text
stringlengths
4
267
እነሱም ዑሪያህን ከግብፅ አምጥተው ወደ ንጉሥ ኢዮዓቄም ወሰዱት፤ እሱም በሰይፍ መትቶ ገደለው፤ አስከሬኑንም ተራ ሰዎች በሚቀበሩበት ስፍራ ጣለው።”
ይሁንና የሳፋን ልጅ አኪቃም ኤርምያስን ረዳው፤ በመሆኑም ኤርምያስ እንዲገደል ለሕዝቡ አልተሰጠም።
በቢንያም አገር በአናቶት ከነበሩት ካህናት አንዱ የሆነው የኬልቅያስ ልጅ የኤርምያስ ቃል ይህ ነው።
የይሁዳ ንጉሥ የአምዖን ልጅ ኢዮስያስ በነገሠ በ13ኛው ዓመት የይሖዋ ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ።
ደግሞም በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮዓቄም ዘመን፣ እንዲሁም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ የሴዴቅያስ 11ኛው ዓመት የግዛት ዘመን እስካበቃበት ጊዜ ድረስ ይኸውም ኢየሩሳሌም ወደ ግዞት እስከተወሰደችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ ቃሉ ወደ እሱ መጣ።
የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
“በማህፀን ውስጥ ሳልሠራህ በፊት አውቄሃለሁ፤ከመወለድህም በፊት ቀድሼሃለሁ። ለብሔራት ነቢይ አድርጌሃለሁ።”
እኔ ግን “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮልኝ! እኔ ገና ልጅ ስለሆንኩ ምን ብዬ እንደምናገር አላውቅም” አልኩ።
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “‘እኔ ገና ልጅ ነኝ’ አትበል። ወደምልክህ ሁሉ ትሄዳለህና፤የማዝህንም ሁሉ ትናገራለህ።
ከቁመናቸው የተነሳ አትፍራ፤‘አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና’ ይላል ይሖዋ።”
ከዚያም ይሖዋ እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ። ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “ቃሌን በአፍህ አኑሬአለሁ።
እንግዲህ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፣ እንድታጠፋና እንድታወድም፣ እንድትገነባና እንድትተክል ዛሬ በብሔራትና በመንግሥታት ላይ ሾሜሃለሁ።”
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ “ኤርምያስ፣ የምታየው ምንድን ነው?” እኔም “የአልሞንድ ዛፍ ቅርንጫፍ አያለሁ” አልኩ።
ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “በትክክል አይተሃል፤ እኔ ቃሌን ለመፈጸም በከፍተኛ ንቃት እየተጠባበቅኩ ነውና።”
የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እኔ መጥቶ “ምን ይታይሃል?” አለኝ። እኔም “የተጣደ ድስት አያለሁ፤ አፉም ከሰሜን ወደ ደቡብ ያዘነበለ ነው” አልኩ።
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “በምድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ ላይከሰሜን ጥፋት ይመጣል።
‘በሰሜን ያሉትን መንግሥታት ነገዶች ሁሉ እጠራለሁና’ ይላል ይሖዋ፤‘እነሱም ይመጣሉ፤ እያንዳንዱም ዙፋኑንበኢየሩሳሌም በሮች መግቢያ፣በቅጥሮቿ ዙሪያ ሁሉናበይሁዳ ከተሞች ሁሉ ላይ ያደርጋል።
ደግሞም እኔን ስለተዉ፣ለሌሎች አማልክትም የሚጨስ መሥዋዕት ስለሚያቀርቡናበገዛ እጃቸው ለሠሯቸው ነገሮች ስለሚሰግዱበክፋታቸው ሁሉ ላይ ፍርዴን አውጃለሁ።’
