text stringlengths 4 267 |
|---|
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ይህ ቁጥር እየጨመረ ነው። |
ታዲያ ቁጥሩ መጨመሩ ሊያሳስበን ይገባል? |
አይገባም። |
በዚህ ረገድ በአእምሯችን ልንይዛቸው የሚገቡ አንዳንድ ነጥቦችን ከዚህ ቀጥሎ እንመለከታለን። |
በመታሰቢያው በዓል ላይ ከቂጣውና ከወይን ጠጁ የሚወስዱ ሰዎችን የሚቆጥሩት ወንድሞች፣ በእርግጥ ሰማያዊ ተስፋ ያለው ማን እንደሆነ ማወቅ አይችሉም። |
ከቂጣውና ከወይን ጠጁ የሚወስዱት ሰዎች ቁጥር፣ ቅቡዓን ነን ብለው በስህተት የሚያስቡ ሰዎችንም ይጨምራል። |
በአንድ ወቅት ከቂጣውና ከወይን ጠጁ ይወስዱ የነበሩ አንዳንዶች ከጊዜ በኋላ አቁመዋል። |
ሌሎች ደግሞ ከክርስቶስ ጋር በሰማይ እንደሚገዙ አድርገው የሚያስቡት ከአእምሮ ወይም ከስሜት ጋር የተያያዘ ችግር ስላለባቸው ሊሆን ይችላል። |
ስለሆነም በመታሰቢያው በዓል ላይ ከቂጣውና ከወይን ጠጁ የሚወስዱ ሰዎች ቁጥር፣ በምድር ላይ የቀሩትን ቅቡዓን ትክክለኛ ቁጥር አያመለክትም። |
በተጨማሪም ታላቁ መከራ ሲጀምር በምድር ላይ ምን ያህል ቅቡዓን እንደሚኖሩ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ነገር የለም። |
ኢየሱስ በቃልም ሆነ በተግባር የደቀ መዛሙርቱን እምነት ገንብቷል። |
እኛም የእሱን ምሳሌ መከተል ይኖርብናል፤ ምክንያቱም ሌሎች እምነታቸውን እንዲያጠናክሩ ስንረዳ የእኛም እምነት ይጠናከራል። |
በምትሰብኩበትና በምታስተምሩበት ጊዜ አምላክ መኖሩን፣ ለእኛ የሚያስብ መሆኑን እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ መሪነት የተጻፈ ቃሉ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ጎላ አድርጋችሁ ጥቀሱ። |
በተጨማሪም ወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ እምነታቸውን እንዲያጠናክሩ እርዷቸው። |
የጥርጣሬ መንፈስ ቢታይባቸው፣ ምናልባትም በተሾሙ ወንድሞች ላይ ማጉረምረም ቢጀምሩ ከእነሱ ለመራቅ አትቸኩሉ። |
ከዚህ ይልቅ እምነታቸውን መልሰው እንዲያጠናክሩ የሚያስችሏቸውን እርምጃዎች እንዲወስዱ በዘዴ እርዷቸው። |
ተማሪ ከሆንክ ስለ ዝግመተ ለውጥ ጽንሰ ሐሳብ ትምህርት በሚሰጥበት ጊዜ ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ስለመሆኑ ያለህን እምነት በድፍረት ተናገር፤ ይህም ሌሎች ጥሩ ምላሽ እንዲሰጡ ሊያደርግ ይችላል። |
ይሖዋ በእምነት ጸንተን እንድንቆም ሁላችንንም ይረዳናል። |
እምነታችንን ለመገንባት የምናደርገው ጥረት የሚያስቆጭ አይደለም፤ ምክንያቱም እምነት የሚያስገኘው ወሮታ የሚተካከለው ነገር የለም። |
ሳሙኤል የሕዝቡን ጥያቄ ለመፈጸም አመንትቶ ስለነበር ይሖዋ ሕዝቡን እንዲሰማ ሦስት ጊዜ ደጋግሞ ነግሮታል። |
ያም ቢሆን ሳሙኤል እሱን በሚተካው ሰው ላይ ጥላቻ ወይም ቅሬታ እንዲያድርበት አልፈቀደም። |
ይሖዋ ሳኦልን እንዲቀባ ሲነግረው ታዟል፤ ይህን ያደረገው ግዴታ ስለሆነበት ሳይሆን በፍቅር ተነሳስቶና ደስ እያለው ነበር። |
በዛሬው ጊዜ ያሉ ሽማግሌዎችም ለሚያሠለጥኗቸው ወንድሞች ልክ እንደ ሳሙኤል ጥሩ መንፈስ ማሳየት አለባቸው። |
