text stringlengths 4 267 |
|---|
ይሖዋ ሆይ፣ ፈውሰኝ፤ እኔም እፈወሳለሁ። አድነኝ፤ እኔም እድናለሁ፤የማወድሰው አንተን ነውና። |
እነሆ፣ “የይሖዋ ቃል የት አለ? እስቲ ይፈጸም!” የሚሉኝ ሰዎች አሉ። |
እኔ ግን እረኛ ሆኜ አንተን ከመከተል ወደኋላ አላልኩም፤የጥፋትንም ቀን ፈጽሞ አልተመኘሁም። አንተ ከንፈሮቼ የተናገሩትን ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ፤ሁሉም የተፈጸመው በፊትህ ነው! |
ሽብር ላይ አትጣለኝ። አንተ በጥፋት ቀን መጠጊያዬ ነህ። |
አሳዳጆቼ ኀፍረት ይከናነቡ፤እኔ ግን ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ። እነሱ በሽብር ይዋጡ፤እኔ ግን አልሸበር። የጥፋት ቀን አምጣባቸው፤አድቅቃቸው፤ ሙሉ በሙሉም አጥፋቸው። |
ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሂድና የይሁዳ ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝቡ ልጆች በር እንዲሁም በኢየሩሳሌም በሮች ሁሉ ቁም። |
እንዲህም በላቸው፦ ‘በእነዚህ በሮች የምትገቡ፣ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፣ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሙሉ የይሖዋን ቃል ስሙ። |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሸክም አትሸከሙ ወይም በኢየሩሳሌም በሮች አታስገቡ። |
በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሸክም ከቤታችሁ ይዛችሁ አትውጡ፤ ምንም ዓይነት ሥራም አትሥሩ። አባቶቻችሁን እንዳዘዝኳቸው ሁሉ እናንተም የሰንበትን ቀን ቀድሱ። |
ሆኖም እነሱ አልሰሙም፤ ጆሯቸውንም አልሰጡም፤ ላለመታዘዝና ተግሣጽ ላለመቀበል በእንቢተኝነታቸው ጸኑ።”’ |
“‘“ይሁን እንጂ በሚገባ ብትታዘዙኝ” ይላል ይሖዋ፣ “በሰንበትም ቀን በከተማዋ በሮች ሸክም ይዛችሁ ባትገቡና በሰንበት ቀን ምንም ዓይነት ሥራ ባለመሥራት ቀኑን ብትቀድሱት፣ |
በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መኳንንት ይኸውም እነሱና መኳንንታቸው እንዲሁም የይሁዳ ሰዎችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በሠረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፤ ይህችም ከተማ ለዘለቄታው የሰው መኖሪያ ትሆናለች። |
ሰዎችም ከይሁዳ ከተሞች፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከሚገኙ ቦታዎች፣ ከቢንያም አገር፣ ከቆላው፣ ከተራራማው አካባቢና ከኔጌብ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎች፣ መሥዋዕቶች፣ የእህል መባዎች፣ ነጭ ዕጣንና የምስጋና መሥዋዕቶች ይዘው ወደ ይሖዋ ቤት ይመጣሉ። |
“‘“የሰንበትን ቀን ሳትቀድሱ፣ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች በመግባት ትእዛዜን ብትጥሱ፣ በሮቿን በእሳት አነዳለሁ፤ እሳቱም የኢየሩሳሌምን የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል፤ ፈጽሞም አይጠፋም።”’” |
“በዚያን ጊዜ” ይላል ይሖዋ፣ “ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።” |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወደ ማረፊያ ቦታው በሄደ ጊዜ፣ከሰይፍ የተረፉት ሰዎች በምድረ በዳ የአምላክን ሞገስ አገኙ።” |
ይሖዋ ከሩቅ ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ፦ “በዘላለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ። ከዚህም የተነሳ በታማኝ ፍቅር ወደ እኔ ሳብኩሽ። |
