text stringlengths 4 267 |
|---|
ምናልባት ለአጭር ጊዜ ከአንተ ጠፍቶ የሄደው፣ ተመልሶ ለዘለቄታው የአንተ ሆኖ እንዲኖር ይሆናል፤ |
ከእንግዲህ ወዲህ እንደ ባሪያ ሳይሆን ከባሪያ ይበልጥ እንደተወደደ ወንድምህ ነው፤ በተለይ ለእኔ ተወዳጅ ወንድም ነው፤ ሆኖም በሰብዓዊ ግንኙነታችሁም ሆነ ከጌታ ጋር ባላችሁ ዝምድና ለአንተ ይበልጥ ተወዳጅ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። |
ስለዚህ እኔን እንደ ወዳጅ አድርገህ ከቆጠርከኝ እኔን እንደምትቀበለኝ አድርገህ እሱን በደግነት ተቀበለው። |
ከዚህም በተጨማሪ የበደለህ ነገር ካለ ወይም የአንተ ዕዳ ካለበት ዕዳውን በእኔ ላይ አስበው። |
እኔ ጳውሎስ ይህን በራሴ እጅ ጽፌልሃለሁ፦ ያለበትን ዕዳ እኔ እከፍልሃለሁ፤ ደግሞም ከሕይወትህ ጋር በተያያዘም እንኳ የእኔ ባለዕዳ እንደሆንክ መናገር አያስፈልገኝም። |
ወንድሜ ሆይ፣ ሁለታችንም የጌታ ደቀ መዛሙርት በመሆናችን በዚህ ረገድ እንድትተባበረኝ እፈልጋለሁ፦ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንደመሆንህ መጠን ልቤን አድስልኝ። |
ይህን የምጽፍልህ በዚህ እንደምትስማማ በመተማመንና ከምጠይቅህም በላይ እንደምታደርግ በማወቅ ነው። |
ከዚህም ሌላ ጸሎታችሁ ተሰምቶ ወደ እናንተ እንደምመለስ ተስፋ ስለማደርግ ማረፊያ አዘጋጅልኝ። |
በክርስቶስ ኢየሱስ የተነሳ አብሮኝ እስረኛ የሆነው ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብልሃል፤ |
የሥራ ባልደረቦቼ የሆኑት ማርቆስ፣ አርስጥሮኮስ፣ ዴማስና ሉቃስም ሰላም ብለውሃል። |
የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እናንተ ከምታሳዩት መንፈስ ጋር ይሁን። |
እምነት ተስፋ የተደረጉትን ነገሮች በእርግጠኝነት መጠበቅ ማለት ነው፤ በተጨማሪም የምናምንበት ነገር በዓይን የሚታይ ባይሆንም እውን መሆኑን የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ ነው። |
በጥንት ዘመን የኖሩት ሰዎች የተመሠከረላቸው በዚህ አማካኝነት ነው። |
ሥርዓቶቹ የተቋቋሙት በአምላክ ቃል መሆኑን የምንረዳው በእምነት ነው፤ በመሆኑም የሚታየው ነገር ወደ ሕልውና የመጣው ከማይታዩ ነገሮች ነው። |
አቤል፣ ቃየን ካቀረበው የበለጠ ዋጋ ያለው መሥዋዕት ለአምላክ በእምነት አቀረበ፤ አምላክ ስጦታውን ስለተቀበለ በዚህ እምነቱ የተነሳ ጻድቅ እንደሆነ ተመሥክሮለታል፤ ቢሞትም እንኳ በእምነቱ አማካኝነት አሁንም ይናገራል። |
ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ወደ ሌላ ቦታ ተወሰደ፤ አምላክ ወደ ሌላ ቦታ ስለወሰደውም የትም ቦታ ሊገኝ አልቻለም፤ ከመወሰዱ በፊት አምላክን በሚገባ ደስ እንዳሰኘ ተመሥክሮለት ነበርና። |
በተጨማሪም ያለእምነት አምላክን በሚገባ ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ አምላክ የሚቀርብ ሁሉ እሱ መኖሩንና ከልብ ለሚፈልጉትም ወሮታ ከፋይ መሆኑን ማመን ይኖርበታልና። |
