text
stringlengths
4
267
አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች መጀመሪያ ወደ ድርጅቱ እንዲሳቡ እንዲሁም ወደ አምላክና ወደ ክርስቶስ እንዲቀርቡ የሚያነሳሳቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ይበልጥ የእኛ ንጹሕና ሰላማዊ ምግባር ነው።
ይሖዋና ኢየሱስ በዛሬው ጊዜ ያለንን ውብ መንፈሳዊ ገነት ሲመለከቱ ምንኛ ይደሰቱ ይሆን! በአሁኑ ጊዜ መንፈሳዊ ገነታችንን ይበልጥ ከማስዋብ የምናገኘው ደስታ ወደፊት ምድርን ቃል በቃል ወደ ገነትነት ስንለውጥ ለምናገኘው እርካታ ቅምሻ ነው።
ዮፍታሔ ሌላ ልጅ ስላልነበረው የዘር ሐረጉ እንዲቀጥል የሚያደርግም ሆነ ርስቱን የሚወርስ ልጅ ማግኘት የሚችለው በሴት ልጁ በኩል ብቻ ነበር።
ያም ሆኖ እንደሚገልጸው ዮፍታሔ አንዴ ለይሖዋ ቃል ገብቻለሁ፤ ልመልሰውም አልችልም በማለት ተናገረ።
ከፍተኛ መሥዋዕት ቢያስከፍለውም በይሖዋ ላይ እምነት እንዳለው ማሳየቱ የአምላክን ሞገስና በረከት አስገኝቶለታል።
አንተ ብትሆን እንዲህ ታደርግ ነበር?
ሕይወታችንን ለይሖዋ ስንወስን ራሳችንን ምንም ሳንቆጥብ የእሱን ፈቃድ ለመፈጸም ተስለናል።
ይህን ቃል መጠበቅ የራሳችንን ጥቅም መሥዋዕት ማድረግ እንደሚጠይቅብን እናውቃለን።
ይሁንና የማንወደውን ነገር እንድናደርግ ስንጠየቅ፣ የፈቃደኝነት መንፈስ ያለን መሆን አለመሆኑ ጥያቄ ውስጥ ይገባል።
የተጠየቅነውን በማድረግና መሥዋዕትነት በመክፈል ከለመድነው ብሎም ከሚመቸን በተለየ መንገድ አምላክን ስናገለግል እምነት እንዳለን እናሳያለን።
የምንከፍለው መሥዋዕት የቱንም ያህል ከባድ ቢሆን፣ ከምናገኘው የላቀ በረከት ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ የሚባል አይሆንም።
ኢየሱስ ምሥራቹ በመላው ምድር እንደሚሰበክ ሲናገር ሥራው ምን ያህል ስፋት እንደሚኖረው ገልጿል።
ተከታዮቹ፣ ደቀ መዛሙርት የሚያደርጉት ከሁሉም ብሔራት የተውጣጡ ሰዎችን ነው።
በመሆኑም ሥራው መካሄድ ያለበት በዓለም አቀፍ ደረጃ ነው።
የይሖዋ ምሥክሮች የስብከቱ ሥራ ከሚከናወንበት ስፋት ጋር በተያያዘ ኢየሱስ የተናገረውን ትንቢት እንዴት እንደፈጸሙ መረዳት እንድንችል አንዳንድ ነጥቦችን እስቲ እንመልከት።
በዩናይትድ ስቴትስ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ቡድኖች ውስጥ ወደ 600,000 የሚጠጉ ቀሳውስት አሉ፤ በዚህች አገር 1,200,000 ገደማ የይሖዋ ምሥክሮች ይገኛሉ።
የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በዓለም ዙሪያ ያሏት ቀሳውስት ከ400,000 ብዙም አይበልጡም።
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተውን የመንግሥቱን ስብከት ሥራ የሚያከናውኑት የይሖዋ ምሥክሮች ምን ያህል እንደሆኑ ደግሞ እንመልከት።
በዓለም ዙሪያ በ240 አገሮች የሚገኙ ወደ ስምንት ሚሊዮን የሚጠጉ ፈቃደኛ አገልጋዮች ለሰዎች ምሥራቹን ይሰብካሉ።
እንዴት ያለ አስደናቂ ሥራ እያከናወኑ ነው! ይህም ለይሖዋ ውዳሴና ክብር ያመጣል።
ኢየሱስ የክርስቲያን ጉባኤን የሚመራው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው።
ፈተናዎችን ለመቋቋም፣ ለአገልግሎት የሚያስፈልገንን ድፍረትና ሥልጠና ለማግኘት እንዲሁም ጥሩ ውሳኔዎችን ለማድረግ የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ያስፈልገናል።
