text
stringlengths
4
267
የገዛ አፍህ ሳይሆን ሌላ ሰው ያመስግንህ፤የገዛ ከንፈርህ ሳይሆን ሌሎች ያወድሱህ።
ድንጋይ ከባድ ነው፤ አሸዋም ሸክም ነው፤የሞኝ ሰው ትንኮሳ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።
ንዴት ጨካኝ ነው፤ ቁጣም ጎርፍ ነው፤ይሁንና ቅናትን ማን ሊቋቋም ይችላል?
ከተሰወረ ፍቅር ይልቅ የተገለጠ ወቀሳ ይሻላል።
የወዳጅ ማቁሰል ከታማኝነት የሚመነጭ ነው፤የጠላት መሳም ግን የበዛ ነው።
የጠገበ ሰው ከማር እንጀራ የሚገኝን ማር አይፈልግም፤የተራበ ግን የሚመር ነገር እንኳ ይጣፍጠዋል።
ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰውከጎጆዋ ወጥታ እንደምትባዝን ወፍ ነው።
ዘይትና ዕጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፤በቀና ምክር ላይ የተመሠረተ ጥሩ ወዳጅነትም እንዲሁ ነው።
መከራ ባጋጠመህ ቀን የራስህንም ሆነ የአባትህን ወዳጅ ትተህወደ ገዛ ወንድምህ ቤት አትግባ፤ሩቅ ቦታ ካለ ወንድም ይልቅ በቅርብ ያለ ጎረቤት ይሻላል።
ልጄ ሆይ፣ ለሚነቅፈኝ መልስ መስጠት እችል ዘንድጥበበኛ ሁን፤ ልቤንም ደስ አሰኘው።
ብልህ ሰው አደጋ አይቶ ይሸሸጋል፤ተሞክሮ የሌለው ሰው ግን ዝም ብሎ ይሄዳል፤ መዘዙንም ይቀበላል።
አንድ ሰው ለማያውቀው ሰው ዋስ ከሆነ ልብሱን ውሰድበት፤ይህን ያደረገው ለባዕድ ሴት ብሎ ከሆነ መያዣውን ውሰድ።
ሰው በማለዳ ድምፁን ከፍ አድርጎ ባልንጀራውን ቢባርክእንደ እርግማን ይቆጠርበታል።
ጨቅጫቃ ሚስት በዝናባማ ቀን ያለማቋረጥ እንደሚያንጠባጥብ ጣሪያ ናት።
እሷን መግታት የሚችል ሁሉ ነፋስን መግታት፣ዘይትንም በቀኝ እጁ መጨበጥ ይችላል።
ብረት ብረትን እንደሚስል ሁሉሰውም ጓደኛውን ይስለዋል።
የበለስን ዛፍ የሚንከባከብ ፍሬዋን ይበላል፤ጌታውንም የሚንከባከብ ክብር ይጎናጸፋል።
ውኃ የሰውን ፊት እንደሚያንጸባርቅ ሁሉ፣የሰውም ልብ የሌላ ሰው ልብ ነጸብራቅ ነው።
መቃብርና የጥፋት ቦታ አይጠግቡም፤ልክ እንደዚሁም የሰው ዓይን ፈጽሞ አይጠግብም።
ማቅለጫ ለብር፣ ምድጃ ለወርቅ ነው፤ሰውም በሚቀበለው ውዳሴ ይፈተናል።
ሞኝን ሙቀጫ ውስጥ ከተህ በዘነዘና ብትወቅጠውናእንደ እህል ብታደቀው እንኳሞኝነቱ ከእሱ አይወገድም።
የመንጋህን ሁኔታ በሚገባ እወቅ። በጎችህን በደንብ ተንከባከብ፤
ሀብት ለዘላለም አይኖርምና፤አክሊልም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ አይኖርም።
ሣሩ በቦታው የለም፤ አዲስ ሣርም በቅሏል፤በተራሮች ላይ ያለው ተክልም ተሰብስቧል።
