text
stringlengths
4
267
በሰይጣን ዓለም ውስጥ ያለው መንፈስ በብዙ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።
በዚህም ምክንያት ብዙዎች፣ ለሌሎች ሰዎች ተገቢውን አክብሮት ከማሳየት ይልቅ አምልኮ አከል ክብር ይሰጧቸዋል።
ለሃይማኖትና ለፖለቲካ መሪዎች፣ ለታዋቂ ስፖርተኞችና በመዝናኛው ዓለም ላሉ ስመ ጥር ሰዎች እንዲሁም ለሌሎች ዝነኛ ግለሰቦች በጣም የተጋነነ አመለካከት ስላላቸው ለሰው ከሚገባው ያለፈ አክብሮት ያሳዩዋቸዋል።
ወጣት አዋቂ ሳይል አብዛኛው ሰው እነዚህን ግለሰቦች እንደ አርዓያ በመውሰድ የእነሱን አኳኋን፣ አለባበስ ወይም ምግባር ይከተላል።
እውነተኛ ክርስቲያኖች ለሰዎች አክብሮት በማሳየት ረገድ እንዲህ ያለ የተዛባ አመለካከት ላለማዳበር ይጠነቀቃሉ።
ፍጹም አርዓያ የተወልን፣ ልንመስለው የሚገባ ሰው ክርስቶስ ብቻ ነው።
ሰዎችን ከሚገባቸው በላይ ክብር የምንሰጣቸው ከሆነ አምላክን እናሳዝናለን።
ሁሉም ኃጢአት ሠርተዋል፤ የአምላክንም ክብር ማንጸባረቅ ተስኗቸዋል የሚለውን እውነታ ማስታወሳችን ጠቃሚ ነው።
በእርግጥም አምልኮ አከል ክብር የሚገባው አንድም ሰው የለም።
እርቅ መፍጠራችን ከይሖዋ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት ለመመሥረት አስችሎናል።
ጳውሎስ ለቅቡዓን ወንድሞቹ በጻፈው ደብዳቤ ላይ ከይሖዋ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት የመመሥረት መብት ማግኘታችንን ከይሖዋ ጸጋ ጋር አያይዞ ገልጾታል፦ አሁን በእምነት አማካኝነት ጻድቃን ናችሁ ስለተባልን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከአምላክ ጋር ያለንን ሰላም ጠብቀን እንኑር፤ ደግሞም በኢየሱስ አማካኝነት የአምላክን ጸጋ ለማግኘት በእምነት ወደ እሱ መቅረብ የቻልን ሲሆን ይህን ጸጋ አሁን አግኝተናል።
ይህ እንዴት ያለ በረከት ነው! ሁላችንም ስንወለድ ጀምሮ ከጽድቅ ጎዳና የራቅን ነበርን።
ይሁንና ነቢዩ ዳንኤል፣ በፍጻሜው ዘመን ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው ይኸውም ቅቡዓን ቀሪዎች የጽድቅን ጎዳና እንዲከተሉ ብዙ ሰዎችን እንደሚረዱ ትንቢት ተናግሯል።
ቅቡዓን፣ በሚያከናውኑት የስብከትና የማስተማር ሥራ አማካኝነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሌሎች በጎች በይሖዋ ፊት የጽድቅ አቋም እንዲኖራቸው ረድተዋል።
ይህ ሊሳካ የቻለው ግን በይሖዋ ጸጋ ነው።
እንዲህ ያለው ጥምረት ከተፈጥሮ ውጭ ነበር፤ ሥጋ የለበሱት መላእክትና የሰው ሴቶች ልጆች፣ ኔፍሊም ተብለው የተጠሩ ዓመፀኛ ልጆች ወለዱ።
በወቅቱ የሰው ልጅ ክፋት በምድር ላይ በዝቶ ነበር።