እንግዲያው የጉባኤ ስብሰባዎችን ጨምሮ፣ ይህን መንፈስ ማግኘት የምንችልበት ማንኛውም አጋጣሚ እንዲያመልጠን አንፍቀድ።
በብዙዎቹ ስብሰባዎቻችን ላይ የመጽሐፍ ቅዱስን ትንቢቶች ፍጻሜ እንመረምራለን።
ይህ ደግሞ ይሖዋ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሰጣቸው ተስፋዎችም እንደሚፈጸሙ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል።
እርግጥ ነው፣ ማበረታቻ የምናገኘው ከመድረክ ከሚቀርበው ትምህርት ብቻ አይደለም።
በስብሰባዎች ላይ ሐሳብ የሚሰጡና ከልባቸው የሚዘምሩ የእምነት ባልንጀሮቻችንም ያንጹናል።
በተጨማሪም ከስብሰባዎቻችን በፊትና በኋላ ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን ጋር ስንጨዋወት፣ ከልብ የሚወዱን ወዳጆች እንዳሉን ስለምንገነዘብ መንፈሳችን ይታደሳል።
መጽሐፍ ቅዱስ በመጨረሻዎቹ ቀናት ክፋት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚባባስ ይነግረናል።
በመሆኑም ዓለም በአሁኑ ጊዜ መጥፎ ሁኔታ ላይ ቢሆንም ወደፊት ከዚህም እየከፋ እንደሚሄድ መጠበቅ እንችላለን።
ይሁንና ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ነገሮች ምን ያህል የከፉ እንደሚሆኑ ትጠብቃለህ?
ለምሳሌ በየአገሩ ጦርነት እንደሚነሳ፣ ማንም ሰው የሚላስ የሚቀመስ እንደማያገኝና በየቤቱ የታመመ ሰው እንደሚኖር ትጠብቃለህ?
ሁኔታዎች እዚህ ደረጃ ላይ ከደረሱ ተጠራጣሪዎች እንኳ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜውን እያገኘ እንዳለ አምነው ለመቀበል ይገደዳሉ።
ሆኖም ኢየሱስ አብዛኞቹ ሰዎች በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ከመጠመዳቸው የተነሳ እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ የመገኘቱን ምልክት ፈጽሞ እንደማያስተውሉ ተናግሯል።
ቅዱሳን መጻሕፍት፣ በመጨረሻዎቹ ቀናት በዓለም ላይ የሚኖረው ሁኔታ እጅግ መጥፎ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች መጨረሻው መቅረቡን እንዲያምኑ የሚያደርግ ነገር እንደሚኖር አይገልጹም።
እምነት በሰብዓዊ ዓይን ሲታይ የማይቻል የሚመስሉ ነገሮችን እንድናደርግ ያስችለናል።
ለምሳሌ ያህል፣ አብዛኞቻችን የቀድሞ ማንነታችንን ያውቁ የነበሩ ሰዎች ሊለዩን እስከማይችሉ ድረስ አስተሳሰባችንና ድርጊታችን በከፍተኛ ሁኔታ ተለውጧል።
ይሖዋ በእሱ በመታመን እነዚህን እርምጃዎች በመውሰዳችን ጥረታችንን ባርኮልናል።
በእምነት ተነሳስተን ራሳችንን ለይሖዋ ከወሰንን በኋላ ከእሱ ጋር ወዳጅነት መመሥረት ችለናል፤ ይህ ደግሞ በራሳችን ኃይል ልናደርገው የምንችለው ነገር አይደለም።
እምነታችን ምንጊዜም ጠንካሮች እንድንሆን ያደርገናል።
ከሰው በላይ ኃይል ያለው ጠላታችን ዲያብሎስ የሚሰነዝርብንን ጥቃት መቋቋም የቻልነው በእምነት ነው።
በተጨማሪም በይሖዋ መታመናችን ፈታኝ በሆኑ ወቅቶች ከልክ በላይ በጭንቀት እንዳንዋጥ ይረዳናል።
ይሖዋ በእምነት ተነሳስተን ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የምናስቀድም ከሆነ ቁሳዊ ፍላጎታችንን እንደሚያሟላልን ቃል ገብቷል።
ከዚህ በላይ ደግሞ እምነታችን፣ የትኛውም ሰው በራሱ ጥረት ሊያገኝ የማይችለውን ስጦታ ይኸውም የዘላለም ሕይወት ያስገኝልናል።
አምላክ አስቀድሞ የወደደን በምን መንገድ ነው?
