማስተዋል ያለው ሰውም ጥበብ ያለበትን መመሪያ ይቀበላል፤
ይህም ምሳሌንና ስውር የሆነ አባባልንእንዲሁም የጥበበኞችን ቃላትና የሚናገሩትን እንቆቅልሽ ይረዳ ዘንድ ነው።
ይሖዋን መፍራት የእውቀት መጀመሪያ ነው። ጥበብንና ተግሣጽን የሚንቁት ሞኞች ብቻ ናቸው።
ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ተግሣጽ አዳምጥ፤የእናትህንም መመሪያ አትተው።
ለራስህ የሚያምር የአበባ ጉንጉን፣ለአንገትህም ውብ ጌጥ ይሆንልሃል።
ልጄ ሆይ፣ ኃጢአተኞች ሊያግባቡህ ቢሞክሩ እሺ አትበላቸው።
እንዲህ ይሉህ ይሆናል፦ “ና አብረን እንሂድ። ደም ለማፍሰስ እናድባ። ንጹሐን ሰዎችን ያለምክንያት ለማጥቃት እናደፍጣለን።
እንደ መቃብር፣ በሕይወት እንዳሉ እንውጣቸዋለን፤ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንሰለቅጣቸዋለን።
ውድ ሀብታቸውን ሁሉ እንውሰድባቸው፤ቤቶቻችንን በዘረፍናቸው ነገሮች እንሞላለን።
ከእኛ ጋር ልትተባበር ይገባል፤ሁላችንም የሰረቅነውን እኩል እንካፈላለን።”
ልጄ ሆይ፣ አትከተላቸው። እግርህን ከመንገዳቸው አርቅ፤
እግሮቻቸው ክፉ ነገር ለመሥራት ይሮጣሉና፤ደም ለማፍሰስ ይጣደፋሉ።
ወፎች ዓይናቸው እያየ እነሱን ለማጥመድ መረብ መዘርጋት ከንቱ ነው።
እነዚህ ሰዎች ደም ለማፍሰስ የሚያደቡት ለዚህ ነው፤የሰዎችን ሕይወት ለማጥፋት ያደፍጣሉ።
በማጭበርበር ትርፍ ለማግኘት የሚሹ መንገዳቸው ይህ ነው፤እንዲህ ያለው ትርፍ የተጠቃሚዎቹን ሕይወት ያጠፋል።
እውነተኛ ጥበብ በጎዳና ላይ ትጮኻለች። በአደባባይ ላይ ያለማቋረጥ ድምፅዋን ታሰማለች።
ሰው በሚበዛባቸው ጎዳናዎች ማዕዘን ላይ ሆና ትጣራለች። በከተማው መግቢያ በሮች ላይ እንዲህ ትላለች፦
“እናንተ አላዋቂዎች እስከ መቼ አላዋቂነትን ትወዳላችሁ? እናንተ ፌዘኞች እስከ መቼ በሌሎች ላይ በማፌዝ ትደሰታላችሁ? እናንተ ሞኞች እስከ መቼ እውቀትን ትጠላላችሁ?
ለወቀሳዬ ምላሽ ስጡ። እንዲህ ብታደርጉ መንፈሴን አፈስላችኋለሁ፤ቃሌን አሳውቃችኋለሁ።
በተጣራሁ ጊዜ በእንቢተኝነታችሁ ጸንታችኋል፤እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ትኩረት አልሰጠም፤
ምክሬን ሁሉ ችላ ብላችኋል፤ወቀሳዬንም አልተቀበላችሁም፤
እኔም ጥፋት ሲደርስባችሁ እስቃለሁ፤የፈራችሁት ነገር ሲደርስ አላግጥባችኋለሁ፤
የፈራችሁት ነገር እንደ ማዕበል ሲደርስባችሁ፣ጥፋታችሁም እንደ አውሎ ነፋስ ከተፍ ሲልባችሁ፣ጭንቀትና መከራ ሲመጣባችሁ አፌዝባችኋለሁ።
በዚያን ጊዜ ደጋግመው ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ሆኖም አያገኙኝም፤
ምክንያቱም እውቀትን ጠልተዋል፤ይሖዋን መፍራትንም አልወደዱም።
ምክሬን አልተቀበሉም፤ወቀሳዬን ሁሉ አቃለዋል።
ስለዚህ መንገዳቸው የሚያስከትለውን መዘዝ ይቀበላሉ፤በገዛ ራሳቸውም ምክር ከልክ በላይ ይጠግባሉ።
ተሞክሮ የሌላቸውን ሰዎች ጋጠወጥነታቸው ይገድላቸዋልና፤ሞኞችን ደግሞ ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል።
እኔን የሚሰማ ሰው ግን ተረጋግቶ ይኖራል፤መከራ ይደርስብኛል የሚል ስጋትም አያድርበትም።”
ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ጠብቅ፤ትእዛዛቴንም እንደ ውድ ሀብት ያዝ።
ትእዛዛቴን ጠብቅ፤ በሕይወትም ትኖራለህ፤መመሪያዬን እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ።
በጣቶችህ ላይ እሰራቸው፤በልብህ ጽላት ላይ ጻፋቸው።
ጥበብን “እህቴ ነሽ” በላት፤ ማስተዋልንም “ዘመዴ” ብለህ ጥራት፤
ጋጠወጥና ባለጌ ከሆነች ሴት፣እንዲሁም ከምትናገረው የሚያባብል ቃል ይጠብቁሃል።
በቤቴ መስኮት በፍርግርጉ በኩልአጮልቄ ወደ ታች ተመለከትኩ፤
ደግሞም ሞኞችን ትክ ብዬ በማይበት ጊዜ፣በዚያ ከነበሩት ወንዶች ልጆች መካከል ማስተዋል የጎደለውን አንድ ወጣት አየሁ።
በቤቷ አቅራቢያ በሚገኝ መታጠፊያ አልፎወደ ቤቷ አቅጣጫ አመራ፤
ቀኑ መሸትሸት ብሎ ለዓይን ያዝ አድርጓል፤የሌሊቱ ጨለማ እየተቃረበ ነበር።
ከዚያም እንደ ዝሙት አዳሪ የለበሰችናበልቧ አታላይ የሆነች ሴት ከእሱ ጋር ስትገናኝ አየሁ።
ሴትየዋ ጯኺና ማን አለብኝ ባይ ነች። ፈጽሞ ቤቷ አትቀመጥም።
አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በአደባባይ ትታያለች፤በየመንገዱ መታጠፊያም ታደባለች።
አፈፍ አድርጋ ይዛ ሳመችው፤ያላንዳች ኀፍረትም እንዲህ አለችው፦
“የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ ነበረብኝ። ዛሬ ስእለቴን ፈጽሜአለሁ።
አንተን ለማግኘት የወጣሁት ለዚህ ነው፤አንተን ፍለጋ ወጣሁ፤ ደግሞም አገኘሁህ!
መኝታዬን ባማረ የአልጋ ልብስ፣ከግብፅ በመጣ በቀለማት ያሸበረቀ በፍታ አስጊጬዋለሁ።
አልጋዬ ላይ ከርቤ፣ እሬትና ቀረፋ አርከፍክፌአለሁ።
ና፣ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፤እርስ በርሳችን ፍቅራችንን በመግለጽ እንደሰት፤
ባሌ ቤት የለምና፤ወደ ሩቅ ቦታ ሄዷል።
በከረጢት ገንዘብ ይዟል፤ደግሞም ጨረቃዋ ሙሉ እስክትሆን ድረስ ወደ ቤት አይመለስም።”
እንደ ምንም ብላ አግባብታ ታሳስተዋለች። በለሰለሰ አንደበቷ ታታልለዋለች።
ለእርድ እንደሚነዳ በሬ፣ለቅጣትም በእግር ግንድ እንደታሰረ ሞኝ ሰው በድንገት ይከተላታል፤
ፍላጻ ጉበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ፣በወጥመድ ለመያዝ እንደምትቸኩል ወፍ ተከትሏት ይሄዳል፤ ሕይወቱን ሊያሳጣው እንደሚችል አላወቀም።
እንግዲህ ልጆቼ ሆይ፣ አዳምጡኝ፤የምናገረውንም ቃል በትኩረት ስሙ።
ልባችሁን ወደ መንገዷ አታዘንብሉ። መንገድ ስታችሁ ወደ ጎዳናዋ አትግቡ፤
ተሰይፈው እንዲወድቁ ያደረገቻቸው ብዙ ናቸውና፤እሷ የገደለቻቸውም እጅግ ብዙ ናቸው።
ቤቷ ወደ መቃብር ይወስዳል፤ሙታን ወዳሉበት ስፍራም ይወርዳል።
እነዚህም የይሁዳ ንጉሥ የሕዝቅያስ ሰዎች የጻፏቸው የሰለሞን ምሳሌዎች ናቸው፦
አንድን ጉዳይ መሰወር ለአምላክ ክብሩ ነው፤ጉዳይን በሚገባ መመርመር ደግሞ ለነገሥታት ክብራቸው ነው።
ሰማያት ከፍ ያሉ እንደሆኑ፣ ምድርም ጥልቅ እንደሆነች ሁሉየንጉሥም ልብ አይመረመርም።
የብርን ቆሻሻ አስወግድ፤ሙሉ በሙሉም የጠራ ይሆናል።
ክፉን ሰው ከንጉሥ ፊት አስወግድ፤ዙፋኑም በጽድቅ ይጸናል።