text stringlengths 4 267 |
|---|
ሕይወት ያስገኙልሃል፤ለአንገትህም ጌጥ ይሆናሉ፤ |
በዚያን ጊዜ በመንገድህ ላይ ተማምነህ ትሄዳለህ፤እግርህም ፈጽሞ አይሰናከልም። |
በምትተኛበት ጊዜ አትፈራም፤ትተኛለህ፤ እንቅልፍህም ጣፋጭ ይሆናል። |
ድንገት የሚከሰት የሚያሸብር ነገርም ሆነበክፉ ሰዎች ላይ የሚመጣ መዓት አያስፈራህም። |
ይሖዋ መታመኛህ ይሆናልና፤እግርህን በወጥመድ እንዳይያዝ ይጠብቃል። |
ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችል አቅም ካለህለሚገባቸው መልካም ነገር ከማድረግ ወደኋላ አትበል። |
ለባልንጀራህ አሁኑኑ መስጠት እየቻልክ “ሂድና በኋላ ተመልሰህ ና! ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው። |
ከአንተ ጋር ተማምኖ እየኖረ ሳለባልንጀራህን ለመጉዳት አታሲር። |
መጥፎ ነገር ካላደረገብህከሰው ጋር ያለምክንያት አትጣላ። |
በዓመፀኛ ሰው አትቅና፤የትኛውንም መንገዱን አትምረጥ፤ |
ይሖዋ ተንኮለኛን ሰው ይጸየፋልና፤ከቅኖች ጋር ግን የጠበቀ ወዳጅነት አለው። |
ይሖዋ የክፉውን ቤት ይረግማል፤የጻድቁን መኖሪያ ግን ይባርካል። |
በፌዘኞች ላይ ይሳለቃል፤ለየዋሆች ግን ሞገስ ያሳያል። |
ጥበበኞች ክብርን ይወርሳሉ፤ሞኞች ግን ለውርደት የሚዳርግን ነገር ከፍ አድርገው ይመለከታሉ። |
የያቄ ልጅ አጉር ለኢቲኤል፣ ለኢቲኤልና ለዑካል የተናገራቸው ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘሉ ቃላት። |
እኔ ከማንም የባሰ አላዋቂ ነኝ፤ሰው ሊኖረው የሚገባው ማስተዋልም የለኝም። |
ጥበብን አልተማርኩም፤እጅግ ቅዱስ የሆነው አምላክ እውቀትም የለኝም። |
ወደ ሰማይ የወጣ፣ ከዚያም የወረደ ማን ነው? ነፋስን በእፍኙ ሰብስቦ የያዘ ማን ነው? ውኃን በልብሱ የጠቀለለ ማን ነው? የምድርን ዳርቻዎች ሁሉ የወሰነ ማን ነው? ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው? ታውቅ እንደሆነ ንገረኝ። |
የአምላክ ቃል ሁሉ የነጠረ ነው። እሱ፣ መጠጊያቸው ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻ ነው። |
በቃሉ ላይ ምንም አትጨምር፤አለዚያ ይወቅስሃል፤ሐሰተኛም ሆነህ ትገኛለህ። |
ሁለት ነገር እንድታደርግልኝ እለምንሃለሁ። እነሱንም ከመሞቴ በፊት አትንፈገኝ። |
ውሸትንና ሐሰትን ከእኔ አርቅ። ድሃም ሆነ ባለጸጋ አታድርገኝ። ብቻ የሚያስፈልገኝን ቀለብ አታሳጣኝ፤ |
አለዚያ እጠግብና እክድሃለሁ፤ ከዚያም “ይሖዋ ማን ነው?” እላለሁ፤ ደግሞም ድሃ ሆኜ እንድሰርቅና የአምላኬን ስም እንዳሰድብ አትፍቀድ። |
