text stringlengths 4 267 |
|---|
ጳውሎስ፣ ቅቡዓን ክርስቲያኖች በምድር ባሉ ነገሮች ላይ ከማተኮር ይልቅ ዜግነታቸው በሰማይ መሆኑን እንዲያስታውሱ አሳስቧቸዋል። |
እነዚህ ክርስቲያኖች ክርስቶስን ተክተው የሚሠሩ አምባሳደሮች ናቸው። |
አምባሳደሮች ደግሞ በተመደቡባቸው አገራት ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ አይገቡም። |
ታማኝ መሆን ያለባቸው ለሌላ መንግሥት ነው። |
ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ክርስቲያኖችም የአምላክ መንግሥት ተገዢዎች በመሆናቸው በዚህ ዓለም ላይ ባሉ ውዝግቦች ረገድ ከማንም ወገን አለመቆማቸው ተገቢ ነው። |
ወጣቷ የአባቷን መመለስ በጭንቀት ስትጠባበቅ ቆይታለች። |
አባቷ ድል ተቀዳጅቶ ከጦር ሜዳ በሰላም መመለሱን ስታይ በደስታ ልትቀበለው ወጣች። |
አባቷ ግን ከእሷ ጋር አብሮ በመደሰትና በመጨፈር ፋንታ ልብሱን ቀዶ ወዮ፣ ልጄ! ልቤን ሰበርሽው አላት። |
ከዚያም ሕይወቷን ለዘለቄታው የሚቀይር ብሎም እንደማንኛውም ሰው የመኖር ምኞቷንና ተስፋዋን የሚያከስም ነገር ተናገረ። |
እሷ ግን ምንም ሳታመነታ፣ አባቷ ለይሖዋ የገባውን ቃል እንዲፈጽም አበረታታችው። |
የተናገረችው ነገር ታላቅ እምነት እንዳላት ያሳያል። |
ይሖዋ የሚጠይቃት ማንኛውም ነገር፣ እሷን የሚጠቅም እንደሆነ እምነት ነበራት። |
አባቷም የእሷን ምላሽ ሲሰማ ልቡ በኩራት ተሞላ፤ ምክንያቱም ውሳኔውን በፈቃደኝነት መደገፏ የይሖዋን ሞገስ እንደሚያስገኝ ያውቃል። |
ዮፍታሔና ልጁ፣ የይሖዋን ፈቃድ ማድረግ ከባድ በሚሆንበት ጊዜም እንኳ አምላክ ነገሮችን በሚያከናውንበት መንገድ ላይ እምነት እንዳላቸው አሳይተዋል። |
የይሖዋን ሞገስ ለማግኘት ሲባል ማንኛውንም መሥዋዕት መክፈል ፈጽሞ እንደማያስቆጭ እርግጠኞች ነበሩ። |
ይሖዋ ኃጢአታችንን ሙሉ በሙሉ ይቅር የሚለን በቤዛው ላይ እምነት ካለን ነው። |
የአምላክ ቃል ኃጢአታችን ሊደመሰስ እንደሚችል ማረጋገጫ ይሰጠናል። |
ይሖዋ በመንፈስ የተቀቡ አገልጋዮቹን በቤዛው አማካኝነት ልጆቹ አድርጎ ተቀብሏቸዋል። |
የሌሎች በጎች ክፍል የሆንነውን ደግሞ እንደ ልጆቹ አድርጎ ለመቀበል የሚያስችል፣ ስማችን የተጻፈበት የምሥክር ወረቀት ያዘጋጀልን ያህል ነው። |
ወደ ፍጽምና ደረጃ ከደረስንና የመጨረሻውን ፈተና ካለፍን በኋላ ይሖዋ በምሳሌያዊ አነጋገር በምሥክር ወረቀቱ ላይ በመፈረም ምድራዊ ልጆቹ አድርጎ ይቀበለናል። |
ይሖዋ ውድ ለሆኑት ልጆቹ ያለው ፍቅር ዘላለማዊ ነው። |
ቤዛው የሚያስገኛቸው ጥቅሞችም ቢሆኑ ዘላለማዊ ናቸው። |
ይህ ስጦታ መቼም ቢሆን ዋጋው አይቀንስም። |
ማንኛውም ሰውም ሆነ ኃይል ይህን ስጦታ ሊወስድብን አይችልም። |
ይሖዋ ወደ ራሱ የሳበን የትኞቹ የኃጢአት ዝንባሌዎች ይበልጥ እንደሚያስቸግሩን በሚገባ እያወቀ ነው። |
አልፎ አልፎ እንደምንሳሳትም ይገነዘባል። |