አሁንም መልሼ እገነባሻለሁ፤ አንቺም ዳግመኛ ትገነቢያለሽ። የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ አታሞዎችሽን እንደገና አንስተሽበደስታ እየጨፈርሽ ትወጫለሽ። |
በሰማርያ ተራሮች ላይ እንደገና የወይን ተክሎችን ትተክያለሽ፤አትክልተኞቹ ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ። |
በኤፍሬም ተራሮች የሚገኙ ጠባቂዎች ‘ተነሱ፤ ወደ ጽዮን፣ ወደ አምላካችን ወደ ይሖዋ እንውጣ’ ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣልና።” |
ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “በታላቅ ደስታ ወደ ያዕቆብ ጩኹ። ከብሔራት በላይ ስለሆናችሁ እልል በሉ። ይህን አውጁ፤ ውዳሴ አቅርቡ፤ደግሞም ‘ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን፣ የእስራኤልን ቀሪዎች አድን’ በሉ። |
ከሰሜን ምድር መልሼ አመጣቸዋለሁ። ከምድር ዳርቻዎች እሰበስባቸዋለሁ። በመካከላቸው ዓይነ ስውርና አንካሳ፣ነፍሰ ጡርና ልትወልድ የተቃረበች ሴት በአንድነት ይገኛሉ። ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ። |
እያለቀሱ ይመጣሉ። ሞገስ ለማግኘት ሲለምኑ እየመራሁ አመጣቸዋለሁ። ወደ ውኃ ጅረቶች እመራቸዋለሁ፤በማይሰናከሉበት ደልዳላ መንገድ እወስዳቸዋለሁ። እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፤ ኤፍሬምም የበኩር ልጄ ነው።” |
እናንተ ብሔራት፣ የይሖዋን ቃል ስሙ፤ርቀው በሚገኙ ደሴቶችም ቃሉን አውጁ፦ “እስራኤልን የበተነው እሱ ይሰበስበዋል። መንጋውን እንደሚጠብቅ እረኛ ይጠብቀዋል። |
ይሖዋ ያዕቆብን ይዋጀዋልና፤ከእሱም ከሚበረታው እጅ ይታደገዋል። |
እነሱም መጥተው በጽዮን ከፍ ያለ ቦታ በደስታ እልል ይላሉ፤ደግሞም በይሖዋ ጥሩነት፣በእህሉ፣ በአዲሱ ወይን፣ በዘይቱእንዲሁም በመንጎቹ ግልገሎችና በከብቶቹ ጥጆች የተነሳ ፊታቸው ይፈካል። ውኃ እንደጠገበ የአትክልት ቦታ ይሆናሉ፤ከእንግዲህም ወዲህ አይደክሙም።” |
“በዚያን ጊዜ ድንግሊቱ በደስታ ትጨፍራለች፤ወጣቶቹና ሽማግሌዎቹም በአንድነት በደስታ ይጨፍራሉ። ሐዘናቸውን ወደ ሐሴት እለውጠዋለሁ። ከሐዘናቸው ተላቀው እንዲጽናኑና ደስ እንዲሰኙ አደርጋለሁ። |
ካህናቱን በተትረፈረፈ ምግብ አጠግባለሁ፤ሕዝቤም በጥሩነቴ ይረካል” ይላል ይሖዋ። |
“ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፦ ራሔል ስለ ወንዶች ልጆቿ አለቀሰች። ወንዶች ልጆቿ ስለሌሉከደረሰባት ሐዘን ለመጽናናት እንቢ አለች።’” |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘አታልቅሺ፤ ዓይኖችሽም እንባ አያፍስሱ፤ሥራሽ ወሮታ አለውና’ ይላል ይሖዋ። ‘ከጠላት ምድር ይመለሳሉ።’ |
‘አንቺም ብሩህ ተስፋ ይጠብቅሻል’ ይላል ይሖዋ። ‘ወንዶች ልጆችሽ ወደ ገዛ ምድራቸው ይመለሳሉ።’” |
“የኤፍሬምን ሲቃ በእርግጥ ሰምቻለሁ፤‘እንዳልተገራ ጥጃ አረምከኝ፤እኔም ታረምኩ። መልሰኝ፤ እኔም ወዲያውኑ እመለሳለሁ፤አንተ አምላኬ ይሖዋ ነህና። |
ከተመለስኩ በኋላ ተጸጽቻለሁና፤እንዳስተውል ከተደረግኩ በኋላ በሐዘን ጭኔን መታሁ። አፈርኩ፤ ተዋረድኩም፤በወጣትነቴ የደረሰብኝን ነቀፋ ተሸክሜአለሁና።’” |
“ኤፍሬም ከፍ አድርጌ የምመለከተው ውድ ልጄ አይደለም? ብዙ ጊዜ እሱን ተቃውሜ የምናገረውን ያህል፣ አሁንም አስበዋለሁና። አንጀቴ ለእሱ የሚንሰፈሰፈው ለዚህ ነው። ደግሞም እራራለታለሁ” ይላል ይሖዋ። |
“የጎዳና ምልክቶችን ለራስሽ አቁሚ፤መንገድ የሚጠቁሙ ዓምዶችን ትከዪ። የምትሄጂበትን አውራ ጎዳና ልብ ብለሽ ተመልከቺ። የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ ተመለሽ፤ የራስሽ ወደሆኑት ወደነዚህ ከተሞች ተመለሽ። |
