text stringlengths 4 267 |
|---|
ብዙ ብሔራትና ታላላቅ ነገሥታት ባሪያዎች ያደርጓቸዋልና፤ እኔም እንደ ድርጊታቸውና እንደ ገዛ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።’” |
የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ብሎኛልና፦ “የቁጣ ወይን ጠጅ ያለበትን ይህን ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ እኔም ወደምልክህ ብሔራት ሁሉ ሄደህ አጠጣቸው። |
እነሱም በመካከላቸው ከምሰደው ሰይፍ የተነሳ ይጠጣሉ፣ ይንገዳገዳሉ፣ እንደ አበደ ሰውም ይሆናሉ።” |
ስለዚህ ከይሖዋ እጅ ጽዋውን ወሰድኩ፤ ይሖዋ ወደላከኝም ብሔራት ሁሉ ሄጄ አጠጣኋቸው፦ |
ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ባድማ፣ መቀጣጫና ማፏጫ እንዲሆኑ እንዲሁም ለእርግማን እንዲዳረጉ በመጀመሪያ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች፣ ነገሥታቷንና መኳንንቷን አጠጣኋቸው፤ |
ከዚያም የግብፅ ንጉሥ ፈርዖንና አገልጋዮቹ፣ መኳንንቱና ሕዝቡ ሁሉ፣ |
ድብልቅ የሆነው ሕዝባቸው ሁሉ፣ የዑጽ ምድር ነገሥታት ሁሉ፣ የፍልስጤማውያን ምድር ነገሥታት ሁሉ፣ አስቀሎን፣ ጋዛ፣ ኤቅሮንና ከአሽዶድ የቀሩት ሰዎች፣ |
ኤዶም፣ ሞዓብና አሞናውያን፣ |
የጢሮስ ነገሥታት ሁሉ፣ የሲዶና ነገሥታት ሁሉና በባሕሩ ላይ ያለው ደሴት ነገሥታት፣ |
ዴዳን፣ ቴማ፣ ቡዝና በሰሪሳራቸው ላይ ያለውን ፀጉር የሚላጩ ሁሉ፣ |
የዓረብ ነገሥታት ሁሉና በምድረ በዳ የሚኖሩት ድብልቅ ሕዝብ ነገሥታት ሁሉ፣ |
የዚምሪ ነገሥታት ሁሉ፣ የኤላም ነገሥታት ሁሉና የሜዶናውያን ነገሥታት ሁሉ፣ |
በቅርብም ሆነ በሩቅ ያሉ የሰሜን ነገሥታት ሁሉ አንድ በአንድ እንዲሁም በምድር ላይ ያሉ ሌሎች የዓለም መንግሥታት ሁሉ ጠጡ፤ ከእነሱም በኋላ የሼሻቅ ንጉሥ ይጠጣል። |
“አንተም እንዲህ በላቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በመካከላችሁ ከምሰደው ሰይፍ የተነሳ ጠጡ፣ ስከሩ፣ አስታውኩ፣ ዳግመኛም ላትነሱ ውደቁ።”’ |
ጽዋውን ከእጅህ ወስደው ለመጠጣት ፈቃደኛ ባይሆኑ እንዲህ በላቸው፦ ‘የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በግድ ትጠጣላችሁ! |
እነሆ፣ በመጀመሪያ የማጠፋው በስሜ የተጠራችውን ከተማ ከሆነ እናንተስ ከቅጣት ታመልጣላችሁ?”’ “‘በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ላይ ሰይፍን ስለምጠራ እናንተም ከቅጣት አታመልጡም’ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። |
“አንተም ይህን ቃል ሁሉ ትተነብይላቸዋለህ፤ እንዲህም ትላቸዋለህ፦‘ይሖዋ ከላይ ሆኖ ይጮኻል፤ከቅዱስ ማደሪያውም ድምፁን ያሰማል። በመኖሪያ ስፍራውም ላይ በኃይል ይጮኻል። ወይን መጭመቂያውን እንደሚረግጡ ሰዎች፣በምድር ነዋሪዎች ሁሉ ላይ በድል አድራጊነት ይዘምራል።’ |
