text stringlengths 4 267 |
|---|
እኔ ግን እላችኋለሁ፣ አንዲትን ሴት በፍትወት ስሜት የሚመለከት ሁሉ በዚያን ጊዜ በልቡ ከእሷ ጋር አመንዝሯል። |
በመሆኑም ምንዝር ከመፈጸም መራቅ ብቻ ሳይሆን የፆታ ብልግና የመፈጸም ምኞትንም ማስወገድ ይኖርብናል። |
በሰማይ ያለው አባታችን ለሚጠይቁት መንፈስ ቅዱስን እንደሚሰጣቸው ኢየሱስ ቃል ገብቷል። |
የአምላክ መንፈስ ፍሬ ማለትም የአምላክ መንፈስ የሚያስገኛቸው መልካም ባሕርያት፣ ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ማንነት ያንጸባርቃሉ። |
የዚህን መንፈስ ፍሬ ስታፈራ ከሌሎች ጋር ያለህ ዝምድና ይሻሻላል። |
ይህ ደግሞ ጭንቀት ሊያስከትሉ የሚችሉ የተለያዩ ሁኔታዎችን ለማስቀረት ይረዳሃል። |
ከኃይለኛው የአምላክ እጅ በታች ራስህን ዝቅ ለማድረግም ሆነ የሚያስጨንቅህን ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ለመጣል ትሕትና እንደሚያስፈልግህ ግልጽ ነው። |
ትሕትና ካዳበርክ ደግሞ የአምላክን ሞገስና ድጋፍ ታገኛለህ። |
አካልህ፣ አእምሮህና ስሜትህ መቋቋም የሚችለው ነገር ውስን እንደሆነ ከተገነዘብክ በአምላክ ትታመናለህ፤ ይህም ከልክ በላይ እንዳትጨነቅ ይረዳሃል። |
እስራኤላውያን የይሖዋን መመሪያ በመከተል የማደሪያውን ድንኳን ሠርተዋል። |
ከጊዜ በኋላ ደግሞ ለይሖዋ አምልኮ ቤተ መቅደስ ገነቡ። |
አይሁዳውያን ከባቢሎን ግዞት ከተመለሱ በኋላ በምኩራቦች ውስጥ አዘውትረው ይሰበሰቡ ነበር። |
የጥንቶቹ ክርስቲያኖች ደግሞ በጉባኤ አባላት ቤት ውስጥ ይሰበሰቡ ነበር። |
በዛሬው ጊዜም የይሖዋ ሕዝቦች ከእሱ ለመማርና እሱን ለማምለክ በዓለም ዙሪያ በአሥር ሺዎች በሚቆጠሩ የመንግሥት አዳራሾች ውስጥ ይሰበሰባሉ። |
ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ለነበረው የይሖዋ ቤተ መቅደስ ታላቅ ፍቅር ያለው ከመሆኑም ሌላ በጣም ከፍ አድርጎ ይመለከተው ነበር፤ በመሆኑም አንድ የወንጌል ጸሐፊ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለው ትንቢት በኢየሱስ ላይ እንደተፈጸመ ገልጿል። |
እርግጥ ነው፣ በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ ጋር በሚመጣጠን ደረጃ የይሖዋ ቤት ሊባል የሚችል አንድም የመንግሥት አዳራሽ የለም። |
ያም ቢሆን በዘመናችን ያሉትን የአምልኮ ቦታዎች እንዴት ልንጠቀምባቸው እንደሚገባና ለእነዚህ ቦታዎች ሊኖረን የሚገባውን አክብሮት የሚያሳዩ መሠረታዊ ሥርዓቶችን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እናገኛለን። |
ገበያ ወጥተህ የበሰሉ ፍራፍሬዎችን ስታማርጥ ሁሉም ፍራፍሬዎች አንድ ዓይነት እንዳልሆኑ ማስተዋልህ አይቀርም። |
ያም ሆኖ ሁሉም መብሰላቸው የሚታወቅበት መንገድ አለ። |
በተመሳሳይም የጎለመሱ ክርስቲያኖች በብሔር፣ በአስተዳደግ፣ በአካላዊ ጤንነት፣ በዕድሜና በልምድ ሊለያዩ ይችላሉ። |
አልፎ ተርፎም የባሕርይ ወይም የባሕል ልዩነት አላቸው። |
