text
stringlengths 4
267
|
|---|
በቀኜ ወይም በግራዬ መቀመጥ ግን ለተዘጋጀላቸው የሚሰጥ እንጂ በእኔ ፈቃድ የሚሆን አይደለም።”
|
የቀሩት አሥሩ ይህን ሲሰሙ በያዕቆብና በዮሐንስ ላይ ተቆጡ።
|
ሆኖም ኢየሱስ ወደ እሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ብሔራትን የሚገዙ ነገሥታት በሕዝባቸው ላይ ሥልጣናቸውን እንደሚያሳዩ፣ ታላላቆቻቸውም በኃይል እንደሚገዟቸው ታውቃላችሁ።
|
በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም፤ ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ሊሆን ይገባል፤
|
እንዲሁም ከመካከላችሁ ፊተኛ መሆን የሚፈልግ ሁሉ፣ የሁሉ ባሪያ ሊሆን ይገባል።
|
ምክንያቱም የሰው ልጅ እንኳ የመጣው ለማገልገልና በብዙ ሰዎች ምትክ ሕይወቱን ቤዛ አድርጎ ለመስጠት እንጂ እንዲገለገል አይደለም።”
|
ከዚያም ወደ ኢያሪኮ መጡ። እሱና ደቀ መዛሙርቱ ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጡ ዓይነ ስውሩ የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ መንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር።
|
እሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን ሲሰማ “የዳዊት ልጅ፣ ኢየሱስ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልኝ!” እያለ ይጮኽ ጀመር።
|
በዚህ ጊዜ ብዙዎች ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እሱ ግን “የዳዊት ልጅ ሆይ፣ ምሕረት አድርግልኝ!” እያለ ይበልጥ መጮኹን ቀጠለ።
|
ኢየሱስም ቆመና “ጥሩት” አለ። እነሱም ዓይነ ስውሩን “አይዞህ! ተነስ፤ እየጠራህ ነው” አሉት።
|
እሱም መደረቢያውን ጥሎ ዘሎ በመነሳት ወደ ኢየሱስ ሄደ።
|
ኢየሱስም “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” አለው። ዓይነ ስውሩም “ራቦኒ፣ የዓይኔን ብርሃን መልስልኝ” አለው።
|
ኢየሱስም “ሂድ፣ እምነትህ አድኖሃል” አለው። ወዲያውም የዓይኑ ብርሃን ተመለሰለት፤ እሱም ከሕዝቡ ጋር አብሮ ይከተለው ጀመር።
|
ሰንበት ካለፈ በኋላም መግደላዊቷ ማርያም፣ የያዕቆብ እናት ማርያምና ሰሎሜ ሄደው አስከሬኑን ሊቀቡ ጥሩ መዓዛ ያላቸው ቅመሞች ገዙ።
|
ከዚያም በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን በማለዳ ፀሐይ ስትወጣ ወደ መቃብሩ መጡ።
|
እርስ በርሳቸውም “በመቃብሩ ደጃፍ ላይ ያለውን ድንጋይ ማን ያንከባልልልናል?” ይባባሉ ነበር።
|
ቀና ብለው ሲመለከቱ ግን በጣም ትልቅ የነበረው ድንጋይ ከቦታው ተንከባሎ አዩ።
|
ወደ መቃብሩ ሲገቡ ነጭ ልብስ የለበሰ አንድ ወጣት በቀኝ በኩል ተቀምጦ አዩና ደነገጡ።
|
እሱም እንዲህ አላቸው፦ “አትደንግጡ። በእንጨት ላይ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን እየፈለጋችሁ እንደሆነ አውቃለሁ። እሱ ተነስቷል። እዚህ የለም። ተመልከቱ፣ እሱን ያኖሩበት ስፍራ ይኸውና።