ይሁንና ይሖዋ ይህንን ሁሉ እያወቀ ወዳጆቹ እንድንሆን ጋብዞናል። |
አምላክ በፍቅር ተነሳስቶ እጅግ ውድ ስጦታ ይኸውም የሚወደውን ልጁን ቤዛ አድርጎ ሰጥቶናል። |
ኃጢአት በምንሠራበት ጊዜ ንስሐ ከገባንና በዋጋ ሊተመን የማይችለውን ይህን ዝግጅት መሠረት በማድረግ ይቅር እንዲለን ይሖዋን ከጠየቅነው፣ ፍጹም ባንሆንም እንኳ ከእሱ ጋር ያለን ወዳጅነት እንደሚቀጥል እርግጠኞች መሆን እንችላለን። |
ኢሳይያስ፣ ይህ ነቢይ መሪና አዛዥ እንደሚሆን አስቀድሞ ተናግሯል። |
ዳንኤልም መሪ የሆነው መሲሕ እንደሚመጣ በመንፈስ መሪነት ጽፏል። |
በመጨረሻም ኢየሱስ ክርስቶስ የአምላክ ሕዝቦች መሪ እሱ እንደሆነ ገልጿል። |
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በገዛ ፈቃዳቸው ተነሳስተው የተከተሉት ሲሆን ይሖዋ እሱን እንደመረጠው ያምኑ ነበር። |
ይሁንና ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ብለው እንዲያምኑ ያደረጋቸው ምንድን ነው? |
አጥማቂው ዮሐንስ፣ ኢየሱስ በተጠመቀበት ወቅት ሰማያት ተከፍተው መንፈስ እንደ ርግብ በእሱ ላይ ሲወርድ ተመልክቶ ነበር። |
ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎቱን ባከናወነበት ጊዜ ሁሉ ተአምራትን እንዲፈጽምና ይሖዋ በሰጠው ሥልጣን እንዲናገር መንፈስ ቅዱስ ኃይል ሰጥቶታል። |
በተጨማሪም መንፈስ ቅዱስ፣ ኢየሱስ እንደ ፍቅር፣ ደስታና ጠንካራ እምነት ያሉትን ባሕርያት እንዲያፈራ ረድቶታል። |
ኢየሱስ የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ድጋፍ እንዳለው በግልጽ ታይቷል። |
ኢየሱስን መሪ እንዲሆን የመረጠው ይሖዋ ነው። |
የዮፍታሔ ልጅ ንጹሑን አምልኮ ለመደገፍ ስትል፣ ባል የማግባትና ልጅ የመወለድ ተፈጥሯዊ ፍላጎቷን መሥዋዕት አድርጋለች። |
እሷ ያሳየችውን የራስን ጥቅም መሥዋዕት የማድረግ መንፈስ መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው? |
በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣት ክርስቲያን ወንዶችና ሴቶች፣ ይሖዋን በተሟላ መንገድ ለማገልገል ሲሉ ትዳር የመመሥረት አሊያም ልጆች የመውለድ አጋጣሚያቸውን ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን በፈቃደኝነት መሥዋዕት አድርገዋል። |
በጉልምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ክርስቲያኖችም ቢሆኑ በቲኦክራሲያዊ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ወይም በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት ለመካፈል አሊያም የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ሄደው ለማገልገል ሲሉ ከልጆቻቸውና ከልጅ ልጆቻቸው ጋር ሊያሳልፉ የሚችሉትን ጊዜ መሥዋዕት አድርገዋል። |