ይሁንና በመንፈሳዊ እድገት የሚያደርጉ ሁሉ የጎለመሱ መሆናቸውን የሚያሳዩ ባሕርያትን ያንጸባርቃሉ። |
እንዴት? |
አንድ የጎለመሰ የይሖዋ አገልጋይ በአኗኗሩ ኢየሱስን ለመምሰልና የእሱን ፈለግ በጥብቅ ለመከተል ጥረት ያደርጋል። |
ኢየሱስ ይበልጥ አስፈላጊ እንደሆነ አድርጎ የገለጸው ነገር ምንድን ነው? |
ይሖዋን በሙሉ ልብ፣ ነፍስና አእምሮ መውደድ እንዲሁም ባልንጀራን እንደ ራስ መውደድ ነው። |
አንድ የጎለመሰ ክርስቲያን ይህን ምክር ተግባራዊ ለማድረግ ይጥራል። |
አኗኗሩ ከይሖዋ ጋር ለመሠረተው ዝምድና ቅድሚያ እንደሚሰጥና ለሌሎች የራስን ጥቅም መሥዋዕት የሚያደርግ ፍቅር እንዳለው ያሳያል። |
ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ሐዋርያቱ በዛሬው የዕለት ጥቅስ ላይ ያለውን ጥያቄ ጠየቁት። |
ኢየሱስ የሰጣቸው መልስ፣ የአምላክ መንግሥት መግዛት የሚጀመርበትን ወቅት የሚያውቁበት ጊዜ እንዳልደረሰ የሚያሳይ ነው። |
ደቀ መዛሙርቱ ሊያከናውኑት በሚገባው አስፈላጊ ሥራ ይኸውም በስብከቱ ተልእኮ ላይ እንዲያተኩሩ ነገራቸው። |
ያም ቢሆን ኢየሱስ፣ የአምላክ መንግሥት የሚመጣበትን ጊዜ በጉጉት እንዲጠባበቁ ተከታዮቹን አስተምሯቸዋል። |
በመሆኑም ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ክርስቲያኖች ይህ መንግሥት እንዲመጣ ሲጸልዩ ኖረዋል። |
ኢየሱስ የሚያስተዳድረው የአምላክ መንግሥት ከሰማይ ሆኖ መግዛት የሚጀምርበት ጊዜ ሲደርስ፣ ይሖዋ ነገሮች የሚከናወኑበትን ጊዜ እንዲያውቁ ሕዝቡን ረድቷቸዋል። |
በ1876 ቻርልስ ቴዝ ራስል የጻፈው አንድ ርዕስ ባይብል ኤግዛሚነር በተባለ መጽሔት ላይ ወጥቶ ነበር። |
የአሕዛብ ዘመናት የሚያበቁት መቼ ነው? |
የሚል ጭብጥ ያለው ይህ ርዕስ 1914 ልዩ ዓመት መሆኑን ጠቁሞ ነበር። |
በዳንኤል ትንቢት ላይ የተገለጹት ሰባት ዘመናት ኢየሱስ ከጠቀሳቸው የተወሰኑት የአሕዛብ ዘመናት ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በዚህ ርዕስ ላይ ተብራርቷል። |
ከጥንት ዘመን ጀምሮ የይሖዋ አገልጋዮች በመንፈስ መሪነት የተነገሩ ትንቢቶችን ፍጻሜ ለማየት ይጠባበቁ ነበር። |
ኢሳይያስ፣ ይሁዳ ባድማ ከሆነች በኋላ ይሖዋ ሕዝቡን ቀድሞ ወደነበሩበት ሁኔታ እንደሚመልስ ትንቢት ሲናገር እሱን በተስፋ የሚጠባበቁ ሁሉ ደስተኞች ናቸው ብሏል። |
ጥንት ስለነበሩት የአምላክ ሕዝቦች ትንቢት የተናገረው ሚክያስም ይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ በማለት የራሱን አቋም ገልጿል። |
የአምላክ አገልጋዮች ስለ መሲሑ ወይም ስለ ክርስቶስ የተነገሩ ትንቢቶችን ፍጻሜም ለዘመናት በተስፋ ሲጠባበቁ ቆይተዋል። |
ከመሲሑ ጋር የተያያዙ ትንቢቶች አሁንም እየተፈጸሙ በመሆናቸው በዛሬው ጊዜ ያሉ የአምላክ ሕዝቦችም የእነዚህን ትንቢቶች ፍጻሜ ለማየት በተስፋ ይጠባበቃሉ። |
በቅርቡ ይሖዋ በመሲሐዊው መንግሥት አማካኝነት ክፉዎችን በማጥፋት የሰው ልጆችን መከራ ያስወግዳል፤ እንዲሁም በሰይጣን ቁጥጥር ሥር ካለው ከዚህ ያልተረጋጋ ዓለም ሕዝቡን ነፃ ያወጣል። |
