text stringlengths 4 267 |
|---|
ለሥጋዊ ፍላጎቷ ያደረች መበለት ግን በሕይወት ብትኖርም የሞተች ናት። |
ስለዚህ ከነቀፋ ነፃ መሆን ይችሉ ዘንድ እነዚህን መመሪያዎች መስጠትህን ቀጥል። |
በእርግጥም አንድ ሰው የራሱ ለሆኑት በተለይ ደግሞ ለቤተሰቡ አባላት የሚያስፈልጋቸውን ነገር የማያቀርብ ከሆነ እምነትን የካደ ከመሆኑም በላይ እምነት የለሽ ከሆነ ሰው የከፋ ነው። |
አንዲት መበለት ከ60 ዓመት በላይ ከሆነች በመዝገብ ላይ ትጻፍ፤ ደግሞም የአንድ ባል ሚስት የነበረች ልትሆን ይገባል፤ |
እንዲሁም ልጆችን በማሳደግ፣ እንግዶችን በመቀበል፣ የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣ የተቸገሩትን በመርዳትና ማንኛውንም በጎ ተግባር በትጋት በማከናወን በመልካም ሥራ ጥሩ ስም ያተረፈች ልትሆን ይገባል። |
በዕድሜ ያልገፉ መበለቶች ግን መዝገብ ላይ መጻፍ የለባቸውም፤ የፆታ ፍላጎታቸው በክርስቲያናዊ አገልግሎታቸው ላይ እንቅፋት በሚፈጥርበት ጊዜ ማግባት ይፈልጋሉና። |
ደግሞም የመጀመሪያውን የእምነት ቃላቸውን ስላፈረሱ በራሳቸው ላይ ፍርድ ያመጣሉ። |
ከዚህ በተጨማሪ በየቤቱ እየዞሩ ሥራ ፈት ይሆናሉ፤ ሥራ ፈት መሆን ብቻ ሳይሆን ማውራት ስለማይገባቸው ነገሮች እያወሩ ሐሜተኞችና በሌሎች ሰዎች ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ ይሆናሉ። |
ስለዚህ በዕድሜ ያልገፉ መበለቶች እንዲያገቡ፣ ልጆች እንዲወልዱ፣ ቤታቸውን እንዲያስተዳድሩና ተቃዋሚው ትችት ሊሰነዝር የሚችልበት አጋጣሚ እንዲያገኝ ከማድረግ እንዲቆጠቡ እፈልጋለሁ። |
እንዲያውም አንዳንዶቹ ከዚህ በፊት ሰይጣንን ለመከተል ዞር ብለዋል። |
አንዲት አማኝ የሆነች ሴት፣ መበለት የሆኑ ዘመዶች ቢኖሯት ጉባኤው ሸክም እንዳይበዛበት እሷ ትርዳቸው። በዚህ መንገድ ጉባኤው በእርግጥ መበለት የሆኑትን መርዳት ይችላል። |
በመልካም ሁኔታ የሚያስተዳድሩ በተለይ ደግሞ በመናገርና በማስተማር ተግተው የሚሠሩ ሽማግሌዎች እጥፍ ክብር ሊሰጣቸው ይገባል። |
የቅዱስ መጽሐፉ ቃል “እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር”፤ እንዲሁም “ለሠራተኛ ደሞዙ ይገባዋል” ይላልና። |
በሁለት ወይም በሦስት ምሥክሮች ማስረጃ ካልሆነ በቀር በሽማግሌ ላይ የሚቀርብን ክስ አትቀበል። |
ለሌሎቹ ማስጠንቀቂያ እንዲሆን ኃጢአት የመሥራት ልማድ ያላቸውን ሰዎች በሁሉ ፊት ውቀሳቸው። |
እነዚህን መመሪያዎች መሠረተ ቢስ ከሆነ ጥላቻና ከአድልዎ በራቀ መንገድ እንድትጠብቅ በአምላክ፣ በክርስቶስ ኢየሱስና በተመረጡት መላእክት ፊት በጥብቅ አዝሃለሁ። |
በማንም ሰው ላይ እጅህን ለመጫን አትቸኩል፤ እንዲሁም በሌሎች ኃጢአት ተካፋይ አትሁን፤ ራስህን በንጽሕና ጠብቅ። |
ከእንግዲህ ውኃ አትጠጣ፤ ከዚህ ይልቅ ለሆድህና በተደጋጋሚ ለሚነሳብህ ሕመም ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ። |