‘ታላቅ ጩኸት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያስተጋባል፤ይሖዋ ከብሔራት ጋር ሙግት አለውና። እሱ ራሱ በሰዎች ሁሉ ላይ ይፈርዳል። ክፉዎችንም ለሰይፍ ይዳርጋል’ ይላል ይሖዋ። |
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፣ ጥፋት ብሔራትን አንድ በአንድ ያዳርሳል፤ታላቅ አውሎ ነፋስም ከምድር ዳርቻዎች ይነሳል። |
“‘በዚያም ቀን፣ ይሖዋ የገደላቸው ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ። አይለቀስላቸውም፣ አይሰበሰቡም ወይም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ።’ |
እናንተ እረኞች፣ ዋይ ዋይ በሉ፤ ጩኹም! እናንተ በመንጋው መካከል ያላችሁ ታላላቆች፣ በአመድ ላይ ተንከባለሉ፤ምክንያቱም የምትታረዱበትና የምትበታተኑበት ጊዜ ደርሷል፤እንደ ውድ የሸክላ ዕቃ ትከሰከሳላችሁ! |
እረኞቹ የሚሸሹበት ቦታ የለም፤በመንጋው መካከል ያሉት ታላላቆችም ማምለጫ የላቸውም። |
አዳምጡ! የእረኞቹ ጩኸትናበመንጋው መካከል ያሉ ታላላቆች ዋይታ ይሰማል፤ይሖዋ ማሰማሪያቸውን እያወደመ ነውና። |
ከሚነደው የይሖዋ ቁጣም የተነሳሰላማዊ የሆኑት የመኖሪያ ቦታዎች ሕይወት አልባ ሆነዋል። |
እንደ ደቦል አንበሳ ከጎሬው ወጥቷል፤ከጨካኙ ሰይፍናከሚነደው ቁጣው የተነሳምድራቸው የሚያስፈራ ቦታ ሆኗልና።” |
ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ሂድና ከተልባ እግር የተሠራ ቀበቶ ግዛ፤ በወገብህም ላይ ታጠቀው፤ ሆኖም ፈጽሞ ውኃ አታስነካው።” |
ስለዚህ ይሖዋ ባዘዘኝ መሠረት ቀበቶውን ገዝቼ ወገቤ ላይ ታጠቅኩት። |
የይሖዋም ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እኔ መጣ፦ |
“የገዛኸውንና የታጠቅከውን ቀበቶ ይዘህ ተነስ፤ ወደ ኤፍራጥስም ሄደህ በቋጥኝ ስንጥቅ ውስጥ ደብቀው።” |
ስለዚህ ይሖዋ ባዘዘኝ መሠረት ሄጄ በኤፍራጥስ አጠገብ ደበቅኩት። |
ሆኖም ከብዙ ቀናት በኋላ ይሖዋ “ተነስ፤ ወደ ኤፍራጥስ ሄደህ፣ በዚያ እንድትደብቀው ያዘዝኩህን ቀበቶ አምጣ” አለኝ። |
እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ፣ ቀበቶውን ከደበቅኩበት ቦታ ቆፍሬ አወጣሁ፤ ቀበቶው ተበላሽቶና ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆኖ አገኘሁት። |
ከዚያም የይሖዋ ቃል ወደ እኔ መጣ፦ |
“ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘የይሁዳን ኩራትና የኢየሩሳሌምን እብሪት ልክ እንደዚሁ አጠፋዋለሁ። |
ቃሌን ለመታዘዝ አሻፈረኝ ያለው፣ ግትር ሆኖ የገዛ ልቡን የሚከተለው እንዲሁም ሌሎች አማልክትን የሚከተለው፣ የሚያገለግለውና ለእነሱ የሚሰግደው ይህ ክፉ ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ እንደሆነው እንደዚህ ቀበቶ ይሆናል።’ |
