text stringlengths 4 267 |
|---|
ከርኅራኄ የመነጨ ምሕረት አባትና የመጽናናት ሁሉ አምላክ የሚያስፈልገንን ስሜታዊና መንፈሳዊ ድጋፍ አትረፍርፎ ይሰጠናል፤ ይህን የሚያደርገውም በእምነት ባልንጀሮቻችን አማካኝነት ሊሆን ይችላል። |
ግርጌ ለሌሎች ርኅራኄ ስናሳይ የይሖዋን ልብ እናስደስታለን። |
በተጨማሪም ይሖዋ ለደግነታችን ወሮታውን እንደሚከፍለን ቃል ገብቷል። |
ኢየሱስ ወደ ምድር ከመጣ በኋላም የመምረጥ ነፃነቱን በሚገባ ተጠቅሞበታል፤ የአምላክ ቀንደኛ ጠላት እሱን ለመፈተን ሲል ያቀረበለትን ግብዣ አልተቀበለም። |
ኢየሱስ፣ ከመሞቱ በፊት ባለው ምሽት ላይ ያቀረበው ከልብ የመነጨ ጸሎት የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ ያለው ቁርጠኝነት እንዳልተቀየረ የሚያረጋግጥ ነበር። |
እንዲህ ብሏል፦ አባት ሆይ፣ ፈቃድህ ከሆነ ይህን ጽዋ ከእኔ አርቅ። |
ይሁንና የእኔ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይፈጸም። |
እኛም የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል፣ የመምረጥ ነፃነታችንን ለይሖዋ ክብር ለማምጣትና የእሱን ፈቃድ ለመፈጸም እንጠቀምበት። |
ይሁንና እንዲህ ማድረግ ይቻላል? |
አዎ፣ የክርስቶስን ምሳሌ መከተል እንችላለን፤ ምክንያቱም ልክ እንደ ኢየሱስ ሁሉ እኛም የተሠራነው በአምላክ መልክና አምሳል ነው። |
ይህ ሲባል ግን እንደ ይሖዋ ገደብ የለሽ ነፃነት አለን ማለት አይደለም። |
የአምላክ ቃል፣ ነፃነታችን ገደብ እንዳለው እንዲሁም ይሖዋ ይህን ምክንያታዊ ገደብ አክብረን እንድንኖር እንደሚጠብቅብን ይናገራል። |
ከዚህም በተጨማሪ ሚስቶች ለባሎቻቸው፣ ልጆች ደግሞ ለወላጆቻቸው መገዛት አለባቸው። |
በቤዛው በማመን ራሳችንን ለይሖዋ ወስነን ስንጠመቅ ለቤዛው አድናቆት እንዳለን እናሳያለን። |
መጠመቃችን የይሖዋ እንደሆንን ያሳያል። |
ይሖዋ ማንኛውንም ነገር የሚያደርገው በፍቅር ተነሳስቶ ስለሆነ አገልጋዮቹ በሙሉ የእሱ ዓይነት ፍቅር እንዲያሳዩ ይፈልጋል። |
ባልንጀራችንን የምንወድ ከሆነ በሰማያት ላለው አባታችን ልጆች መሆን እንደምንፈልግ እናሳያለን። |
ከሁሉ ከሚበልጡት ሁለት ትእዛዛት የመጀመሪያው ይሖዋን እንድንወድ የሚያዘው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ባልንጀራችንን መውደድ እንዳለብን ይገልጻል። |
የአምላክን መንግሥት ምሥራች እንድንሰብክ የተሰጠንን ትእዛዝ በመፈጸም ለባልንጀራችን እንዲህ ዓይነት ፍቅር እንዳለን እናሳያለን። |
ለሰዎች ፍቅር ስናሳይ የአምላክን ክብር እናንጸባርቃለን። |
እንዲያውም ሌሎችን በተለይ ደግሞ ወንድሞቻችንን እንድንወድ የተሰጠንን መመሪያ ስንታዘዝ ለአምላክ ያለን ፍቅር ፍጹም ይሆናል። |
የተቀቡ ክርስቲያኖች የአምላክ መንፈስ በግለሰብ ደረጃ ሳይመሠክርላቸው በፊት፣ በምድር ላይ የመኖር ተስፋን ከፍ አድርገው ይመለከቱት ነበር። |
ይሖዋ ይህችን ምድር የሚያጸዳበትን ጊዜ ለማየት ይጓጉ እንዲሁም በዚያ ከሚገኘው በረከት መካፈል ይፈልጉ ነበር። |
