text stringlengths 4 267 |
|---|
“‘“እኔ ግን እንዳላጠፋቸው ራራሁላቸው፤ ደግሞም አላጠፋኋቸውም፤ በምድረ በዳም ፈጽሜ አልፈጀኋቸውም። |
በምድረ በዳ ልጆቻቸውን እንዲህ አልኳቸው፦ ‘የአባቶቻችሁን ሥርዓት አትከተሉ፤ ድንጋጌዎቻቸውንም አታክብሩ፤ ወይም አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻቸው ራሳችሁን አታርክሱ። |
እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ። ደንቦቼን አክብራችሁ ተመላለሱ፤ ድንጋጌዎቼንም ጠብቁ፤ በሥራም አውሏቸው። |
ደግሞም ሰንበቶቼን ቀድሱ፤ እኔ አምላካችሁ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ሆነው ያገለግላሉ።’ |
“‘“ሆኖም ልጆቹ በእኔ ላይ ያምፁ ጀመር። ደንቦቼን አክብረው አልተመላለሱም፤ ሰው ቢከተላቸው በሕይወት እንዲኖር የሚያደርጉትን ድንጋጌዎቼን አላከበሩም፤ ደግሞም በሥራ ላይ አላዋሉም። ሰንበቶቼን አረከሱ። በመሆኑም በምድረ በዳ ንዴቴን በላያቸው ለማፍሰስና ቁጣዬን በእነሱ ላይ ሙሉ በሙሉ ለማውረድ ቃል ገባሁ። |
ይሁንና እነሱን ሳወጣቸው ባዩት ብሔራት ፊት ስሜ እንዳይረክስ ስል እጄን መለስኩ፤ ስለ ስሜም ስል እርምጃ ወሰድኩ። |
ደግሞም በብሔራት መካከል እንደምበታትናቸውና ወደተለያዩ አገሮች እንደምሰዳቸው በምድረ በዳ ማልኩ፤ |
ምክንያቱም እነሱ ድንጋጌዎቼን አላከበሩም፤ ደንቦቼንም አቃለዋል፤ ሰንበቶቼን አርክሰዋል፤ ደግሞም እነሱ አስጸያፊ የሆኑትን የአባቶቻቸውን ጣዖቶች ተከትለዋል። |
እኔም ጥሩ ባልሆነ ሥርዓት እንዲመላለሱና ሕይወት የማያስገኙላቸውን ድንጋጌዎች እንዲከተሉ ተውኳቸው። |
አስከፊ ሁኔታ ይደርስባቸው ዘንድ እያንዳንዱን የበኩር ልጅ ለእሳት አሳልፈው ሲሰጡ በገዛ መሥዋዕታቸው እንዲረክሱ አደረግኩ፤ ይህም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቁ ዘንድ ነው።”’ |
“ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በዚህም መንገድ አባቶቻችሁ ለእኔ ያላቸውን ታማኝነት በማጉደል ሰደቡኝ። |
ለእነሱ ለመስጠት ወደማልኩላቸው ምድር አመጣኋቸው። ከፍ ያለ ኮረብታና የለመለመ ዛፍ ሁሉ ባዩ ጊዜ በዚያ መሥዋዕታቸውንና ቁጣ የሚያነሳሳ መባቸውን ያቀርቡ ጀመር። በዚያም ደስ የሚያሰኘውን የመሥዋዕቶቻቸውን መዓዛ አቀረቡ፤ የመጠጥ መባቸውንም አፈሰሱ። |
እኔም እንዲህ አልኳቸው፦ ‘እናንተ የምትሄዱበት ይህ ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ ምንድን ነው? (ይህ ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ባማ ተብሎ ይጠራል።)’”’ |
“እንግዲህ ለእስራኤል ቤት ሰዎች እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “አባቶቻችሁ አስጸያፊ ከሆኑ ጣዖቶቻቸው ጋር መንፈሳዊ ምንዝር ለመፈጸም ሲሉ እነሱን በመከተል ራሳቸውን እንዳረከሱ ሁሉ እናንተም ራሳችሁን ታረክሳላችሁ? |
አስጸያፊ ለሆኑት ጣዖቶቻችሁ ሁሉ መሥዋዕት በማቅረብ ይኸውም ልጆቻችሁን ለእሳት አሳልፋችሁ በመስጠት እስከ ዛሬ ድረስ ራሳችሁን እያረከሳችሁ ነው? የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ታዲያ እንዲህ እያደረጋችሁ ለጥያቄያችሁ ምላሽ መስጠት ይኖርብኛል?”’ “‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ለጥያቄያችሁ ምላሽ አልሰጥም። |