ይሖዋ ክፉዎችን ለማጥፋት ሲል በኖኅ ዘመን የጥፋት ውኃ አመጣ።
በወቅቱ የነበሩት ሰዎች፣ ትዳርን ጨምሮ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ከሚገባው በላይ ተጠምደው ስለነበር የጽድቅ ሰባኪ የነበረው ኖኅ ስለሚመጣው ጥፋት የሚናገረውን መልእክት በቁም ነገር አልተመለከቱትም።
ኢየሱስ በኖኅ ዘመን የነበረውን ሁኔታ በዘመናችን ካለው ሁኔታ ጋር አመሳስሎታል።
በዛሬው ጊዜ ያሉት አብዛኞቹ ሰዎች፣ ይህ ክፉ ሥርዓት ከመጥፋቱ በፊት ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር እየተሰበከ ያለውን የአምላክን መንግሥት ምሥራች ለመስማት አሻፈረን ብለዋል።
እኛም እንደ ትዳርና ልጆችን እንደ ማሳደግ የመሳሰሉት የቤተሰብ ጉዳዮችም እንኳ የይሖዋን ቀን በጥድፊያ ስሜት እንዳንጠባበቅ እንቅፋት እንዲሆኑብን ልንፈቅድ አይገባም።
የምንኖረው የመጨረሻዎቹ ቀናት እየተገባደዱ ባሉበት ጊዜ ላይ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ጊዜ ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን በማለት ገልጾታል።
ያም ቢሆን ምንጊዜም በመንፈሳዊ ጠንካሮች መሆናችን የዚህን ዓለም መጥፎ ተጽዕኖ እንድናሸንፍ ኃይል ይሰጠናል።
ጳውሎስ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን ሲል ያገቡ ክርስቲያኖች፣ ትዳር የሚያስከትላቸውን ኃላፊነቶች ቸል እንዲሉ መምከሩ አይደለም።
ሆኖም የቀረው ጊዜ አጭር በመሆኑ ቅድሚያ መስጠት ያለባቸው ለመንፈሳዊ ጉዳዮች ነው።
የምንኖረው በጣም ተፈታታኝ በሆነ ዘመን ውስጥ ከመሆኑም ሌላ ብዙ ትዳሮች ሲፈርሱ እንመለከታለን፤ ያም ቢሆን ትዳራችን ደስታ የሰፈነበትና ስኬታማ እንዲሆን ማድረግ እንችላለን።
በእርግጥም ከይሖዋና ከሕዝቡ ጋር ተቀራርበው የሚኖሩ፣ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክሮችን ተግባራዊ የሚያደርጉ እንዲሁም የይሖዋ ቅዱስ መንፈስ እንዲመራቸው የሚፈቅዱ ያገቡ ክርስቲያኖች አምላክ ያጣመረውን ማንም ሰው አይለያየው የሚለውን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ።
በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ እረኛ ሆነው የሚያገለግሉ ብዙ ወንዶች ያስፈልጋሉ፤ በመሆኑም ወደፊት ይህን ኃላፊነት የሚቀበሉት ወንድሞች ቀጣይ የሆነ ሥልጠና ያስፈልጋቸዋል።
ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ እንዲህ ብሎታል፦ ከእኔ የሰማኸውንና ብዙዎች የመሠከሩለትን ነገር፣ ታማኝ ለሆኑ ሰዎች አደራ ስጥ፤ እነሱም በበኩላቸው ሌሎችን ለማስተማር ብቃቱን ያሟላሉ።