በመሆኑም የዚህ ሥርዓት ፍጻሜ በፍጥነት እየተቃረበ እንደሆነ በመገንዘብ ምንጊዜም ንቁ ሆነን እንጠብቅ። |
ምሥራቹን ለሰዎች መስበክ ትሕትናን እንዲሁም የአምላክ መንፈስ ፍሬ ገጽታዎችን ማዳበር እንድንችል ይረዳናል። |
ከዚህም ሌላ የክርስቶስ ዓይነት ባሕርያት ስናንጸባርቅ መልእክታችንን እናስውባለን፤ ይህ ደግሞ የአንዳንድ ሰዎች አመለካከት እንዲለወጥ ሊያደርግ ይችላል። |
ለምሳሌ በአውስትራሊያ ሁለት የይሖዋ ምሥክሮች፣ ለአንዲት ሴት ሊመሠክሩላት ሲሉ ሥርዓት የጎደለው ምላሽ ሰጠቻቸው፤ እነሱ ግን ስትናገር በአክብሮት አዳመጧት። |
ይሁንና በኋላ ላይ ሴትየዋ በድርጊቷ ስለተጸጸተች ለቅርንጫፍ ቢሮው ደብዳቤ ጻፈች። |
ደብዳቤው በከፊል እንዲህ ይላል፦ እነዚያን በጣም ታጋሽና ትሑት ሰዎች፣ ራሴን በማመጻደቅና እነሱን ዝቅ በማድረግ ስላናገርኳቸው ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ። |
የአምላክን ቃል የሚናገሩ ሰዎችን በዚያ መንገድ ማባረሬ ሞኝነት እንደሆነ ተሰምቶኛል። |
አስፋፊዎቹ በትንሹም እንኳ እንደተናደዱ የሚያሳይ ነገር አድርገው ቢሆን ኖሮ ሴትየዋ እንዲህ ዓይነት ደብዳቤ ትጽፍ ነበር? |
ላትጽፍ ትችላለች። |
ይህ በትክክለኛው ጊዜ የተሰጠ ጠቃሚ ምክር ነበር። |
ይሖዋ ለቃየን ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጠው አደገኛ የሆነ አካሄድ እየተከተለ እንደሆነ ስለተገነዘበ ነው። |
የሚያሳዝነው ግን ቃየን የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ሳይቀበል ቀረ፤ ይህም ለከባድ ችግር ዳርጎታል። |
የኤርምያስ ጸሐፊ የነበረው ባሮክ በተሰላቸና ደስታ በራቀው ጊዜ ይሖዋ የችግሩ መንስኤ ምን እንደሆነ እንዲያስተውል ምክር ሰጥቶታል። |
ከቃየን በተቃራኒ ባሮክ ይሖዋ የሰጠውን ምክር በመቀበሉ ሕይወቱን ማትረፍ ችሏል። |
ጳውሎስ፣ ይሖዋ የሚወዳቸውን ይገሥጻልና፤ እንዲያውም እንደ ልጁ አድርጎ የሚቀበለውን ሁሉ ይቀጣል ሲል ጽፏል። |
ይሁንና ተግሣጽ ሁልጊዜ ቅጣትን ብቻ የሚያመለክት አይደለም። |
በተለያዩ መንገዶች ሊሰጥ ይችላል። |
በርካታ የአምላክ ታማኝ አገልጋዮች ከባድ ፈተና እንደደረሰባቸው የሚገልጹ ዘገባዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰው እናገኛለን፤ አንዳንዶቹ ፈተናዎች ተግሣጽንና ሥልጠናን ያካተቱ ናቸው። |
ታማኝ የሆኑ ሰዎች በዚያ ወቅት ይሸለማሉ፤ ታማኝ ያልሆኑት ደግሞ ይቀጣሉ። |
በማቴዎስ ዘገባ ላይ እንደተገለጸው ኢየሱስ የተለያዩ ገጽታዎች ስላሉት ምልክት በተናገረው ሐሳብ መደምደሚያ ላይ የበጎቹንና የፍየሎቹን ምሳሌ ተናግሯል፤ እንዲህ ብሏል፦ የሰው ልጅ ከመላእክቱ ሁሉ ጋር በክብሩ ሲመጣ በክብራማ ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል። |
ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛ በጎቹን ከፍየሎቹ እንደሚለይ ሁሉ እሱም ሰዎችን አንዱን ከሌላው ይለያል። |
በጎቹን በቀኙ፣ ፍየሎቹን ግን በግራው ያደርጋቸዋል። |
