text
stringlengths
4
267
ሁላችንም ሽማግሌዎች የሚሰጡንን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ አለብን።
ጳውሎስ በጉባኤ ውስጥ ሥርዓት በጎደለው መንገድ የሚሄዱ ሰዎችን አስመልክቶ የሰጠውን ምክር እንመልከት።
አንዳንድ የጉባኤው አባላት በማይመለከታቸው ጉዳይ ጣልቃ ይገቡ ነበር።
በወቅቱ የነበሩት ሽማግሌዎች ለእነዚህ ክርስቲያኖች ምክር ሳይሰጧቸው አልቀሩም፤ ይሁንና እነዚህ ሰዎች ምክሩን ችላ ብለው በድርጊታቸው ቀጥለዋል።
ታዲያ ጉባኤው እንዲህ በሚያደርግ ግለሰብ ላይ ምን እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል?
ጳውሎስ ይህን ሰው ምልክት አድርጉበት፤ ከእሱ ጋር አትግጠሙ ብሏል።
ሆኖም ጳውሎስ፣ ግለሰቡን እንደ ጠላት እንዳይመለከቱት አስጠንቅቋቸዋል።
በዛሬው ጊዜም አንድ ሰው የጉባኤውን መልካም ስም የሚያጎድፍ ጎዳና መከተሉን ለማቆም ፈቃደኛ ባይሆን ለምሳሌ ከማያምን ሰው ጋር መጠናናቱን ቢቀጥል፣ ሽማግሌዎች ይህን በተመለከተ ለጉባኤው የማስጠንቀቂያ ንግግር እንዲቀርብ ሊያደርጉ ይችላሉ።
ታዲያ ሽማግሌዎች ለሚሰጡት ምክር ምን ምላሽ ትሰጣለህ?
በንግግሩ ላይ የተጠቀሰውን አካሄድ የሚከተለውን ግለሰብ የምታውቀው ከሆነ ከእሱ ጋር ባለህ ቅርርብ ላይ ገደብ ታበጃለህ?
በዚህ መንገድ ፍቅር ማሳየትህና ቁርጥ አቋም መውሰድህ፣ ሥርዓት በጎደለው መንገድ የሚሄደው ሰው አቋሙን እንዲያስተካክል ይረዳው ይሆናል።
ከሌላ አገር የመጡ ሰዎች ከሄዱበት አገር ባሕል ጋር ለመላመድ የተቻላቸውን ጥረት ማድረግ አባቸው።
በዚህ ረገድ ሩት ግሩም ምሳሌ ትሆናለች።
አንደኛ፣ ለመቃረም ፈቃድ በመጠየቅ፣ ለሄደችበት አገር ባሕል አክብሮት እንዳላት አሳይታለች።
መቃረም መብቷ እንደሆነ ወይም ደግሞ ሌሎች እሷን የመንከባከብ ግዴታ እንዳለባቸው አልተሰማትም።
ሁለተኛ፣ ለተደረገላት ደግነት አድናቆቷን ገልጻለች።
የሌላ አገር ዜጎች እንዲህ ያለ መልካም ባሕርይ ካላቸው፣ የአገሩ ነዋሪዎችም ሆኑ የእምነት ባልንጀሮቻቸው አክብሮት ያሳዩዋቸዋል።
ይሖዋ የተለያየ ባሕልና ዜግነት ያላቸው ሰዎች ምሥራቹን እንዲሰሙ አጋጣሚ በመክፈት ጸጋውን ስላሳየን በጣም ደስተኞች ነን።
አንዳንዶች በትውልድ አገራቸው መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናት ወይም ከይሖዋ ሕዝቦች ጋር በነፃነት የመሰብሰብ አጋጣሚ አላገኙ ይሆናል።
የአምላክ ሕዝቦች የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ተግባራዊ ለማድረግ ይጥራሉ፦ በምድር ያሉትን የአካል ክፍሎቻችሁን ግደሉ፤ እነሱም የፆታ ብልግና፣ ርኩሰት፣ ልቅ የሆነ የፍትወት ስሜት ናቸው።
የእምነት ባልንጀሮቻችን ይህን ምክር በተግባር ማዋል ከባድ እንዲሆንባቸው ማድረግ አንፈልግም።
ልቅ የፆታ ሥነ ምግባር የነበራቸውና እንዲህ ዓይነቱን ሕይወት የተዉ ወንድሞችና እህቶች የኃጢአት ዝንባሌዎች እንዳያሸንፏቸው መታገል ይኖርባቸው ይሆናል።
ታዲያ እኛ ትግሉ ከባድ እንዲሆንባቸው ማድረግ እንፈልጋለን?