“እንጨትና ድንጋይ እንደሚያመልኩት ብሔራት፣ እንደ ሌሎቹም አገሮች ሕዝቦች እንሁን” በማለት የምታውጠነጥኑት ሐሳብ ፈጽሞ አይሳካም።’” |
“‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘በኃያል እጅና በተዘረጋች ክንድ እንዲሁም ታላቅ ቁጣ በማፍሰስ በእናንተ ላይ ንጉሥ ሆኜ እገዛለሁ። |
በኃያል እጅና በተዘረጋች ክንድ እንዲሁም ታላቅ ቁጣ በማፍሰስ ከሕዝቦች መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች እሰበስባችኋለሁ። |
ወደ ሕዝቦች ምድረ በዳ አመጣችኋለሁ፤ በዚያም ፊት ለፊት እፋረዳችኋለሁ። |
“‘አባቶቻችሁን በግብፅ ምድረ በዳ እንደተፋረድኳቸው ሁሉ እናንተንም እፋረዳችኋለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
‘ከእረኛ በትር በታች አሳልፋችኋለሁ፤ ደግሞም በቃል ኪዳኑ ግዴታ ውስጥ እንድትገቡ አደርጋለሁ። |
ሆኖም በእኔ ላይ የሚያምፁትንና በደል የሚፈጽሙትን ከመካከላችሁ አስወግዳለሁ። የባዕድ አገር ሰው ሆነው ከሚኖሩበት ምድር አወጣቸዋለሁና፤ ወደ እስራኤል ምድር ግን አይገቡም፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’ |
“የእስራኤል ቤት ሰዎች ሆይ፣ እናንተን በተመለከተ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እያንዳንዳችሁ ሄዳችሁ አስጸያፊ የሆኑትን ጣዖቶቻችሁን አገልግሉ። ከዚያ በኋላ ግን እኔን ባለመስማታችሁ መዘዙን ትቀበላላችሁ፤ በመሥዋዕቶቻችሁና አስጸያፊ በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ከእንግዲህ ወዲህ ቅዱስ ስሜን አታረክሱም።’ |
“‘በቅዱሱ ተራራዬ፣ ከፍ ባለውም የእስራኤል ተራራ ላይ፣’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘መላው የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ አዎ ሁሉም በዚያ በምድሪቱ ላይ ያገለግሉኛልና። በዚያም በእነሱ ደስ እሰኛለሁ፤ ደግሞም ቅዱስ ከሆኑት ነገሮቻችሁ ሁሉ መዋጮዎቻችሁንና የመባችሁን የፍሬ በኩራት እሻለሁ። |
ከሕዝቦች መካከል በማወጣችሁና ከተበተናችሁባቸው አገሮች በምሰበስባችሁ ጊዜ ደስ በሚያሰኘው መዓዛ የተነሳ በእናንተ እረካለሁ፤ በብሔራትም ፊት በእናንተ መካከል እቀደሳለሁ።’ |
“‘ለአባቶቻችሁ ለመስጠት ወደማልኩላቸው አገር፣ ወደ እስራኤል ምድር ሳመጣችሁ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። |
በዚያም ራሳችሁን ያረከሳችሁባቸውን ምግባራችሁንና ድርጊቶቻችሁን ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤ በሠራችኋቸውም መጥፎ ነገሮች ሁሉ የተነሳ ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ። |
የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እንደ ክፉ ምግባራችሁ ወይም እንደ ብልሹ ተግባራችሁ ሳይሆን፣ ስለ ስሜ ስል እርምጃ በምወስድበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ፊትህን በስተ ደቡብ አቅጣጫ አዙረህ ወደ ደቡብ ተናገር፤ በደቡብም ምድር ባለው ደን ላይ ትንቢት ተናገር። |