በጎቹና ፍየሎቹ ምን ዓይነት ፍርድ ይሰጣቸዋል? |
ኢየሱስ ምሳሌውን የደመደመው ፍየሎቹ ወደ ዘላለም ጥፋት ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ በማለት ነው። |
ለይሖዋ ያለንን ፍቅር የምናሳይባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። |
ለምሳሌ ያህል፣ በመንግሥቱ የስብከት ሥራ በቅንዓት በመካፈል ለአምላክና ለሰዎች ፍቅር እንዳለን ማሳየት እንችላለን። |
የእምነት ፈተናዎች ሲያጋጥሙን ንጹሕ አቋማችንን ከጠበቅን ለይሖዋ እውነተኛ ፍቅር እንዳለን እናሳያለን። |
የሚያጋጥሙን ፈተናዎች ከባድ በሚሆኑበት ጊዜም እንኳ አምላክ ሥቃያችንን እንደሚያውቅ እንዲሁም እንደሚደግፈን እርግጠኞች መሆን እንችላለን፤ ምክንያቱም በእሱ ፊት ውድ ነን። |
ለይሖዋ ያለን ፍቅር በፍጥረት ሥራዎቹ ላይ እንድናሰላስል እንዲሁም ስላደረጋቸው ሌሎች ድንቅ ነገሮች እንድናስብ ይገፋፋናል። |
መጽሐፍ ቅዱስን በትጋት በማጥናት አምላክን እንደምንወደው እንዲሁም ለቃሉ የላቀ አክብሮት እንዳለን እናሳያለን። |
ለይሖዋ ያለን ፍቅር ይበልጥ በጸሎት እንድንቀርበው ያነሳሳናል። |
በተጨማሪም አምላክ ለኃጢአታችን ማስተሰረያ እንዲሆን ባደረገው የቤዛ ዝግጅት ላይ ስናሰላስል ለእሱ ያለን ፍቅር የበለጠ ይጨምራል። |
ይሖዋ ጽኑ ፍቅር ስላሳየን እኛም በምላሹ እሱን እንድንወደው ከሚያደርጉን ብዙ ምክንያቶች መካከል እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው። |
ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን ያሉ ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ እድገት ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ጽፎላቸዋል። |
በእምነትና ስለ አምላክ ልጅ ትክክለኛ እውቀት በመቅሰም ወደሚገኘው አንድነት እንዲሁም ሙሉ ሰው ወደ መሆን ይኸውም እንደ ክርስቶስ የተሟላ የጉልምስና ደረጃ ላይ ለመድረስ እንዲጣጣሩ አበረታቷቸዋል። |
ጳውሎስ ደብዳቤውን በጻፈበት ወቅት የኤፌሶን ጉባኤ ከተቋቋመ የተወሰኑ ዓመታት አልፈው ነበር። |
በዚያ የሚገኙ በርካታ ደቀ መዛሙርት ከፍ ያለ መንፈሳዊ የእድገት ደረጃ ላይ ደርሰው ነበር። |
አንዳንዶቹ ግን አሁንም ወደ ጉልምስና ደረጃ ላይ ለመድረስ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋቸው ነበር። |
በዛሬው ጊዜ በይሖዋ ምሥክሮች መካከል ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነው። |
ብዙዎቹ ወንድሞችና እህቶች አምላክን ረዘም ላሉ ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩና በመንፈሳዊ የጎለመሱ ናቸው። |
ሆኖም ሁሉም የጉልምስና ደረጃ ላይ ደርሰዋል ማለት አይደለም። |
ለምሳሌ ያህል፣ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ሰዎች ይጠመቃሉ፤ እነዚህ ሰዎች ደግሞ መንፈሳዊ ጉልምስና ላይ ለመድረስ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። |