አንተ ግን ለሥራ ተዘጋጅ፤ደግሞም ተነስ፤ እኔ የማዝህንም ሁሉ ንገራቸው። እኔ ራሴ በፊታቸው እንዳላሸብርህ፣እነሱን አትፍራቸው።
ምድሪቱን ሁሉ፣ የይሁዳን ነገሥታትና መኳንንቷን፣ካህናቷንና የምድሪቱን ሕዝብ እንድትቋቋም፣ዛሬ አንተን የተመሸገ ከተማ፣የብረት ዓምድና የመዳብ ቅጥር አድርጌሃለሁ።
እነሱም በእርግጥ ይዋጉሃል፤ሆኖም አያሸንፉህም፤‘አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና’ ይላል ይሖዋ።”
የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦
“አንድ ጥቅልል ውሰድና በኢዮስያስ ዘመን ለአንተ መናገር ከጀመርኩበት ቀን አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤል፣ በይሁዳና በብሔራት ሁሉ ላይ አመጣዋለሁ ብዬ የነገርኩህን ቃል በሙሉ ጻፍበት።
ምናልባት የይሁዳ ቤት ሰዎች በእነሱ ላይ ላመጣ ያሰብኩትን ጥፋት ሁሉ ሲሰሙ ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ።”
ከዚያም ኤርምያስ የነሪያህን ልጅ ባሮክን ጠራው፤ ይሖዋ የነገረውንም ቃል ሁሉ በቃሉ አስጻፈው፤ ባሮክም በጥቅልሉ ላይ ጻፈው።
ኤርምያስም ባሮክን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “እኔ ታግጃለሁ፤ ወደ ይሖዋ ቤትም መግባት አልችልም።
ስለዚህ ገብተህ እኔ ያስጻፍኩህን የይሖዋን ቃል ከጥቅልሉ ላይ ጮክ ብለህ ማንበብ ያለብህ አንተ ነህ። በጾም ቀን በይሖዋ ቤት የተሰበሰቡ ሰዎች እየሰሙ አንብበው፤ በዚህ መንገድ፣ ከየከተሞቻቸው ለመጡት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ታነብላቸዋለህ።
ምናልባት ሞገስ ለማግኘት የሚያቀርቡት ልመና ወደ ይሖዋ ሊደርስና እያንዳንዳቸው ከክፉ መንገዳቸው ሊመለሱ ይችላሉ፤ ይሖዋ በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቁጣና መዓት ታላቅ ነውና።”
በመሆኑም የነሪያህ ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ፤ በይሖዋ ቤት የይሖዋን ቃል ከጥቅልሉ ላይ ጮክ ብሎ አነበበ።
የኢዮስያስ ልጅ የሆነው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት፣ በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም ያለው ሕዝብ ሁሉና ከይሁዳ ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጣው ሕዝብ ሁሉ በይሖዋ ፊት ጾም አወጀ።
ከዚያም ባሮክ በይሖዋ ቤት በላይኛው ግቢ ይኸውም በይሖዋ ቤት በአዲሱ በር መግቢያ አጠገብ ባለው፣ የቅዱሳን መጻሕፍት ገልባጭ በሆነው በሳፋን ልጅ በገማርያህ ክፍል ሕዝቡ ሁሉ እየሰማ የኤርምያስን ቃል ከጥቅልሉ ላይ አነበበ።
የሳፋን ልጅ፣ የገማርያህ ልጅ ሚካያህ ከጥቅልሉ ላይ የተነበበውን የይሖዋን ቃል ሁሉ በሰማ ጊዜ
ወደ ንጉሡ ቤት፣ ወደ ጸሐፊው ክፍል ወረደ። መኳንንቱ ሁሉ ይኸውም ጸሐፊው ኤሊሻማ፣ የሸማያህ ልጅ ደላያህ፣ የአክቦር ልጅ ኤልናታን፣ የሳፋን ልጅ ገማርያህ፣ የሃናንያህ ልጅ ሴዴቅያስና ሌሎቹ መኳንንት ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።
ሚካያህ፣ ባሮክ ሕዝቡ እየሰማ ከጥቅልሉ ላይ ሲያነብ ያዳመጠውን ቃል ሁሉ ነገራቸው።