ኖኅ ገና ስላልታዩት ነገሮች መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ከተቀበለ በኋላ አምላካዊ ፍርሃት ያሳየውና ቤተሰቡን ለማዳን መርከብ የሠራው በእምነት ነበር፤ በዚህ እምነት አማካኝነትም ዓለምን ኮንኗል፤ እንዲሁም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ለመውረስ በቅቷል። |
አብርሃም በተጠራ ጊዜ ወደፊት ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ በመሄድ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም ይኖርበት የነበረውን ስፍራ ለቆ ወጣ። |
በባዕድ አገር እንደሚኖር እንግዳ በተስፋይቱ ምድር በእምነት ኖረ፤ ደግሞም አብረውት የዚሁ ተስፋ ቃል ወራሾች ከሆኑት ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር በድንኳን ኖረ። |
አምላክ ንድፍ ያወጣላትንና የገነባትን፣ እውነተኛ መሠረት ያላትን ከተማ ይጠባበቅ ነበርና። |
ሣራም የተስፋን ቃል የሰጠው እሱ ታማኝ እንደሆነ አድርጋ ስላሰበች ዕድሜዋ ካለፈ በኋላም እንኳ ዘር ለመፀነስ በእምነት ኃይል አገኘች። |
ከዚህም የተነሳ እንደሞተ ያህል ከሚቆጠረው ከአንድ ሰው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዙና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የማይቆጠሩ ልጆች ተወለዱ። |
እነዚህ ሁሉ የተስፋውን ቃል ፍጻሜ ባያዩም እምነታቸውን እንደጠበቁ ሞቱ፤ ሆኖም ከሩቅ አይተው በደስታ ተቀበሉት፤ በምድሩም ላይ እንግዶችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች መሆናቸውን በይፋ ተናገሩ። |
እንዲህ ብለው የሚናገሩት ሰዎች የራሳቸው የሆነ ቦታ ለማግኘት ከልብ እንደሚሹ ያሳያሉ። |
ይሁንና ትተውት የወጡትን ቦታ ሁልጊዜ ቢያስቡ ኖሮ መመለስ የሚችሉበት አጋጣሚ በኖራቸው ነበር። |
አሁን ግን የተሻለውን ይኸውም ከሰማይ የሆነውን ስፍራ ለማግኘት ይጣጣራሉ። ስለዚህ አምላክ፣ እሱን አምላካችን ብለው ቢጠሩት አያፍርባቸውም፤ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና። |
አብርሃም በተፈተነ ጊዜ ይስሐቅን መሥዋዕት አድርጎ እስከ ማቅረብ ድረስ እምነት አሳይቷል፤ የተስፋን ቃል በደስታ የተቀበለው ይህ ሰው አንድያ ልጁን መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ተዘጋጅቶ ነበር፤ |
ይህን ያደረገው “ዘርህ የሚጠራልህ በይስሐቅ በኩል ይሆናል” ተብሎ ተነግሮት እያለ ነው። |
ይሁንና አምላክ ከሞት እንኳ ሳይቀር ሊያስነሳው እንደሚችል ተገንዝቦ ነበር፤ ልጁንም ከሞት አፋፍ መልሶ አገኘው፤ ይህም እንደ ምሳሌ ሆኖ አገልግሏል። |
ይስሐቅም ወደፊት ከሚሆኑት ነገሮች ጋር በተያያዘ ያዕቆብንና ኤሳውን በእምነት ባረካቸው። |
ያዕቆብ መሞቻው በተቃረበ ጊዜ የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸውን የባረካቸውና የበትሩን ጫፍ ተመርኩዞ ለአምላክ የሰገደው በእምነት ነበር። |