ጢሞቴዎስ ሥልጠና ያገኘው በዕድሜ ከሚበልጠው ሐዋርያ ጋር አብሮ በማገልገል ነው።
ከዚያም ጢሞቴዎስ ከጳውሎስ የተማረውን ነገር በስብከቱና በሌሎች የቅዱስ አገልግሎት ዘርፎች ተግባራዊ አድርጓል።
ጳውሎስ፣ ጢሞቴዎስን በራሱ ይሠልጥን ብሎ አልተወውም።
ከዚህ ይልቅ ይህ ወጣት አብሮት እንዲሠራ አድርጓል።
ሽማግሌዎችም እረኝነት ሲያደርጉ፣ ጥሩ ችሎታ ያላቸውን የጉባኤ አገልጋዮች ተገቢ በሚሆንበት ጊዜ ይዘዋቸው በመሄድ የጳውሎስን ምሳሌ መከተል ይችላሉ።
ሽማግሌዎች እንዲህ ማድረጋቸው፣ የጉባኤ አገልጋዮች ከክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች የሚጠበቁትን ባሕርያት ይኸውም የማስተማር ችሎታን፣ እምነትን፣ ትዕግሥትንና ፍቅርን እንዴት ማንጸባረቅ እንደሚቻል ለማየት አጋጣሚ ይሰጣቸዋል።
ይህም ወደፊት የአምላክ መንጋ እረኞች የሚሆኑት ወንድሞች ተገቢውን ሥልጠና ማግኘት እንዲችሉ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
ብዙዎች ከሚታገሏቸው ነገሮች አንዱ የሥጋ ድክመት ነው።
ሌሎች ደግሞ ለአገልግሎቱ አዎንታዊ አመለካከት ለመያዝ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አስፈልጓቸዋል።
አንተም ካለብህ የጤና እክል ወይም ከብቸኝነት ስሜት ጋር እየታገልክ ይሆናል።
ያስቀየማቸውን ወይም ከባድ በደል የፈጸመባቸውን ሰው ይቅር ለማለት የሚታገሉም አሉ።
በይሖዋ አገልግሎት ያሳለፍነው ጊዜ ምንም ያህል ቢሆን ሁላችንም፣ ለታማኞቹ ወሮታ ከፋይ የሆነውን አምላክ ማገልገል አስቸጋሪ እንዲሆንብን ከሚያደርጉ ነገሮች ጋር መታገል አለብን።
ልባችሁ መጥፎ ተጽዕኖ እያሳደረባችሁ እንደሆነ ከተሰማችሁ መንፈስ ቅዱስን ለማግኘት አጥብቃችሁ ጸልዩ።
መጸለያችሁና መንፈስ ቅዱስን ማግኘታችሁ፣ ትክክለኛውንና የይሖዋን በረከት የሚያስገኝላችሁን አካሄድ ለመከተል ብርታት ይሰጣችኋል።
በተጨማሪም ከጸሎታችሁ ጋር የሚስማማ እርምጃ ውሰዱ።
በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ጥረት አድርጉ፤ እንዲሁም የግል ጥናትና ቋሚ የቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራም ይኑራችሁ።
ሰዎች፣ አምላክ አለ የሚለው ሐሳብ በእምነት ላይ የተመሠረተ፣ ዝግመተ ለውጥ ግን በሳይንስ ላይ የተመሠረተ እንደሆነ ሲናገሩ ሰምተህ ታውቃለህ?
ብዙዎች እንዲህ ያለ አመለካከት አላቸው።
ይሁንና ልንዘነጋው የማይገባ አንድ ሐቅ አለ፦ አምላክ እንዳለ ለመቀበልም ሆነ ዝግመተ ለውጥን ለማመን እምነት ያስፈልጋል።
እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው?