በዚህ ጊዜ መኳንንቱ ሁሉ የኩሺ ልጅ፣ የሸሌምያህ ልጅ፣ የነታንያህ ልጅ የሆነውን የሁዲን “ሕዝቡ እየሰማህ ያነበብከውን ጥቅልል ይዘህ ና” ብሎ እንዲነግረው ወደ ባሮክ ላኩት። የነሪያህ ልጅ ባሮክም ጥቅልሉን ይዞ ወደ እነሱ ሄደ።
እነሱም “እባክህ ተቀመጥና ጥቅልሉን ጮክ ብለህ አንብብልን” አሉት። ባሮክም አነበበላቸው።
እነሱም ቃሉን ሁሉ እንደሰሙ በፍርሃት ተውጠው እርስ በርስ ተያዩ፤ ከዚያም ባሮክን “ይህን ቃል ሁሉ ለንጉሡ ልንነግረው ይገባል” አሉት።
ደግሞም ባሮክን “ይህን ሁሉ ቃል የጻፍከው እንዴት እንደሆነ እስቲ ንገረን። በቃሉ ነው ያስጻፈህ?” ብለው ጠየቁት።
ባሮክም “ይህን ሁሉ በቃሉ አስጻፈኝ፤ እኔም በጥቅልሉ ላይ በቀለም ጻፍኩት” ብሎ መለሰላቸው።
መኳንንቱ ባሮክን “ሂድ፣ አንተና ኤርምያስ ተደበቁ፤ ያላችሁበትንም ማንም ሰው አይወቅ” አሉት።
ከዚያም ንጉሡ ወደሚገኝበት ግቢ ሄዱ፤ ጥቅልሉንም በጸሐፊው በኤሊሻማ ክፍል አስቀመጡት፤ የሰሙትንም ነገር ሁሉ ለንጉሡ ነገሩት።
ንጉሡም ጥቅልሉን እንዲያመጣ የሁዲን ላከው፤ እሱም ጥቅልሉን ከጸሐፊው ከኤሊሻማ ክፍል ይዞት መጣ። የሁዲም ንጉሡና በንጉሡ አጠገብ ቆመው የነበሩት መኳንንት ሁሉ እየሰሙ ያነበው ጀመር።
ንጉሡ በዘጠነኛው ወር የክረምቱን ወቅት በሚያሳልፍበት ቤት ተቀምጦ ነበር፤ በፊቱም በምድጃ የሚነድ እሳት ነበር።
የሁዲ ሦስት ወይም አራት ዓምድ ካነበበ በኋላ ንጉሡ የተነበበውን ክፍል በጸሐፊ ቢላ እየቀደደ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ይወረውረው ነበር፤ ጥቅልሉ ሙሉ በሙሉ ተቃጥሎ እስኪያልቅ ድረስ እንዲሁ አደረገ።
ይህን ሁሉ ቃል ሲሰሙ የነበሩት ንጉሡም ሆነ አገልጋዮቹ በሙሉ ምንም ፍርሃት አልተሰማቸውም፤ ልብሳቸውንም አልቀደዱም።
ኤልናታን፣ ደላያህና ገማርያህ ንጉሡ ጥቅልሉን እንዳያቃጥለው ቢለምኑትም እንኳ አልሰማቸውም።
በተጨማሪም ንጉሡ ጸሐፊውን ባሮክንና ነቢዩን ኤርምያስን እንዲይዟቸው የንጉሡን ልጅ የራህምኤልን፣ የአዝርዔልን ልጅ ሰራያህንና የአብድዔልን ልጅ ሸሌምያህን አዘዘ፤ ይሖዋ ግን ሰውሯቸው ነበር።
ንጉሡ፣ ባሮክ ከኤርምያስ አፍ እየሰማ የጻፈውን ቃል የያዘውን ጥቅልል ካቃጠለው በኋላ የይሖዋ ቃል እንደገና እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦
“ሌላ ጥቅልል ውሰድና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም ባቃጠለው በመጀመሪያው ጥቅልል ላይ የነበረውን ያንኑ ቃል ሁሉ ጻፍበት።
የይሁዳን ንጉሥ ኢዮዓቄምንም እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህን ጥቅልል አቃጥለሃል፤ ደግሞም ‘“የባቢሎን ንጉሥ ያላንዳች ጥርጥር መጥቶ ይህችን ምድር ያወድማል፤ ሰውንና እንስሳንም ከምድሪቱ ላይ ያጠፋል” ብለህ በጥቅልሉ ላይ የጻፍከው ለምንድን ነው?’ ብለሃል።
ስለዚህ ይሖዋ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓቄም ላይ እንዲህ ይላል፦ ‘በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው አይኖረውም፤ ሬሳውም የቀን ሐሩርና የሌሊት ቁር ይፈራረቅበታል።
እሱን፣ ልጆቹንና አገልጋዮቹን ለፈጸሙት በደል ተጠያቂ አደርጋቸዋለሁ፤ ደግሞም በእነሱ፣ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎችና በይሁዳ ሰዎች ላይ አመጣባቸዋለሁ ብዬ የተናገርኩትን ጥፋት ሁሉ አወርድባቸዋለሁ፤ እነሱ ግን አልሰሙም።’”’”