ዮሴፍ ሊሞት በተቃረበ ጊዜ ስለ እስራኤል ልጆች ከግብፅ መውጣት በእምነት ተናገረ፤ ስለ አፅሙም መመሪያ ሰጣቸው። |
ሙሴ ከተወለደ በኋላ ወላጆቹ መልኩ የሚያምር ሕፃን መሆኑን ስላዩ የንጉሡን ትእዛዝ ሳይፈሩ ለሦስት ወር የሸሸጉት በእምነት ነበር። |
ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ ተብሎ ለመጠራት በእምነት እንቢ አለ፤ |
በኃጢአት ከሚገኝ ጊዜያዊ ደስታ ይልቅ ከአምላክ ሕዝብ ጋር መንገላታትን መረጠ፤ |
ምክንያቱም ቅቡዕ ሆኖ የሚደርስበት ነቀፋ በግብፅ ከሚገኝ ውድ ሀብት የላቀ እንደሆነ አስቧል፤ የሚከፈለውን ወሮታ በትኩረት ተመልክቷልና። |
ደግሞም በእምነት ግብፅን ለቆ ወጣ፤ ሆኖም ይህን ያደረገው የንጉሡን ቁጣ ፈርቶ አይደለም፤ የማይታየውን አምላክ እንደሚያየው አድርጎ በጽናት ቀጥሏልና። |
አጥፊው የበኩር ልጆቻቸውን እንዳይገድል ሙሴ ፋሲካን ያከበረውና መቃኖቹ ላይ ደም የረጨው በእምነት ነው። |
እስራኤላውያን በደረቅ ምድር የሚሄዱ ያህል ቀይ ባሕርን በእምነት ተሻገሩ፤ ይሁንና ግብፃውያን እንዲህ ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ሰመጡ። |
እስራኤላውያን የኢያሪኮን ግንብ ሰባት ቀን ከዞሩት በኋላ በእምነት ወደቀ። |
ዝሙት አዳሪዋ ረዓብ ታዛዥ ሳይሆኑ ከቀሩት ሰዎች ጋር ከመጥፋት የዳነችው በእምነት ነው፤ ምክንያቱም ሰላዮቹን በሰላም ተቀብላለች። |
እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን እላለሁ? ስለ ጌድዮን፣ ስለ ባርቅ፣ ስለ ሳምሶን፣ ስለ ዮፍታሔ፣ ስለ ዳዊት እንዲሁም ስለ ሳሙኤልና ስለ ሌሎቹ ነቢያት እንዳልተርክ ጊዜ ያጥረኛል። |
እነዚህ ሰዎች በእምነት መንግሥታትን ድል አድርገዋል፤ ጽድቅን አስፍነዋል፤ የተስፋን ቃል ተቀብለዋል፤ የአንበሶችን አፍ ዘግተዋል፤ |
የእሳትን ኃይል አጥፍተዋል፤ ከሰይፍ ስለት አምልጠዋል፤ ደካማ የነበሩት ብርታት አግኝተዋል፤ በጦርነት ኃያላን ሆነዋል፤ ወራሪ ሠራዊትን አባረዋል። |
ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀብለዋል፤ ሌሎች ወንዶች ግን ቤዛ ተከፍሎላቸው ነፃ መሆን ስላልፈለጉ ከባድ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፤ ይህን ያደረጉት የተሻለ ትንሣኤ ለማግኘት ሲሉ ነው። |
አዎ፣ ሌሎች ደግሞ መዘባበቻ በመሆንና በመገረፍ ይባስ ብሎም በመታሰርና ወህኒ ቤት በመጣል ፈተና ደርሶባቸዋል። |
በድንጋይ ተወግረዋል፤ ተፈትነዋል፤ በመጋዝ ለሁለት ተሰንጥቀዋል፤ በሰይፍ ተቀልተዋል፤ እየተቸገሩ፣ መከራ እየተቀበሉና እየተንገላቱ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ተንከራተዋል፤ |
ዓለም እንዲህ ዓይነት ሰዎች የሚገቡት ሆኖ አልተገኘም። በየበረሃው፣ በየተራራው፣ በየዋሻውና በምድር ውስጥ ባሉ ጉድጓዶች ተቅበዝብዘዋል። |
ይሁንና እነዚህ ሁሉ በእምነታቸው ምክንያት በመልካም የተመሠከረላቸው ቢሆኑም እንኳ የተስፋውን ቃል ፍጻሜ አላዩም፤ |
ምክንያቱም አምላክ ያለእኛ ወደ ፍጽምና እንዲደርሱ ዓላማው ስላልነበረ ለእኛ የተሻለ ነገር ለመስጠት አስቀድሞ አስቧል። |