ማንኛችንም ብንሆን አምላክን አይተን አሊያም አንድ ነገር ሲፈጠር ተመልክተን አናውቅም።
በሌላ በኩል ደግሞ ሕይወት ያለው አንድ ነገር በዝግመተ ለውጥ አማካኝነት ወደ ሌላ ሕያው ነገር ሲቀየር ተመልክቶ የሚያውቅ የሳይንስ ሊቅም ሆነ ሌላ ሰው የለም።
ለምሳሌ፣ በደረቱ የሚሳብ እንስሳ ወደ አጥቢ እንስሳ ሲቀየር ተመልክቶ የሚያውቅ ሰው የለም።
በመሆኑም ሁላችንም ብንሆን ያሉትን ማስረጃዎች መመርመርና በማመዛዘን ችሎታችን ተጠቅመን ምክንያታዊ የሆነ መደምደሚያ ላይ መድረስ ያስፈልገናል።
ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ አምላክ የፍጥረት ሥራዎች ሲናገር እንዲህ በማለት ጽፏል፦ የማይታዩት ባሕርያቱ ይኸውም ዘላለማዊ ኃይሉና አምላክነቱ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ በግልጽ ይታያሉ፤ ምክንያቱም ባሕርያቱን ከተሠሩት ነገሮች ማስተዋል ይቻላል፤ ስለሆነም የሚያመካኙበት ነገር የላቸውም።
ይሖዋ በፍቅር ተነሳስቶ በእስራኤል ይኖሩ ለነበሩ የባዕድ አገር ሰዎች እንደ ቃርሚያ ዝግጅት ያሉ አንዳንድ ዝግጅቶችን አድርጎላቸው ነበር።
ይሖዋ፣ እስራኤላውያን ለባዕድ አገር ሰው አክብሮት እንዲያሳዩ ከማዘዝ ይልቅ ራሳቸውን በእነሱ ቦታ አድርገው እንዲያስቡ አበረታቷቸዋል።
እስራኤላውያን የባዕድ አገር ሰው መሆን ምን ስሜት እንደሚያሳድር ያውቃሉ።
ዕብራውያኑ፣ ባሪያ ከመሆናቸው በፊትም እንኳ በዘራቸው ወይም በሃይማኖታቸው ምክንያት ግብፃውያኑ ያገልሏቸው ነበር።
እስራኤላውያን በግብፅ የባዕድ አገር ሰው እያሉ ሕይወት መራራ ሆኖባቸው ነበር፤ በመሆኑም ይሖዋ የባዕድ አገር ሰዎችን እንደ አገራቸው ተወላጅ አድርገው እንዲመለከቱ ነግሯቸዋል።
ይሖዋ በጉባኤ ስብሰባ ላይ ለሚገኙ የሌላ አገር ሰዎችም በጥንት ጊዜ ያሳየው ዓይነት አሳቢነት እንደሚያሳያቸው መተማመን እንችላለን።
እነዚህ ሰዎች መድልዎ ሊደርስባቸው እንደሚችል ወይም የአገሩን ቋንቋ ባለመቻላቸው እንደሚቸገሩ አሊያም ሌሎች ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሊያጋጥሟቸው እንደሚችሉ ካሰብን ለእነሱ ደግነት ለማሳየትና ስሜታቸውን ለመረዳት እንጥራለን።
ብዙዎቻችን ከመጠመቃችን በፊት ሕይወታችንን መሠረታዊ ከሆኑት የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ጋር ለማስማማት ጉልህ የሆኑ ለውጦችን ማድረግ አስፈልጎናል።
ከተጠመቅን በኋላ ደግሞ አምላክንና ክርስቶስን በቅርብ መከተል እንድንችል አንዳንድ ለውጦችን ማድረጋችንን መቀጠል እንደሚያስፈልገን ተገንዝበናል፤ እነዚህ ለውጦች ያን ያህል ጎልተው የማይታዩ ሊሆኑ ይችላሉ።
ለምሳሌ ነቃፊዎች እንደሆንን፣ ሰዎችን እንደምንፈራ፣ የሐሜት ልማድ እንዳለን አሊያም ሌላ ድክመት እንዳለብን አስተውለን ይሆናል።
ከእነዚህ ድክመቶች ጋር በተያያዘ ለውጥ ማድረግ ከጠበቅነው በላይ ከባድ ሆኖብናል?