ምናልባትም በሞት የተለዩአቸው የሚወዷቸው ሰዎች ትንሣኤ ሲያገኙና እነሱን ሲቀበሉ በዓይነ ሕሊናቸው ያዩ ነበር። |
ራሳቸው በሠሩት ቤት ውስጥ ለመኖርና የተከሏቸውን ዛፎች ፍሬ ለመብላት ይጓጉ ነበር። |
ታዲያ አመለካከታቸው የተለወጠው ለምንድን ነው? |
በዚህ ተስፋ ስላልረኩ አይደለም። |
አስተሳሰባቸው የተለወጠው ጭንቀት ወይም መከራ ስለበዛባቸው አይደለም። |
በምድር ላይ ለዘላለም መኖር አሰልቺ እንደሆነና ደስታ እንደማያስገኝ ተሰምቷቸው በድንገት ሐሳባቸውን ስለቀየሩም አይደለም፤ አሊያም በሰማይ መኖር ምን ሊመስል እንደሚችል ለማወቅ ስለፈለጉ አይደለም። |
ከዚህ ይልቅ አመለካከታቸው የተቀየረው የአምላክ መንፈስ ስለጠራቸው አልፎ ተርፎም አስተሳሰባቸውንና ተስፋቸውን ስለለወጠው ነው። |
ይሖዋ ከሁሉ የላቀ ነው፤ የሁሉም ነገር ፈጣሪ እንዲሁም ተወዳዳሪ የሌለው ጥበብና ኃይል ያለው አምላክ ነው። |
ኢዮብ ይህን እውነታ ተገንዝቧል። |
ይሖዋ የፍጥረት ሥራዎቹን በተመለከተ ለኢዮብ ጥያቄ ካቀረበለት በኋላ ኢዮብ አንተ ሁሉን ነገር ማድረግ እንደምትችል፣ ደግሞም ያሰብከውን ነገር ሁሉ ማድረግ እንደማይሳንህ አሁን አወቅኩ በማለት መልሷል። |
ይሖዋ፣ ያሰበውን ለማከናወን የማንም እገዛ የማያስፈልገው ቢሆንም ዓላማውን ዳር በማድረስ ረገድ ሌሎችም አብረውት እንዲሠሩ ገና ከጅምሩ በመጋበዝ ፍቅሩን አሳይቷል። |
የአምላክ የመጀመሪያ ፍጥረት፣ መንፈሳዊ አካል የሆነው አንድያ ልጁ ነው። |
ይሖዋ ከዚያ በኋላ ሕይወት ያላቸውንና የሌላቸውን ነገሮች በሙሉ ሲፈጥር ልጁ አብሮት እንዲሠራ አድርጓል። |
በመሆኑም ይሖዋ አንድያ ልጁ በፍጥረት ሥራው እንዲካፈል በማድረግ እንዲሁም ኢየሱስ የተጫወተውን ቁልፍ ሚና ለሌሎች በመግለጽ ልጁን አክብሮታል። |
ኢየሱስ ስለ አምላክ መንግሥት መናገር ያስደስተው ነበር። |
የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ እንደሚያሳየው ከማንኛውም ርዕሰ ጉዳይ ይበልጥ ስለ አምላክ መንግሥት ብዙ ጊዜ ተናግሯል፤ አገልግሎቱን ሲያከናውን ስለዚህ መንግሥት ከ100 ጊዜ በላይ ጠቅሷል። |
በእርግጥም ለመንግሥቱ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቷል። |
ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ ብዙም ሳይቆይ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ለሚሆኑ ከ500 የሚበልጡ ደቀ መዛሙርት ታይቶ ነበር። |
የመንግሥቱን መልእክት ከሁሉም ብሔራት ለተውጣጡ ሰዎች እንዲያደርሱ ያዘዛቸው በዚያ ወቅት ሳይሆን አይቀርም፤ በወቅቱ ይህን ሥራ ማከናወን ተፈታታኝ ነበር! ኢየሱስ ይህ ታላቅ ሥራ እስከ ሥርዓቱ መደምደሚያ ድረስ እንደሚከናወን የተነበየ ሲሆን ይህም እየተፈጸመ ነው። |
አንተም ይህ ተልእኮና ትንቢት ፍጻሜውን እንዲያገኝ የበኩልህን አስተዋጽኦ እያደረግክ ሊሆን ይችላል። |
አምላካችንም ይህን ተልእኮ ለመወጣት በሚረዳን መልካም ነገር ሁሉ አስታጥቆናል። |
ይሖዋ ሆይ፣ የሰው መንገድ በራሱ እጅ እንዳልሆነ በሚገባ አውቃለሁ። |