በደቡብ ለሚገኘው ደን እንዲህ በል፦ ‘የይሖዋን ቃል ስማ። ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ በአንተ ላይ እሳት አነዳለሁ፤ እሳቱም በአንተ ውስጥ ያለውን የለመለመውንና ደረቁን ዛፍ ሁሉ ይበላል። የሚንቦገቦገው ነበልባል አይጠፋም፤ እሱም ከደቡብ እስከ ሰሜን ያለውን ፊት ሁሉ ይለበልባል። |
ሥጋ ለባሽም ሁሉ እሳቱን ያነደድኩት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያያል፤ በመሆኑም እሳቱ አይጠፋም።”’” |
እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ወዮ! እነሱ ስለ እኔ ‘ሁልጊዜ የሚናገረው እንቆቅልሽ ነው’ ይላሉ።” |
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ የምትኖረው በዓመፀኛ ሕዝብ መካከል ነው። እነሱ የሚያዩበት ዓይን አላቸው፣ ግን አያዩም፤ የሚሰሙበት ጆሮ አላቸው፣ ነገር ግን አይሰሙም፤ እነሱ ዓመፀኛ ሕዝብ ናቸውና። |
የሰው ልጅ ሆይ፣ አንተ ግን በግዞት እንደሚወሰድ ሰው ለመሄድ ጓዝህን አዘጋጅ። ከዚያም እነሱ እያዩህ በቀን ጉዞ ጀምር። እነሱ እያዩህ ከቤትህ ተነስተህ ወደ ሌላ ቦታ እንደ ግዞተኛ ሂድ። ዓመፀኛ ሕዝብ ቢሆኑም እንኳ ትርጉሙ ምን እንደሆነ ይገባቸው ይሆናል። |
በቀን እነሱ እያዩህ በግዞት እንደሚወሰድ ሰው ለመሄድ ጓዝህን አዘጋጅተህ አውጣ፤ ከዚያም ምሽት ላይ እነሱ እያዩህ በግዞት እንደሚወሰድ ሰው ውጣ። |
“እነሱ እያዩ ግንቡን ነድለህ በዚያ በኩል ጓዝህን ተሸክመህ ውጣ። |
እነሱ እያዩ ጓዝህን በትከሻህ ተሸክመህ በጨለማ ይዘኸው ውጣ። መሬቱን እንዳታይ ፊትህን ሸፍን፤ ለእስራኤል ቤት ምልክት አደርግሃለሁና።” |
እኔም ልክ እንደታዘዝኩት አደረግኩ። ቀን ላይ በግዞት እንደሚሄድ ሰው ጓዝ፣ ጓዜን ጠቅልዬ አወጣሁ፤ ከዚያም ምሽት ላይ ግንቡን በእጄ ነደልኩት። ሲጨልምም ዓይናቸው እያየ ጓዜን በትከሻዬ ተሸክሜ ወጣሁ። |
ጠዋት ላይ የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ዓመፀኛ ሕዝብ የሆኑት የእስራኤል ቤት ሰዎች ‘ምን እያደረግክ ነው?’ ብለው አልጠየቁህም? |
እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ቃል የተነገረው በኢየሩሳሌም ለሚኖረው አለቃና በከተማዋ ውስጥ ለሚኖረው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ነው።”’ |
“እንዲህ በል፦ ‘እኔ ለእናንተ ምልክት ነኝ። ልክ እኔ እንዳደረግኩት በእነሱም ላይ እንዲሁ ይደረግባቸዋል። ተማርከው በግዞት ይወሰዳሉ። |
በመካከላቸው ያለው አለቃ በጨለማ ጓዙን በትከሻው ተሸክሞ ይወጣል። ግንቡን ይነድልና ጓዙን ተሸክሞ በዚያ በኩል ይወጣል። መሬቱን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል።’ |
መረቤን በእሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ እሱም በማጥመጃ መረቤ ይያዛል። ከዚያም ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ምድሪቱን ግን አያይም፤ በዚያም ይሞታል። |
በእሱም ዙሪያ ያሉትን ሁሉ ይኸውም ረዳቶቹንና ወታደሮቹን በየአቅጣጫው እበትናቸዋለሁ፤ እነሱንም ለማሳደድ ሰይፍ እመዛለሁ። |
በብሔራት መካከል ስበትናቸውና በአገሮችም መካከል ስዘራቸው እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ። |