የአንዳንድ ሰዎች ኃጢአት በይፋ የታወቀ ስለሚሆን ወዲያውኑ ፍርድ ያስከትላል፤ የሌሎቹ ሰዎች ኃጢአት ደግሞ ውሎ አድሮ መታወቁ አይቀርም። |
በተመሳሳይም መልካም ሥራዎች በይፋ የታወቁ ናቸው፤ በይፋ ያልታወቁትም ቢሆኑ ተደብቀው ሊቀሩ አይችሉም። |
ይሁን እንጂ በመንፈስ መሪነት የተነገረው ቃል በኋለኞቹ ዘመናት አንዳንዶች ከመናፍስት ለሚመነጩ አሳሳች ቃሎችና ለአጋንንት ትምህርቶች ጆሯቸውን በመስጠት ከእምነት መውጣታቸው እንደማይቀር በግልጽ ይናገራል፤ |
ይህም የሚሆነው በጋለ ብረት የተተኮሰ ያህል ሕሊናቸው የደነዘዘባቸው ግብዝ ሰዎች በሚናገሩት ውሸት የተነሳ ነው። |
እነዚህ ሰዎች ጋብቻን ይከለክላሉ፤ እንዲሁም እምነት ያላቸውና እውነትን በትክክል የተረዱ ሰዎች ምስጋና አቅርበው እንዲበሏቸው አምላክ የፈጠራቸውን ምግቦች ‘አትብሉ’ ብለው ያዛሉ። |
ይሁንና አምላክ የፈጠረው ነገር ሁሉ መልካም ነው፤ በምስጋና እስከተቀበሉት ድረስ ምንም የሚጣል ነገር የለም፤ |
በአምላክ ቃልና በጸሎት ተቀድሷልና። |
ይህን ምክር ለወንድሞች በመስጠት የእምነትንና አጥብቀህ የተከተልከውን የመልካም ትምህርት ቃል በሚገባ የተመገብክ የክርስቶስ ኢየሱስ ጥሩ አገልጋይ ትሆናለህ። |
ነገር ግን አሮጊቶች እንደሚያወሯቸው ካሉ አምላክን የሚጻረሩ የውሸት ታሪኮች ራቅ። ከዚህ ይልቅ ለአምላክ ማደርን ግብ አድርገህ ራስህን አሠልጥን። |
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በጥቂቱ ይጠቅማል፤ ለአምላክ ማደር ግን ለአሁኑም ሆነ ለወደፊቱ ሕይወት ተስፋ ስለሚሰጥ ለሁሉም ነገር ይጠቅማል። |
ይህ ቃል እምነት የሚጣልበትና ሙሉ በሙሉ ሊቀበሉት የሚገባ ነው። |
ጠንክረን በመሥራትና ብርቱ ጥረት በማድረግ ላይ ያለነውም ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም ሁሉንም ዓይነት ሰዎች በተለይ ደግሞ ታማኝ የሆኑትን በሚያድነው ሕያው አምላክ ላይ ተስፋችንን ጥለናል። |
እነዚህን ትእዛዛት መስጠትህንና ማስተማርህን ቀጥል። |
ወጣት በመሆንህ ማንም ሰው ሊንቅህ አይገባም። ከዚህ ይልቅ ታማኞች ለሆኑት በንግግር፣ በምግባር፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና አርዓያ ሁን። |
እኔ እስክመጣ ድረስ ለሰዎች ለማንበብ፣ አጥብቀህ ለመምከርና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ። |
የሽማግሌዎች አካል እጁን በአንተ ላይ በጫነበት ጊዜ በትንቢት የተሰጠህን ስጦታ ቸል አትበል። |
እድገትህ በሁሉም ሰዎች ዘንድ በግልጽ እንዲታይ በእነዚህ ነገሮች ላይ አሰላስል፤ እንዲሁም ትኩረትህ ሙሉ በሙሉ በእነዚህ ነገሮች ላይ ያረፈ ይሁን። |
ለራስህና ለምታስተምረው ትምህርት ምንጊዜም ትኩረት ስጥ። በእነዚህ ነገሮች ጽና፤ ይህን በማድረግ ራስህንም ሆነ የሚሰሙህን ታድናለህና። |
የአምላክ ስምና ትምህርት ፈጽሞ እንዳይሰደብ በባርነት ቀንበር ሥር ያሉ ሁሉ ጌቶቻቸው ሙሉ ክብር እንደሚገባቸው ይገንዘቡ። |