አሁንም ፍጹማን አይደለንም።
በመሆኑም ከተጠመቅን ሌላው ቀርቶ በእውነት ውስጥ በርካታ ዓመታት ካስቆጠርን በኋላ እንኳ ፈጽመን ስህተት እንደማንሠራ፣ ድክመታችን ሊያሸንፈን እንደማይችል ወይም መጥፎ ስሜትና ዝንባሌ እንደማያስቸግረን ማሰቡ ምክንያታዊ አይሆንም።
አንዳንድ ድክመቶችን ለማሸነፍ ለዓመታት መታገል ሊያስፈልገን ይችላል።
በአዲሱ ዓለም ውስጥ ምድር ገነት ስትሆን ለማየት የምንጓጓ ቢሆንም በዚያ የምናገኛቸው መንፈሳዊ በረከቶች ትልቁን ቦታ ይይዛሉ።
የይሖዋ ስም እንደተቀደሰና ሉዓላዊነቱ እንደተረጋገጠ ማወቃችን እንዴት ያለ ጥልቅ ደስታ ያመጣልናል! ይሖዋ ለሰዎችም ሆነ ለምድር ከመጀመሪያው የነበረው ዓላማ ሲፈጸም ስናይ እጅግ እንደሰታለን።
ከዚህም ሌላ ቀስ በቀስ ወደ ፍጽምና ስንደርስ ወደ ይሖዋ መቅረብ ምን ያህል ቀላል እንደሚሆንልን አስበው! ኢየሱስ በአምላክ ዘንድ ሁሉ ነገር ይቻላል የሚል ማረጋገጫ ስለሰጠን እነዚህን በረከቶች እንደምናገኝ ጥያቄ የለውም።
ይሁንና በዚያ አዲስ ዓለም ውስጥ ለመኖር፣ ብሎም ከክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ባሻገር በሕይወት ለመቀጠል ተስፋ የምናደርግ ከሆነ የዘላለምን ሕይወት አጥብቀን ለመያዝ እርምጃ መውሰድ ያለብን ዛሬ ነው።
የዚህን ክፉ ዓለም ፍጻሜ እየተጠባበቅን መኖር ያለብን ከመሆኑም ሌላ በአዲሱ ዓለም ለሚኖረው ሕይወት ለመዘጋጀት የሚረዱንን እርምጃዎች አሁኑኑ መውሰድ ያስፈልገናል።
በራስ የመመራት መንፈስ ሰዎች የኩራት፣ የራስ ወዳድነትና የፉክክር መንፈስ እንዲያሳዩ ያደርጋል፤ ይህ ዓለም የተሞላው ደግሞ እንዲህ ባሉ ሰዎች ነው።
በዚህ መንፈስ መመራት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው፣ አንድ ግለሰብ የሚያደርገው ነገር በሌሎች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ምንም ይሁን ምን የራሱን ፍላጎት ብቻ ማርካቱ የተሻለ እንደሆነ የሚገልጸውን የሰይጣንን ሐሳብ በተዘዋዋሪ መንገድ እየደገፈ ነው።
ይህ ዓይነቱ የራስ ወዳድነት አካሄድ ጠብ እንዲፈጠር ያደርጋል።
ከዚህ በተቃራኒ ኢየሱስ፣ የግል ጥቅማቸውን የሚነካ ቢሆንም እንኳ ሰላምን እንዲፈልጉ ሰዎችን አስተምሯል።
ኢየሱስ አለመግባባቶችን ወይም ግጭት ሊፈጥሩ የሚችሉ ሁኔታዎችን መፍታት ስለሚቻልበት መንገድ በተራራው ስብከቱ ላይ ግሩም ምክር ሰጥቷል።
ለምሳሌ ደቀ መዛሙርቱ ገሮችና ሰላም ፈጣሪዎች እንዲሆኑ፣ ተቆጥተው እንዳይቆዩ፣ አለመግባባቶችን ቶሎ እንዲፈቱ እንዲሁም ጠላቶቻቸውን እንዲወዱ አሳስቧቸዋል።
አብዛኛውን ጊዜ ልጆች የማወቅ ጉጉት ያላቸው ከመሆኑም ሌላ ትሑቶች ናቸው።