ሌሎች ደግሞ በአገልግሎት ዘመቻዎች ላይ ለመካፈል ሲሉ የግል ጉዳዮቻቸውን ለመተው ፈቃደኛ ሆነዋል። |
እንዲህ ያለው በሙሉ ልብ የሚቀርብ አገልግሎት ይሖዋን በጣም ያስደስተዋል፤ ይሖዋም ሥራቸውንና ለእሱ ያሳዩትን ፍቅር ፈጽሞ አይረሳም። |
የአምላክን ሕግ ለማይከተሉ ሰዎች እንኳ ደግነት ማሳየት ቢገባንም ከእነሱ ጋር ወዳጅነት ልንመሠርት ወይም የቅርብ ጓደኛችን ልናደርጋቸው አይገባም። |
በመሆኑም አንድ ያላገባ የይሖዋ ምሥክር፣ ራሱን ለአምላክ ካልወሰነና ለይሖዋ ታማኝ ካልሆነ እንዲሁም የአምላክን የላቁ መሥፈርቶች ከማያከብር ሰው ጋር የፍቅር ጓደኝነት መመሥረቱ ስህተት ይሆናል። |
በይሖዋ ሕግጋት በማይመሩ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ከማግኘት ይበልጥ ትልቅ ቦታ ልንሰጠው የሚገባው ነገር፣ ክርስቲያናዊ አቋማችንን ይዘን መቀጠላችን ነው። |
የቅርብ ወዳጆቻችን ሊሆኑ የሚገባው የአምላክን ፈቃድ የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው። |
መጥፎ ጓደኝነት የሚያስከትለው አስከፊ መዘዝ በእስራኤላውያን ላይ ደርሷል። |
ለአምላክ ታማኝ ባለመሆናቸው ከጊዜ በኋላ ኢየሱስ እነሆ፣ ቤታችሁ ለእናንተ የተተወ ይሆናል ብሏቸዋል። |
በመሆኑም ይሖዋ እስራኤላውያንን ትቶ በረከቱን አዲስ በተቋቋመው የክርስቲያን ጉባኤ ላይ አደረገ። |
የይሖዋ ሕዝቦች ትሕትና የሚያዳብሩ ከሆነ ኢየሱስ በተራራው ስብከቱ ላይ የተናገረውን አስፈላጊ መሠረታዊ ሥርዓት ተግባራዊ ያደርጋሉ። |
ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ ባልንጀራህን ውደድ፤ ጠላትህን ጥላ እንደተባለ ሰምታችኋል። |
እኔ ግን እላችኋለሁ፦ ጠላቶቻችሁን ውደዱ እንዲሁም ስደት ለሚያደርሱባችሁ ጸልዩ፤ ይህን ብታደርጉ በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ፤ እሱ በክፉዎችም ሆነ በጥሩ ሰዎች ላይ ፀሐዩን ያወጣልና፤ በጻድቃንም ሆነ ጻድቃን ባልሆኑ ሰዎች ላይ ዝናብ ያዘንባል። |
በእርግጥም የአምላክ አገልጋዮች እንደመሆናችን መጠን፣ ሰዎች ለእኛ ያላቸው አመለካከት ምንም ይሁን ምን ጠላቶቻችንን መውደድን መማር አለብን። |
የይሖዋ ሕዝቦች እሱንና ባልንጀራቸውን እንደሚወዱ በአመለካከታቸውም ሆነ በድርጊታቸው፣ በሁሉም የሕይወታቸው ዘርፎች ማሳየት ይኖርባቸዋል። |
ለምሳሌ ያህል፣ የመንግሥቱን መልእክት የማይቀበሉ ሰዎችም እንኳ በሚቸገሩበት ጊዜ ፍቅር እናሳያቸዋለን። |
አስቀድሞ የተነገረው የስብከት ሥራ የሚቆየው ለምን ያህል ጊዜ ነው? |
ኢየሱስ ይህ ዓለም አቀፋዊ የስብከት ሥራ በመጨረሻዎቹ ቀናት ውስጥም እንደሚከናወንና ከዚያም መጨረሻው እንደሚመጣ ተናግሯል። |