ከዚያም ኤርምያስ ሌላ ጥቅልል ወስዶ ለነሪያህ ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው፤ እሱም ኤርምያስ በቃል እያስጻፈው የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በእሳት ባቃጠለው ጥቅልል ላይ የነበረውን ቃል ሁሉ ጻፈበት። ደግሞም ከዚያ ጋር የሚመሳሰል ብዙ ቃል ተጨመረበት።
ከይሖዋ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፦
“በይሖዋ ቤት በር ላይ ቆመህ በዚያ ይህን መልእክት አውጅ፦ ‘ለይሖዋ ለመስገድ በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ፣ የይሖዋን ቃል ስሙ።
የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መንገዳችሁንና ተግባራችሁን አስተካክሉ፤ እኔም በዚህ ስፍራ እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።
‘ይህ የይሖዋ ቤተ መቅደስ፣ የይሖዋ ቤተ መቅደስ፣ የይሖዋ ቤተ መቅደስ ነው!’ እያላችሁ በአሳሳች ቃል አትታመኑ።
በእርግጥ መንገዳችሁንና ተግባራችሁን ብታስተካክሉ፣ በሰውና በባልንጀራው መካከል ፍትሕ ብታሰፍኑ፣
ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው፣ ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና መበለቶችን ባትጨቁኑ፣ በዚህ ቦታ የንጹሕ ሰው ደም ባታፈሱ እንዲሁም ጉዳት ላይ የሚጥሏችሁን ሌሎች አማልክት ባትከተሉ፣
በዚህች ስፍራ፣ ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው በዚህ ምድር ለዘለቄታው እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።”’”
“እናንተ ግን አሳሳች በሆነ ቃል ታምናችኋል፤ ይህ ደግሞ ፈጽሞ አይጠቅማችሁም።
እየሰረቃችሁ፣ እየገደላችሁ፣ እያመነዘራችሁ፣ በሐሰት እየማላችሁ፣ ለባአል መሥዋዕት እያቀረባችሁና የማታውቋቸውን አማልክት እየተከተላችሁ፣
በስሜ ወደሚጠራው ወደዚህ ቤት መጥታችሁ በፊቴ መቆምና እነዚህን ሁሉ አስጸያፊ ነገሮች እያደረጋችሁ ‘ምንም ችግር አይደርስብንም’ ማለት ትችላላችሁ?
ስሜ የሚጠራበት ይህ ቤት በእናንተ ዓይን የዘራፊዎች ዋሻ ሆኗል ማለት ነው? እነሆ፣ እኔ ራሴ ይህን አይቻለሁ” ይላል ይሖዋ።
“‘አሁን ግን መጀመሪያ የስሜ ማደሪያ አድርጌው ወደነበረው በሴሎ ወዳለው ስፍራዬ ሂዱ፤ ከሕዝቤ ከእስራኤል ክፋት የተነሳም ምን እንዳደረግኩት እዩ።
እናንተ ግን እነዚህን ሁሉ ነገሮች መሥራታችሁን ቀጠላችሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለእናንተ ደግሜ ደጋግሜ ብናገርም እንኳ አልሰማችሁም። ደጋግሜ ጠራኋችሁ፤ እናንተ ግን መልስ አትሰጡም።
ስለዚህ በሴሎ እንዳደረግኩት ሁሉ በስሜ በተጠራው፣ እናንተም በምትታመኑበት በዚህ ቤት ላይ እንዲሁም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጠሁት በዚህ ቦታ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።
ወንድሞቻችሁን ሁሉ ይኸውም መላውን የኤፍሬም ዘር እንዳስወገድኩ እናንተንም ከፊቴ አስወግዳችኋለሁ።’
“አንተም ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ። እኔ ስለማልሰማህ ስለ እነሱ የልመና ጩኸትም ሆነ ጸሎት አታሰማ ወይም እኔን አትማጸን።
በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የሚያደርጉትን አታይም?