ሐዋርያው ጳውሎስ አምላክ ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ እንዲሞትልን በማድረግ ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር አሳይቷል ብሏል።
ፍቅር የይሖዋ ዋነኛ ባሕርይ ነው፤ በመሆኑም ኢየሱስ፣ አምላክ የሰጠው የመጀመሪያው ትእዛዝ የቱ እንደሆነ ጥያቄ ላቀረበለት ሰው አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣ በሙሉ አእምሮህና በሙሉ ኃይልህ ውደድ በማለት መልስ የሰጠው ለምን እንደሆነ መረዳት አያዳግትም።
ኢየሱስ፣ አምላክን ስለ መውደድ ሲናገር መጀመሪያ ላይ የጠቀሰው ልብን እንደሆነ መመልከት እንችላለን።
ይሖዋ የተከፈለ ልብ አያስደስተውም።
ይሁን እንጂ በሙሉ ነፍሳችን፣ በሙሉ አእምሯችንና በሙሉ ኃይላችን አምላክን መውደድ እንዳለብንም መዘንጋት አይኖርብንም።
ይህም ማለት ለአምላክ ያለን እውነተኛ ፍቅር እንዲሁ ከልባችን ብቻ የሚመነጭ ስሜት እንዳልሆነ ያስገነዝበናል።
ለአምላክ ያለን ፍቅር ከልብ የሚመነጭ ከመሆንም አልፎ መንፈሳዊና አካላዊ ችሎታዎቻችንን በሙሉ የሚጨምር መሆን አለበት።
ነቢዩ ሚክያስ በገለጸው መሠረት ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው ይህን ነው።
በሕይወታችን ውስጥ የአምላክን እጅ በግልጽ ማየት የሚሳነን ለምን ሊሆን ይችላል?
የሕይወት ውጣ ውረዶች አስተሳሰባችንን ሊቆጣጠሩት ይችላሉ።
እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥመን ይሖዋ ከዚህ በፊት እንዴት እንደረዳን ማየት ሊሳነን ይችላል።
ንግሥት ኤልዛቤል፣ ነቢዩ ኤልያስን እንደምትገድለው በዛተች ጊዜ ኤልያስ፣ አምላክ ከዚህ በፊት ያደረገለትን ነገር ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ዘንግቶ ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ኤልያስ እንዲሞትም መለመን ጀመረ ይላል።
ኤልያስ ያጋጠመው ችግር መፍትሔ ምን ነበር?
ይሖዋ ብርታት እንዲሰጠው መጠየቅ ነበረበት።
ኢዮብም ባስጨነቁት ጉዳዮች ከመዋጡ የተነሳ ነገሮችን ከአምላክ አንጻር መመልከት ተስኖት ነበር።
እኛም አምላክ እንዲታየን እንደ ኢዮብ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ሊያስፈልገን ይችላል።
ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?