እንዳይረግምህና በደለኛ ሆነህ እንዳትገኝበጌታው ፊት የአገልጋዩን ስም አታጥፋ። |
አባቱን የሚረግም፣እናቱንም የማይባርክ ትውልድ አለ። |
በገዛ ዓይኑ ፊት ንጹሕ የሆነ፣ሆኖም ከቆሻሻው ያልነጻ ትውልድ አለ። |
እጅግ ትዕቢተኛ ዓይን ያለው ትውልድ አለ፤ዓይኖቹም በታላቅ እብሪት ይመለከታሉ! |
ጥርሱ ሰይፍ፣መንገጭላው ደግሞ ቢላ የሆነ ትውልድ አለ፤በምድር ላይ ያሉ ምስኪኖችን፣በሰው ዘር መካከል ያሉ ድሆችንም ይውጣል። |
አልቅቶች “ስጡን! ስጡን!” እያሉ የሚጮኹ ሁለት ሴቶች ልጆች አሏቸው። ፈጽሞ የማይጠግቡ ሦስት ነገሮች አሉ፤ደግሞም “በቃኝ!” የማያውቁ አራት ነገሮች አሉ። |
እነሱም መቃብር፣ መሃን የሆነ ማህፀን፣ውኃ የተጠማ መሬትእንዲሁም “በቃኝ!” የማይል እሳት ናቸው። |
በአባቷ ላይ የምታፌዝን፣ የእናቷንም ትእዛዝ የምትንቅን ዓይንየሸለቆ ቁራዎች ይጎጠጉጧታል፤የንስር ጫጩቶችም ይበሏታል። |
ከመረዳት አቅሜ በላይ የሆኑ ሦስት ነገሮች አሉ፤የማልገነዘባቸውም አራት ነገሮች አሉ፦ |
ንስር በሰማያት የሚበርበት መንገድ፣እባብ በዓለት ላይ የሚሄድበት መንገድ፣መርከብ በባሕር ላይ የሚጓዝበት መንገድ፣ሰውም ከሴት ልጅ ጋር የሚሄድበት መንገድ ናቸው። |
የአመንዝራ ሴት መንገድ ይህ ነው፦ በልታ አፏን ከጠራረገች በኋላ“ምንም የሠራሁት ጥፋት የለም” ትላለች። |
ምድርን የሚያናውጡ ሦስት ነገሮች አሉ፤መታገሥ የማትችላቸውም አራት ነገሮች አሉ፦ |
ባሪያ ንጉሥ ሆኖ ሲገዛ፣ሞኝ በልቶ ሲጠግብ፣ |
የተጠላች ሴት ባል ስታገኝ፣ሴት አገልጋይም የእመቤቷን ቦታ ስትወስድ የሚከሰቱ ሁኔታዎች ናቸው። |
በምድር ላይ በጣም ትናንሽ የሆኑ አራት ፍጥረታት አሉ፤ሆኖም በደመ ነፍስ ጥበበኞች ናቸው፦ |
ጉንዳኖች ኃይል የሌላቸው ፍጥረታት ናቸው፤ይሁንና ምግባቸውን በበጋ ያዘጋጃሉ። |
ሽኮኮዎች ኃያላን ፍጥረታት አይደሉም፤ነገር ግን መኖሪያቸውን በቋጥኞች ውስጥ ያደርጋሉ። |
አንበጦች ንጉሥ የላቸውም፤ሆኖም ሁሉም በሰልፍ ወደ ፊት ይጓዛሉ። |
እንሽላሊት በእግሮቿ ቆንጥጣ ትይዛለች፤ወደ ንጉሥ ቤተ መንግሥትም ትገባለች። |
ግርማ የተላበሰ አረማመድ ያላቸው ሦስት ፍጥረታት አሉ፤አዎ፣ እየተጎማለሉ የሚሄዱ አራት ፍጥረታት አሉ፦ |
ከአራዊት ሁሉ ኃያል የሆነውናማንንም አይቶ ወደ ኋላ የማይመለሰው አንበሳ፣ |
አዳኝ ውሻ፣ አውራ ፍየል፣እንዲሁም በሠራዊቱ የታጀበ ንጉሥ ናቸው። |
በሞኝነት ራስህን ከፍ ከፍ ካደረግክ፣ወይም እንዲህ ለማድረግ ካሰብክእጅህን በአፍህ ላይ አድርግ። |
ወተት ሲናጥ ቅቤ እንደሚወጣው፣አፍንጫም ሲጨመቅ እንደሚደማ ሁሉቁጣን ማነሳሳትም ጠብ ያስከትላል። |
እውነተኛ ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ሰባቱን ምሰሶዎቿንም ጠርባ አዘጋጀች። |