በመሆኑም ጥበበኛ ወላጆች የእውነትን እውቀት በልጆቻቸው ልብና አእምሮ ውስጥ ለመቅረጽ እንዲሁም ልጆቻቸው ለእውነት ፍቅር እንዲያድርባቸው ለመርዳት ይጥራሉ።
እርግጥ ነው፣ ወላጆች በዚህ ረገድ እንዲሳካላቸው በቅድሚያ እውነትን በራሳቸው ልብ ውስጥ መቅረጽና በአኗኗራቸው ማሳየት ይኖርባቸዋል።
ወላጆች እውነትን በቃል ከመናገር አልፈው በሕይወታቸው ተግባራዊ የሚያደርጉት ከሆነ ልጆቻቸው እውነትን መውደድ ቀላል ይሆንላቸዋል።
በተጨማሪም ወላጆቻቸው ተግሣጽ የሚሰጧቸው ስለሚወዷቸው እንደሆነና እንዲህ ያለው ተግሣጽ ይሖዋ ለእነሱ ያለውን ፍቅር እንደሚያሳይ ይገነዘባሉ።
እኛም ትሑቶችና ምንጊዜም ይሖዋን የምንታዘዝ ከሆንን ልክ እንደ ነቢዩ ዳንኤል በይሖዋ ፊት የተወደድን እንሆናለን።
ከዚህም በላይ ይሖዋ በቃሉ፣ በመንፈሱና በድርጅቱ አማካኝነት ሁልጊዜ ይቀርጸናል።
ይሖዋ ስለ ራሳችን መንፈሳዊ ደህንነት ብቻ ሳይሆን እንደበደሉን የሚሰማንን ሰዎች ጨምሮ ስለ ሌሎች መንፈሳዊ ፍላጎትም እንድናስብ ይፈልጋል።
በእርግጥ ብዙውን ጊዜ የሚደርሱብን በደሎች ቀላል ናቸው፤ ሆኖም ወንድሞቻችንን ይቅር ስንላቸው፣ ከልብ እንደምንወዳቸውና መሐሪው አምላክ ይቅር እንዳለን ሁሉ እኛም እነሱን ይቅር ለማለት ፈቃደኛ እንደሆንን እናሳያለን።
የሚያሳዝነው ነገር፣ ፍጽምና የጎደለን ሰዎች በመሆናችን አንዳንድ ጊዜ በሌሎች ላይ ቂም እንይዝ ይሆናል።
ስለ ጉዳዩ ለሌሎች የምናወራ ከሆነ አንዳንዶች ከእኛ ጋር እንዲወግኑና በጉባኤ ውስጥ መከፋፈል እንዲፈጠር እናደርጋለን።
እንዲህ ያለው ሁኔታ እንዲቀጥል የምንፈቅድ ከሆነ ደግሞ ለአምላክ ምሕረትና ለቤዛው አድናቆት እንደጎደለን እናሳያለን።
የይቅር ባይነት መንፈስ የማናሳይ ከሆነ አባታችን በልጁ ቤዛዊ መሥዋዕት መሠረት እኛን ይቅር ማለቱን ይተዋል።
ኢየሱስ የጸሎት ናሙናውን ካስተማረ በኋላ ወዲያውኑ ስለዚህ ጉዳይ ማብራሪያ ሰጥቷል።
በመጨረሻም አምላክ ኃጢአታችንን ይቅር እንዲለን፣ በኃጢአት ጎዳና ላለመመላለስ ጥረት ማድረግ አለብን።
ይሖዋ ለመንፈሳዊ ገነታችን ውበት አስተዋጽኦ እንድናበረክት የፈቀደልን መሆኑ ትልቅ መብት ነው።
የመንግሥቱን ምሥራች በቅንዓት በመስበክና ተጨማሪ ደቀ መዛሙርት በማፍራት መንፈሳዊውን ገነት ይበልጥ እናስውበዋለን።
አንድ ሰው ራሱን ወስኖ ክርስቲያን እንዲሆን በረዳን ቁጥር የመንፈሳዊው ገነት ወሰን እንዲሰፋ እያደረግን ነው ሊባል ይችላል።
ክርስቲያናዊ ባሕርያችንን በየጊዜው በማሻሻልም መንፈሳዊው ገነት ይበልጥ ማራኪ እንዲሆን ማድረግ እንችላለን።
በዚህ መንገድ መንፈሳዊው ገነት ለሚመለከቱት ሰዎች ይበልጥ ውብ እንዲሆን እናደርጋለን።