በተጨማሪም አማኝ የሆኑ ጌቶች ያሏቸው ባሪያዎች፣ ጌቶቻቸው ወንድሞች ስለሆኑ ብቻ አክብሮት አይንፈጓቸው። ከዚህ ይልቅ እነሱ ከሚሰጡት ጥሩ አገልግሎት እየተጠቀሙ ያሉት፣ የእምነት ባልንጀሮቻቸውና የተወደዱ ወንድሞቻቸው ስለሆኑ ይበልጥ በትጋት ያገልግሏቸው። እነዚህን ነገሮች ማስተማርህንና እነዚህን ማሳሰቢያዎች መስጠትህን ቀጥል። |
አንድ ሰው የተለየ ትምህርት ቢያስተምርና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ካስተማረው ትክክለኛ ትምህርትም ሆነ ለአምላክ ማደርን ከሚያበረታታው ትምህርት ጋር የማይስማማ ቢሆን |
ይህ ሰው በትዕቢት የተወጠረና ምንም የማያስተውል ነው። ስለ ቃላት የመጨቃጨቅና የመከራከር አባዜ የተጠናወተው ነው። እንዲህ ያሉ ነገሮች ቅናት፣ ጠብ፣ ስም ማጥፋትና መጥፎ ጥርጣሬ ያስከትላሉ፤ |
በተጨማሪም ለአምላክ ማደር ጥቅም ማግኛ እንደሆነ አድርገው በሚያስቡ፣ አእምሯቸው በተበላሸና እውነትን መረዳት ባቆሙ ሰዎች መካከል ተራ በሆኑ ጉዳዮች የማያባራ ጭቅጭቅ ያስነሳሉ። |
እንደ እውነቱ ከሆነ ለአምላክ ያደርን መሆናችንና ባለን ነገር ረክተን መኖራችን ትልቅ ጥቅም ያስገኛል። |
ወደ ዓለም ያመጣነው ምንም ነገር የለምና፤ ምንም ነገር ይዘን መሄድም አንችልም። |
ስለዚህ ምግብና ልብስ ካለን በእነዚህ ነገሮች ረክተን መኖር ይገባናል። |
ሀብታም ለመሆን ቆርጠው የተነሱ ግን ፈተናና ወጥመድ ውስጥ ይወድቃሉ፤ እንዲሁም ሰዎችን ጥፋትና ብልሽት ውስጥ በሚዘፍቁ ከንቱና ጎጂ በሆኑ ብዙ ምኞቶች ይያዛሉ። |
የገንዘብ ፍቅር የብዙ ዓይነት ጎጂ ነገሮች ሥር ነውና፤ አንዳንዶች በዚህ ፍቅር ተሸንፈው ከእምነት ጎዳና ስተው ወጥተዋል፤ እንዲሁም ሁለንተናቸውን በብዙ ሥቃይ ወግተዋል። |
የአምላክ ሰው ሆይ፣ አንተ ግን ከእነዚህ ነገሮች ሽሽ። ከዚህ ይልቅ ጽድቅን፣ ለአምላክ ማደርን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ጽናትንና ገርነትን ተከታተል። |
መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤ የተጠራህለትንና በብዙ ምሥክሮች ፊት በጥሩ ሁኔታ በይፋ የተናገርክለትን የዘላለም ሕይወት አጥብቀህ ያዝ። |
ሁሉንም ነገሮች ሕያው አድርጎ በሚያኖረው አምላክና ለጳንጥዮስ ጲላጦስ በይፋ ግሩም ምሥክርነት በሰጠው በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት ይህን አዝሃለሁ፦ |
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ትእዛዙን ያለእንከንና ያለነቀፋ ጠብቅ፤ |
ደስተኛውና ብቸኛው ኃያል ገዢ በተወሰነለት ጊዜ ራሱን ይገልጣል። እሱ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ ነው፤ |