የበግ ጠቦቶች ለልብስ፣አውራ ፍየሎችም ለመሬት መግዣ ይሆኑልሃል።
ደግሞም አንተንና ቤተሰብህን ለመመገብ፣ልጃገረዶችህንም በሕይወት ለማኖር የሚያስችል በቂ የፍየል ወተት ይኖርሃል።
ልጄ ሆይ፣ ቃሌን ብትቀበልናትእዛዛቴን እንደ ውድ ሀብት ብታስቀምጥ፣
ይህን ለማድረግ ጆሮህን ወደ ጥበብ ብታቀና፣ጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ልብህን ብታዘነብል፣
ደግሞም ማስተዋልን ብትጣራናጥልቅ ግንዛቤ ለማግኘት ድምፅህን ብታሰማ፣
እንደ ብር ተግተህ ብትፈልጋት፣እንዲሁም እንደተሸሸገ ሀብት አጥብቀህ ብትሻት፣
ያን ጊዜ ይሖዋን መፍራት ምን ማለት እንደሆነ ትረዳለህ፤ደግሞም ስለ አምላክ እውቀት ትቀስማለህ።
ይሖዋ ራሱ ጥበብ ይሰጣልና፤ከአፉ እውቀትና ጥልቅ ግንዛቤ ይወጣል።
ለቅኖች ጥበብን እንደ ውድ ሀብት ያከማቻል፤ንጹሕ አቋማቸውን ጠብቀው ለሚመላለሱት ጋሻ ነው።
የፍትሕን ጎዳና ይከታተላል፤የታማኞቹንም መንገድ ይጠብቃል።
በዚህ ጊዜ ጽድቅ፣ ፍትሕና ትክክል የሆነውን ነገርይኸውም የጥሩነትን ጎዳና በሙሉ ትረዳለህ።
ጥበብ ወደ ልብህ ስትገባናእውቀት ነፍስህን ደስ ስታሰኝ፣
የማመዛዘን ችሎታ ምንጊዜም ይጠብቅሃል፤ጥልቅ ግንዛቤም ይጋርድሃል፤
ይህም አንተን ከክፉ መንገድ ለማዳንእንዲሁም ጠማማ ነገር ከሚናገር ሰው፣
በጨለማ መንገድ ለመጓዝቀናውን ጎዳና ከሚተዉ፣
መጥፎ ድርጊት በመፈጸም ሐሴት ከሚያደርጉ፣ጠማማ በሆኑ ክፉ ነገሮች ከሚደሰቱ፣
መንገዳቸው ጠማማ ከሆነናአካሄዳቸው በተንኮል ከተሞላ ሰዎች አንተን ለመታደግ ነው።
ጋጠወጥ ከሆነች ሴት፣ባለጌ ሴት ከምትናገረው የሚያባብል ቃል ያድንሃል፤
ይህች ሴት በወጣትነቷ የነበራትን የቅርብ ወዳጇን የምትተውእንዲሁም ከአምላኳ ጋር የገባችውን ቃል ኪዳን የምትረሳ ናት፤
ቤቷ ሰውን ይዞ ወደ ሞት ይወርዳልና፤አካሄዷም በሞት ወደተረቱት ይወስዳል።
ከእሷ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሁሉ አይመለሱም፤የሕይወትንም መንገድ ዳግመኛ አያገኙም።
በመሆኑም የጥሩ ሰዎችን መንገድ ተከተል፤እንዲሁም ከጻድቃን ጎዳና አትውጣ፤
በምድር ላይ የሚኖሩት ቅኖች ብቻ ናቸውና፤በእሷም ላይ የሚቀሩት ነቀፋ የሌለባቸው ናቸው።
ክፉዎች ግን ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፤ከዳተኞችም ከእሷ ይወገዳሉ።
የሰለሞን ምሳሌዎች። ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ሞኝ ልጅ ግን እናቱን ያሳዝናል።