አካሄዱን እንኳ በራሱ አቃንቶ መምራት አይችልም የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ትክክል መሆኑን ታሪክ በበቂ ሁኔታ አረጋግጧል። |
በእርግጥም ይሖዋ የሰው ልጆችን ሲፈጥር ከእሱ አገዛዝ ርቀው ራሳቸውን ለመምራት የሚያበቃ ችሎታም ሆነ መብት አልሰጣቸውም። |
አምላክ ክፋት ለተወሰነ ጊዜ እንዲቀጥል መፍቀዱ የሰዎች አገዛዝ ከንቱ እንደሆነ ከማሳየቱም ባሻገር ዘላቂ ጥቅም አለው። |
ውጤታማ የሚሆነው የአምላክ አገዛዝ ብቻ እንደሆነ በማያዳግም ሁኔታ ያረጋግጣል። |
ይሖዋ ክፋትንና ክፉ አድራጊዎችን ካጠፋ በኋላ፣ የእሱ አገዛዝ በፍቅር ላይ የተመሠረተ ስለመሆኑ ጥያቄ የሚያነሳ አካል ቢኖር አምላክ ይህ ጥያቄ መልስ እንዲያገኝ ጊዜ መስጠት አያስፈልገውም። |
እንዲህ ያሉት ዓመፀኞች ወዲያውኑ ሊጠፉ እንጂ ክፋትን እንደገና እንዲያስፋፉ ሊፈቀድላቸው እንደማይገባ የሰው ልጆች ታሪክ በቂ ማስረጃ ይሆናል። |
ጳውሎስ ይበልጥ አስፈላጊ በሆኑት ነገሮች ላይ ትኩረት ያደረገ ከመሆኑም በላይ ወደ ሶርያ፣ ትንሿ እስያ፣ መቄዶንያና ይሁዳ ብዙ ጊዜ በመሄድ አምላክን በትጋት አገልግሏል። |
ጳውሎስ ከኋላዬ ያሉትን ነገሮች እየረሳሁ ከፊቴ ወዳሉት ነገሮች እንጠራራለሁ፤ . . . የሰማያዊውን ሕይወት ሽልማት አገኝ ዘንድ ግቡ ላይ ለመድረስ እየተጣጣርኩ ነው በማለት ጽፏል። |
ነጠላ መሆኑ ባስገኘለት አጋጣሚ ሙሉ በሙሉ በመጠቀም ሐሳቡ ሳይከፋፈል ዘወትር ለጌታ ያደረ መሆን ችሏል። |
እንደ ጳውሎስ ሁሉ አንዳንድ የአምላክ አገልጋዮችም ነጠላ ሆነው ለመኖር ወስነዋል፤ ይህ ደግሞ የቤተሰብ ኃላፊነት እንዳይበዛባቸው ስለሚያደርግ የመንግሥቱን አገልግሎት በቅንዓት ለማከናወን አስችሏቸዋል። |
አብዛኛውን ጊዜ ያገቡ ክርስቲያኖች ብዙ የቤተሰብ ኃላፊነት ይኖርባቸዋል። |
ይሁንና ያገቡም ሆኑ ያላገቡ ክርስቲያኖች ማንኛውንም ሸክም አንስተው በመጣል ብዙ ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮች ሳይኖሩባቸው አምላክን ማገልገል ይችላሉ። |
ይህ ደግሞ ጊዜ የሚያባክኑ ልማዶችን ማስወገድና በአምላክ አገልግሎት የሚያሳልፉትን ጊዜ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ግብ ማውጣት ይጠይቅባቸው ይሆናል። |
አምላክን እንደምንወደው ማሳየት የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው? |
በአገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ የሚካሄደውን የመንግሥቱን ሥራ ባለን ሀብት መደገፍ እንችላለን። |
በቁሳዊ ረገድ ያለን ብዙም ይሁን ጥቂት ለይሖዋ ያለንን ፍቅር በዚህ መንገድ መግለጽ እንደምንችል የታወቀ ነው። |
ይሁን እንጂ ይሖዋን እንደምንወደው ማሳየት የምንችልበት ሌላም መንገድ አለ። |
ኢየሱስ ለተከታዮቹ ስለ ምግብና ልብስ መጨነቃቸውን ትተው መንግሥቱን እንዲያስቀድሙ ማሳሰቢያ እንደሰጣቸው አስታውስ። |
ኢየሱስ በሰማይ የሚኖረው አባታችን የሚያስፈልገንን ነገር እንደሚያውቅ ተናግሯል። |