ሥጋዋን በሚገባ አዘጋጀች፤የወይን ጠጇንም ደባለቀች፤ደግሞም ገበታዋን አሰናዳች። |
ከከተማዋ በላይ ባሉ ከፍታ ቦታዎች ላይ ሆነውእንዲህ ብለው እንዲጣሩ ሴት አገልጋዮቿን ላከች፦ |
“ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።” ማስተዋል ለጎደለው እንዲህ ትላለች፦ |
“ኑ፣ ያዘጋጀሁትን ምግብ ብሉ፤የደባለቅኩትንም የወይን ጠጅ ጠጡ። |
አላዋቂነታችሁን ተዉ፤ በሕይወትም ኑሩ፤በማስተዋል መንገድ ወደ ፊት ሂዱ።” |
ፌዘኛን የሚያርም በራሱ ላይ ውርደት ያመጣል፤ክፉን ሰው የሚወቅስም ሁሉ ጉዳት ይደርስበታል። |
ፌዘኛን አትውቀስ፤ አለዚያ ይጠላሃል። ጥበበኛን ሰው ውቀሰው፤ እሱም ይወድሃል። |
ጥበበኛን ሰው አስተምረው፤ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል። ጻድቅን ሰው አስተምረው፤ ተጨማሪ እውቀት ያገኛል። |
የጥበብ መጀመሪያ ይሖዋን መፍራት ነው፤እጅግ ቅዱስ ስለሆነው አምላክ ማወቅም ማስተዋል ነው። |
በእኔ ምክንያት ዘመንህ ይረዝማል፤በሕይወትህም ላይ ዕድሜ ይጨመርልሃል። |
ጥበበኛ ብትሆን፣ ጥበበኛነትህ የሚጠቅመው ራስህን ነው፤ፌዘኛ ብትሆን ግን መዘዙን የምትቀበለው አንተው ነህ። |
ማስተዋል የጎደላት ሴት ጯኺ ናት። እሷ ጨርሶ ማመዛዘን አትችልም፤ ደግሞም አንዳች ነገር አታውቅም። |
በከተማዋ ከፍ ያሉ ቦታዎች ላይ፣በቤቷ ደጃፍ ወንበር ላይ ትቀመጣለች፤ |
በጎዳናው የሚያልፉትን፣ቀጥ ብለው በመንገዳቸው የሚሄዱትን ትጣራለች፦ |
“ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።” ማስተዋል ለጎደላቸው ሁሉ እንዲህ ትላለች፦ |
“የተሰረቀ ውኃ ይጣፍጣል፤ተደብቀው የበሉት ምግብም ይጥማል።” |
እሱ ግን በሞት የተረቱት በዚያ እንዳሉ፣እንግዶቿም በመቃብር ጥልቅ ውስጥ እንደሚገኙ አያውቅም። |
በክፉ ሰዎች አትቅና፤ከእነሱም ጋር ለመሆን አትጓጓ፤ |
ልባቸው ዓመፅን ያውጠነጥናልና፤ከንፈራቸውም ተንኮልን ያወራል። |
ቤት በጥበብ ይገነባል፤በማስተዋልም ይጸናል። |
በእውቀት አማካኝነት ክፍሎቹበተለያዩ ውድ የሆኑና ያማሩ ነገሮች ተሞልተዋል። |
ጥበበኛ ሰው ኃያል ነው፤ሰውም በእውቀት ኃይሉን ይጨምራል። |
ጥበብ ያለበት አመራር ተቀብለህ ለውጊያ ትወጣለህ፤በብዙ አማካሪዎችም ድል ይገኛል። |
ለሞኝ ሰው እውነተኛ ጥበብ ሊገኝ የማይችል ነገር ነው፤በከተማው በር ላይ አንዳች የሚናገረው ነገር የለውም። |
መጥፎ ነገር ለማድረግ የሚያሴር ሁሉሴራ በመጠንሰስ የተካነ ተብሎ ይጠራል። |
በሞኝነት የሚጠነሰስ ሴራ ኃጢአት ነው፤ሰዎችም ፌዘኛን ይጸየፋሉ። |
በመከራ ቀን ተስፋ የምትቆርጥ ከሆነጉልበትህ እጅግ ይዳከማል። |