|
ይልቁንስ ሄዳችሁ ለደቀ መዛሙርቱና ለጴጥሮስ ‘ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል። እንደነገራችሁም እዚያ ታዩታላችሁ’ በሏቸው።”
|
እነሱም ከመቃብሩ ከወጡ በኋላ በአድናቆት ተውጠው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ ሸሽተው ሄዱ። ከፍርሃታቸውም የተነሳ ለማንም ምንም ነገር አልተናገሩም።
|
ከዚያም ወደ ባሕሩ ማዶ ተሻግረው ጌርጌሴኖን ወደተባለው ክልል ደረሱ።
|
ኢየሱስ ከጀልባ እንደወረደ፣ ርኩስ መንፈስ ያደረበት አንድ ሰው ከመቃብር ቦታ ወጥቶ ከእሱ ጋር ተገናኘ።
|
ይህ ሰው በመቃብር ቦታ ይኖር የነበረ ሲሆን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በሰንሰለት እንኳ አጥብቆ ሊያስረው የቻለ አንድም ሰው አልነበረም።
|
ብዙ ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር የነበረ ቢሆንም ሰንሰለቱን ይበጣጥስ፣ እግር ብረቱንም ይሰባብር ነበር፤ እሱን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የሚያስችል ጉልበት ያለው አንድም ሰው አልነበረም።
|
ዘወትር ሌሊትና ቀን በመቃብር ቦታና በተራሮች ላይ ይጮኽ እንዲሁም ሰውነቱን በድንጋይ ይተለትል ነበር።
|
ኢየሱስን ከሩቅ ባየው ጊዜ ግን ወደ እሱ ሮጦ በመሄድ ሰገደለት።
|
ከዚያም በታላቅ ድምፅ እየጮኸ “የልዑል አምላክ ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ምን ጉዳይ አለኝ? እንዳታሠቃየኝ በአምላክ ስም አስምልሃለሁ” አለው።
|
ይህን ያለው ኢየሱስ “አንተ ርኩስ መንፈስ ከዚህ ሰው ውጣ” ብሎት ስለነበር ነው።
|
ኢየሱስም “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው። እሱም “ብዙ ስለሆንን ስሜ ሌጌዎን ነው” ብሎ መለሰለት።
|
መናፍስቱን ከአገሪቱ እንዳያስወጣቸውም ኢየሱስን ተማጸነው።
|
በዚያም በተራራው ላይ ብዙ የአሳማ መንጋ ተሰማርቶ ነበር።
|
ርኩሳን መናፍስቱም “አሳማዎቹ ውስጥ እንድንገባ ወደ እነሱ ስደደን” ብለው ተማጸኑት።
|
እሱም ፈቀደላቸው። በዚህ ጊዜ ርኩሳን መናፍስቱ ወጥተው አሳማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ ወደ 2,000 የሚጠጉ አሳማዎችም ከገደሉ አፋፍ እየተንደረደሩ በመውረድ ባሕሩ ውስጥ ሰጠሙ።
|
የአሳማዎቹ እረኞች ግን ሸሽተው በመሄድ ወሬውን በከተማውና በገጠሩ አዳረሱ፤ ሰዎችም የሆነውን ነገር ለማየት መጡ።
|
ወደ ኢየሱስም መጥተው ጋኔን ያደረበትን ይኸውም ቀደም ሲል ሌጌዎን የነበረበትን ሰው ልብስ ለብሶና አእምሮው ተመልሶለት ተቀምጦ አዩት፤ በዚህ ጊዜ ፍርሃት አደረባቸው።
|
የተፈጸመውንም ነገር ያዩ ሰዎች አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው እንዴት እንዲህ ሊሆን እንደቻለና በአሳማዎቹ ላይ የሆነውን ነገር አወሩላቸው።
|
በመሆኑም አካባቢያቸውን ለቆ እንዲሄድ ኢየሱስን ይማጸኑት ጀመር።
|