ይሁንና በሚሄዱባቸው ብሔራት መካከል አስጸያፊ ስለሆኑት ልማዶቻቸው ሁሉ እንዲናገሩ ከእነሱ መካከል ጥቂት ሰዎች ከሰይፍ፣ ከረሃብና ከቸነፈር እንዲተርፉ አደርጋለሁ፤ እነሱም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ ምግብህን እየተንቀጠቀጥክ ብላ፤ ውኃህንም በስጋትና በጭንቀት ጠጣ። |
ለምድሪቱም ሕዝብ እንዲህ በል፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በእስራኤል ምድር ላሉት የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲህ ይላል፦ “ምግባቸውን በጭንቀት ይበላሉ፤ ውኃቸውንም በፍርሃት ይጠጣሉ፤ በምድሪቱ ላይ የሚኖሩት ሰዎች ሁሉ ከሚፈጽሙት ዓመፅ የተነሳ ምድራቸው ፈጽማ ባድማ ትሆናለችና። |
ሰው ይኖርባቸው የነበሩት ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም ወና ትሆናለች፤ እናንተም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።”’” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ በእስራኤል ምድር ‘ዘመኑ አልፏል፤ ራእይም ሁሉ መና ቀርቷል’ የምትሉት ይህ አባባል ምንድን ነው? |
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ይህን አባባል አስቀራለሁ፤ በእስራኤልም ምድር ይህን አባባል ዳግመኛ አይጠቀሙበትም።”’ ሆኖም እንዲህ በላቸው፦ ‘ዘመኑ ቀርቧል፤ እያንዳንዱም ራእይ ይፈጸማል።’ |
በእስራኤል ቤት መካከል ከእንግዲህ የሐሰት ራእይ ወይም አሳሳች ሟርት አይኖርምና። |
‘“እኔ ይሖዋ እናገራለሁና። የተናገርኩት ቃል ሁሉ ከእንግዲህ ሳይዘገይ ይፈጸማል። ዓመፀኛው ቤት ሆይ፣ በእናንተ ዘመን እኔ እናገራለሁ፤ የተናገርኩትንም እፈጽማለሁ” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።’” |
የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“የሰው ልጅ ሆይ፣ የእስራኤል ሰዎች ‘እሱ የሚያየው ራእይ የሚፈጸመው ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው፤ ትንቢት የሚናገረውም በጣም ሩቅ ስለሆነ ጊዜ ነው’ ይላሉ። |
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “‘ከተናገርኩት ቃል ውስጥ የሚዘገይ አይኖርም፤ የተናገርኩት ቃል ሁሉ ይፈጸማል’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”’” |
“ከሰሜናዊ ጫፍ አንስቶ የነገዶቹ ስም ይህ ነው፦ የዳን ድርሻ የሄትሎንን መንገድ ተከትሎ እስከ ሌቦሃማት እንዲሁም በስተ ሰሜን በደማስቆ ድንበር በኩል፣ ከሃማት አጠገብ እስካለው እስከ ሃጻርኤናን ድረስ ይዘልቃል፤ ድርሻውም ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። |
የአሴር ድርሻ ከዳን ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። |
የንፍታሌም ድርሻ ከአሴር ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። |
የምናሴ ድርሻ ከንፍታሌም ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። |