ወደ ሞት እየተወሰዱ ያሉትን ታደግ፤ለእርድ እየተውተረተሩ የሚሄዱትንም አስጥል። |
“እኛ ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም አናውቅም” ብትል፣ ልብን የሚመረምረው እሱ ይህን አያስተውልም? አዎ፣ አንተን የሚመለከተው አምላክ ያውቃል፤ለእያንዳንዱም ሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል። |
ልጄ ሆይ፣ መልካም ስለሆነ ማር ብላ፤ከማር እንጀራ የሚገኝ ማር ጣፋጭ ጣዕም አለው። |
በተመሳሳይም ጥበብ ለአንተ መልካም እንደሆነ እወቅ። ጥበብን ብታገኝ የወደፊት ሕይወትህ የተሳካ ይሆናል፤ተስፋህም ከንቱ አይሆንም። |
በጻድቁ ቤት ላይ በክፋት አትሸምቅ፤ማረፊያ ቦታውንም አታፍርስበት። |
ጻድቅ ሰባት ጊዜ ቢወድቅ እንኳ መልሶ ይነሳልና፤ክፉ ሰው ግን በሚደርስበት መከራ ይሰናከላል። |
ጠላትህ ሲወድቅ ሐሴት አታድርግ፤ሲሰናከልም ልብህ ደስ አይበለው፤ |
አለዚያ ይሖዋ ይህን አይቶ ያዝናል፤ቁጣውንም ከእሱ ይመልሳል። |
መጥፎ በሆኑ ሰዎች አትበሳጭ፤በክፉዎች አትቅና፤ |
መጥፎ ሰው ሁሉ ምንም ተስፋ የለውምና፤የክፉዎች መብራት ይጠፋል። |
ልጄ ሆይ፣ ይሖዋንና ንጉሥን ፍራ። ከተቃዋሚዎች ጋር አትተባበር፤ |
ጥፋታቸው ድንገት ይመጣልና። ሁለቱም በእነሱ ላይ የሚያመጡትን ጥፋት ማን ያውቃል? |
እነዚህም አባባሎች የጥበበኞች ናቸው፦ በፍርድ ማዳላት ጥሩ አይደለም። |
ክፉውን “አንተ ጻድቅ ነህ” የሚለውን ሰው ሁሉ ሕዝቦች ይረግሙታል፤ ብሔራትም ያወግዙታል። |
እሱን የሚወቅሱት ግን መልካም ይሆንላቸዋል፤በመልካም ነገሮችም ይባረካሉ። |
ሰዎች በሐቀኝነት መልስ የሚሰጥን ሰው ከንፈር ይስማሉ። |
በደጅ ያለህን ሥራ አሰናዳ፤ በእርሻም ላይ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ አዘጋጅ፤ከዚያ በኋላ ቤትህን ሥራ። |
ምንም መሠረት ሳይኖርህ በባልንጀራህ ላይ አትመሥክር። በከንፈሮችህ ሌሎችን አታታል። |
“እሱ እንዳደረገብኝ እንዲሁ አደርግበታለሁ፤እንደ ሥራው እከፍለዋለሁ” አትበል። |
በሰነፍ ሰው እርሻ፣ማስተዋል በጎደለው ሰው የወይን ቦታ አለፍኩ። |
እርሻው አረም ወርሶት አየሁ፤መሬቱን ሳማ ሸፍኖት፣የድንጋዩም አጥር ፈራርሶ ነበር። |
ይህን ተመልክቼ በጥሞና አሰብኩበት፤ካየሁትም ነገር ይህን ትምህርት አገኘሁ፦ |
ቆይ ትንሽ ልተኛ፣ ቆይ ትንሽ ላንቀላፋ፣እጄንም አጣጥፌ እስቲ ትንሽ ጋደም ልበል ካልክ፣ |
ድህነት እንደ ወንበዴ፣ችጋርም መሣሪያ እንደታጠቀ ሰው ይመጣብሃል። |
ነገ በሚሆነው ነገር አትመካ፤ቀን የሚያመጣውን አታውቅምና። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.