text stringlengths 4 267 |
|---|
ብዙ የሕዝበ ክርስትና አባላት መነጠቅ የሚለው ትምህርት ክርስቲያኖች ሥጋዊ አካላቸውን እንደለበሱ ከምድር መወሰዳቸውን እንደሚያመለክት ያምናሉ። |
ከዚያም ኢየሱስ በሚታይ መንገድ በመመለስ ምድርን እንደሚገዛ ይጠብቃሉ። |
ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ እንደሚታይ እንዲሁም ኢየሱስ በሰማይ ደመና እንደሚመጣ በግልጽ ይናገራል። |
ሁለቱም አገላለጾች የሚያመለክቱት በዓይን የማይታይ ሁኔታን ነው። |
በተጨማሪም ሥጋና ደም የአምላክን መንግሥት አይወርስም። |
በመሆኑም ወደ ሰማይ የሚወሰዱ ሰዎች የመጨረሻው መለከት በሚነፋበት ወቅት ድንገት፣ በቅጽበተ ዓይን መለወጥ ይኖርባቸዋል። |
በምድር የቀሩት ታማኝ ቅቡዓን በቅጽበት ወደ ሰማይ ይሰበሰባሉ። |
ለምን? |
እርስ በርሳችን እንደ ወንድማማች መዋደዳችንን መቀጠል አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? |
ዋነኛው ምክንያት፣ ይሖዋ አንዳችን ለሌላው የወንድማማች ፍቅር እንድናሳይ የሚጠብቅብን መሆኑ ነው። |
ወንድሞቻችንን ሳንወድ አምላክን እንወደዋለን ማለት የማይመስል ነገር ነው። |
በተጨማሪም አንዳችን የሌላው ድጋፍ ያስፈልገናል። |
በተለይ በአስቸጋሪ ጊዜያት ወንድሞቻችን ይበልጥ ያስፈልጉናል። |
ጳውሎስ ደብዳቤውን ከጻፈላቸው ዕብራውያን ክርስቲያኖች አንዳንዶቹ ብዙም ሳይቆይ ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሸሽ እንደሚኖርባቸው ያውቃል። |
ይህ ወቅት ምን ያህል ከባድ እንደሚሆን ኢየሱስ ተናግሯል። |
በመሆኑም እነዚያ ክርስቲያኖች፣ አንዳቸው ለሌላው ያላቸውን ፍቅር ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ማጠናከር ይኖርባቸዋል። |
እስከ ዛሬ ሆኖ የማያውቀው ታላቅ መከራ የጥፋት ነፋሳት በቅርቡ ይለቀቃሉ። |
አዘውትረን መሰብሰባችን ብቻውን በቂ አይደለም። |
ጳውሎስ እነዚህን አጋጣሚዎች ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች እርስ በርስ ለመነቃቃት እንዲጠቀሙባቸው ዕብራውያን ክርስቲያኖችን አሳስቧቸዋል። |
እዚህ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ሊያጎላው የፈለገው ነጥብ ምንድን ነው? |
አንድ ቅቡዕ ክርስቲያን ከይሖዋ ጋር ያለውን ጥሩ ግንኙነት ጠብቆ ካልተመላለሰ ከቂጣው የሚበላውና ከጽዋው የሚጠጣው ሳይገባው ይሆናል። |
እንዲህ ያለው ማስጠንቀቂያ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ሽልማታቸውን ገና እንዳላገኙ እንዲያስታውሱ ያደርጋል። |
አምላክ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የሚሰጠውን የሰማያዊውን ሕይወት ሽልማት ያገኙ ዘንድ ግባቸው ላይ ለመድረስ ጥረት ማድረጋቸውን መቀጠል አለባቸው። |