ከዳተኛዪቱ ሴት ልጅ ሆይ፣ የምትወላውዪው እስከ መቼ ድረስ ነው? ይሖዋ በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሯልና፦ ሴት ወንድን አጥብቃ ታሳድዳለች።” |
የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የተማረኩባቸውን ሰዎች በምሰበስብበት ጊዜ በይሁዳ ምድርና በከተሞቹ ‘አንተ ጻድቅ መኖሪያ፣ አንተ ቅዱስ ተራራ፣ ይሖዋ ይባርክህ’ የሚል ቃል እንደገና ይናገራሉ። |
በእሷም ውስጥ ይሁዳና ከተሞቹ ሁሉ እንዲሁም ገበሬዎችና የመንጋ እረኞች በአንድነት ይኖራሉ። |
የዛለውን አድሳለሁና፤ የደከመውንም ሁሉ አበረታለሁ።” |
በዚህ ጊዜ ነቃሁ፤ ዓይኔንም ገለጥኩ፤ እንቅልፌም ጣፋጭ ሆኖልኝ ነበር። |
“እነሆ፣ በእስራኤል ቤትና በይሁዳ ቤት የሰውን ዘርና የከብትን ዘር የምዘራበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ። |
“እነሱን ለመንቀል፣ ለማፍረስ፣ ለማውደም፣ ለማጥፋትና ለመደምሰስ እከታተላቸው እንደነበረ ሁሉ፣ እነሱን ለመገንባትና ለመትከልም እከታተላቸዋለሁ” ይላል ይሖዋ። |
“በዚያም ዘመን ‘የሚጎመዝዝ ወይን የበሉት አባቶች ሆነው ሳለ የልጆቹ ጥርስ ጠረሰ’ ብለው ዳግመኛ አይናገሩም። |
ከዚህ ይልቅ በዚያ ጊዜ እያንዳንዱ ሰው በገዛ በደሉ ይሞታል። የሚጎመዝዝ ወይን የሚበላ ሰው ሁሉ፣ የገዛ ራሱ ጥርስ ይጠርሳል።” |
“እነሆ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ። |
“ይህም ቃል ኪዳን አባቶቻቸውን እጃቸውን ይዤ ከግብፅ ምድር እየመራሁ ባወጣኋቸው ቀን ከእነሱ ጋር እንደገባሁት ዓይነት ቃል ኪዳን አይሆንም፤ ‘እኔ እውነተኛ ጌታቸው ብሆንም እንኳ እነሱ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋል’ ይላል ይሖዋ።” |
“ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና” ይላል ይሖዋ። “ሕጌን በውስጣቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ። እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።” |
“እነሱም እያንዳንዳቸው ባልንጀራቸውን፣ እያንዳንዳቸውም ወንድማቸውን ‘ይሖዋን እወቅ!’ ብለው ከእንግዲህ አያስተምሩም፤ ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና” ይላል ይሖዋ። “በደላቸውን ይቅር እላለሁና፤ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስታውስም።” |
ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ የሆነው፣በቀን እንድታበራ ፀሐይን የሰጠው፣በሌሊትም እንዲያበሩ የጨረቃንና የከዋክብትን ሕጎች ያወጣው፣ባሕሩን የሚያናውጠውና ኃይለኛ ማዕበል የሚያስነሳውይሖዋ እንዲህ ይላል፦ |
“‘የእስራኤል ዘር ምንጊዜም በፊቴ የሚኖር ብሔር መሆኑ የሚያከትመው’ ይላል ይሖዋ፣‘ይህ ሥርዓት ከተሻረ ብቻ ነው።’” |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘መላውን የእስራኤል ዘር፣ በሠሩት ነገር ሁሉ የተነሳ ልተዋቸው የምችለው፣ በላይ ያሉትን ሰማያት መለካት፣ በታች ያሉትንም የምድር መሠረቶች መመርመር የሚቻል ከሆነ ብቻ ነው’ ይላል ይሖዋ።” |
“እነሆ፣ ከተማዋ ከሃናንኤል ማማ እስከ ማዕዘን በር ድረስ ለይሖዋ የምትገነባበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ። |
“የመለኪያ ገመዱም በቀጥታ ወደ ጋሬብ ኮረብታ ይዘረጋል፤ ደግሞም ወደ ጎዓ ይዞራል። |