እንዲህ ያሉ ሽማግሌዎች በጉባኤ ውስጥ ያሏቸውን አንዳንድ መብቶች ተማሪዎቹ ሊወስዱባቸው እንደሚችሉ በመፍራት እነሱን ከማሠልጠን ወደኋላ አይሉም። |
ደጎችና ሌሎችን በደስታ የሚረዱ አስተማሪዎች፣ ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ ተማሪዎችን የሚመለከቷቸው እንደ ተቀናቃኝ ሳይሆን ከእነሱ ጋር አብረው እንደሚሠሩና ለጉባኤው ውድ ስጦታ እንደሆኑ አድርገው ነው። |
ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ ስሜት ሌሎችን የሚያሠለጥኑ እንዲህ ያሉ አስተማሪዎች፣ ተማሪዎቹ ችሎታቸውን ተጠቅመው ጉባኤውን ሲያገለግሉ ማየታቸው ልዩ የእርካታ ስሜት እንደሚፈጥርላቸው ግልጽ ነው!—፤ |
የአምላክ መንግሥት ንጉሥ የሆነው ኢየሱስ የእባቡን ራስ ይጨፈልቃል፤ እንዲሁም ሰይጣን ያስነሳው ዓመፅ ያስከተላቸውን ችግሮች በሙሉ ያስወግዳል። |
ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት፣ ደቀ መዛሙርቱ የአምላክ መንግሥት ምን ያህል ትልቅ ቦታ እንዳለው እንዲገነዘቡ ረድቷቸዋል። |
ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ ወዲያውኑ የአምላክን መንግሥት ምሥራች በስፋት ማወጅ ጀምሯል። |
ወደ ሰማይ ከመመለሱ በፊት ደቀ መዛሙርቱን ለመጨረሻ ጊዜ ባነጋገራቸው ወቅት እስከ ምድር ዳር ድረስ ምሥክሮቹ እንዲሆኑ አዟቸዋል። |
በመላው ምድር የሚኖሩ ሰዎች ስለ አምላክ መንግሥት በሚገልጸው የስብከት ሥራ አማካኝነት ስለ ቤዛው መማርና የአምላክ መንግሥት ተገዢዎች መሆን የሚችሉበት አጋጣሚ ያገኛሉ። |
በዛሬው ጊዜ የመንግሥቱን ምሥራች በዓለም ዙሪያ እንድንሰብክ የተሰጠንን ተልዕኮ በመወጣት በምድር ያሉትን የክርስቶስ ወንድሞች ስንረዳ መንግሥቱን እንደምንደግፍ እናሳያለን። |
በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ማሰላሰል አንድ ሰው ወደ መንፈሳዊ ጉልምስና እንዲደርስ ይረዳዋል። |
ስለ ይሖዋና ስለ ኢየሱስ ለማሰላሰል በቂ ጊዜ የማይሰጥ ሰው ጠንካራ እምነት ሊኖረው አይችልም። |
እንዲህ ዓይነቱ ሰው ቀስ በቀስ የመወሰድ ወይም ከእውነት የመራቅ አደጋ ተደቅኖበታል። |
ኢየሱስ የአምላክን ቃል በመልካምና በጥሩ ልብ የማንሰማ ወይም የማንቀበል ከሆነ ቃሉን በውስጣችን ማኖር እንደማንችል ተናግሯል። |
ከዚህ ይልቅ የዚህ ዓለም የኑሮ ጭንቀት፣ ሀብትና ሥጋዊ ደስታ ትኩረታችንን ሊከፋፍልብንና ለፍሬ እንዳንበቃ ሊያደርገን ይችላል። |
በመሆኑም በአምላክ ቃል ላይ ዘወትር እናሰላስል። |
ይህ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተገለጸውን የይሖዋን ክብርና ባሕርይ ለማንጸባረቅ ያነሳሳናል። |
ደግሞስ ከዚህ የበለጠ ምን እንፈልጋለን? |
በአምላክ እውቀት ማደግና የእሱን ክብር ማንጸባረቅ መቻል ግሩም መብት ከመሆኑም ሌላ በሰማይ የሚኖረውን አፍቃሪ አባታችንን እንዴት መምሰል እንደምንችል በተማርን መጠን ክብሩን ማንጸባረቃችንን እንቀጥላለን። |
መናገር፣ የዕለት ተዕለት ሕይወታችን ክፍል ቢሆንም ሁልጊዜ ማውራት አለብን ማለት አይደለም። |
እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ ዝም ለማለት ጊዜ አለው ይላል። |