በክፋት የተገኘ ሀብት ምንም ፋይዳ የለውም፤ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።
ይሖዋ ጻድቅ ሰው እንዲራብ አያደርግም፤የክፉዎችን ምኞት ግን ያጨናግፋል።
ሥራ የፈቱ እጆች ያደኸያሉ፤ትጉ እጆች ግን ብልጽግና ያስገኛሉ።
ጥልቅ ማስተዋል ያለው ልጅ እህሉን በበጋ ይሰበስባል፤አሳፋሪ ልጅ ግን በመከር ወቅት ለጥ ብሎ ይተኛል።
በረከት በጻድቅ ራስ ላይ ነው፤የክፉዎች አፍ ግን የዓመፅ ዕቅዳቸውን ይሰውራል።
የጻድቅ መታሰቢያ በረከት ያስገኛል፤የክፉዎች ስም ግን ይጠፋል።
ጥበበኛ ልብ ያለው ሰው መመሪያዎችን ይቀበላል፤በሞኝነት የሚናገር ሰው ግን ጥፋት ይደርስበታል።
ንጹሕ አቋሙን ጠብቆ የሚሄድ ያለስጋት ይመላለሳል፤መንገዱን ጠማማ የሚያደርግ ግን ይጋለጣል።
በተንኮል የሚጣቀስ ሐዘን ያመጣል፤በሞኝነት የሚናገር ሰውም ጥፋት ይደርስበታል።
የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ነው፤የክፉዎች አፍ ግን የዓመፅ ዕቅዳቸውን ይሰውራል።
ጥላቻ ጭቅጭቅ ያስነሳል፤ፍቅር ግን በደልን ሁሉ ይሸፍናል።
አስተዋይ በሆነ ሰው ከንፈር ጥበብ ትገኛለች፤በትር ግን ማስተዋል ለጎደለው ሰው ጀርባ ነው።
ጥበበኞች እውቀትን እንደ ውድ ሀብት ያከማቻሉ፤የሞኝ ሰው አፍ ግን ጥፋት ይጋብዛል።
የባለጸጋ ሀብት የተመሸገ ከተማው ነው። ድሆችን የሚያጠፋቸው ድህነታቸው ነው።
የጻድቅ ሰው ሥራ ወደ ሕይወት ይመራል፤የክፉ ሰው ፍሬ ግን ወደ ኃጢአት ይመራል።
ተግሣጽን የሚቀበል ለሌሎች የሕይወት መንገድ ይሆናል፤ወቀሳን ችላ የሚል ግን ሌሎች መንገድ እንዲስቱ ያደርጋል።
ጥላቻውን የሚሸፋፍን ሰው ሐሰት ይናገራል፤ተንኮል ያዘለ ወሬ የሚያስፋፋ ሰውም ሞኝ ነው።
ከቃላት ብዛት ስህተት አይታጣም፤ከንፈሩን የሚገታ ግን ልባም ሰው ነው።
የጻድቅ አንደበት ጥራት ያለው ብር ነው፤የክፉ ሰው ልብ ግን እርባና የለውም።
የጻድቅ ከንፈሮች ብዙዎችን ይመግባሉ፤ሞኞች ግን ማስተዋል ስለሚጎድላቸው ይሞታሉ።
የይሖዋ በረከት ባለጸጋ ታደርጋለች፤እሱም ከበረከቱ ጋር ሥቃይን አይጨምርም።
አሳፋሪ ምግባር መፈጸም ለሞኝ ሰው እንደ ጨዋታ ነው፤ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው ግን ጥበበኛ ነው።
ክፉ ሰው የፈራው ነገር ይደርስበታል፤ጻድቅ ግን የተመኘውን ያገኛል።
አውሎ ነፋስ ሲያልፍ ክፉ ሰው ተጠርጎ ይወሰዳል፤ጻድቅ ግን ለዘላለም እንደሚኖር መሠረት ነው።
ኮምጣጤ ጥርስን፣ ጭስም ዓይንን እንደሚጎዳ፣ሰነፍም ለሚልከው ሰው እንዲሁ ነው።
ይሖዋን መፍራት ዕድሜን ያስረዝማል፤የክፉዎች ዕድሜ ግን በአጭሩ ይቀጫል።