ታሪካዊ በሆኑት በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ ምሥራቹን እየሰበከ ያለ ሌላ ሃይማኖታዊ ቡድን አለ? |
በአገልግሎት ላይ የምናገኛቸው አንዳንድ ሰዎች መንፈስ ቅዱስ ያለን እኛ ነን፤ ሥራውን የምታከናውኑት ግን እናንተ ናችሁ ይሉናል። |
ይሁን እንጂ በሥራው በጽናት መቀጠላችን የአምላክ መንፈስ እንዳለን የሚያሳይ ማስረጃ አይደለም? |
አንዳንድ ሃይማኖታዊ ቡድኖች የይሖዋ ምሥክሮች አዘውትረው የሚያከናውኑትን ሥራ ለመሥራት የሞከሩባቸው ጊዜያት አሉ፤ ይሁንና አብዛኛውን ጊዜ ጥረታቸው ውጤታማ አልሆነም። |
ሌሎች ደግሞ በሚስዮናዊነት ሥራ ለተወሰነ ጊዜ ቢሳተፉም ብዙም ሳይቆይ ወደ ወትሮው ኑሯቸው ይመለሳሉ። |
ከቤት ወደ ቤት ለመሄድ የሚሞክሩም አሉ፤ ሆኖም የሚሰብኩት ስለ ምንድን ነው? |
የዚህ ጥያቄ መልስ እነዚህ ሰዎች ክርስቶስ የጀመረውን ሥራ እያከናወኑ እንዳልሆኑ በግልጽ ያሳያል። |
‘ለመስተካከል እና አዲሱን ስብዕና ለመልበስ ሁልጊዜ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል። |
ጳውሎስ ለእምነት አጋሮቹ የሚከተለውን ማሳሰቢያ ሰጥቷል፦ ከቀድሞ አኗኗራችሁ ጋር የሚስማማውንና አታላይ በሆነው ምኞቱ እየተበላሸ የሚሄደውን አሮጌውን ስብዕናችሁን አውልቃችሁ እንድትጥሉ ተምራችኋል። |
ደግሞም አእምሯችሁን የሚያሠራው ኃይል እየታደሰ ይሂድ፤ እንዲሁም እንደ አምላክ ፈቃድ የተፈጠረውንና ከእውነተኛ ጽድቅና ታማኝነት ጋር የሚስማማውን አዲሱን ስብዕና መልበስ ይኖርባችኋል። |
እየታደሰ ይሂድ የሚለው አገላለጽ አዲሱን ስብዕና መልበስ ቀጣይነት ያለው ሂደት መሆኑን ይጠቁማል። |
ይህን ማወቅ የሚያበረታታ ነው፤ ምክንያቱም ይሖዋን በማገልገል ያሳለፍነው ጊዜ ምንም ያህል ቢሆን፣ አዲሱን ስብዕና ለመልበስ የሚረዱንን ክርስቲያናዊ ባሕርያት ምንጊዜም እያዳበርንና እያሻሻልን መሄድ እንደምንችል ማረጋገጫ ይሰጠናል። |
በእርግጥም መጽሐፍ ቅዱስ በሕይወታችን ውስጥ ምንጊዜም ለውጥ ማምጣት ይችላል። |
የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት፣ ኢየሱስ በገሊላ ባሕር ላይ ሲራመድ አዩት። |
ጴጥሮስ ኢየሱስን ጠርቶ በውኃው ላይ እየተራመደ ወደ እሱ መምጣት ይችል እንደሆነ ጠየቀው። |
ኢየሱስም እንዲመጣ ሲነግረው ጴጥሮስ ከጀልባዋ ላይ ወርዶ በሚናወጠው ውኃ ላይ በተአምር እየተራመደ ወደ ኢየሱስ ሄደ። |
ብዙም ሳይቆይ ግን ጴጥሮስ መስመጥ ጀመረ። |
ለምን? |
ምክንያቱም ማዕበሉን ሲያይ ፈራ። |
ጴጥሮስ፣ ኢየሱስ እንዲረዳው ጮኸ፤ እሱም ወዲያውኑ እጁን ዘርግቶ ያዘውና ከላይ ያለውን ተናገረ። |
ጴጥሮስ ከጀልባዋ ወርዶ በውኃው ላይ እንዲራመድ ያስቻለው እምነት ነው። |
ኢየሱስ ጴጥሮስን ሲጠራው ጴጥሮስ የአምላክ ኃይል ኢየሱስን እንደረዳው ሁሉ እሱንም ሊረዳው እንደሚችል ተማምኖ ነበር። |