አንተስ እድገት ማድረግ ያስፈልግህ ይሆን?—፤ |
ረሃቡ በምድሪቱ ላይ በርትቶ ነበር። |
ስለሆነም ከግብፅ ያመጡትን እህል በልተው ሲጨርሱ አባታቸው “ተመልሳችሁ ሂዱና ጥቂት እህል ግዙልን” አላቸው። |
በዚህ ጊዜ ይሁዳ እንዲህ አለው፦ “ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁት ካልመጣችሁ በምንም ዓይነት ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ በማለት በግልጽ አስጠንቅቆናል። |
ወንድማችንን ከእኛ ጋር የምትልከው ከሆነ ወደዚያ ወርደን እህል እንገዛልሃለን። |
እሱን የማትልከው ከሆነ ግን ወደዚያ አንወርድም፤ ምክንያቱም ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁት ካልመጣችሁ በምንም ዓይነት ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎናል።” |
እስራኤልም “ምነው እንዲህ ላለ ችግር ዳረጋችሁኝ? ሌላ ወንድም እንዳላችሁ ለምን ለሰውየው ነገራችሁት?” አላቸው። |
እነሱም እንዲህ አሉት፦ “ሰውየው ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ?’ በማለት በቀጥታ ስለ እኛና ስለ ዘመዶቻችን ጠየቀን፤ እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው። ታዲያ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ኑ’ ይለናል ብለን እንዴት ልንጠረጥር እንችላለን?” |
ከዚያም ይሁዳ አባቱን እስራኤልን እንዲህ በማለት ለመነው፦ “እኛም ሆን አንተ እንዲሁም ትናንሽ ልጆቻችን በረሃብ ከምናልቅ፣ በሕይወት እንድንተርፍ ልጁ ከእኔ ጋር እንዲሄድ ፍቀድና ተነስተን ወደዚያ እንሂድ። |
የልጁን ደህንነት በተመለከተ ኃላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ። አንድ ነገር ቢሆን እኔን ተጠያቂ ልታደርገኝ ትችላለህ። ልጁን ወደ አንተ መልሼ ባላመጣውና ባላስረክብህ በሕይወቴ ሙሉ በፊትህ በደለኛ ልሁን። |
ዝም ብለን ጊዜ ባናጠፋ ኖሮ እስካሁን ሁለት ጊዜ እዚያ ደርሰን በተመለስን ነበር።” |
በመሆኑም አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፦ “እንግዲህ ሌላ አማራጭ ከጠፋ እንዲህ አድርጉ፦ ምድሪቱ ከምታፈራቸው ምርጥ ነገሮች መካከል ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ጥሩ መዓዛ ያለው ሙጫ፣ ከርቤ፣ ለውዝና አልሞንድ ለሰውየው ስጦታ እንዲሆን በከረጢቶቻችሁ ይዛችሁ ውረዱ። |
በተጨማሪም እጥፍ ገንዘብ ያዙ፤ በከረጢቶቻችሁ አፍ ላይ ተደርጎ የተመለሰላችሁንም ገንዘብ ይዛችሁ ሂዱ። ምናልባት በስህተት የመጣ ሊሆን ይችላል። |
በሉ ተነሱና ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደ ሰውየው ሂዱ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.