‘ቀበቶ በሰው ወገብ ላይ እንደሚጣበቅ፣ መላው የእስራኤል ቤትና መላው የይሁዳ ቤት ከእኔ ጋር እንዲጣበቅ አደረግኩ’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ይህም ሕዝቤ፣ ስሜ፣ ውዳሴዬና ውበቴ እንዲሆኑ ነው። እነሱ ግን አልታዘዙም።’ |
“አንተም ይህን መልእክት አክለህ ንገራቸው፦ ‘የእስራኤል አምላክ ይሖዋ “እያንዳንዱ ትልቅ እንስራ በወይን ጠጅ ይሞላል” ይላል።’ እነሱም ‘እያንዳንዱ ትልቅ እንስራ በወይን ጠጅ እንደሚሞላ እኛ መች ጠፋን?’ ብለው ይመልሱልሃል። |
በዚህ ጊዜ እንዲህ በላቸው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ፣ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡትን ነገሥታት፣ ካህናቱንና ነቢያቱን እንዲሁም የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች በሙሉ በስካር እሞላቸዋለሁ። |
እነሱንም እርስ በርሳቸው፣ አባቶችንና ልጆችንም አጋጫለሁ” ይላል ይሖዋ። “ምንም ዓይነት ርኅራኄም ሆነ ሐዘኔታ አላሳይም፤ ምሕረትም አላደርግላቸውም፤ እነሱን ከማጥፋት ምንም ነገር አያግደኝም።”’ |
ስሙ፤ ልብ በሉ። ትዕቢተኞች አትሁኑ፤ ይሖዋ ተናግሯልና። |
ጨለማን ከማምጣቱ በፊትናጨለምለም ባሉት ተራሮች ላይ እግሮቻችሁ ከመደናቀፋቸው በፊትለአምላካችሁ ለይሖዋ ክብር ስጡ። እናንተ ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ፤እሱ ግን ፅልማሞትን ያመጣል፤ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይለውጠዋል። |
ለመስማት አሻፈረን ካላችሁ፣በኩራታችሁ የተነሳ በስውር አለቅሳለሁ። የይሖዋ መንጋ በምርኮ ስለተወሰደእንባዬ እንደ ጎርፍ ይወርዳል፤ ዓይኔም በእንባ ይታጠባል። |
ንጉሡንና የንጉሡን እናት እንዲህ በላቸው፦ ‘የሚያምረው አክሊላችሁ ከራሳችሁ ላይ ስለሚወድቅ፣ዝቅ ባለ ስፍራ ተቀመጡ።’ |
የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፤ የሚከፍታቸውም የለም። መላው ይሁዳ በግዞት ተወስዷል፤ ሙሉ በሙሉም ተግዟል። |
ዓይንሽን አንስተሽ ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቺ። ለአንቺ የተሰጠው መንጋ፣ ያማሩት በጎችሽ የት አሉ? |
ከመጀመሪያው አንስቶ የተወዳጀሻቸው የቅርብ ጓደኞችሽአንቺን ለመቅጣት ሲነሱ ምን ትዪ ይሆን? ልክ እንደምትወልድ ሴት ምጥ አይዝሽም? |
በልብሽም ‘እነዚህ ነገሮች የደረሱብኝ ለምንድን ነው?’ በምትይበት ጊዜ፣ ቀሚስሽን የተገፈፍሽውና ተረከዝሽ ለሥቃይ የተዳረገው በፈጸምሽው ታላቅ በደል የተነሳ መሆኑን ልታውቂ ይገባል። |
ኢትዮጵያዊ መልኩን፣ ነብርስ ዥጉርጉርነቱን መለወጥ ይችላል? እንዲህ ማድረግ የሚችል ከሆነ፣ክፉ ነገር መሥራት የለመዳችሁት እናንተም መልካም ማድረግ ትችላላችሁ ማለት ነው። |
ስለዚህ የበረሃ ነፋስ ይዞት እንደሚሄድ ገለባ እበትናቸዋለሁ። |
ይህ ዕጣሽ፣ ሰፍሬም የሰጠሁሽ ድርሻሽ ነው” ይላል ይሖዋ፤“ምክንያቱም እኔን ረስተሽኛል፤ በሐሰትም ትታመኛለሽ። |
