text stringlengths 4 267 |
|---|
በንጉሥ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤ታላላቅ ሰዎችም ባሉበት ስፍራ አትቀመጥ፤ |
በተከበረ ሰው ፊት ከሚያዋርድህ እሱ ራሱ “ወደዚህ ከፍ በል” ቢልህ ይሻላልና። |
ክስ ለመመሥረት አትቸኩል፤የኋላ ኋላ ባልንጀራህ ቢያዋርድህ ምን ይውጥሃል? |
ከባልንጀራህ ጋር ስለ ራስህ ጉዳይ ተሟገት፤ሆኖም በሚስጥር የተነገረህን ጉዳይ አትግለጥ፤ |
አለዚያ የሚሰማህ ሰው ያዋርድሃል፤ያናፈስከውንም መጥፎ ወሬ መመለስ አትችልም። |
በተገቢው ጊዜ የተነገረ ቃልከብር በተሠራ ዕቃ ላይ እንዳለ የወርቅ ፖም ነው። |
በጥበብ ወቀሳ የሚሰጥ ሰው፣ የሚሰማ ጆሮ ላለውእንደ ወርቅ ጉትቻና ከጥሩ ወርቅ እንደተሠራ ጌጥ ነው። |
ታማኝ መልእክተኛ ለላኩት ሰዎችበመከር ወቅት እንደሚገኝ የበረዶ ቅዝቃዜ ነው፤የጌታውን መንፈስ ያድሳልና። |
የማይሰጠውን ስጦታ እሰጣለሁ እያለ ጉራውን የሚነዛ ሰውዝናብ እንደማያመጣ ደመናና ነፋስ ነው። |
በትዕግሥት አዛዥን ማሸነፍ ይቻላል፤ለስላሳም አንደበት አጥንትን ይሰብራል። |
ማር ካገኘህ የሚበቃህን ያህል ብቻ ብላ፤ከልክ በላይ ከበላህ ሊያስመልስህ ይችላልና። |
እንዳይሰለችህና እንዳይጠላህወደ ባልንጀራህ ቤት እግር አታብዛ። |
በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሠክርእንደ ቆመጥ፣ እንደ ሰይፍና እንደ ሹል ፍላጻ ነው። |
በችግር ወቅት እምነት በማይጣልበት ሰው መተማመን፣እንደተሰበረ ጥርስና እንደሰለለ እግር ነው። |
ላዘነ ልብ የሚዘምር ሰው፣በብርድ ቀን ልብሱን እንደሚያወልቅ፣በሶዳም ላይ እንደተጨመረ ኮምጣጤ ነው። |
ጠላትህ ቢራብ ምግብ ስጠው፤ቢጠማ ውኃ ስጠው፤ |
ይህን ብታደርግ በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህና፤ይሖዋም ወሮታ ይከፍልሃል። |
የሰሜን ነፋስ ኃይለኛ ዝናብ ያመጣል፤ሐሜተኛ ምላስም የሰውን ፊት ያስቆጣል። |
ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖርበጣሪያ ማዕዘን ላይ መኖር ይሻላል። |
ቀዝቃዛ ውኃ የዛለችን ነፍስ እንደሚያረካ ሁሉከሩቅ አገር የመጣ መልካም ወሬም እንዲሁ ነው። |
ለክፉ ሰው የሚንበረከክ ጻድቅ፣እንደጨቀየ ምንጭና እንደተበከለ የውኃ ጉድጓድ ነው። |
ብዙ ማር መብላት ጥሩ አይደለም፤የራስንም ክብር መሻት አያስከብርም። |
ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል ሰውቅጥር እንደሌላት የፈረሰች ከተማ ነው። |
ጥበበኛ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይቀበላል፤ፌዘኛ ግን ተግሣጽን አይሰማም። |
ሰው ከአፉ ፍሬ መልካም ነገር ይበላል፤ከዳተኞች ግን ዓመፅን ይመኛሉ። |
አፉን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል። አፉን የሚከፍት ግን ይጠፋል። |
ሰነፍ ሰው ይመኛል፤ ነገር ግን ምንም አያገኝም፤ትጉ ሰው ግን በሚገባ ይጠግባል። |
ጻድቅ ውሸትን ይጠላል፤የክፉ ሰው ድርጊት ግን ኀፍረትና ውርደት ያመጣበታል። |
በመንገዱ ነቀፋ የሌለበትን ሰው ጽድቅ ትጠብቀዋለች፤ክፋት ግን ኃጢአተኛውን ትጥለዋለች። |
ምንም ሳይኖረው ባለጸጋ መስሎ ለመታየት የሚሞክር ሰው አለ፤ሌላው ደግሞ ብዙ ሀብት እያለው ድሃ መስሎ ይኖራል። |
የሰው ሀብት ለሕይወቱ ቤዛ ነው፤ድሃ ግን ምንም ዓይነት ስጋት የለበትም። |
የጻድቃን ብርሃን ደምቆ ይበራል፤የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል። |
እብሪተኝነት ጠብ ከመፍጠር ውጭ የሚያመጣው ነገር የለም፤ምክር በሚሹ ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች። |