እኛም በተመሳሳይ ራሳችንን ለይሖዋ እንድንወስንና እንድንጠመቅ ያስቻለን እምነታችን ነው። |
ኢየሱስ የእሱ ተከታዮች እንድንሆን ይኸውም ፈለጉን እንድንከተል ጠርቶናል። |
ኢየሱስም ሆነ አምላክ በተለያዩ መንገዶች እንደሚረዱን በመተማመን በእነሱ ላይ እምነት እንዳለን ማሳየት ይኖርብናል። |
አንድ አፍቃሪ አባት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ነገሮች አንዱ ቤተሰቡን ከጉዳት ወይም አደጋ ሊያደርስ ከሚችል ነገር መጠበቅ ወይም መታደግ እንደሆነ ግልጽ ነው። |
በሰማይ የሚኖረው አባታችን ይሖዋ ከዚህ ያነሰ ነገር እንደማያደርግ የታወቀ ነው። |
አንድ ምሳሌ እንመልከት። |
መቼም ለዓይንህ በጣም እንደምትሳሳ ግልጽ ነው! ይሖዋ ለሕዝቡ ያለው ስሜትም ልክ እንደዚህ ነው። |
በእርግጥም አምላክ ለሕዝቡ በጣም ይሳሳል! እርግጥ ነው፣ ይሖዋ እንደ እስጢፋኖስ ያሉ ታማኝ አገልጋዮቹ በጠላቶቻቸው እጅ ሕይወታቸው እንዲያልፍ የፈቀደበት ጊዜ አለ። |
ይሁንና አምላክ የሰይጣንን መሠሪ ዘዴዎች መቋቋም እንዲችሉ ወቅታዊ ማስጠንቀቂያዎችን በመስጠት ሕዝቡን በአጠቃላይ ከአደጋ ይጠብቃል። |
ይሖዋ በቃሉና ድርጅቱ በሚያዘጋጃቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች አማካኝነት ሀብት ስላለው የማታለል ኃይል፣ ብልግናና ዓመፅ ስለተሞላባቸው መዝናኛዎች፣ ተገቢ ስላልሆነ የኢንተርኔት አጠቃቀምና ስለመሳሰሉት ነገሮች እውነቱን መገንዘብ እንድንችል ይረዳናል። |
ከዚህ በግልጽ መረዳት እንደምንችለው ይሖዋ ልክ እንደ አንድ አፍቃሪ አባት ሕዝቡን ከአደጋ ይጠብቃል። |
የመንግሥት አዳራሽ በአንድ አካባቢ ለሚካሄደው ንጹሕ አምልኮ ማዕከል ነው። |
ይሖዋ እኛን በመንፈሳዊ ለመመገብ ካደረጋቸው ዝግጅቶች መካከል በመንግሥት አዳራሾች ውስጥ የሚከናወኑት ሳምንታዊ ስብሰባዎች ይገኙበታል። |
በድርጅቱ በኩል አስፈላጊ የሆነ መንፈሳዊ ምግብና መመሪያ የሚሰጠን በስብሰባዎቻችን ላይ ነው። |
ከይሖዋ ማዕድ እንድንመገብ ሁልጊዜም ግብዣ ይቀርብልናል፤ ይህ መሆኑ ግን ግብዣውን አቅልለን እንድንመለከተው በፍጹም ሊያደርገን አይገባም። |
ይሖዋ፣ ለአምልኮና እርስ በርስ ለመበረታታት የሚያስችሉን እነዚህ አጋጣሚዎች በጣም አስፈላጊ እንደሆኑ ስለሚያውቅ መሰብሰባችንን ቸል እንዳንል የሚያሳስብ መልእክት ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት እንዲጽፍ አድርጓል። |
በማይረባ ምክንያት ከክርስቲያናዊ ስብሰባዎች የምንቀር ከሆነ ለይሖዋ አክብሮት እያሳየን ነው ማለት እንችላለን? |
በሌላ በኩል ግን ለክርስቲያናዊ ስብሰባዎች በመዘጋጀትና በሙሉ ልብ ተሳትፎ በማድረግ ለይሖዋና ለዝግጅቱ ምን ያህል አድናቆት እንዳለን ማሳየት እንችላለን። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.