በመሆኑም ቀሚስሽን እስከ ፊትሽ እገልባለሁ፤ኀፍረትሽም ይታያል፤ |
የፈጸምሽው ምንዝር፣ በፍትወት ማሽካካትሽ፣ጸያፍ የሆነው ዝሙት አዳሪነትሽ ይገለጣል። አስጸያፊ ምግባርሽንበኮረብቶቹና በሜዳው ላይ አይቼአለሁ። ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ወዮልሽ! ርኩስ ሆነሽ የምትኖሪው እስከ መቼ ድረስ ነው?” |
ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በባቢሎንና በሌብቃማይ ነዋሪዎች ላይአጥፊ ነፋስ አስነሳለሁ። |
እህል የሚያዘሩ ሰዎችን ወደ ባቢሎን እሰዳለሁ፤እነሱም ያዘሯታል፤ ምድሯንም ባዶ ያደርጋሉ፤በጥፋት ቀን ከሁሉም አቅጣጫ ይመጡባታል። |
ቀስተኛው ደጋኑን አይወጥር። በተጨማሪም ማንም ሰው ጥሩሩን ለብሶ አይነሳ። ለወጣቶቿ ምንም ዓይነት ርኅራኄ አታሳዩ። ሠራዊቷን ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ። |
እነሱም በከለዳውያን ምድር ታርደው፣በጎዳናዎቿም ላይ ክፉኛ ቆስለው ይወድቃሉ። |
እስራኤልና ይሁዳ ከአምላካቸው፣ ከሠራዊት ጌታ ከይሖዋ ተለይተው መበለት አልሆኑም። ምድራቸው ግን በእስራኤል ቅዱስ ፊት በበደል ተሞልታለች። |
ከባቢሎን መካከል ሸሽታችሁ ውጡ፤ሕይወታችሁን አድኑ። በእሷ በደል የተነሳ አትጥፉ። ይህ የይሖዋ የበቀል ጊዜ ነውና። ላደረገችው ነገር የእጇን ይከፍላታል። |
ባቢሎን በይሖዋ እጅ ያለች የወርቅ ጽዋ ነበረች፤ምድርን ሁሉ አሰከረች። ብሔራት ወይን ጠጇን ጠጥተው ሰከሩ፤ብሔራት ያበዱት ለዚህ ነው። |
ባቢሎን በድንገት ወድቃ ተሰበረች። ዋይ ዋይ በሉላት! ለሕመሟ የሚሆን በለሳን ውሰዱላት፤ ምናልባት ትፈወስ ይሆናል።” |
“ባቢሎንን ለመፈወስ ሞክረን ነበር፤ እሷ ግን ልትፈወስ አልቻለችም። ትታችኋት ሂዱ፤ እያንዳንዳችንም ወደ ገዛ ምድራችን እንሂድ። ፍርዷ እስከ ሰማያት ደርሷልና፤እስከ ደመናት ድረስ ከፍ ብሏል። |
ይሖዋ ፍትሕ አስፍኖልናል። ኑ፣ የአምላካችንን የይሖዋን ሥራ በጽዮን እንናገር።” |
“ፍላጻዎቻችሁን አሹሉ፤ ክብ የሆኑትን ጋሻዎች አንሱ። ይሖዋ የሜዶናውያንን ነገሥታት መንፈስ አነሳስቷል፤ምክንያቱም ባቢሎንን ለማጥፋት አስቧል። ይህ የይሖዋ በቀል ይኸውም ስለ ቤተ መቅደሱ የሚወስደው የበቀል እርምጃ ነውና። |
የባቢሎንን ቅጥሮች ለማጥቃት ምልክት አቁሙ። ጥበቃውን አጠናክሩ፤ ጠባቂዎችን አቁሙ። ሽምቅ ተዋጊዎችን አዘጋጁ። ይሖዋ በባቢሎን ነዋሪዎች ላይ የጦር ስልት ነድፏልና፤በእነሱ ላይ የተናገረውንም ቃል ይፈጽማል።” |
“አንቺ በብዙ ውኃዎች ላይ የምትኖሪ፣በሀብትም የበለጸግሽ ሆይ፣መጨረሻሽ ቀርቧል፤ አላግባብ የምታገኚው ትርፍ ገደቡ ላይ ደርሷል። |
የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ሲል በራሱ ምሏል፦‘እንደ አንበጣ ብዛት ባላቸው ሰዎች እሞላሻለሁ፤እነሱም በአንቺ ላይ በድል አድራጊነት ይጮኻሉ።’ |
ምድርን በኃይሉ የሠራው፣ፍሬያማ የሆነችውን መሬት በጥበቡ የመሠረተውናሰማያትን በማስተዋሉ የዘረጋው እሱ ነው። |