የኤፍሬም ድርሻ ከምናሴ ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። |
የሮቤል ድርሻ ከኤፍሬም ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። |
የይሁዳ ድርሻ ከሮቤል ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። |
በይሁዳ ድንበር፣ ከምሥራቁ ወሰን አንስቶ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ መዋጮ አድርጋችሁ ለመስጠት የምትለዩት መሬት ወርዱ 25,000 ክንድ ይሁን፤ ደግሞም ይህ መሬት ከምሥራቁ ወሰን አንስቶ እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ርዝመቱ ከሌሎቹ ነገዶች ድርሻ ጋር እኩል ይሁን። መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል። |
“መዋጮ አድርጋችሁ በመስጠት ለይሖዋ የምትለዩት መሬት ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ ይሆናል። |
ይህ ለካህናቱ የሚሰጥ የተቀደሰ መዋጮ ይሆናል። በሰሜን በኩል 25,000 ክንድ፣ በምዕራብ በኩል 10,000፣ በምሥራቅ በኩል 10,000፣ በደቡብ በኩል ደግሞ 25,000 ይሆናል። የይሖዋ መቅደስ በመካከሉ ይሆናል። |
ይህ የሳዶቅ ልጆች ለሆኑት የተቀደሱ ካህናት ይሆናል፤ እነሱ በእኔ ፊት ያለባቸውን ኃላፊነት ተወጥተዋል፤ እንዲሁም እስራኤላውያንና ሌዋውያን በባዘኑ ጊዜ ከእነሱ ጋር አልባዘኑም። |
በሌዋውያን ድንበር በኩል፣ እጅግ ቅዱስ ተደርጎ ከተለየውና መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው መሬት ላይ ድርሻ ያገኛሉ። |
ሌዋውያኑ ከካህናቱ መሬት አጠገብ ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ የሆነ ድርሻ ይኖራቸዋል። (አጠቃላይ ርዝመቱ 25,000፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ይሆናል።) |
ምርጥ ከሆነው ከዚህ የመሬቱ ድርሻ ላይ የትኛውንም ቦታ መሸጥ፣ መለወጥ ወይም ለሌሎች አሳልፈው መስጠት የለባቸውም፤ ለይሖዋ የተቀደሰ ነውና። |
“ደግሞም 25,000 ክንድ ከሆነው ወሰን አጠገብ የሚገኘው፣ ወርዱ 5,000 ክንድ የሆነው የቀረው ቦታ ለከተማዋ የጋራ ጥቅም፣ ለመኖሪያ ቤትና ለግጦሽ መሬት ይውላል። ከተማዋ በመካከሉ ትሆናለች። |
የከተማዋም መጠን ይህ ነው፦ የሰሜኑ ወሰን 4,500፣ የደቡቡ ወሰን 4,500፣ የምሥራቁ ወሰን 4,500 እንዲሁም የምዕራቡ ወሰን 4,500 ክንድ ነው። |
የከተማዋ የግጦሽ መሬት በስተ ሰሜን 250፣ በስተ ደቡብ 250፣ በስተ ምሥራቅ 250 እና በስተ ምዕራብ 250 ክንድ ይሆናል። |
“የቀረው ድርሻ ርዝመቱ በመዋጮ ከተሰጠው የተቀደሰ መሬት ጋር እኩል ይሆናል፤ ይኸውም በስተ ምሥራቅ 10,000፣ በስተ ምዕራብም 10,000 ክንድ ይሆናል። ርዝመቱ በመዋጮ ከተሰጠው የተቀደሰ መሬት ጋር እኩል ይሆናል፤ በዚያም የሚመረተው ከተማዋን ለሚያገለግሉ ምግብ ይሆናል። |
ከተማዋን የሚያገለግሉ ከሁሉም የእስራኤል ነገዶች የተውጣጡ ሰዎች መሬቱን ያርሳሉ። |
“በመዋጮ የተሰጠው መሬት በአጠቃላይ አራቱም ማዕዘኑ እኩል ሲሆን እያንዳንዱ ማዕዘን 25,000 ክንድ ነው። ከከተማዋ ይዞታ ጋር፣ በመዋጮ የተሰጠ የተቀደሰ መሬት አድርጋችሁ ትለዩታላችሁ። |