ጳውሎስ ለቅቡዓን ክርስቲያኖች ከተጠራችሁበት ጥሪ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ በማለት በመንፈስ መሪነት ጽፎላቸዋል። |
ይህን የሚያደርጉት እንዴት ነው? |
ጳውሎስ በመቀጠል እንዲህ ብሏል፦ በፍጹም ትሕትናና ገርነት፣ በትዕግሥት እንዲሁም እርስ በርሳችሁ በፍቅር በመቻቻል ኑሩ፤ አንድ ላይ በሚያስተሳስረው የሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ልባዊ ጥረት አድርጉ። |
የይሖዋ መንፈስ ኩራትን ሳይሆን ትሕትናን ማዳበርን ያበረታታል። |
ኖኅ በክፋት በተሞላ ዓለም ውስጥ ይኖር ነበር፤ ሆኖም ኖኅ በዘመኑ የነበሩ ሰዎችን የቅርብ ጓደኞቹ አላደረገም። |
ኖኅ፣ ፈሪሃ አምላክ ከሌላቸው ሰዎች ጋር ፈጽሞ ወዳጅነት አልመሠረተም። |
እሱም ሆነ ሰባቱ የቤተሰቡ አባላት መርከብ መሥራትን ጨምሮ አምላክ የሰጣቸውን ኃላፊነት በመወጣት ላይ ትኩረት አድርገው ነበር። |
በተጨማሪም ኖኅ የጽድቅ ሰባኪ ነበር። |
ኖኅ መስበኩ፣ መርከብ መሥራቱና ከቤተሰቡ ጋር የነበረው ቅርርብ አምላክ የሚደሰትባቸውን መልካም ነገሮች በማከናወን እንዲጠመድ አስችሎታል። |
በዚህም የተነሳ ኖኅና ቤተሰቡ ከጥፋት ውኃው መትረፍ ችለዋል። |
በዛሬው ጊዜ ያለን በሙሉ የእነዚህ የይሖዋ አገልጋዮች ዘሮች ነን፤ ታማኙ ኖኅ፣ ሚስቱ፣ ልጆቹና ሚስቶቻቸው ባለውለታችን ናቸው። |
በተመሳሳይም በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ታማኝና ታዛዥ ክርስቲያኖች አምላካዊ ፍርሃት ከሌላቸው ሰዎች በመራቃቸው በ70 ዓ.ም. ኢየሩሳሌምና የአይሁድ ሥርዓት ሲጠፉ መትረፍ ችለዋል። |
ማንኛውም ዓይነት ጊዜ ማሳለፊያ ጠቃሚ እንዲሁም አእምሮንና ሰውነትን የሚያድስ ነው ማለት አይደለም፤ በተጨማሪም ረዘም ያለ ሰዓት በመዝናኛ ማጥፋት አሊያም ብዙ ጊዜ ለመዝናኛ መመደብ ጥሩ አይደለም። |
ሕሊናችን ገንቢ በሆነ መዝናኛ እንድንደሰትና ከመዝናኛ ጥቅም እንድናገኝ ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው? |
መጽሐፍ ቅዱስ የሥጋ ሥራዎች ብሎ ከሚጠራቸው አንዳንድ ምግባሮች እንድንርቅ ያስጠነቅቀናል። |
የሥጋ ሥራዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ የፆታ ብልግና፣ ርኩሰት፣ ዓይን ያወጣ ምግባር፣ ጣዖት አምልኮ፣ መናፍስታዊ ድርጊት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ በቁጣ መገንፈል፣ ጭቅጭቅ፣ መከፋፈል፣ መናፍቅነት፣ ምቀኝነት፣ ሰካራምነት፣ መረን የለቀቀ ፈንጠዝያና እነዚህን የመሳሰሉ ናቸው። |
ጳውሎስ እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚፈጽሙ የአምላክን መንግሥት አይወርሱም ሲል ጽፏል። |