ያለመሞትን ባሕርይ የተላበሰው እሱ ብቻ ነው፤ ሊቀረብ በማይችል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፤ እሱን ያየ ወይም ሊያየው የሚችል አንድም ሰው የለም። ክብርና ዘላለማዊ ኃይል ለእሱ ይሁን። አሜን። |
አሁን ባለው ሥርዓት ሀብታም የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ እንዲሁም ተስፋቸውን አስተማማኝነት በሌለው ሀብት ላይ ሳይሆን የሚያስደስቱንን ነገሮች ሁሉ አትረፍርፎ በሚሰጠን አምላክ ላይ እንዲጥሉ እዘዛቸው። |
በተጨማሪም መልካም ነገር እንዲያደርጉ፣ በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ እንዲሆኑ እንዲሁም ለጋሶችና ለሌሎች ለማካፈል ዝግጁ እንዲሆኑ ምከራቸው፤ |
እውነተኛ የሆነውን ሕይወት አጥብቀው መያዝ ይችሉ ዘንድ ለራሳቸው ውድ ሀብት ማከማቸታቸውን ይኸውም ለወደፊቱ ጊዜ የሚሆን መልካም መሠረት መጣላቸውን ይቀጥሉ። |
ጢሞቴዎስ ሆይ፣ ቅዱስ የሆነውን ነገር ከሚጻረሩ ከንቱ ንግግሮችና በውሸት “እውቀት” ተብለው ከሚጠሩ እርስ በርሳቸው ከሚቃረኑ ሐሳቦች በመራቅ በአደራ የተሰጠህን ነገር ጠብቅ። |
አንዳንዶች እንዲህ ዓይነቱ እውቀት እንዲታይላቸው ለማድረግ ሲጣጣሩ ከእምነት ጎዳና ወጥተዋል። የአምላክ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን። |
በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት የሚገኘውን ሕይወት በተመለከተ ከተገባው ቃል ጋር በሚስማማ ሁኔታ በአምላክ ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ |
ለተወዳጁ ልጄ ለጢሞቴዎስ፦ አባት ከሆነው አምላክና ከጌታችን ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም ለአንተ ይሁን። |
የቀድሞ አባቶቼ እንዳደረጉት ቅዱስ አገልግሎት የማቀርብለትንና በንጹሕ ሕሊና የማገለግለውን አምላክ አመሰግናለሁ፤ ደግሞም ሌት ተቀን አንተን ዘወትር በምልጃዬ አስታውሳለሁ። |
እንባህን ሳስታውስ፣ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ። |
በአንተ ውስጥ ያለውን ግብዝነት የሌለበት እምነት አስታውሳለሁና፤ ይህ እምነት በመጀመሪያ በአያትህ በሎይድ እንዲሁም በእናትህ በኤውንቄ ዘንድ ነበር፤ ይሁንና በአንተም ውስጥ እንዳለ እርግጠኛ ነኝ። |
ስለዚህ በአንተ ላይ እጄን በጫንኩበት ጊዜ የተቀበልከውን የአምላክ ስጦታ በቅንዓት እንድትጠቀምበት አሳስብሃለሁ። |
አምላክ የኃይል፣ የፍቅርና የጤናማ አእምሮ መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና። |
ስለሆነም ስለ ጌታችን መመሥከር አያሳፍርህ፤ ደግሞም ለእሱ ስል እስረኛ በሆንኩት በእኔ አትፈር፤ ከዚህ ይልቅ በአምላክ ኃይል በመታመን አንተም ለምሥራቹ የበኩልህን መከራ ተቀበል። |
እሱ በእኛ ሥራ ሳይሆን በራሱ ዓላማና ጸጋ የተነሳ አዳነን፤ እንዲሁም ቅዱስ በሆነ ጥሪ ጠራን። ይህን ጸጋ ከረጅም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ሰጠን፤ |