ከመንፈሳዊ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር በምንሆንበት ጊዜ ለአለባበሳችን የምንጠነቀቅ ከሆነ ጉባኤው ከፍተኛ የሥነ ምግባር ደረጃ የሚጠብቁ ሰዎች ያሉበት ቦታ እንዲሆን አስተዋጽኦ እናደርጋለን።
እርግጥ የምንለብሰውን ነገር የመምረጥ ነፃነት አለን።
ያም ሆኖ ሁላችንም፣ ሌሎች በሥነ ምግባር ንጹሕ ሆነው መመላለስ እንዲሁም በአስተሳሰባቸው፣ በንግግራቸውና በድርጊታቸው የአምላክን የቅድስና መሥፈርቶች መጠበቅ ቀላል እንዲሆንላቸው የሚያደርግ አለባበስ የመምረጥ ኃላፊነት ተጥሎብናል።
ባል የሚስቱ ራስ መሆኑ፣ ሚስት የባሏ የበታች እንድትሆን አያደርጋትም።
እንዲያውም አምላክ ለሚስት ያሰበውን ድርሻ ለመወጣት ያስችላታል፤ አምላክ ሴትን ሲፈጥር አዳም ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለም።
ማሟያ የምትሆነውን ረዳት እሠራለታለሁ ብሎ ነበር።
የጉባኤ ራስ የሆነው ክርስቶስ ፍቅር እንደሚያሳይ ሁሉ አንድ ክርስቲያን ባልም የራስነት ሥልጣኑን በፍቅር ሊጠቀምበት ይገባል።
ባል እንዲህ ሲያደርግ ሚስቱ ከስጋት ነፃ ትሆናለች፤ እንዲሁም ባሏን ማክበር፣ እሱን መደገፍና ለእሱ መገዛት ያስደስታታል።
የኢየሱስ ተከታዮች እሱን መምሰል ከፈለጉ፣ እሱ እንደወደዳቸው እርስ በርሳቸው መዋደድ ይኖርባቸዋል።
በመሆኑም ክርስቲያን ባለትዳሮች፣ አስፈላጊ ከሆነ አንዳቸው ለሌላው ሕይወታቸውን እንኳ ለመስጠት የሚያነሳሳ ጠንካራ ፍቅር ማዳበር ይኖርባቸዋል።
ብዙ ሰዎች የሚጸልዩት፣ እንዲሁ የአእምሮ እረፍት ለማግኘት እንጂ አምላክ ጸሎታቸውን እንደሚሰማ ስለሚያምኑ አይደለም።
በመሆኑም ይሖዋ ጸሎት ሰሚ መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋቸዋል።
ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ማንኛውንም ነገር በስሜ ከለመናችሁ እኔ አደርገዋለሁ ብሏቸዋል።
ማንኛውንም ነገር ሲል ከይሖዋ ፈቃድ ጋር የሚስማማ ማንኛውንም ነገር ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው።
ዮሐንስ በእሱ ላይ ያለን ትምክህት ይህ ነው፤ የምንጠይቀው ነገር ምንም ይሁን ምን ከፈቃዱ ጋር በሚስማማ ሁኔታ እስከለመንን ድረስ ይሰማናል የሚል ማረጋገጫ ሰጥቶናል።
ጸሎት አእምሮን ከማረጋጋት ያለፈ ጥቅም እንዳለውና ወደ ይሖዋ የጸጋ ዙፋን ለመቅረብ የሚያስችል ግሩም መንገድ እንደሆነ ሌሎች እንዲያውቁ መርዳት ትልቅ ነገር ነው! ሰዎች በትክክለኛው መንገድ፣ ወደ ትክክለኛው አካል እንዲሁም ተገቢ ስለሆኑ ነገሮች እንዲጸልዩ ስናስተምራቸው ወደ ይሖዋ እንዲቀርቡና በተጨነቁበት ወቅት መጽናኛ እንዲያገኙ እንረዳቸዋለን።
እነዚህ ቃላት የሁሉንም ታማኝ የይሖዋ አገልጋዮች ስሜት በሚገባ ይገልጻሉ።
ነገር ግን ሕመም ወይም የዕድሜ መግፋት የምታቀርበውን አገልግሎት ቢገድቡብህስ?