ኢየሱስ ወደ ጀልባው በመውጣት ላይ ሳለ ጋኔን አድሮበት የነበረው ሰው አብሮት ይሄድ ዘንድ ተማጸነው።
|
ኢየሱስ ግን አልፈቀደለትም፤ ከዚህ ይልቅ “ወደ ቤት ሄደህ ይሖዋ ያደረገልህን ነገር ሁሉና ያሳየህን ምሕረት ለዘመዶችህ ንገራቸው” አለው።
|
ሰውየውም ሄዶ ኢየሱስ ያደረገለትን ነገር በሙሉ በዲካፖሊስ ያውጅ ጀመር፤ ሕዝቡም ሁሉ ተደነቁ።
|
ኢየሱስ በጀልባ ዳግመኛ ወደ ባሕሩ ማዶ ከተሻገረ በኋላ እጅግ ብዙ ሕዝብ ወደ እሱ ተሰበሰበ፤ እሱም በባሕሩ አጠገብ ነበር።
|
በዚህ ጊዜ ከምኩራብ አለቆች አንዱ የሆነ ኢያኢሮስ የሚባል ሰው ወደዚያ መጣ፤ ኢየሱስንም ባየው ጊዜ እግሩ ላይ ወደቀ።
|
ከዚያም “ትንሿ ልጄ በጠና ታምማለች። እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር፣ እባክህ መጥተህ እጅህን ጫንባት” በማለት ደጋግሞ ተማጸነው።
|
ኢየሱስም አብሮት ሄደ፤ እጅግ ብዙ ሕዝብም ተከትሎት እየተጋፋው ይሄድ ነበር።
|
በዚያም፣ ለ12 ዓመት ደም ሲፈሳት የኖረች አንዲት ሴት ነበረች።
|
ይህች ሴት በርካታ ሐኪሞች ጋር የሄደች ሲሆን ሕክምናው ለብዙ ሥቃይ ዳርጓት ነበር፤ ያላትን ጥሪት ሁሉ ብትጨርስም ሕመሙ ባሰባት እንጂ አልተሻላትም።
|
ስለ ኢየሱስ የተወራውን በሰማች ጊዜ በሰዎች መካከል ከበስተኋላው መጥታ ልብሱን ነካች፤
|
ምክንያቱም “ልብሱን ብቻ እንኳ ብነካ እድናለሁ” ብላ ታስብ ነበር።
|
ወዲያውም ይፈሳት የነበረው ደም ቆመ፤ ያሠቃያት ከነበረው ሕመም እንደተፈወሰችም ታወቃት።
|
ወዲያውኑ ኢየሱስ ኃይል ከእሱ እንደወጣ ታወቀው፤ በመሆኑም ወደ ሕዝቡ በመዞር “ልብሴን የነካው ማን ነው?” ሲል ጠየቀ።
|
ደቀ መዛሙርቱ ግን “ሕዝቡ እንዲህ ሲጋፋህ እያየህ ‘የነካኝ ማን ነው?’ እንዴት ትላለህ?” አሉት።
|
ይሁንና ኢየሱስ ይህን ያደረገው ማን እንደሆነ ለማየት ዙሪያውን ተመለከተ።
|
ሴትየዋ በእሷ ላይ የተፈጸመውን ነገር ስላወቀች በፍርሃት እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፤ ከዚያም ምንም ሳታስቀር እውነቱን ነገረችው።
|
እሱም “ልጄ ሆይ፣ እምነትሽ አድኖሻል። በሰላም ሂጂ፤ ከሚያሠቃይ ሕመምሽም ተፈወሽ” አላት።
|
ገና እየተናገረ ሳለ ከምኩራብ አለቃው ቤት የመጡ ሰዎች “ልጅህ ሞታለች! ከዚህ በኋላ መምህሩን ለምን ታስቸግረዋለህ?” አሉት።
|
ኢየሱስ ግን የተናገሩትን ሰምቶ የምኩራብ አለቃውን “አትፍራ፤ ብቻ እመን” አለው።
|
ከዚህ በኋላ ከጴጥሮስ፣ ከያዕቆብና ከያዕቆብ ወንድም ከዮሐንስ በስተቀር ማንም እንዲከተለው አልፈቀደም።
|
ወደ ምኩራብ አለቃው ቤት በደረሱም ጊዜ ትርምሱን እንዲሁም የሚያለቅሱትንና ዋይ ዋይ የሚሉትን ሰዎች ተመለከተ።
|
ወደ ውስጥ ከገባም በኋላ “የምታለቅሱትና የምትንጫጩት ለምንድን ነው? ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው።
|
በዚህ ጊዜ በማፌዝ ይስቁበት ጀመር። እሱ ግን ሁሉንም ወደ ውጭ ካስወጣ በኋላ የልጅቷን አባትና እናት እንዲሁም ከእሱ ጋር የነበሩትን አስከትሎ ልጅቷ ወዳለችበት ገባ።
|
ከዚያም የልጅቷን እጅ ይዞ “ጣሊታ ቁሚ” አላት፤ ትርጉሙም “አንቺ ልጅ፣ ተነሽ!” ማለት ነው።
|