“በመዋጮ ከተሰጠው የተቀደሰ መሬትና ከከተማዋ ይዞታ ግራና ቀኝ ያለው የቀረው ቦታ የአለቃው ይሆናል። ይህ ቦታ በመዋጮ ከተሰጠው መሬት በስተ ምሥራቅና በስተ ምዕራብ ከሚገኙት 25,000 ክንድ ከሆኑት ወሰኖች አጠገብ ይሆናል። በአቅራቢያው ካሉት የነገዶቹ ድርሻዎች ጋር ይዋሰናል፤ ይህም ለአለቃው ይሆናል። በመዋጮ የተሰጠው የተቀደሰ መሬትና የቤተ መቅደሱ መቅደስ በመካከሉ ይሆናል። |
“የሌዋውያኑ ይዞታና የከተማዋ ይዞታ በአለቃው ክልል መካከል ይሆናል። የአለቃው ክልል በይሁዳ ድንበርና በቢንያም ድንበር መካከል ይሆናል። |
“የቀሩትን ነገዶች በተመለከተ፣ የቢንያም ድርሻ ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። |
የስምዖን ድርሻ ከቢንያም ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። |
የይሳኮር ድርሻ ከስምዖን ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። |
የዛብሎን ድርሻ ከይሳኮር ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። |
የጋድ ድርሻ ከዛብሎን ምድር ጋር የሚዋሰን ሲሆን ከምሥራቁ ወሰን እስከ ምዕራቡ ወሰን ድረስ ነው። |
በጋድ ወሰን በኩል ያለው ደቡባዊ ድንበር ከትዕማር እስከ የመሪባትቃዴስ ውኃዎች፣ እስከ ደረቁ ወንዝና እስከ ታላቁ ባሕር ይዘልቃል። |
“ለእስራኤል ነገዶች ርስት አድርጋችሁ የምታከፋፍሏት ምድር ይህች ናት፤ ይህም ድርሻቸው ይሆናል” ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። |
“የከተማዋ መውጫዎች እነዚህ ይሆናሉ፦ በሰሜን በኩል ያለው 4,500 ክንድ ነው። |
“የከተማዋ በሮች በእስራኤል ነገዶች ስም ይሰየማሉ። በስተ ሰሜን ሦስት በሮች ያሉ ሲሆን አንዱ በር ለሮቤል፣ አንዱ በር ለይሁዳ፣ አንዱ በር ደግሞ ለሌዊ ይሆናል። |
“ምሥራቃዊው አቅጣጫ 4,500 ክንድ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን ሦስት በሮች ይኖሩታል፦ አንዱ በር ለዮሴፍ፣ አንዱ በር ለቢንያም፣ አንዱ በር ደግሞ ለዳን ይሆናል። |
“ደቡባዊው አቅጣጫ 4,500 ክንድ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን ሦስት በሮች ይኖሩታል፦ አንዱ በር ለስምዖን፣ አንዱ በር ለይሳኮር፣ አንዱ በር ደግሞ ለዛብሎን ይሆናል። |
“ምዕራባዊው አቅጣጫ 4,500 ክንድ ርዝመት የሚኖረው ሲሆን ሦስት በሮች ይኖሩታል፦ አንዱ በር ለጋድ፣ አንዱ በር ለአሴር፣ አንዱ በር ደግሞ ለንፍታሌም ይሆናል። |
“ዙሪያውን መጠኑ 18,000 ክንድ ይሆናል። ከዚያን ቀን ጀምሮ ከተማዋ ‘ይሖዋ በዚያ አለ’ ተብላ ትጠራለች።” |
የይሖዋም ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦ |
“በእስራኤል ምድር ‘ጎምዛዛ ወይን የበሉት አባቶች ሆነው ሳለ የልጆቹ ጥርስ ጠረሰ’ የሚለውን ምሳሌያዊ አባባል የምትጠቅሱት ምን ለማለት ነው? |
“‘በሕያውነቴ እምላለሁ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘ከእንግዲህ በእስራኤል ይህን ምሳሌ አትጠቅሱም። |
እነሆ፣ ነፍስ ሁሉ የእኔ ነው። የአባት ነፍስ የእኔ እንደሆነች ሁሉ የልጅም ነፍስ የእኔ ናት። ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እሷ ትሞታለች። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.