የጻድቃን ተስፋ ደስታ ያስገኛል፤የክፉዎች ተስፋ ግን መና ይቀራል።
የይሖዋ መንገድ፣ ያለነቀፋ ለሚመላለስ ሰው መሸሸጊያ ነው፤ለክፉ አድራጊዎች ግን መጥፊያቸው ነው።
ጻድቅ ሰው ምንም ነገር አይጥለውም፤ክፉዎች ግን በምድር ላይ መኖራቸውን አይቀጥሉም።
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያፈልቃል፤ጠማማ ምላስ ግን ትቆረጣለች።
የጻድቅ ሰው ከንፈሮች ደስ የሚያሰኘው ነገር ምን እንደሆነ ያውቃሉ፤የክፉዎች አፍ ግን ጠማማ ነው።
ሰው የልቡን ሐሳብ ያዘጋጃል፤የሚሰጠው መልስ ግን ከይሖዋ ዘንድ ነው።
ሰው መንገዱ ሁሉ ትክክል መስሎ ይታየዋል፤ይሖዋ ግን ውስጣዊ ዓላማን ይመረምራል።
የምታደርገውን ሁሉ ለይሖዋ አደራ ስጥ፤ዕቅድህም ሁሉ ይሳካል።
ይሖዋ ማንኛውንም ነገር ያዘጋጀው ለራሱ ዓላማ ነው፤ክፉውም ሰው እንኳ በመዓት ቀን እንዲጠፋ ያደርጋል።
ይሖዋ ኩሩ ልብ ያለውን ሁሉ ይጸየፋል። እንዲህ ያለው ሰው ሳይቀጣ እንደማይቀር እርግጠኛ ሁን።
በታማኝ ፍቅርና በታማኝነት በደል ይሰረያል፤ሰውም ይሖዋን በመፍራት ከክፋት ይርቃል።
ይሖዋ በሰው አካሄድ ደስ በሚሰኝበት ጊዜጠላቶቹ እንኳ ሳይቀሩ ከሰውየው ጋር ሰላም እንዲኖራቸው ያደርጋል።
አግባብ ባልሆነ መንገድ ከሚገኝ ብዙ ገቢ ይልቅበጽድቅ የሚገኝ ጥቂት ነገር ይሻላል።
ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፤ይሖዋ ግን አካሄዱን ይመራለታል።
የንጉሥ ከንፈር በመንፈስ ተመርቶ ውሳኔ መስጠት ይገባዋል፤ፍትሕን ፈጽሞ ማዛባት የለበትም።
ትክክለኛ መለኪያና ሚዛን ከይሖዋ ናቸው፤በከረጢት ውስጥ ያሉት መለኪያዎች ሁሉ የእሱ ሥራ ናቸው።
ክፉ ድርጊት በነገሥታት ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ዙፋን የሚጸናው በጽድቅ ነውና።
ነገሥታት የጽድቅ ንግግር ደስ ያሰኛቸዋል። ሐቁን የሚናገር ሰው ይወዳሉ።
የንጉሥ ቁጣ እንደ ሞት መልእክተኛ ነው፤ጥበበኛ ሰው ግን ቁጣውን ያበርደዋል።
የንጉሥ ፊት ሲፈካ ሰው በደስታ ይኖራል፤ሞገሱም ዝናብ እንዳዘለ የበልግ ደመና ነው።
ጥበብን ማግኘት ወርቅ ከማግኘት ምንኛ የተሻለ ነው! ማስተዋልን ማግኘትም ብር ከማግኘት ይመረጣል።
ቅኖች ከክፋት ጎዳና ይርቃሉ። መንገዱን የሚጠብቅ ሁሉ በሕይወት ይኖራል።
ኩራት ጥፋትን፣የትዕቢት መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።
የትዕቢተኞችን ምርኮ ከመካፈል ይልቅከየዋሆች ጋር የትሕትና መንፈስ ማሳየት ይሻላል።
አንድን ነገር ጠለቅ ብሎ የሚያስተውል ሰው ስኬታማ ይሆናል፤በይሖዋ የሚታመንም ደስተኛ ነው።