በጸሎት ናሙናው ላይ አባቴ ሆይ ሳይሆን አባታችን ሆይ መባሉ እርስ በርስ ከልብ በሚዋደድ የወንድማማች ማኅበር ውስጥ እንደታቀፍን ያስታውሰናል። |
ይህ እንዴት ያለ ውድ መብት ነው! አምላክ እንደ ልጆቹ አድርጎ የወሰዳቸውና ሰማያዊ ሕይወት የሚያገኙ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ይሖዋን አባት ብለው የመጥራት ልዩ የሆነ መብት አላቸው። |
በምድር ላይ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ያላቸው ክርስቲያኖችም ቢሆኑ ይሖዋን አባት ብለው መጥራት ይችላሉ። |
ይሖዋ ሕይወት ሰጪያቸው ከመሆኑም ሌላ ለሁሉም እውነተኛ አምላኪዎቹ የሚያስፈልጋቸውን ነገር በፍቅር ተነሳስቶ ያቀርብላቸዋል። |
ምድራዊ ተስፋ ያላቸው እነዚህ የአምላክ አገልጋዮች ፍጽምና ደረጃ ላይ ከደረሱና በመጨረሻው ፈተና ታማኝ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ የአምላክ ልጆች ተብለው ይጠራሉ። |
ወላጆች ልጆቻቸውን መጸለይ ሲያስተምሯቸውና ይሖዋን እንደ አፍቃሪ ሰማያዊ አባታቸው አድርገው እንዲመለከቱት ሲረዷቸው ትልቅ ስጦታ እየሰጧቸው ነው። |
ወላጆች፣ ለልጆቻቸው ሊሰጧቸው ከሚችሉት ስጦታ ሁሉ የላቀው ከይሖዋ ጋር የቀረበና የጠበቀ ወዳጅነት እንዲመሠርቱ መርዳት ነው። |
የሚያስጨንቁንን ሐሳቦች ካልተቆጣጠርናቸው በአካላዊም ሆነ በመንፈሳዊ ሁኔታ ጉዳት ሊያደርሱብን ይችላሉ። |
በመሆኑም በይሖዋ መታመን ይኖርብናል፤ እንዲሁም በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ የተገለጸውን ሐሳብ ማስታወሳችን ጠቃሚ ነው። |
ስሜታችንን የሚረዳልን ሰው የሚሰጠን ማበረታቻ ልባችን በደስታ እንዲሞላ ያደርጋል። |
ነገሮችን በአምላክ ዓይን መመልከት ለሚችል ሰው ለምሳሌ ለወላጆቻችን፣ ለትዳር ጓደኛችን ወይም ለምናምነው ወዳጃችን የውስጣችንን አውጥተን መናገራችን ጭንቀታችን እንዲቀለን ሊረዳን ይችላል። |
ከይሖዋ የበለጠ ጭንቀታችንን ሊረዳልን የሚችል ማንም የለም። |
ጳውሎስ እንዲህ በማለት ጽፏል፦ ስለ ምንም ነገር አትጨነቁ፤ ከዚህ ይልቅ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር ልመናችሁን ለአምላክ አቅርቡ፤ ከመረዳት ችሎታ ሁሉ በላይ የሆነው የአምላክ ሰላም በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ልባችሁንና አእምሯችሁን ይጠብቃል። |
እንግዲያው የሚያስጨንቅ ነገር ሲያጋጥመን ከመንፈሳዊ ጉዳት የሚጠብቁንን አካላት ይኸውም የእምነት ባልንጀሮቻችንን፣ ሽማግሌዎችን፣ ታማኙን ባሪያ፣ መላእክትን፣ ኢየሱስንና ይሖዋን ለማሰብ እንሞክር። |
ዓለም ባለን የገለልተኝነት አቋም የተነሳ ቢጠላን መገረም አይኖርብንም፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ይህ እንደሚሆን አስጠንቅቆናል። |
አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች ከክርስቲያናዊ ገለልተኝነት ጋር የተያያዙት ጉዳዮች ምን ያህል ትልቅ ቦታ እንዳላቸው አይገነዘቡም። |
እኛ ግን ትልቅ ቦታ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። |
ለይሖዋ ታማኝ ለመሆን ከፈለግን ዛቻ ቢሰነዘርብንም መጽናት ይኖርብናል። |
የሰው ፍርሃት በሁሉም ዕድሜ ባሉ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ቢሆንም በተለይ ታዳጊዎች ከሌሎች የተለዩ መሆን ይከብዳቸው ይሆናል። |
ልጆቻችሁ ለባንዲራ ሰላምታ ከመስጠት ወይም ከብሔራዊ በዓላት ጋር በተያያዘ አቋማቸውን የሚፈትን ሁኔታ እያጋጠማቸው ከሆነ እርዳታ ልታደርጉላቸው ይገባል። |
ልጆቻችሁ ጉዳዩ ምን ያህል ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እንደሆነ እንዲገነዘቡ በቤተሰብ አምልኳችሁ ወቅት ለመርዳት ጥረት አድርጉ፤ ይህም የሚያጋጥማቸውን ፈተና በድፍረት ለመወጣት ያስችላቸዋል። |
የሚያምኑበትን ነገር በግልጽና አክብሮት በሚንጸባረቅበት መንገድ እንዲናገሩ እርዷቸው። |
አስፈላጊ ከሆነ ከመምህሮቻቸው ጋር ስለ እነዚህ ጉዳዮች ተነጋገሩ። |
አዳም ፍጽምና ስለጎደለው የአምላክን ባሕርያት ፍጹም በሆነ መንገድ ማንጸባረቅ አልቻለም። |
አዳም ሊያገኝ ይችል የነበረውን አስደናቂ ሕይወት ከማጣቱም ሌላ ለልጆቹ አለፍጽምናን፣ ኃጢአትንና ሞትን አውርሷል። |
ዘሮቹ ለዘላለም የመኖር አጋጣሚ እንዳያገኙ እንቅፋት ሆኗል። |
ከዚህም ሌላ አዳምና ሔዋንም ሆኑ ዘሮቻቸው ፍጹም የሆኑ ልጆች ሊወልዱ አይችሉም። |
ሰይጣን ዲያብሎስ የመጀመሪያዎቹን ወላጆቻችንን በአምላክ ላይ እንዲያምፁ ከማድረግም አልፎ በታሪክ ዘመናት በሙሉ የሰው ልጆችን ለማሳት ጥረት ማድረጉን ቀጥሏል። |
አምላክ ለሰው ልጆች ያለው ፍቅር ግን አልቀነሰም። |
አዳምና ሔዋን ቢያምፁም ይሖዋ፣ የሰው ልጆች ከእሱ ጋር ጥሩ ዝምድና እንዲኖራቸው ይፈልጋል። |
ማንም ሰው እንዲጠፋ አይፈልግም። |
ስለዚህ አዳምና ሔዋን ካመፁ በኋላ ብዙም ሳይቆይ አምላክ የሰው ልጆች ከእሱ ጋር የነበራቸውን ዝምድና መልሰው እንዲያገኙ የሚያስችል ዝግጅት አደረገ፤ እርግጥ ይህን ያደረገው የጽድቅ መሥፈርቶቹን ሳያላላ ነው። |
ልክ እንደ ይሖዋ ሌሎች ባላቸው አዎንታዊ ጎን ላይ ማተኮራችን በይሖዋ አገልግሎት ውስጥ ለተሰጠን ቦታ ያለን አድናቆት እንዲጨምር ያደርጋል። |
የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ወይም በሌሎች ላይ ለመሠልጠን ከመሞከር ይልቅ ልካችንን በማወቅ የሌሎችን ምክር እንጠይቃለን፤ እንዲሁም የሚሰጡንን ሐሳብ እንቀበላለን። |
ወንድሞቻችን መብት ሲያገኙ አብረናቸው እንደሰታለን። |
በተጨማሪም ይሖዋ በዓለም ዙሪያ በመላው የወንድማማች ማኅበር ውስጥ ያሉትን ወንድሞቻችንን እንደባረካቸው ስናይ እሱን ለማወደስ እንገፋፋለን። |