አምላክ በገባልን በዚህ ቃል ላይ ያለን እምነት ለይሖዋ ያለን ፍቅር ምን ያህል ጥልቀት እንዳለው ያሳያል፤ ምክንያቱም ፍቅርና እምነት የማይነጣጠሉ ነገሮች ናቸው። |
የማናምነውን ሰው ልንወደው አንችልም። |
ኢየሱስ የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ከሁሉ የተሻለ የሕይወት መመሪያ እንደሆነ በእርግጠኝነት ያምን ነበር። |
የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል መጽሐፍ ቅዱስን በየቀኑ ማንበብ፣ ማጥናትና ባወቅነው ነገር ላይ ማሰላሰል ይኖርብናል። |
መጽሐፍ ቅዱስን በጥቅሉ ከማጥናት በተጨማሪ ጥያቄዎች በሚፈጥሩብህ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ምርምር አድርግ። |
ለምሳሌ ያህል፣ የምንኖረው በመጨረሻዎቹ ቀኖች ውስጥ መሆኑን የሚያሳየውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃ በዝርዝር በማጥናት የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ በእርግጥ እንደቀረበ ያለህን እምነት ማጠናከር ትችላለህ። |
ከዚህ በፊት ፍጻሜያቸውን ያገኙ በርካታ ትንቢቶችን በማጥናት ገና ፍጻሜያቸውን ባላገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋዎች ላይ ያለህን እምነት አጠናክር። |
መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት እንደሚለውጥ የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን በማንበብ የአምላክ ቃል የያዘው ምክር ጠቃሚ መሆኑን በተመለከተ ያለህን እምነት ገንባ። |
በተጨማሪም ይሖዋ በገባልህ ግሩም ተስፋዎች ላይ በማሰላሰል የኢየሱስን አርዓያ መከተል ትችላለህ። |
አምላክ የሰጣቸው እነዚህ ተስፋዎች በጥቅሉ ለሰው ልጆች ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ለአንተ እንደተሰጡ አድርገህ አስብ። |
ብዙ ሰዎች ለመዝናናት ብለው የሚያዩአቸው ወይም የሚፈጽሟቸው ነገሮች መጽሐፍ ቅዱስ ዓመፅ፣ የፆታ ብልግና፣ መናፍስትነት ወይም ርኩሰት እንደሆኑ የሚገልጻቸው ድርጊቶች ናቸው። |
ለምሳሌ ኢንተርኔት፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች፣ ፊልሞች፣ ልብ ወለድ መጻሕፍትና መጽሔቶች ዓመፅንና የፆታ ብልግናን እንደ መልካም ነገር አድርገው ያቀርባሉ። |
በአንድ ወቅት ተቀባይነት እንደሌላቸው የሚታዩ ድርጊቶች በአሁኑ ጊዜ ተቀባይነት ከማግኘትም አልፈው በአንዳንድ አገሮች ሕጋዊ ሆነዋል። |
ይህ መሆኑ ግን እነዚህ ድርጊቶች በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ አያደርግም። |
በመጀመሪያው መቶ ዘመን የኖሩ የኢየሱስ ተከታዮች ርኩስ ከሆነ መዝናኛ ይርቁ ነበር። |
እንዲህ በማድረጋቸውና አምላካዊ ባሕርያትን በማንጸባረቃቸው መጥፎ ስም ይሰጣቸው እንዲሁም ስደት ይደርስባቸው ነበር። |