ድምፁን ሲያሰማበሰማያት ያሉ ውኃዎች ይናወጣሉ፤ደመና ከምድር ዳርቻዎች ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርጋል። በዝናብ ጊዜ መብረቅን ያበርቃል፤ነፋሱንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል። |
እያንዳንዱ ሰው ማስተዋልና እውቀት የጎደለው ድርጊት ይፈጽማል። እያንዳንዱ አንጥረኛ፣ በተቀረጸው ምስል የተነሳ ኀፍረት ይከናነባል፤ከብረት የተሠራው ምስሉ ሐሰት ነውና፤በውስጣቸውም መንፈስ የለም። |
እነሱ ከንቱና መሳለቂያ ናቸው። የሚመረመሩበት ቀን ሲመጣ ይጠፋሉ። |
የያዕቆብ ድርሻ ግን እንደነዚህ ነገሮች አይደለም፤እሱ የርስቱን በትር ጨምሮየሁሉ ነገር ሠሪ ነውና። ስሙ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው።” |
“አንቺ ለእኔ እንደ ቆመጥ፣ እንደ ጦር መሣሪያም ነሽ፤በአንቺ ብሔራትን አደቃለሁ። በአንቺ መንግሥታትን አወድማለሁ። |
በአንቺ ፈረሱንና ፈረሰኛውን አደቃለሁ። በአንቺ የጦር ሠረገላውንና ነጂውን አደቃለሁ። |
በአንቺ ወንድንና ሴትን አደቃለሁ። በአንቺ ሽማግሌንና ልጅን አደቃለሁ። በአንቺ ወጣቱንና ወጣቷን አደቃለሁ። |
በአንቺ እረኛንና መንጋውን አደቃለሁ። በአንቺ ገበሬንና ጥማድ ከብቶቹን አደቃለሁ። በአንቺ ገዢዎችንና የበታች ገዢዎችን አደቃለሁ። |
ደግሞም በጽዮን፣ በፊታችሁ ለሠሩት ክፋት ሁሉባቢሎንንና የከለዳውያን ምድር ነዋሪዎችን በሙሉ ዋጋቸውን እከፍላቸዋለሁ” ይላል ይሖዋ። |
“አንቺ ምድርን ሁሉ ያጠፋሽ፣አጥፊ ተራራ ሆይ፣ እነሆ እኔ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ” ይላል ይሖዋ። “በአንቺ ላይ እጄን እዘረጋለሁ፤ ከቋጥኞችም ላይ አንከባልልሻለሁ፤የተቃጠለም ተራራ አደርግሻለሁ።” |
“ሰዎች የማዕዘን ድንጋይም ሆነ የመሠረት ድንጋይ ከአንቺ አይወስዱም፤ምክንያቱም አንቺ ለዘላለም ባድማ ትሆኛለሽ” ይላል ይሖዋ። |
“በምድሪቱ ላይ ምልክት አቁሙ። በብሔራት መካከል ቀንደ መለከት ንፉ። በእሷ ላይ እንዲዘምቱ ብሔራትን መድቡ። የአራራት፣ የሚኒ እና የአሽከናዝ መንግሥታት እሷን እንዲወጉ ሰብስቧቸው። በላይዋም ወታደሮችን የሚመለምል መኮንን ሹሙባት። ፈረሶችንም እንደ ኩብኩባ ስደዱባት። |
ብሔራትን፣ የሜዶንን ነገሥታት፣ ገዢዎቿን፣ የበታች ገዢዎቿን ሁሉናበእያንዳንዳቸው ግዛት ሥር ያለውን ምድር ሁሉበእሷ ላይ እንዲዘምቱ መድቧቸው። |
ምድርም ትናወጣለች፤ ትንቀጠቀጣለችም፤ይሖዋ የባቢሎንን ምድር አስፈሪ ቦታና ሰው አልባ ለማድረግበባቢሎን ላይ ያሰበው ሐሳብ ይፈጸማልና። |
የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋት አቁመዋል። በምሽጎቻቸው ውስጥ ይቀመጣሉ። ጉልበት ከድቷቸዋል። እንደ ሴት ሆነዋል። መኖሪያዎቿ በእሳት ነደዋል። መቀርቀሪያዎቿ ተሰብረዋል። |
ከተማው በየአቅጣጫው እንደተያዘች ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገርአንዱ መልእክተኛ ሲሮጥ ከሌላው መልእክተኛ ጋር፣አንዱም ወሬ ነጋሪ ሲሮጥ ከሌላው ወሬ ነጋሪ ጋር ይገናኛል፤ |