ሬሳና አመድ ያለበት ሸለቆ ሁሉ እንዲሁም የቄድሮንን ሸለቆ ይዞ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረስ በር ማዕዘን ድረስ ያለው ደልዳላ ቦታ ሁሉ ለይሖዋ የተቀደሰ ይሆናል። ከእንግዲህ ወዲህ አይነቀልም ወይም አይወድምም።” |
የኢዮስያስ ልጅ፣ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ የነሪያህ ልጅ ባሮክ ይህን ቃል ከኤርምያስ አፍ እየሰማ በመጽሐፍ በጻፈበት ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ለባሮክ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ |
“ባሮክ፣ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ አንተን በተመለከተ እንዲህ ይላል፦ |
‘አንተ “ወዮልኝ፣ ይሖዋ በሥቃዬ ላይ ሐዘን ጨምሮብኛልና! ከማሰማው ሲቃ የተነሳ ዝያለሁ፤ ማረፊያ ቦታም አላገኘሁም” ብለሃል።’ |
“እሱን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልኩትንም እነቅላለሁ፤ ምድሪቱን በሙሉ አወድማለሁ። |
አንተ ግን ለራስህ ታላላቅ ነገሮችን ትፈልጋለህ። እንዲህ ያሉ ነገሮችን ፈጽሞ አትፈልግ።”’ “‘በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ጥፋት ላመጣ ነውና’ ይላል ይሖዋ፤ ‘በምትሄድበትም ቦታ ሁሉ ሕይወትህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።’” |
ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “ሄደህ፣ ከሸክላ ሠሪ ገንቦ ግዛ። ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከካህናቱ ሽማግሌዎች መካከል የተወሰኑትን ይዘህ |
በገል በር መግቢያ አጠገብ ወዳለው ወደ ሂኖም ልጅ ሸለቆ ውጣ። የምነግርህንም ቃል በዚያ አውጅ። |
እንዲህ ትላለህ፦ ‘እናንተ የይሁዳ ነገሥታትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የይሖዋን ቃል ስሙ። የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘“በዚህ ስፍራ ላይ ጥፋት ላመጣ ነው፤ ስለሚመጣው ጥፋት የሚሰማ ሰው ሁሉ ጆሮውን ይነዝረዋል። |
ምክንያቱም እኔን ትተውኛል፤ ይህን ስፍራም የማይታወቅ ቦታ አድርገውታል። በዚህ ስፍራ እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው እንዲሁም የይሁዳ ነገሥታት ለማያውቋቸው ሌሎች አማልክት መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ይህን ስፍራም በንጹሐን ደም ሞልተውታል። |
እኔ ያላዘዝኩትን ወይም ያልተናገርኩትን፣ በልቤም እንኳ ፈጽሞ ያላሰብኩትን ነገር ለማድረግ ይኸውም ወንዶች ልጆቻቸውን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርገው ለባአል በእሳት ለማቃጠል ከፍ ያሉትን የባአል የማምለኪያ ቦታዎች ሠሩ።”’ |
“‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ስለዚህ፣ እነሆ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ እንጂ ቶፌት ወይም የሂኖም ልጅ ሸለቆ ተብሎ የማይጠራበት ጊዜ ይመጣል። |
በዚህ ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ዕቅድ አጨናግፋለሁ፤ በጠላቶቻቸው ፊት በሰይፍ እንዲወድቁ፣ ሕይወታቸውንም በሚሹ ሰዎች እጅ እንዲጠፉ አደርጋለሁ። አስከሬናቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል እንዲሆን እሰጣለሁ። |
ይህችንም ከተማ አስፈሪ ቦታና ማፏጫ አደርጋታለሁ። በዚያ የሚያልፍ ሁሉ በደረሰባት መቅሰፍት የተነሳ በፍርሃት አፍጥጦ ይመለከታል፤ ደግሞም ያፏጫል። |