ለሚንከባከቡህ ሰዎችና ለሌሎች ምሥራቹን ስትናገር የምታቀርበው ቅዱስ አገልግሎት ታላቁን አምላካችንን ከፍ ከፍ እንደሚያደርግ አትዘንጋ።
በእምነትህ ምክንያት ታስረህ ከሆነ ደግሞ ሁኔታዎች በፈቀዱልህ መጠን ስለ እውነት መመሥከርህ አይቀርም፤ ይህም የይሖዋን ልብ ያስደስተዋል።
በሃይማኖት በተከፋፈለ ቤተሰብ ውስጥ ሆነህ መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን አዘውትረህ ለማከናወን ጥረት ስታደርግም ይሖዋን ታስደስታለህ።
በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ብትሆንም እንኳ ይሖዋን ማወደስ እንዲሁም መንፈሳዊ እድገት ማድረግ ትችላለህ።
የአምላክን ውድ እውነትና እሱ የሰጠውን ተስፋ ለሰዎች ስታካፍል ይሖዋ እንደሚባርክህ ጥርጥር የለውም።
የይሖዋ አገልጋዮች፣ የአምላክ ቃል የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን ከፍ አድርገው ይመለከቱታል።
ሁላችንም ፍጽምና ስለሚጎድለን አልፎ አልፎ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክር ያስፈልገናል።
ታዲያ ምክር ሲሰጠን ምን እናደርጋለን?
በመጀመሪያው መቶ ዘመን የኖሩትን ኤዎድያን እና ሲንጤኪ የተባሉ ክርስቲያኖች እንደ ምሳሌ እንመልከት።
በእነዚህ ቅቡዕ እህቶች መካከል ከባድ አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር።
በኤዎድያንና በሲንጤኪ መካከል የተፈጠረው ችግር የጉባኤውን ሰላም ሊያደፈርስ ይችል ነበር።
መጽሐፍ ቅዱስ፣ እነዚህ እህቶች መጨረሻ ላይ ምን እንዳደረጉ ባይገልጽልንም ጳውሎስ በፍቅር ተነሳስቶ ለሰጣቸው ምክር ጥሩ ምላሽ ሰጥተው መሆን አለበት።
በዛሬው ጊዜም በይሖዋ ሕዝቦች ጉባኤዎች ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች ሊያጋጥሙ ይችላሉ።
ሆኖም የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ምክር በተግባር ካዋልን እንዲህ ያሉ ችግሮችን መፍታት አልፎ ተርፎም እንዳይፈጠሩ ማድረግ እንችላለን።
የአምላክን ቃል ከፍ አድርገን የምንመለከት ከሆነ ደግሞ በውስጡ የሚገኙትን መመሪያዎች እንከተላለን።
ሁላችንም ማበረታቻ ያስፈልገናል።
በተለይ ከልጆች ጋር በተያያዘ ይህ እውነት ነው።
ቲሞቲ ኤቫንዝ የተባሉ ምሁር ተክሎች ውኃ እንደሚያስፈልጋቸው ሁሉ ልጆችም ማበረታቻ ያስፈልጋቸዋል በማለት ተናግረዋል።
አክለውም አንድ ልጅ ማበረታቻ የሚሰጠው ከሆነ ዋጋ እንዳለውና ሌሎች እንደሚያደንቁት ይሰማዋል ብለዋል።
ይሁንና የምንኖረው በሚያስጨንቅ ዘመን ውስጥ ነው።
ሰዎች ራስ ወዳዶችና ተፈጥሯዊ ፍቅር የሌላቸው ስለሆኑ ሌሎችን ማበረታታት የተለመደ አይደለም።
ሰይጣን ዲያብሎስ፣ ተስፋ ከቆረጥን በመንፈሳዊም ሆነ በሌሎች አቅጣጫዎች እንደምንዳከም ስለሚያውቅ ተስፋ ሊያስቆርጠን ይፈልጋል።