መልካዎቹ እንደተያዙ፣የደንገል ጀልባዎቹ በእሳት እንደተቃጠሉናወታደሮቹ እንደተሸበሩ ሊነግሩት ይሯሯጣሉ።” |
የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎን ሴት ልጅ እንደ አውድማ ናት። ይህ በኃይል የምትረገጥበት ጊዜ ነው። በአጭር ጊዜ ውስጥ የመከር ወቅት ይደርስባታል።” |
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ዋጠኝ፤ጨርሶ ግራ አጋባኝ። እንደ ባዶ ዕቃ አደረገኝ። እንደ ትልቅ እባብ ዋጠኝ፤የእኔን መልካም ነገሮች በልቶ ሆዱን ሞላ። በውኃም ጠራርጎ አስወገደኝ። |
የጽዮን ነዋሪ ‘በእኔና በአካሌ ላይ የተፈጸመው ግፍ በባቢሎን ላይ ይድረስ!’ ትላለች። ኢየሩሳሌም ‘ደሜም በከለዳውያን ምድር ነዋሪዎች ላይ ይሁን!’ ትላለች።” |
ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ እኔ እሟገትልሻለሁ፤ደግሞም እበቀልልሻለሁ። ባሕሯን አደርቃለሁ፤ የውኃ ጉድጓዶቿንም ደረቅ አደርጋለሁ። |
ባቢሎንም የድንጋይ ቁልል፣የቀበሮዎች ጎሬ፣አስፈሪ ቦታና ማፏጫ ትሆናለች፤የሚኖርባትም አይገኝም። |
ሁሉም በአንድነት እንደ ደቦል አንበሳ ያገሳሉ። እንደ አንበሳ ግልገሎች ያጉረመርማሉ።” |
“ፍላጎታቸው በኃይል ሲነሳሳ እጅግ ደስ እንዲሰኙድግሳቸውን አዘጋጅላቸዋለሁ፤ እንዲሰክሩም አደርጋለሁ፤ከዚያም ጨርሶ ላይነቁእስከ ወዲያኛው ያንቀላፋሉ” ይላል ይሖዋ። |
“እንደ ጠቦቶች፣እንደ አውራ በጎችም ከፍየሎች ጋር ወደሚታረዱበት ቦታ አወርዳቸዋለሁ።” |
“ሼሻቅ እንዴት ተማረከች!የምድር ሁሉ ‘ውዳሴ’ እንዴት ተያዘች! ባቢሎን በብሔራት መካከል ምንኛ አስፈሪ ቦታ ሆነች! |
ባሕሩ ባቢሎንን አጥለቅልቋታል። በማዕበሉ ብዛት ተሸፍናለች። |
ከተሞቿ አስፈሪ ቦታ እንዲሁም ውኃ የሌለበት ምድርና በረሃ ሆነዋል። ማንም ሰው የማይኖርበትና አንድም ሰው የማያልፍበት ምድር ሆነዋል። |
ትኩረቴን በባቢሎን በሚገኘው በቤል ላይ አደርጋለሁ፤የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ። ብሔራት ከእንግዲህ ወደ እሱ አይጎርፉም፤የባቢሎንም ቅጥር ይፈርሳል። |
ሕዝቤ ሆይ፣ ከመካከሏ ውጡ! ከሚነደው የይሖዋ ቁጣ ሕይወታችሁን ለማትረፍ ሽሹ! |
በምድሪቱ ላይ በሚሰማው ወሬ ልባችሁ አይሸበር፤ በፍርሃትም አትዋጡ። በምድሪቱ ላይ ዓመፅ ስለመኖሩ፣ገዢም በገዢ ላይ ስለመነሳቱ፣ በአንደኛው ዓመት አንድ ወሬ ይሰማል፤በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ሌላ ወሬ ይናፈሳል። |
ስለዚህ፣ እነሆ ትኩረቴንበባቢሎን የተቀረጹ ምስሎች ላይ የማደርግበት ጊዜ ይመጣል። ምድሪቱ በሙሉ ኀፍረት ትከናነባለች፤የታረዱባትም ሰዎች ሁሉ በመካከሏ ይወድቃሉ። |
ሰማያትና ምድር እንዲሁም በውስጣቸው ያሉት ሁሉበባቢሎን የተነሳ እልል ይላሉ፤አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና” ይላል ይሖዋ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.