ጠላቶቻቸውና ሕይወታቸውን ለማጥፋት የሚሹ ሰዎች ሲከቧቸውና መፈናፈኛ አሳጥተው ሲያስጨንቋቸው የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸው የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።”’ |
“ከዚያም ገንቦውን ከአንተ ጋር በሚሄዱ ሰዎች ፊት ስበረው፤ |
እንዲህም በላቸው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አንድ ሰው የሸክላ ሠሪን ዕቃ ሊጠገን በማይችል መንገድ እንደሚሰብረው፣ እኔም ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እንዲሁ እሰባብራለሁ፤ እነሱም የመቃብር ቦታ እስኪታጣ ድረስ የሞቱትን በቶፌት ይቀብራሉ።”’ |
“‘ይህችን ከተማ እንደ ቶፌት አደርጋት ዘንድ በዚህ ስፍራና በነዋሪዎቹ ላይ ይህን እፈጽማለሁ’ ይላል ይሖዋ። |
‘የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፣ አዎ በጣሪያዎቻቸው ላይ ለሰማያት ሠራዊት መሥዋዕቶች ያቀረቡባቸውና ለሌሎች አማልክት የመጠጥ መባዎች ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ እንደዚህ ስፍራ፣ እንደ ቶፌት የረከሱ ይሆናሉ።’” |
ኤርምያስ፣ ይሖዋ ትንቢት እንዲናገር ልኮት ከነበረበት ከቶፌት ሲመለስ በይሖዋ ቤት ግቢ ቆሞ ለመላው ሕዝብ እንዲህ አለ፦ |
“የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ በዚህች ከተማና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ሁሉ ላይ አመጣዋለሁ ብዬ የተናገርኩትን ጥፋት ሁሉ አወርድባቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ቃሌን ለመታዘዝ በግትርነት አሻፈረን ብለዋል።’” |
ኤርምያስ በክብር ዘቦቹ ግቢ ታስሮ ሳለ የይሖዋ ቃል ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል ወደ እሱ መጣ፦ |
“ምድርን የሠራት ይሖዋ፣ አዎ፣ ያበጃትና አጽንቶ የመሠረታት ይሖዋ እንዲህ ይላል፤ ስሙ ይሖዋ ነው፤ |
‘ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተ የማታውቀውን ታላቅና ለመረዳት አዳጋች የሆነ ነገር ወዲያውኑ እነግርሃለሁ።’” |
“እኔ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ፣ በዙሪያዋ በተደለደለው የአፈር ቁልልና በሰይፍ የተነሳ ስለፈረሱት የዚህች ከተማ ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች እንዲህ እላለሁ፤ |
ደግሞም ከከለዳውያን ጋር ሊዋጉ የሚመጡትን ሰዎች እንዲሁም ከክፋታቸው የተነሳ ፊቴን ከዚህች ከተማ እንድሰውር ባደረጉኝና በታላቅ ቁጣዬ በመታኋቸው ሰዎች ሬሳ የሚሞሉትን ቦታዎች በተመለከተ እንዲህ እላለሁ፦ |
‘እነሆ፣ ከተማዋ እንድታገግም አደርጋለሁ፤ ጤናም እሰጣታለሁ፤ እኔም እፈውሳቸዋለሁ እንዲሁም የተትረፈረፈ ሰላምና እውነት እሰጣቸዋለሁ። |
ከይሁዳ የተማረኩትንና ከእስራኤል የተማረኩትን እመልሳለሁ፤ እንደቀድሞውም እገነባቸዋለሁ። |
እኔንም ከበደሉበት ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ፤ በእኔ ላይ የሠሩትን ኃጢአትና በደል ሁሉ ይቅር እላለሁ። |
እሷም የማደርግላቸውን መልካም ነገር በሙሉ በሚሰሙ የምድር ብሔራት ሁሉ ፊት የሐሴት ስም፣ ውዳሴና ውበት ትሆንልኛለች። በማደርግላት መልካም ነገር ሁሉና በምሰጣት ሰላም ሁሉ የተነሳ በፍርሃት ይርዳሉ፤ ይንቀጠቀጣሉም።’” |
“ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰውም ሆነ ከብት የማይኖርበት ጠፍ መሬት በምትሉት በዚህ ቦታ እንዲሁም ሰው ወይም ነዋሪ ወይም ከብት በሌለባቸው ወና የሆኑ የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ጎዳናዎች እንደገና ድምፅ ይሰማል፤ |