አሁን ግን ይህ ጸጋ አዳኛችን የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ በመገለጡ ግልጽ ሆኖ ታይቷል፤ እሱ ሞትን አስወግዶ በምሥራቹ አማካኝነት ሕይወትንና አለመበስበስን በተመለከተ ብርሃን ፈንጥቋል፤ |
እኔም ለዚህ ምሥራች ሰባኪ፣ ሐዋርያና አስተማሪ ሆኜ ተሹሜአለሁ። |
አሁን መከራ እየተቀበልኩ ያለሁትም ለዚሁ ነው፤ ሆኖም አላፍርበትም። ያመንኩበትን እሱን አውቀዋለሁና፤ በአደራ የሰጠሁትንም እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ጠብቆ ማቆየት እንደሚችል እተማመናለሁ። |
ከእኔ የሰማኸውን የትክክለኛ ትምህርት መሥፈርት ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ባለህ አንድነት ካገኘኸው እምነትና ፍቅር ጋር አጥብቀህ ያዝ። |
ይህን መልካም አደራ በእኛ ውስጥ በሚኖረው መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ጠብቅ። |
ፊጌሎስንና ሄርሞጌኔስን ጨምሮ በእስያ አውራጃ ያሉት ሁሉ ትተውኝ እንደሄዱ ታውቃለህ። |
ጌታ ለኦኔሲፎሮስ ቤተሰብ ምሕረትን ይስጥ፤ እሱ ብዙ ጊዜ መንፈሴን አድሶልኛልና፤ በታሰርኩበት ሰንሰለትም አላፈረም። |
እንዲያውም ሮም በነበረ ጊዜ አፈላልጎ አገኘኝ። |
ጌታ ይሖዋ በዚያ ቀን ምሕረቱን ይስጠው። ደግሞም በኤፌሶን ያከናወነውን አገልግሎት ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ። |
ነገር ግን በመጨረሻዎቹ ቀናት ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን እንደሚመጣ ይህን እወቅ። |
ምክንያቱም ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፣ ገንዘብ የሚወዱ፣ ጉረኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ታማኝ ያልሆኑ፣ |
ተፈጥሯዊ ፍቅር የሌላቸው፣ ለመስማማት ፈቃደኞች ያልሆኑ፣ ስም አጥፊዎች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች፣ ጥሩ ነገር የማይወዱ፣ |
ከዳተኞች፣ ግትሮች፣ በኩራት የተወጠሩ፣ ከአምላክ ይልቅ ሥጋዊ ደስታን የሚወዱ ይሆናሉ፤ |
ለአምላክ ያደሩ መስለው ይታያሉ፤ በሥራቸው ግን ኃይሉን ይክዳሉ፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። |
በየቤቱ ሾልከው የሚገቡ ሰዎች የሚነሱት ከእነዚህ መካከል ነው፤ እነዚህ ሰዎች በተለያዩ ምኞቶች የሚነዱትን፣ በኃጢአት የተተበተቡትን ደካማ ሴቶች ይማርካሉ፤ |
እንደነዚህ ያሉት ሴቶች ሁልጊዜ ይማራሉ፤ ሆኖም ትክክለኛውን የእውነት እውቀት መረዳት አይችሉም። |
እንግዲህ ኢያኔስና ኢያንበሬስ ሙሴን እንደተቃወሙት ሁሉ እነዚህም እውነትን ይቃወማሉ። እንዲህ ያሉ ሰዎች አእምሯቸው ሙሉ በሙሉ የተበላሸ ከመሆኑም ሌላ በእምነት ጎዳና ስለማይመላለሱ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት አጥተዋል። |