ሌሎች ሲናገሩ ዝም ማለት አክብሮት እንዳለን ያሳያል። |
ሚስጥር ከሆኑ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ አንደበታችንን በመቆጣጠር ዝም ማለታችን ደግሞ የማስተዋልና የማመዛዘን ችሎታ እንዳለን ይጠቁማል። |
የሚያስቆጣ ነገር ሲያጋጥመን አንደበታችንን መግታትም የጥበብ እርምጃ ነው። |
በሌላ በኩል ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ለመናገርም ጊዜ አለው ይላል። |
አንድ ጓደኛህ የሚያምር ስጦታ ቢሰጥህ ማንም የማያየው ቦታ አታስቀምጠውም። |
ከዚህ ይልቅ በስጦታው በተገቢው መንገድ በመጠቀም አድናቆትህን ታሳያለህ። |
በተመሳሳይም ከይሖዋ ባገኘነው የመናገር ስጦታ በጥበብ በመጠቀም አመስጋኝነታችንን እናሳያለን። |
ይህም ስሜታችንን መግለጽን፣ የሚያስፈልገንን ነገር መናገርን፣ ሌሎችን ማበረታታትንና አምላክን ማወደስን ሊጨምር ይችላል። |
ክርስትና እየተስፋፋ ሲሄድ ክርስቲያኖች በአብዛኛው የሚነጋገሩት በግሪክኛ ነበር። |
እንዲያውም ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ፣ ኢየሱስ ያስተማረውንና ያደረገውን ነገር በተመለከተ በመንፈስ መሪነት ያሰፈሯቸው የወንጌል ዘገባዎች በስፋት የተሰራጩት በግሪክኛ ነው። |
በመሆኑም አብዛኞቹ ደቀ መዛሙርት የሚጠቀሙት በዕብራይስጥ ሳይሆን በግሪክኛ ነበር። |
ሐዋርያው ጳውሎስ የጻፋቸው ደብዳቤዎችና በመንፈስ መሪነት የተጻፉ ሌሎች መጻሕፍትም የተሰራጩት በግሪክኛ ነው። |
የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ጸሐፊዎች፣ ከዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ሲጠቅሱ በአብዛኛው የሚጠቀሙት ሰብዓ ሊቃናትን መሆኑ ትኩረት የሚስብ ነው። |
ከዕብራይስጡ ጽሑፍ በተወሰነ መጠን የሚለዩት እነዚህ ጥቅሶች በአሁኑ ጊዜ፣ በመንፈስ መሪነት የተጻፉት ቅዱሳን መጻሕፍት ክፍል ሆነዋል። |
በመሆኑም ፍጹም ያልሆኑ ሰዎች የትርጉም ሥራ በመንፈስ መሪነት የተጻፈው የአምላክ ቃል ክፍል ሆነ፤ ይህም አምላክ አንዱን ባሕል ወይም ቋንቋ ከሌላው እንደማያበላልጥ ያሳያል። |
አምላክ ከማንኛውም ዝግጅት ጋር በተያያዘ የራስነት ሥርዓት እንዲኖር አድርጓል፤ በዚህም የተነሳ ፍቅር በጣም አስፈላጊ ነው። |
ያም ሆኖ የራስነት ሥልጣን አምባገነናዊ በሆነ መንገድ ሊሠራበት አይገባም። |
ባል የሚስቱ ራስ ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስ ሚስቱን እንዲያከብራት ያዛል። |
ባሎች ለሚስቶቻቸው አክብሮት ማሳየት ከሚችሉባቸው መንገዶች አንዱ፣ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ግምት ውስጥ ማስገባትና በአንዳንድ ጉዳዮች ረገድ የእነሱን ምርጫ ማስቀደም ነው። |
ደግሞም የአምላክ ቃል እንዲህ ይላል፦ ባሎች ሆይ፣ ክርስቶስ ጉባኤውን እንደወደደና ራሱን ለጉባኤው አሳልፎ እንደሰጠ ሁሉ እናንተም ሚስቶቻችሁን መውደዳችሁን ቀጥሉ። |
ኢየሱስ ለተከታዮቹ ሕይወቱን ሳይቀር ሰጥቷል። |
አንድ ባል እንደ ኢየሱስ የራስነት ሥልጣኑን በፍቅር የሚጠቀምበት ከሆነ ሚስቱ እሱን መውደድና ማክበር እንዲሁም ለእሱ መገዛት ይበልጥ ቀላል ይሆንላታል። |
ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆቻችሁ በመንፈሳዊ ጤናማ ሆነው እንዲቀጥሉ ትፈልጋላችሁ። |
አምላክም ልጆቻችሁን በይሖዋ ተግሣጽና ምክር እንድታሳድጓቸው ይፈልጋል። |
በመሆኑም አምላክ የሰጣችሁን ኃላፊነት ለመወጣት ቋሚ የሆነ መንፈሳዊ ፕሮግራም እንዲኖራችሁ አድርጉ። |
ነጥቡን በምሳሌ ለማስረዳት፣ ልጆቻችሁ ትምህርት መቅሰማቸው አስፈላጊ እንደሆነ ስለምታውቁና የመማር ፍቅር እንዲያዳብሩ ስለምትፈልጉ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ታደርጋላችሁ። |
በተመሳሳይም አፍቃሪ ወላጆች፣ ልጆቻቸው በጉባኤ ስብሰባዎችና በሌሎች መንፈሳዊ ፕሮግራሞች አማካኝነት ከሚቀርበው የይሖዋ ተግሣጽ እንዲጠቀሙ ጥረት ያደርጋሉ። |
መለኮታዊ ትምህርት በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ልጆቻችሁ ለመንፈሳዊ ነገሮች ፍቅር እንዲያድርባቸውና ጥበብን እንዲወዱ ለመርዳት ትጥራላችሁ። |
ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዳደረገው ሁሉ እናንተም በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆቻችሁ የአምላክን ቃል የማስተማር ፍቅር እንዲያድርባቸውና በመስክ አገልግሎት ዘወትር እንዲካፈሉ በማገዝ በአገልግሎታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ መርዳት ትችላላችሁ። |
በእጅ የተገለበጡ ጥንታዊ የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ቅጂዎችን ለምሳሌ የሙት ባሕር ጥቅልሎችን የሚያጠኑ ምሁራን፣ ቴትራግራማተን በእነዚህ ጽሑፎች ላይ በብዛት የሚገኝ መሆኑ አስገርሟቸዋል። |
መለኮታዊው ስም፣ በእነዚያ ጥንታዊ የዕብራይስጥ ቅጂዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ከሁለተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. እስከ አንደኛው መቶ ዘመን ዓ.ም. ባሉት ዓመታት ውስጥ በተገለበጡ አንዳንድ የግሪክኛው ሰብዓ ሊቃናት ቅጂዎች ላይም ይገኛል። |
የአምላክ የግል ስም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መግባት እንዳለበት ግልጽ ማስረጃ ቢኖርም በርካታ ተርጓሚዎች ቅዱስ የሆነውን መለኮታዊ ስም ከትርጉም ሥራዎቻቸው ውስጥ ሙሉ በሙሉ አውጥተውታል። |
በ1952 ሪቫይዝድ ስታንዳርድ ቨርዥን የተባለው ትርጉም ወጣ። |
ይህ ትርጉም በ1901 ከወጣው አሜሪካን ስታንዳርድ ቨርዥን ላይ ተሻሽሎ የተዘጋጀ ሲሆን የአሜሪካን ስታንዳርድ ቨርዥን አዘጋጆች የተከተሉትን ፖሊሲ በመሻር የአምላክን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አውጥቶታል። |
ለምን? |
መቅድሙ እንዲህ ይላል፦ አንድና ብቸኛ የሆነውን አምላክ በተጸውኦ ስም መጥራት ለዓለም አቀፉ የክርስትና እምነት ፈጽሞ ተገቢ አይደለም። |
ከዚያ በኋላ በእንግሊዝኛም ሆነ በሌሎች ቋንቋዎች የተዘጋጁ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህን አካሄድ ተከትለዋል። |
በወረስነው ኃጢአት የተነሳ ሁላችንም የሞት ቅጣት ይጠብቀናል። |