አዎ፣ የሐሴት ድምፅ፣ የደስታ ድምፅ፣ የሙሽራና የሙሽሪት ድምፅ እንዲሁም “ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ የሠራዊት ጌታ ይሖዋን አመስግኑ፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል!” የሚሉ ሰዎች ድምፅ ይሰማል።’ “‘ቀድሞ እንደነበረው ከምድሪቱ ተማርከው የተወሰዱትን ስለምመልስ ወደ ይሖዋ ቤት የምሥጋና መባዎች ይዘው ይመጣሉ’ ይላል ይሖዋ።” |
“የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰው ወይም ከብት በሌለበት በዚህ ጠፍ መሬት እንዲሁም በከተሞቹ ሁሉ እረኞች መንጎቻቸውን የሚያሳርፉበት የግጦሽ መሬት ዳግመኛ ያገኛሉ።’ |
“‘በተራራማው ምድር በሚገኙ ከተሞች፣ በዝቅተኛው ስፍራ በሚገኙ ከተሞች፣ በደቡብ ባሉ ከተሞች፣ በቢንያም አገር፣ በኢየሩሳሌም ዙሪያ ባሉ ቦታዎችና በይሁዳ ከተሞች፣ እረኞች በጎቻቸውን የሚቆጥሩበት ጊዜ ዳግመኛ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ።” |
“‘እነሆ፣ ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የገባሁትን የተስፋ ቃል የምፈጽምበት ጊዜ ይመጣል’ ይላል ይሖዋ። |
‘በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜ ለዳዊት ቀንበጥ ይኸውም ጻድቅ ቀንበጥ አበቅላለሁ፤ እሱም በምድሪቱ ላይ ፍትሕንና ጽድቅን ያሰፍናል። |
በዚያ ዘመን ይሁዳ ትድናለች፤ ኢየሩሳሌምም ያለስጋት ትቀመጣለች። እሷም “ይሖዋ ጽድቃችን ነው” ተብላ ትጠራለች።’” |
“ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘ከዳዊት ዘር፣ በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አይታጣም፤ |
ከሌዋውያን ካህናትም መካከል ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችን ለማቅረብ፣ የእህል መባዎችን ለማቃጠልና መሥዋዕቶችን ለማቅረብ በፊቴ የሚቆም ሰው ጨርሶ አይታጣም።’” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ |
“ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዳይፈራረቁ፣ የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ የምትችሉ ከሆነ፣ |
ያን ጊዜ ከአገልጋዬ ከዳዊት ጋር የገባሁት ቃል ኪዳኔ ሊፈርስ ይችላል፤ ያን ጊዜ በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ አይኖረውም፤ አገልጋዮቼ ከሆኑት ከሌዋውያን ካህናት ጋር የገባሁት ቃል ኪዳንም ይፈርሳል። |
የሰማያት ሠራዊት ሊቆጠር፣ የባሕርም አሸዋ ሊሰፈር እንደማይችል ሁሉ የአገልጋዬን የዳዊትን ዘርና አገልጋዮቼን ሌዋውያንን እንዲሁ አበዛቸዋለሁ።’” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፦ |
“እነዚህ ሰዎች፣ ‘ይሖዋ የመረጣቸውን ሁለቱን ወገኖች ይተዋቸዋል’ እንደሚሉ አላስተዋልክም? የገዛ ሕዝቤንም ይንቃሉ፤ እነሱን እንደ ብሔር አድርገው መመልከት አቁመዋል። |
“ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማቋቋሜ እንዲሁም የሰማይንና የምድርን ሕግ መደንገጌ የተረጋገጠ እንደሆነ ሁሉ፣ |
በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ ልጆች ላይ የሚነግሡ ገዢዎች ከዘሩ እንዳይታጡ የያዕቆብንና የአገልጋዬን የዳዊትን ዘር ፈጽሞ አልጥልም። ተማርከው የተወሰዱባቸውን መልሼ እሰበስባለሁና፤ ርኅራኄም አሳያቸዋለሁ።’” |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.