ልጅቷም ወዲያው ተነስታ መራመድ ጀመረች። (ዕድሜዋ 12 ዓመት ነበር።) ወዲያውም እጅግ ከመደሰታቸው የተነሳ የሚሆኑት ጠፋቸው።
|
እሱ ግን ይህን ለማንም እንዳይናገሩ ደጋግሞ አስጠነቀቃቸው፤ ለልጅቷም የሚበላ ነገር እንዲሰጧት ነገራቸው።
|
ፋሲካና የቂጣ በዓል ሁለት ቀን ቀርቶት ነበር። የካህናት አለቆችና ጸሐፍት የተንኮል ዘዴ ተጠቅመው እሱን የሚይዙበትንና የሚገድሉበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፤
|
ደግሞም “ሕዝቡ ሁከት ሊያስነሳ ስለሚችል በበዓሉ ወቅት መሆን የለበትም” ይሉ ነበር።
|
በቢታንያ፣ የሥጋ ደዌ በሽተኛ በነበረው በስምዖን ቤት እየበላ ሳለ አንዲት ሴት እጅግ ውድ የሆነና ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ይኸውም ንጹሕ ናርዶስ የያዘ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች። ብልቃጡንም ሰብራ በመክፈት ዘይቱን ራሱ ላይ ታፈስ ጀመር።
|
በዚህ ጊዜ አንዳንዶቹ ተቆጥተው እንዲህ ተባባሉ፦ “ይህ ዘይት እንዲህ የሚባክነው ለምንድን ነው?
|
ከ300 ዲናር በላይ ተሸጦ ገንዘቡ ለድሆች ሊሰጥ ይችል ነበር!” በሴትየዋም እጅግ ተበሳጩ።
|
ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ፦ “ተዉአት። ለምን ታስቸግሯታላችሁ? እሷ ለእኔ መልካም ነገር አድርጋለች።
|
ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ በፈለጋችሁ ጊዜ ሁሉ መልካም ልታደርጉላቸው ትችላላችሁ፤ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም።
|
እሷ የምትችለውን አድርጋለች፤ ሰውነቴን ለቀብሬ ለማዘጋጀት ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት አስቀድማ ቀብታዋለች።
|
እውነት እላችኋለሁ፣ በመላው ዓለም ምሥራቹ በሚሰበክበት ቦታ ሁሉ ይህች ሴት ያደረገችውም መታሰቢያ ሆኖ ይነገርላታል።”
|
ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ ሊሰጠው ወደ ካህናት አለቆች ሄደ።
|
እነሱም ይህን ሲሰሙ ደስ አላቸውና የብር ገንዘብ ሊሰጡት ቃል ገቡለት። ስለዚህ እሱን አሳልፎ የሚሰጥበትን አጋጣሚ ይፈልግ ጀመር።
|
የቂጣ በዓል በሚከበርበት የመጀመሪያ ቀን፣ እንደተለመደው የፋሲካን መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ዕለት ደቀ መዛሙርቱ “ፋሲካን እንድትበላ የት ሄደን እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” አሉት።
|
እሱም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፦ “ወደ ከተማው ሂዱ፤ በዚያም የውኃ እንስራ የተሸከመ ሰው ታገኛላችሁ። እሱንም ተከተሉት፤
|
ወደሚገባበት ቤት ሄዳችሁ የቤቱን ጌታ ‘መምህሩ “ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የት ነው?” ብሏል’ በሉት።
|
እሱም የተነጠፈና የተሰናዳ ሰፊ ሰገነት ያሳያችኋል። እዚያ አዘጋጁልን።”
|
ደቀ መዛሙርቱም ሄዱ፤ ወደ ከተማውም ገቡ፤ እንዳላቸውም ሆኖ አገኙት፤ ለፋሲካ በዓሉም ዝግጅት አደረጉ።