ቅዱሳን መጻሕፍት በሚፈነጥቁልን ብርሃን ተጠቅመን ባጋጠመን ሁኔታ ላይ በማሰላሰል ነው።
ይሖዋ እንዴት እየረዳን እንዳለ ስንገነዘብ እሱ ይበልጥ እውን ይሆንልናል።
ኢየሱስ አገልግሎቱን ባከናወነበት ወቅት ትኩረቱን ሊከፋፍሉ የሚችሉ ብዙ ነገሮች አጋጥመውት ነበር፤ እሱ ግን ለእነዚህ ነገሮች አልተሸነፈም።
በአገልግሎቱ መጀመሪያ ላይ በቅፍርናሆም ብዙ ሕዝብ ካስተማረና ተአምር ከፈጸመ በኋላ የከተማዋ ነዋሪዎች እዚያው እንዲቆይ ለመኑት።
ታዲያ ኢየሱስ ሰዎቹ ባቀረቡለት በዚህ ጥያቄ ተሸንግሎ ይሆን?
በፍጹም፤ ለሌሎች ከተሞችም የአምላክን መንግሥት ምሥራች ማወጅ አለብኝ፤ ምክንያቱም የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው ሲል ተናግሯል።
ኢየሱስ ልክ እንደተናገረው እየሰበከና እያስተማረ በመላው የፓለስቲና ምድር ተዘዋውሯል።
ፍጹም ቢሆንም እንኳ እንደ ማንኛውም ሰው መሠረታዊ ነገሮች ያስፈልጉት ነበር፤ እንዲሁም በአምላክ አገልግሎት በትጋት በመካፈሉ በጣም የደከመው ጊዜ ነበር።
በሌላ ጊዜ ደግሞ ኢየሱስ ተከታዮቹ የሚያጋጥማቸውን ተቃውሞ እንዴት መቋቋም እንደሚችሉ እያስተማራቸው ሳለ አንድ ሰው በንግግሩ መሃል ጣልቃ ገብቶ መምህር፣ ወንድሜ ውርሳችንን እንዲያካፍለኝ ንገረው አለው።
ኢየሱስ ግን እዚህ ጭቅጭቅ ውስጥ መግባት አልፈለገም።
ፍቅር ዋነኛውና ከሁሉ የላቀው የአምላክ ባሕርይ ነው።
ይሖዋ አፍቃሪ ብቻ ሳይሆን የፍቅር ተምሳሌት ነው።
የጽንፈ ዓለምና የሁሉም ሕይወት ያላቸው ነገሮች ፈጣሪ የፍቅር አምላክ መሆኑን ማወቅ ምንኛ የሚያስደስት ነው! ይሖዋ ማንኛውንም ነገር የሚያደርገው በፍቅር ተነሳስቶ ነው።
አምላክ ለፍጡራኑ ደግነት የሚንጸባረቅበትና ጥልቅ የሆነ ፍቅር ያለው መሆኑ፣ ለሰው ዘር ቤተሰብ ያለው ዓላማ በሙሉ ከሁሉ በተሻለ መንገድ እንደሚፈጸምና ይህም በእሱ አገዛዝ ሥር ላሉ ሁሉ ወደር የሌለው ጥቅም እንደሚያስገኝ ለመተማመን ያስችለናል።
ለምሳሌ፣ ይሖዋ በሾመው ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በዓለም ሁሉ ላይ በጽድቅ ለመፍረድ ዓላማ ያለው ሲሆን ይህን ለማድረግም ቀን ወስኗል፤ እንዲህ ያደረገው በፍቅር ተነሳስቶ ነው።
ይህ ዓላማው መፈጸሙ እንደማይቀር እርግጠኛ መሆን እንችላለን።
ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ያላቸውና ታዛዥ የሆኑ ሰዎች መልካም ፍርድ የሚበየንላቸው ሲሆን ይህም በበረከት የተሞላና ማብቂያ የሌለው ዘላለማዊ ሕይወት ያስገኝላቸዋል።
ሐዋርያቱ ወሳኝ በሆነ ጊዜ ላይ ኢየሱስን ጥለውት ሸሽተዋል።
ቀደም ሲል ጴጥሮስ፣ ሌሎቹ ኢየሱስን ቢተዉት እንኳ እሱ እንደማይተወው ተናግሮ ነበር።
የሚያሳዝነው ግን ኢየሱስ ሲያዝ፣ ጴጥሮስን ጨምሮ ሐዋርያቱ ሁሉ ጥለውት ሸሹ።
ጴጥሮስ ኢየሱስን ጨርሶ እንደማያውቀው በመግለጽ በተደጋጋሚ ጊዜ ካደው።
ያም ሆኖ ጴጥሮስ በመጸጸቱ ይሖዋ ከዚያም በኋላ ተጠቅሞበታል።
በዚያን ጊዜ የምትኖር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ብትሆን ኖሮ የጴጥሮስ ድርጊት ይሖዋን በታማኝነት እንዳታገለግል እንቅፋት ይሆንብህ ነበር?