ልካችንን በማወቅ ነገሮችን ከይሖዋ አመለካከት አንጻር ለመመልከት ጥረት ማድረጋችን አምላክን የሚያስደስቱ ውሳኔዎችን ለማድረግም ይረዳናል። |
አዘውትረን በማጥናት፣ በመጸለይ እንዲሁም የተማርነውን ተግባራዊ በማድረግ ሕሊናችንን ቀስ በቀስ ማሠልጠን እንችላለን። |
በተጨማሪም ለሌሎች ቅድሚያ መስጠትን እንማራለን። |
እኛ ድርሻችንን ከተወጣን ይሖዋ ልክን ማወቅንና ሌሎች አምላካዊ ባሕርያትን እንድናዳብር በመርዳት ሥልጠናችን እንዲጠናቀቅ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል። |
አንዳንዶች፣ ጥቅሱ የሚያነጻጽረው እውነት ውስጥ ያሉና የሌሉ በሌላ አባባል ክርስቲያን የሆኑና ያልሆኑ ሰዎችን እንደሆነ ያስቡ ይሆናል። |
ይሁንና ጳውሎስ ደብዳቤውን የጻፈው ቅዱሳን እንዲሆኑ ለተጠሩና በአምላክ ለተወደዱ በሮም የሚኖሩ ሰዎች ነው። |
በመሆኑም ጳውሎስ ያነጻጸረው፣ እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚመላለሱ ክርስቲያኖችን እንደ መንፈስ ፈቃድ ከሚመላለሱ ክርስቲያኖች ጋር ነው። |
እንደ ሥጋ ፍላጎት መኖርን በክርስቲያኖች ሰውነት ውስጥ ይሠሩ ከነበሩት የኃጢአት ምኞቶች ጋር አያይዞ ጠቅሶታል። |
በመሆኑም ጳውሎስ አእምሯቸው በሥጋዊ ነገሮች ላይ ስላተኮረ ሰዎች ሲናገር የኃጢአት ምኞቶችና ዝንባሌዎች እንዲመሯቸውና እንዲቆጣጠሯቸው የሚፈቅዱ ወይም በሥጋዊ ፍላጎታቸው ላይ የሚያተኩሩ ሰዎችን ማመልከቱ ነበር። |
በጥቅሉ ሲታይ እነዚህ ሰዎች ከፆታ ጋር በተያያዘም ይሁን በሌሎች ጉዳዮች ረገድ ምኞታቸውን፣ ፍላጎታቸውንና ስሜታቸውን የሚከተሉ ናቸው። |
አንዳንዶች ቀደም ሲል ባደረጉት ነገር ወይም በፈጸሙት ስህተት የተነሳ ይጨነቁ ይሆናል። |
ንጉሥ ዳዊት የፈጸማቸው ስህተቶች በራሱ ላይ እንደሚያንዣብቡ የተሰማው ጊዜ ነበር። |
በጭንቀት ከተዋጠው ልቤ የተነሳ እጅግ እቃትታለሁ በማለት ተናግሯል። |
በዚያ ወቅት ጥበብ የሚሆነው ምን ማድረግ ነበር? |
ዳዊትስ ምን አድርጓል? |
ይሖዋ ምሕረት እንደሚያደርግለትና ይቅር እንደሚለው ተማምኗል። |
ሌሎችን የሚያስጨንቃቸው ደግሞ አሁን ያሉበት ሁኔታ ነው። |
ለምሳሌ ያህል፣ ዳዊት ን በጻፈበት ወቅት ለሕይወቱ ሰግቶ ነበር። |
ያም ቢሆን የነበረበት አስጨናቂ ሁኔታ በይሖዋ እንዳይተማመን እንዲያደርገው አልፈቀደም። |
ዳዊት ስላጋጠመው ችግር አጥብቆ በመጸለይ ብቻ ሳይወሰን የጭንቀቱን መንስኤ ለማስወገድ እርምጃ ወስዷል። |
አንተም ከዳዊት ትምህርት ማግኘት ትችላለህ። |
ጭንቀት እንዲቆጣጠርህ ከመፍቀድ ይልቅ ችግሩን ለመፍታት የቻልከውን ያህል ጥረት አድርግ፤ ከዚያም ይሖዋ እንደሚረዳህ በመተማመን ጉዳዩን ለእሱ ተወው። |
ስጦታ ሲሰጥህ ምን ታደርጋለህ? |
መቼም አድናቆትህን በሆነ መንገድ መግለጽህ አይቀርም። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.