እኔን ያሳዝኑ ዘንድ ‘ለሰማይ ንግሥት’ መሥዋዕት የሚሆን ቂጣ ለመጋገር ወንዶች ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፣ አባቶች እሳት ያቀጣጥላሉ፣ ሚስቶች ደግሞ ሊጥ ያቦካሉ፤ ለሌሎች አማልክትም የመጠጥ መባ ያፈሳሉ።
‘ለመሆኑ የሚጎዱት እኔን ነው?’ ይላል ይሖዋ። ‘በራሳቸው ላይ ውርደት በማምጣት የሚጎዱት ራሳቸውን አይደለም?’
ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ንዴቴና ቁጣዬ በዚህ ቦታ፣ በሰውና በእንስሳ፣ በዱር ዛፎችና በምድሪቱ ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ቁጣዬ ይነድዳል፤ ፈጽሞም አይጠፋም።’
“የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የጀመራችሁትን ግፉበት፤ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን በሌሎች መሥዋዕቶቻችሁ ላይ ጨምሩ፤ ሥጋውንም ራሳችሁ ብሉ።
አባቶቻችሁን ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ ሙሉ በሙሉ ስለሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች አልነገርኳቸውም ወይም አላዘዝኳቸውም።
ከዚህ ይልቅ ይህን ትእዛዝ ሰጥቻቸው ነበር፦ “ድምፄን ስሙ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ። መልካም እንዲሆንላችሁ በማዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።”’
እነሱ ግን አልሰሙም ወይም ጆሯቸውን አልሰጡም፤ ይልቁንም ግትር ሆነው ክፉ ልባቸውን በመከተል በገዛ ራሳቸው ዕቅድ ሄዱ፤ ወደ ፊት በመሄድ ፋንታ ወደ ኋላ ተመለሱ፤
አባቶቻችሁ ከግብፅ ምድር ከወጡበት ጊዜ አንስቶ እስከዚህ ቀን ድረስ ይህን አደረጉ። በመሆኑም አገልጋዮቼ የሆኑትን ነቢያት ሁሉ ወደ እናንተ መላኬን ቀጠልኩ፤ ደግሜ ደጋግሜ በየዕለቱ ላክኋቸው።
እነሱ ግን እኔን ለመስማት እንቢተኛ ሆኑ፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም። ይልቁንም ግትር ሆኑ፤ አባቶቻቸው ከሠሩት የከፋ ነገር አደረጉ!