ሰይጣን፣ ጻድቁን ኢዮብን ተስፋ ለማስቆረጥ ሲል የተለያዩ መከራዎች ያመጣበት ከመሆኑም ሌላ የሐሰት ውንጀላዎች እንዲሰነዘሩበት አድርጓል፤ ሆኖም ሙከራው አልተሳካለትም።
እኛም የቤተሰባችንንና የጉባኤውን አባላት በማበረታታት የዲያብሎስን ሥራ ማክሸፍ እንችላለን።
እንዲህ ማድረጋችን ቤታችንንም ሆነ የመንግሥት አዳራሻችንን ደስታ የምናገኝበትና ከመንፈሳዊ አደጋ ነፃ የምንሆንበት ስፍራ ለማድረግ ይረዳል።
የይሖዋ ታላቅ ፍቅር በብዙ መንገዶች ታይቷል።
አስደናቂ የሆነውን ጽንፈ ዓለም እንደ ምሳሌ እንመልከት።
በብዙ ቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ከዋክብትንና ፕላኔቶችን የያዙ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ጋላክሲዎች አሉ።
ፍኖተ ሐሊብ በተባለው በእኛ ጋላክሲ ውስጥ ከታቀፉት ከዋክብት መካከል ፀሐይ ትገኝበታለች፤ ፀሐይ ባትኖር ኖሮ በምድር ላይ ያሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሕያዋን ፍጥረታት ሕልውና ያከትም ነበር።
እነዚህ ሁሉ ፍጥረታት ይሖዋ፣ አምላክ ለመሆኑ እንዲሁም እንደ ኃይል፣ ጥበብና ፍቅር ላሉት ባሕርያቱ ማስረጃ ናቸው።
ይሖዋ ምድርን ሲፈጥር በእሷ ላይ እንዲኖሩ ላሰባቸው ሕያዋን ፍጥረታት አስፈላጊ ነገሮችን በሙሉ አብሮ ፈጥሯል።
ለሰው ልጆች ውብ የአትክልት ቦታ ያዘጋጀ ሲሆን ለዘላለም መኖር የሚያስችላቸው ፍጹም አእምሮና አካል ሰጥቷቸዋል።
በተጨማሪም ሕይወት ላለው ሁሉ ምግብ ይሰጣል፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና።
ንጉሣችን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የመንግሥቱን መልእክት እንዲቀበሉ ልባቸውን ለማዘጋጀት የሚረዱ የተለያዩ መሣሪያዎችን ባለፉት ዓመታት ሰጥቶናል።
ከእነዚህ መሣሪያዎች አንዳንዶቹ ያገለገሉት ለተወሰኑ አሥርተ ዓመታት ሲሆን አንዳንዶቹ ግን አሁንም ጠቃሚ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው።
ይሁንና ሁሉም መሣሪያዎች ከወንጌላዊነቱ ሥራችን ጋር በተያያዘ በተለያየ መንገድ ችሎታችንን እንድናዳብር ረድተውናል።
ብዙዎች አገልግሎት እንዲጀምሩ የረዳቸው አንዱ መሣሪያ የምሥክርነት መስጫ ካርድ ሲሆን የመንግሥቱ አስፋፊዎች ይህን መሣሪያ መጠቀም የጀመሩት በ1933 ነው።
ካርዱ አጠር ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት የያዘ ነበር።
የምሥክርነት መስጫ ካርድ ብዙ ጥቅሞች ነበሩት።
አንዳንድ አስፋፊዎች በስብከቱ ሥራ የመካፈል ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖራቸውም ዓይናፋር ነበሩ፤ ምን ብለው መናገር እንዳለባቸው አያውቁም።