አፍቃሪ የሆነው ይሖዋ ግን ኢየሱስ ወደ ምድር እንዲመጣና ለሰው ሁሉ ሲል ሞትን እንዲቀምስ ዝግጅት አድርጓል። |
ይሖዋ ይህን በማድረጉ ከሞት የታደገን ከመሆኑም ባሻገር ለሞት መንስኤ የሆነውን ነገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የሚያስችለውን መሠረት ጥሏል። |
በኢየሱስ ላይ እምነት ያላቸው ሁሉ በክርስቶስ በሚመራው የአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር በምድር ላይ በሰላምና በደስታ ለዘላለም የሚኖሩ ሲሆን ቅቡዓኑ ደግሞ በዚህ መንግሥት ውስጥ ተባባሪ ገዢዎች ይሆናሉ። |
ይሖዋ የሰጠን ይህ ስጦታ የሚያስገኛቸው ሌሎች በረከቶችስ አሉ? |
ከይሖዋ ያገኘነው ስጦታ ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች መካከል ማንኛውም በሽታ ሙሉ በሙሉ መወገዱ፣ ምድራችን ወደ ገነትነት መለወጧ እንዲሁም የሞቱ ሰዎች መነሳታቸው ይገኙበታል። |
ይሖዋና ውድ ልጁ በቃላት ሊገለጽ የማይችል ነፃ ስጦታ ስለሰጡን እንደምንወዳቸው ጥያቄ የለውም። |
በዛሬው ጊዜ አንድ ክርስቲያን በመፈወስ ስጦታ ተጠቅሞ ከሕመማችን ሊያድነን አይችልም። |
ይሁንና አንዳንድ ወንድሞች ምክር ባንጠይቃቸውም እንኳ በአሳቢነት ተነሳስተው ከጤና ጋር የተያያዙ አስተያየቶችን ይሰጣሉ። |
በእርግጥ አንዳንዶች የሚሰጡት ሐሳብ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። |
ጢሞቴዎስ በአካባቢው ያለው ውኃ በመበከሉ የተነሳ ሳይሆን አይቀርም፣ ሆዱን ባመመው ጊዜ ጳውሎስ እንዲህ ዓይነት ምክር ሰጥቶታል። |
ይህ ግን የእምነት ባልንጀራችን፣ አንዳንድ ዕፀዋትን ወይም መድኃኒቶችን እንዲወስድ አሊያም አንድን የአመጋገብ ሥርዓት እንዲከተል ለማሳመን ከመሞከር በጣም የተለየ ነው፤ ምናልባትም ይህ ዓይነቱ ሕክምና ውጤታማ ላይሆን እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። |
አንዳንድ ጊዜ የጤና ምክር የሚሰጡ ሰዎች አንድ ዘመዴ እንዲህ ዓይነት ሕመም ነበረበት፤ ሲወስድ ግን ተሻለው እንደሚለው ዓይነት ሐሳብ ሲሰነዝሩ ይሰማል። |
ምክሩ የተሰጠው በአሳቢነት ሊሆን ይችላል፤ ያም ቢሆን በሰፊው የሚሠራበት መድኃኒትም ሆነ የሕክምና ዓይነት እንኳ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ማስታወስ ይኖርብናል። |
ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ለእስራኤል ብሔር የተሰጠው ሕግ በውስጡ ካካተታቸው መመሪያዎች ጥቅም ማግኘት እንችላለን። |
እንዴት? |
ከሕጉ በስተ ጀርባ ያሉትን መሠረታዊ ሥርዓቶች ቆም ብለን በመመርመር ነው። |
በእነዚህ ሕጎች ሥር ባንሆንም እንኳ አብዛኞቹ ከዕለት ተዕለት ሕይወታችንና ለቅዱሱ አምላካችን ለይሖዋ ከምናቀርበው አምልኮ ጋር በተያያዘ አስተማማኝ መመሪያ ይሰጡናል። |
አምላክ እነዚህ ሕጎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲጻፉ ያደረገው ትምህርት እንድንቀስምባቸውና ከክርስቲያኖች የሚጠበቀውን የላቀ የሥነ ምግባር ደረጃ መገንዘብ እንድንችል ነው። |
ኢየሱስ ምን እንዳለ ልብ በል፦ አታመንዝር እንደተባለ ሰምታችኋል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.