|
እሱም ከመሸ በኋላ ከአሥራ ሁለቱ ጋር መጣ።
|
በማዕድ ተቀምጠው እየበሉ ሳለም ኢየሱስ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ፣ ከእኔ ጋር እየበላ ያለ አሳልፎ ይሰጠኛል” አለ።
|
እነሱም አዝነው በየተራ “እኔ እሆን?” ይሉት ጀመር።
|
እሱም እንዲህ አላቸው፦ “ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ይኸውም ከእኔ ጋር በሳህኑ ውስጥ የሚያጠቅሰው ነው።
|
የሰው ልጅ ስለ እሱ በተጻፈው መሠረት ይሄዳል፤ የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት! ያ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር።”
|
እየበሉም ሳሉ ቂጣ አንስቶ ባረከ፤ ከቆረሰውም በኋላ ሰጣቸውና “እንኩ፣ ይህ ሥጋዬን ያመለክታል” አለ።
|
ጽዋ አንስቶም አምላክን ካመሰገነ በኋላ ሰጣቸው፤ ሁሉም ከእሱ ጠጡ።
|
እንዲህም አላቸው፦ “ይህ ለብዙዎች የሚፈሰውን ‘የቃል ኪዳን ደሜን’ ያመለክታል።
|
እውነት እላችኋለሁ፣ በአምላክ መንግሥት አዲሱን ወይን እስከምጠጣበት ቀን ድረስ ከእንግዲህ በኋላ ከዚህ ወይን አልጠጣም።”
|
በመጨረሻ የውዳሴ መዝሙር ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄዱ።
|
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “‘እረኛውን እመታለሁ፤ በጎቹም ይበተናሉ’ ተብሎ ስለተጻፈ ሁላችሁም ትሰናከላላችሁ።
|
ከተነሳሁ በኋላ ግን ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ።”
|
ይሁንና ጴጥሮስ “ሌሎቹ ሁሉ ቢሰናከሉ እንኳ እኔ አልሰናከልም” አለው።
|
በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “እውነት እልሃለሁ፦ ዛሬ፣ አዎ በዚህች ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ አንተ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” አለው።
|
እሱ ግን “አብሬህ መሞት ቢኖርብኝ እንኳ በምንም ዓይነት አልክድህም” በማለት አጥብቆ ይናገር ጀመር። የቀሩትም ሁሉ እንደዚሁ አሉ።
|
ከዚያም ጌትሴማኒ ወደተባለ ቦታ መጡ፤ ደቀ መዛሙርቱንም “እኔ በምጸልይበት ጊዜ እናንተ እዚህ ተቀመጡ” አላቸው።
|
ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ከእሱ ጋር ይዟቸው ሄደ፤ ከዚያም እጅግ ይጨነቅና ይረበሽ ጀመር።
|
ኢየሱስም “እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዝኛለሁ። እዚህ ሁኑና ነቅታችሁ ጠብቁ” አላቸው።
|
ትንሽ ወደ ፊት ራቅ በማለት መሬት ላይ ተደፍቶ ቢቻል ሰዓቱ ከእሱ እንዲያልፍ ይጸልይ ጀመር።
|
እንዲህም አለ፦ “አባ፣ አባት ሆይ፣ አንተ ሁሉን ነገር ማድረግ ትችላለህ፤ ይህን ጽዋ ከእኔ አርቅ። ሆኖም እኔ የምፈልገው ሳይሆን አንተ የምትፈልገው ይሁን።”
|
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.