ሌሎች ደግሞ የሚያውቁትን ሁሉ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ለቤቱ ባለቤት መናገር ይችላሉ፤ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ ዘዴኛነት ይጎድላቸው ነበር! የምሥክርነት መስጫ ካርዶች ግን በሚገባ የተመረጡ ጥቂት ቃላትን ስለሚጠቀሙ ለአስፋፊዎቹ እንደ አንደበት ሆነውላቸዋል።
በዛሬው ጊዜ ስለ ይሖዋ የፍጥረት ሥራዎችና ዓላማው እየተፈጸመ ስላለበት መንገድ ሰፊ እውቀት በማግኘት ተባርከናል።
ዓለም ከፍተኛ ትምህርትንና ብዙ መማርን ያበረታታል።
ይሁንና የብዙዎች ተሞክሮ እንደሚያሳየው እንዲህ ዓይነቱን ግብ መከታተል አብዛኛውን ጊዜ አንድ ሰው እምነቱንም ሆነ ለአምላክ ያለውን ፍቅር እንዲያጣ ያደርገዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን እውቀትን እንድንወድ ብቻ ሳይሆን ጥበብና ማስተዋልም እንዲኖረን ያበረታታናል።
ይህም አምላክ የሰጠንን እውቀት ተግባራዊ በማድረግ ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን መጥቀም የምንችልበትን መንገድ ማስተዋል እንደሚገባን ያሳያል።
የአምላክ ፈቃድ ሁሉም ዓይነት ሰዎች እንዲድኑና የእውነትን ትክክለኛ እውቀት እንዲያገኙ ነው።
ለሰዎች ሁሉ የመንግሥቱን ምሥራች ለመንገርና ሰዎች አምላክ ለሰው ዘር ያለውን ታላቅ ዓላማ እንዲያውቁ ለመርዳት ልባዊ ጥረት ስናደርግ ይሖዋን እንደምንወደው እናሳያለን።
የሰዎች ቋንቋ የመማር ችሎታ ከአምላክ የተገኘ ተአምራዊ ስጦታ ነው።
አምላክ የሰጠን አእምሮ ከሌላም አቅጣጫ ሲታይ በጣም ጠቃሚ የሆነ ስጦታ ነው።
ከእንስሳት በተለየ ሰዎች የተፈጠሩት በአምላክ መልክ ነው።
ሰዎች ነፃ ምርጫ ስላላቸው የቋንቋ ችሎታቸውን ተጠቅመው አምላክን ማወደስ ይችላሉ።
ቋንቋን የፈጠረው አምላክ እሱን ማክበር ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ግሩም የሆነ ስጦታ ይኸውም መጽሐፍ ቅዱስን ሰጥቷቸዋል።
መጽሐፍ ቅዱስ በከፊልም ሆነ በሙሉ ከ2,800 በሚበልጡ ቋንቋዎች ይገኛል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሰፈረውን ሐሳብ ስታነብ የአምላክ ዓይነት አስተሳሰብ ይኖርሃል።
በዚህ መንገድ ለመዳን የሚያበቃ ጥበብ እንድታገኝ በሚያስችሉህ ነገሮች ላይ ማሰላሰል ትችላለህ።
ማሰላሰል ሲባል አእምሮ በአንድ ነገር ላይ እንዲያተኩር ማድረግ ይኸውም በአንድ ጉዳይ ላይ ጥሩ ወይም መጥፎ ሊሆን ይችላል ማውጠንጠን ወይም በተመስጦ ማሰብ ማለት ነው።
ከምንም ነገር በላይ የሚጠቅመን ስለ ይሖዋና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማሰላሰል ነው።
በክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ ከቂጣውና ከወይን ጠጁ የሚወስዱ ሰዎች ቁጥር ለበርካታ አሥርተ ዓመታት እየቀነሰ ሲሄድ ተመልክተናል።