በፍጥነት የተገኘ ሀብት ይመናመናል፤ጥቂት በጥቂት የሚያጠራቅም ሰው ግን ሀብቱ ይጨምራል። |
የዘገየ ተስፋ ልብን ያሳምማል፤የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው። |
መመሪያን የሚንቅ ሁሉ ይቀጣል፤ትእዛዝን የሚያከብር ግን ብድራት ያገኛል። |
የጥበበኛ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው፤ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ይረዳዋል። |
ጥልቅ ማስተዋል ሞገስ ያስገኛል፤የከዳተኞች መንገድ ግን አስቸጋሪ ነው። |
ብልህ ሰው ተግባሩን በእውቀት ያከናውናል፤ሞኝ ሰው ግን የገዛ ራሱን ሞኝነት ይገልጣል። |
ክፉ መልእክተኛ ችግር ውስጥ ይወድቃል፤ታማኝ መልእክተኛ ግን ፈውስ ያመጣል። |
ተግሣጽን ችላ የሚል ሁሉ ይደኸያል፤ ይዋረዳልም፤እርማትን የሚቀበል ግን ይከበራል። |
ሰው የተመኘው ነገር ሲፈጸም ደስ ይለዋል፤ሞኞች ግን ከክፋት መራቅን ይጸየፋሉ። |
ከጥበበኞች ጋር የሚሄድ ጥበበኛ ይሆናል፤ከሞኞች ጋር የሚገጥም ግን ጉዳት ይደርስበታል። |
ኃጢአተኞችን ጥፋት ያሳድዳቸዋል፤ጻድቃንን ግን ብልጽግና ይክሳቸዋል። |
ጥሩ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ይተዋል፤የኃጢአተኛ ሀብት ግን ለጻድቅ ይከማቻል። |
የድሃ እርሻ ብዙ እህል ያስገኛል፤ሆኖም ከፍትሕ መጓደል የተነሳ ተጠራርጎ ይጠፋል። |
ልጁን በበትር ከመምታት ወደኋላ የሚል ይጠላዋል፤የሚወደው ግን ተግቶ ይገሥጸዋል። |
ጻድቅ ይበላል፤ የምግብ ፍላጎቱንም ያረካል፤የክፉ ሰው ሆድ ግን ባዶ ነው። |
የንጉሥ ልብ በይሖዋ እጅ እንዳለ ጅረት ነው። እሱ ደስ ወዳሰኘው አቅጣጫ ሁሉ ይመራዋል። |
ሰው መንገዱ ሁሉ ትክክል መስሎ ይታየዋል፤ይሖዋ ግን ልብን ይመረምራል። |
መሥዋዕት ከማቅረብ ይልቅትክክልና ፍትሐዊ የሆነ ነገር ማድረግ ይሖዋን ይበልጥ ደስ ያሰኘዋል። |
ትዕቢተኛ ዓይንና እብሪተኛ ልብየክፉዎች መብራት ናቸው፤ ደግሞም ኃጢአት ናቸው። |
የትጉ ሰው ዕቅድ ለስኬት ያበቃዋል፤ችኩሎች ሁሉ ግን ለድህነት ይዳረጋሉ። |
በሐሰተኛ ምላስ የሚገኝ ውድ ሀብትወዲያው እንደሚጠፋ ጉም ነው፤ ገዳይ ወጥመድም ነው። |
ክፉዎች ፍትሕን ማስፈን ስለማይፈልጉየሚፈጽሙት ግፍ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል። |
የበደለኛ ሰው መንገድ ጠማማ ነው፤የንጹሕ ሰው ሥራ ግን ቀና ነው። |
ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖርበጣሪያ ማዕዘን ላይ መኖር ይሻላል። |
ክፉ ሰው መጥፎ ነገር ይመኛል፤ለባልንጀራው ሞገስ አያሳይም። |
ፌዘኛ ሲቀጣ ተሞክሮ የሌለው ሰው ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ጥበበኛ ሰው ጥልቅ ማስተዋል ሲያገኝም እውቀት ይቀስማል። |
ጻድቅ የሆነው አምላክ፣ የክፉውን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤ክፉዎችንም ይጠፉ ዘንድ ይገለብጣቸዋል። |
ችግረኛው የሚያሰማውን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን ሁሉ፣እሱ ራሱ ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም። |
በድብቅ የተሰጠ ስጦታ ቁጣን ያበርዳል፤በስውር የተሰጠ ጉቦም ኃይለኛ ቁጣ እንዲከስም ያደርጋል። |
ጻድቅ ፍትሐዊ ነገር ማድረግ ያስደስተዋል፤ክፉ ድርጊት ለሚፈጽሙ ግን አስከፊ ነገር ነው። |
ከማስተዋል መንገድ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣በሞት ከተረቱት ጋር ያርፋል። |