ሐዋርያው ጴጥሮስ ለክርስቲያኖች ሲጽፍ እንዲህ ብሏል፦ ይህን በመሰለው ያዘቀጠ ወራዳ ሕይወት ከእነሱ ጋር መሮጣችሁን ስለማትቀጥሉ ግራ ይጋባሉ፤ በመሆኑም ይሰድቧችኋል። |
አንዳንዶች፣ የፈለግነውን ውሳኔ ብናደርግ ምንም ለውጥ አያመጣም የሚል አመለካከት አላቸው። |
ይሁንና ይሖዋን የሚያስደስትና ጥበብ የተንጸባረቀበት ውሳኔ ለማድረግ ይሖዋ ባስጻፈው በቃሉ ውስጥ የሚገኙትን ሕጎችና መሠረታዊ ሥርዓቶች መመርመር ብሎም ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል። |
ለምሳሌ ያህል፣ የአምላክን ሞገስ ለማግኘት ደምን አስመልክቶ የሰጠውን ሕግ ተግባራዊ ማድረግ አለብን። |
ጸሎት፣ በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ከሚገኙ መሠረታዊ ሥርዓቶችና ሕጎች ጋር የሚስማማ ውሳኔ እንድናደርግ ይረዳናል። |
በሕይወታችን ውስጥ የምናደርጋቸው ከበድ ያሉ ውሳኔዎች በመንፈሳዊ ጤንነታችን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። |
የምናደርገው እያንዳንዱ ውሳኔ ከይሖዋ ጋር ባለን ግንኙነት ላይ ጥሩ ወይም መጥፎ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። |
ጥሩ ውሳኔ ማድረግ ከአምላክ ጋር ያለንን ዝምድና እንደሚያጠናክረው ሁሉ መጥፎ ውሳኔ ማድረግም ከይሖዋ ጋር ያለንን ዝምድና ያበላሸዋል። |
በተጨማሪም መጥፎ ውሳኔ ማድረጋችን ሌሎች እንዲረበሹ አልፎ ተርፎም እንዲሰናከሉ በማድረግ እምነታቸውን ሊያናጋው ይችላል፤ አሊያም ደግሞ የጉባኤውን ሰላም ያደፈርሰዋል። |
በእርግጥም የምናደርጋቸው ውሳኔዎች ለውጥ ያመጣሉ። |
የስብከቱን ሥራ ስናከናውን ሰዎች የተለያየ ምላሽ ይሰጡናል፤ አንዳንዶች ይቀበሉናል፤ ሌሎች ደግሞ ይቃወሙናል። |
ሰዎች የሚሰጡት ምላሽ ምንም ይሁን ምን የይሖዋ አገልጋዮች ምንጊዜም ሊኖራቸው የሚገባውን አቋም የአምላክ ቃል ይገልጻል። |
ስለ ተስፋችን፣ ምክንያት እንድናቀርብ ለሚጠይቀን ሰው መልስ የምንሰጠው በገርነት መንፈስና በጥልቅ አክብሮት ሊሆን ይገባል፤ ምክንያቱም ባልንጀራችንን እንወዳለን። |
የምናነጋግራቸው ሰዎች መልእክቱን ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ተቆጥተው ቢጮኹብንም እንኳ ለባልንጀራችን ፍቅር እንዳለን እናሳያለን። |
ኢየሱስ ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም። |
መከራ ሲደርስበት አልዛተም፤ ከዚህ ይልቅ በጽድቅ ለሚፈርደው ለይሖዋ ራሱን በአደራ ሰጥቷል፤ እኛም የኢየሱስን ምሳሌ እንከተላለን። |
ከእምነት ባልንጀሮቻችንም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ትሕትና በማሳየት የሚከተለውን ምክር ተግባራዊ እናደርጋለን፦ ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ አትመልሱ። |
ከዚህ ይልቅ ባርኩ። |
አንዳንዶች ለማንበብ፣ ለማሰላሰልና ለመጸለይ በማለዳ ይነሳሉ። |
ሌሎች በምሳ እረፍታቸው ወቅት እንዲህ ያደርጋሉ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.