በዛሬው ጊዜ ይሖዋ ስህተት የሠሩ ሰዎች ንስሐ እንዲገቡ ጊዜ እንደሚሰጣቸው እንዲሁም የተፈጸመውን ስህተት ውሎ አድሮ እንደሚያስተካክለውና ትክክለኛውን እርምጃ እንደሚወስድ ትተማመናለህ?
በሌላ በኩል ደግሞ ከባድ ኃጢአት የፈጸሙ አንዳንድ ሰዎች ንስሐ ገብተው የይሖዋን ምሕረት ለማግኘት ጥረት ላያደርጉ ይችላሉ።
ይሖዋ ሰዎችን ሲመለከት ትኩረት የሚሰጠው ለውጫዊ ገጽታቸው አይደለም።
ከዚህ ይልቅ ልባቸውን ይኸውም ውስጣዊ ማንነታቸውን ይመረምራል።
አምላክ የክርስቲያን ጉባኤን ሲያቋቁም ያደረገው ነገር ይህን በግልጽ ያሳያል።
ከሰብዓዊ አመለካከት አንጻር እምብዛም የማይፈለጉ የሚመስሉ ብዙ ሰዎችን ወደ ራሱና ወደ ልጁ ስቧል።
ሳኦል የተባለን ፈሪሳዊ እንደ ምሳሌ መውሰድ ይቻላል።
ልብን የሚመረምረው አምላክ ሳኦልን ዋጋ እንደሌለው ሸክላ አድርጎ አልቆጠረውም።
ከዚህ ይልቅ ውድ ዕቃ ተደርጎ ሊቀረጽ እንደሚችል የሸክላ አፈር አድርጎ ተመልክቶታል፤ እንዲያውም በአሕዛብ እንዲሁም በነገሥታትና በእስራኤል ልጆች ፊት የሚመሠክር የተመረጠ ዕቃ ተብሎ ተጠርቷል።
በተጨማሪም አምላክ ቀደም ሲል ሰካራሞች፣ የፆታ ብልግና የሚፈጽሙና ሌቦች የነበሩ አንዳንድ ሰዎችን ክቡር ለሆነ አገልግሎት ሊውሉ እንደሚችሉ ዕቃዎች አድርጎ ተመልክቷቸዋል።
እነዚህ ሰዎች ከአምላክ ቃል ትክክለኛ እውቀት እየቀሰሙና እምነታቸው እያደገ ሲሄድ በይሖዋ ለመቀረጽ ፈቃደኞች ሆነዋል።
እንዲህ ያለውን ክፍፍል የሚፈጥር አመለካከት ለማስወገድ መፍትሔው ምንድን ነው?
ጳውሎስ ለክርስቲያኖች የሚከተለውን ምክር ሰጥቷቸዋል፦ ወንድሞች፣ ሁላችሁም ንግግራችሁ አንድ እንዲሆንና በመካከላችሁ መከፋፈል እንዳይኖር፣ ከዚህ ይልቅ በአስተሳሰብም ሆነ በዓላማ ፍጹም አንድነት እንዲኖራችሁ አጥብቄ አሳስባችኋለሁ።
ዛሬም ቢሆን በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ምንም ዓይነት መከፋፈል ሊኖር አይገባም።