ፈንጠዝያ የሚወድ ሰው ይደኸያል፤የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድ ባለጸጋ አይሆንም። |
ክፉ ሰው ለጻድቅ ቤዛ ነው፤ከዳተኛ የሆነ ሰውም በቅን ሰው ፋንታ ይወሰዳል። |
ጨቅጫቃና ቁጡ ከሆነች ሚስት ጋር ከመኖርበምድረ በዳ መኖር ይሻላል። |
ውድ ሀብትና ምርጥ ዘይት በጥበበኛ ሰው ቤት ይገኛል፤ሞኝ ሰው ግን ያለውን ያባክናል። |
ጽድቅንና ታማኝ ፍቅርን የሚከታተል ሰው ሁሉሕይወትን፣ ጽድቅንና ክብርን ያገኛል። |
ጥበበኛ ሰው የኃያላን ሰዎች ከተማ ላይ ይወጣል፤የሚታመኑበትንም ብርታት ያዳክማል። |
አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ፣ራሱን ከችግር ይጠብቃል። |
በእብሪት የመሰለውን የሚያደርግ ሰውእብሪተኛና ጉረኛ ይባላል። |
ሰነፍ ሰው ምኞቱ ይገድለዋል፤እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና። |
ቀኑን ሙሉ በስግብግብነት ሲመኝ ይውላል፤ጻድቅ ግን ምንም ሳይሰስት ይሰጣል። |
የክፉ ሰው መሥዋዕት አስጸያፊ ነው። በክፉ ዓላማ ተነሳስቶ ሲያቀርብማ ምንኛ የከፋ ይሆናል! |
ውሸታም ምሥክር ይጠፋል፤በጥሞና የሚያዳምጥ ሰው ግን የምሥክርነት ቃሉ ተቀባይነት ያገኛል። |
ክፉ ሰው ኀፍረት የሚባል ነገር አያውቅም፤የቅን ሰው አካሄድ ግን አስተማማኝ ነው። |
ይሖዋን የሚጻረር ጥበብ፣ ማስተዋልም ሆነ ምክር ከንቱ ነው። |
ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤መዳን ግን ከይሖዋ ዘንድ ነው። |
ልጄ ሆይ፣ ትምህርቴን አትርሳ፤ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ፤ |
ረጅም ዕድሜና የሕይወት ዘመንእንዲሁም ሰላም ያስገኙልሃልና። |
ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት አይለዩህ። በአንገትህ ዙሪያ እሰራቸው፤በልብህ ጽላት ላይ ጻፋቸው፤ |
ያን ጊዜ በአምላክና በሰው ፊት ሞገስ ታገኛለህ፤እንዲሁም ጥሩ ማስተዋል እንዳለህ ታስመሠክራለህ። |
በሙሉ ልብህ በይሖዋ ታመን፤ደግሞም በገዛ ራስህ ማስተዋል አትመካ። |
በመንገድህ ሁሉ እሱን ግምት ውስጥ አስገባ፤እሱም ጎዳናህን ቀና ያደርገዋል። |
በራስህ አመለካከት ጥበበኛ አትሁን። ይሖዋን ፍራ፤ ከክፉም ራቅ። |
ለሰውነትህ ፈውስ፣ለአጥንትህም ብርታት ይሆንልሃል። |
ባሉህ ውድ ነገሮች፣ከምርትህ ሁሉ በኩራት ይሖዋን አክብር፤ |
ይህን ካደረግክ ጎተራዎችህ ጢም ብለው ይሞላሉ፤በወይን መጭመቂያዎችህም አዲስ የወይን ጠጅ ሞልቶ ይፈስሳል። |
ልጄ ሆይ፣ የይሖዋን ተግሣጽ ለመቀበል እንቢተኛ አትሁን፤ወቀሳውም አያስመርርህ፤ |
አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚወቅስ ሁሉይሖዋም የሚወዳቸውን ይወቅሳልና። |
ጥበብን የሚያገኝ፣ጥልቅ ግንዛቤንም የራሱ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው፤ |
ጥበብን ማግኘት ብርን ከማግኘት የተሻለ ነው፤እሷንም ማትረፍ ወርቅ ከማግኘት የተሻለ ነው። |
ከዛጎል ይበልጥ ውድ ናት፤አንተ የምትመኘው ማንኛውም ነገር ሊተካከላት አይችልም። |
በቀኟ ረጅም ዕድሜ አለ፤በግራዋም ሀብትና ክብር ይገኛል። |
መንገዷ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ጎዳናዋም ሁሉ ሰላም የሰፈነበት ነው። |
ለሚይዟት የሕይወት ዛፍ ናት፤አጥብቀው የሚይዟትም ደስተኞች ይባላሉ። |
ይሖዋ በጥበብ ምድርን መሠረተ። በማስተዋል ሰማያትን አጸና። |
በእውቀቱ ጥልቅ ውኃዎች ተከፈሉ፤ደመና ያዘሉ ሰማያትም ጠል አንጠባጠቡ። |
ልጄ ሆይ፣ እነዚህ ባሕርያት ከእይታህ አይራቁ። ጥበብንና የማመዛዘን ችሎታን ጠብቅ፤ |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.