“ይህን ሁሉ ቃል ትነግራቸዋለህ፤ እነሱ ግን አይሰሙህም፤ ትጠራቸዋለህ፤ እነሱ ግን አይመልሱልህም።
እንዲህም ትላቸዋለህ፦ ‘ይህ ብሔር የአምላኩን የይሖዋን ድምፅ አልሰማም፤ ተግሣጽ ለመቀበልም እንቢተኛ ሆኗል። ታማኝነት ጠፍቷል፤ በመካከላቸውም ጨርሶ አይነሳም።’
“ያልተቆረጠውን ፀጉርሽን ሸልተሽ ጣይው፤ በተራቆቱት ኮረብቶችም ላይ ሙሾ አውርጂ፤ ይሖዋ እጅግ ያስቆጣውን ይህን ትውልድ ጥሎታልና፤ እርግፍ አድርጎም ይተወዋል።
‘የይሁዳ ሰዎች በፊቴ መጥፎ ነገር ሠርተዋልና’ ይላል ይሖዋ። ‘አስጸያፊ ጣዖቶቻቸውን በስሜ በተጠራው ቤት ውስጥ በማስቀመጥ አርክሰውታል።
ያላዘዝኩትንና በልቤ እንኳ ፈጽሞ ያላሰብኩትን ነገር ለማድረግ ይኸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ለማቃጠል በሂኖም ልጅ ሸለቆ የሚገኘውን የቶፌትን ከፍ ያሉ የማምለኪያ ቦታዎች ሠርተዋል።’
“‘ከዚህ የተነሳ፣’ ይላል ይሖዋ፣ ‘የእርድ ሸለቆ እንጂ ቶፌት ወይም የሂኖም ልጅ ሸለቆ ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል። እነሱም ቦታ እስኪታጣ ድረስ በቶፌት ይቀብራሉ።
የዚህ ሕዝብ አስከሬንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ ፈርተው እንዲሸሹ የሚያደርጋቸውም የለም።
የሐሴትንና የደስታን ድምፅ እንዲሁም የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ፣ ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም ጎዳናዎች አጠፋለሁ፤ ምድሪቱ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለችና።’”
የይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ ኢዮዓቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት ይኸውም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት መላውን የይሁዳን ሕዝብ በተመለከተ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
ነቢዩ ኤርምያስ የይሁዳን ሕዝብ ሁሉና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች በሙሉ አስመልክቶ እንዲህ ሲል ተናገረ፦
“ከይሁዳ ንጉሥ ከአምዖን ልጅ ከኢዮስያስ 13ኛ ዓመት የግዛት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ላለፉት 23 ዓመታት የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፤ እኔም ደግሜ ደጋግሜ ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን አትሰሙም።
ይሖዋም ደግሞ ደጋግሞ አገልጋዮቹን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ ላከ፤ እናንተ ግን አትሰሙም ወይም ጆሯችሁን አትሰጡም።
እነሱም እንዲህ ይላሉ፦ ‘እባካችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ድርጊታችሁ ተመለሱ፤ ይህን ካደረጋችሁ ይሖዋ ለብዙ ዘመን እንድትኖሩባት ሲል ከረጅም ጊዜ በፊት ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣት ምድር ላይ ትኖራላችሁ።
በእጃችሁ ሥራ ታስቆጡኝ ዘንድ ሌሎች አማልክትን አትከተሉ፣ አታገልግሏቸው፣ አትስገዱላቸውም፤ አለዚያ ጥፋት አመጣባችኋለሁ።’
“‘እናንተ ግን እኔን አትሰሙም’ ይላል ይሖዋ። ‘ይልቁንም በራሳችሁ ላይ ጥፋት ታመጡ ዘንድ አስቆጣችሁኝ።’
“ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘“ቃሌን ስለማትታዘዙ፣
የሰሜንን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁ” ይላል ይሖዋ፤ “አገልጋዬን የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነጾርን እጠራለሁ፤ በዚህች ምድር፣ በነዋሪዎቿና በዙሪያዋ ባሉ በእነዚህ ብሔራት ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ። ፈጽሞ አጠፋቸዋለሁ፤ እንዲሁም መቀጣጫና ማፏጫ እንዲሆኑ ብሎም ባድማ ሆነው እንዲቀሩ አደርጋለሁ።
የሐሴትንና የደስታን ድምፅ፣ የሙሽራንና የሙሽሪትን ድምፅ፣ የወፍጮን ድምፅና የመብራትን ብርሃን ከመካከላቸው አስቀራለሁ።
መላ ምድሪቱ ትወድማለች፤ እንዲሁም አስፈሪ ቦታ ትሆናለች፤ እነዚህም ብሔራት የባቢሎንን ንጉሥ 70 ዓመት ያገለግሉታል።”’
“‘ይሁንና ሰባው ዓመት ሲፈጸም በበደላቸው የተነሳ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ብሔር ተጠያቂ አደርጋለሁ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘የከለዳውያንንም ምድር እስከ ወዲያኛው ባድማ አደርገዋለሁ።
በምድሪቱ ላይ የተናገርኩትን ቃል ሁሉ ይኸውም ኤርምያስ በሁሉም ብሔራት ላይ የተነበየውንና በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈውን ነገር ሁሉ አመጣባታለሁ።