ይሁንና የእነዚያ ሁለት ሰዎች ሞኝነት ለሰው ሁሉ በጣም ግልጽ እንደነበረ ሁሉ የእነዚህ ሰዎች ሞኝነትም ግልጽ ስለሚሆን በአካሄዳቸው ብዙም ሊገፉበት አይችሉም። |
አንተ ግን ትምህርቴን፣ አኗኗሬን፣ ዓላማዬን፣ እምነቴን፣ ትዕግሥቴን፣ ፍቅሬንና ጽናቴን በጥብቅ ተከትለሃል፤ |
እንደ አንጾኪያ፣ ኢቆንዮንና ልስጥራ ባሉ ቦታዎች የደረሰብኝን ስደትና መከራ ታውቃለህ። ይህን ሁሉ ስደት በጽናት አሳልፌአለሁ፤ ጌታም ከዚህ ሁሉ ታደገኝ። |
በእርግጥም የክርስቶስ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በመሆን ለአምላክ ያደሩ ሆነው መኖር የሚፈልጉ ሁሉ ስደት ይደርስባቸዋል። |
ሆኖም ክፉ ሰዎችና አስመሳዮች እያሳሳቱና እየተሳሳቱ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ። |
አንተ ግን በተማርካቸውና አምነህ በተቀበልካቸው ነገሮች ጸንተህ ኑር፤ ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች እነማን እንዳስተማሩህ ታውቃለህ፤ |
እንዲሁም በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ለመዳን የሚያበቃ ጥበብ እንድታገኝ የሚያስችሉህን ቅዱሳን መጻሕፍት ከጨቅላነትህ ጀምሮ አውቀሃል። |
ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው፤ እንዲሁም ለማስተማር፣ ለመውቀስ፣ ነገሮችን ለማቅናትና በጽድቅ ለመገሠጽ ይጠቅማሉ፤ |
ይኸውም የአምላክ ሰው ለማንኛውም መልካም ሥራ በሚገባ በመታጠቅ ሙሉ በሙሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው። |
እንግዲህ ልጄ ሆይ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ በሚገኘው ጸጋ አማካኝነት በርታ፤ |
ከእኔ የሰማኸውንና ብዙዎች የመሠከሩለትን ነገር፣ ታማኝ ለሆኑ ሰዎች አደራ ስጥ፤ እነሱም በበኩላቸው ሌሎችን ለማስተማር ብቃቱን ያሟላሉ። |
የክርስቶስ ኢየሱስ ምርጥ ወታደር እንደመሆንህ መጠን አንተም በበኩልህ መከራ ተቀበል። |
ወታደር ሆኖ የሚያገለግል ማንኛውም ሰው ለውትድርና የመለመለውን ሰው ደስ ማሰኘት ስለሚፈልግ ራሱን በንግድ ሥራ አያጠላልፍም። |
በውድድር የሚሳተፍ ማንኛውም ሰው የውድድሩን ደንብ ጠብቆ ካልተወዳደረ የድሉን አክሊል አይሸለምም። |
ጠንክሮ የሚሠራ ገበሬ ከፍሬው የመጀመሪያው ተቋዳሽ መሆን አለበት። |
ለምናገረው ነገር ምንጊዜም ትኩረት ስጥ፤ ጌታም በሁሉም ነገር ማስተዋል ይሰጥሃል። |
ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ እንዲሁም የዳዊት ዘር እንደሆነ አስታውስ፤ እኔም የምሰብከው ምሥራች ይህ ነው፤ |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.