በጥንት ዘመን አምላክ በተለያዩ ጊዜያትና በብዙ መንገዶች በነቢያት አማካኝነት ለአባቶቻችን ተናግሯል። |
አሁን ደግሞ በእነዚህ ቀናት መጨረሻ የሁሉም ነገር ወራሽ አድርጎ በሾመውና የተለያዩ ሥርዓቶችን በፈጠረበት በልጁ አማካኝነት ለእኛ ተናገረ። |
እሱ የአምላክ ክብር ነጸብራቅና የማንነቱ ትክክለኛ አምሳያ ነው፤ እሱም በኃያል ቃሉ ሁሉንም ነገር ደግፎ ያኖራል። እኛን ከኃጢአታችን ካነጻ በኋላም በሰማይ በግርማዊው ቀኝ ተቀምጧል። |
ስለዚህ ከመላእክት ስም እጅግ የላቀ ስም የወረሰ በመሆኑ ከእነሱ የተሻለ ሆኗል። |
ለምሳሌ፣ አምላክ “አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድኩህ” ደግሞም “አባት እሆነዋለሁ፤ እሱም ልጄ ይሆናል” ብሎ ከመላእክት መካከል ስለ የትኛው መልአክ ተናግሮ ያውቃል? |
ሆኖም የበኩር ልጁን እንደገና ወደ ዓለም የሚያመጣበትን ጊዜ በተመለከተ “የአምላክ መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ይላል። |
በተጨማሪም ስለ መላእክት ሲናገር “መላእክቱን መናፍስት፣ አገልጋዮቹን ደግሞ የእሳት ነበልባል ያደርጋል” ይላል። |
ስለ ልጁ ሲናገር ግን እንዲህ ይላል፦ “አምላክ ለዘላለም ዙፋንህ ነው፤ የመንግሥትህ በትርም የቅንነት በትረ መንግሥት ነው። |
ጽድቅን ወደድክ፤ ዓመፅን ጠላህ። ስለዚህ አምላክ ይኸውም አምላክህ ከባልንጀሮችህ ይበልጥ በደስታ ዘይት ቀባህ።” |
ደግሞም እንዲህ ይላል፦ “ጌታ ሆይ፣ አንተ በመጀመሪያ የምድርን መሠረት ጣልክ፤ ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው። |
እነሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ |
እንደ ካባ፣ እንደ ልብስም ትጠቀልላቸዋለህ፤ ደግሞም እንደ ልብስ ትለውጣቸዋለህ። አንተ ግን ያው ነህ፤ ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።” |
ይሁንና “ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” ብሎ ከመላእክት መካከል ስለ የትኛው መልአክ ተናግሮ ያውቃል? |
ሁሉም መዳን የሚወርሱትን እንዲያገለግሉ የሚላኩ ቅዱስ አገልግሎት የሚያከናውኑ መናፍስት አይደሉም? |
አብርሃም ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ የሳሌም ንጉሥና የልዑሉ አምላክ ካህን የሆነው ይህ መልከጼዴቅ አግኝቶት ባረከው፤ |
አብርሃም ደግሞ ከሁሉ ነገር አንድ አሥረኛ ሰጠው። በመጀመሪያ ስሙ “የጽድቅ ንጉሥ” ማለት ነው፤ ደግሞም የሳሌም ንጉሥ ማለትም “የሰላም ንጉሥ” ነው። |
አባትና እናትም ሆነ የዘር ሐረግ እንዲሁም ለዘመኑ መጀመሪያ፣ ለሕይወቱም መጨረሻ የለውም፤ ከዚህ ይልቅ የአምላክን ልጅ እንዲመስል በመደረጉ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል። |
እንግዲህ የቤተሰብ ራስ የሆነው አብርሃም ምርጥ ከሆነው ምርኮ ላይ አንድ አሥረኛውን የሰጠው ይህ ሰው ምን ያህል ታላቅ እንደነበረ ተመልከቱ። |
እርግጥ የክህነት ኃላፊነት የሚቀበሉ ከሌዊ ልጆች ወገን የሆኑት ሰዎች ምንም እንኳ ወንድሞቻቸው የአብርሃም ዘሮች ቢሆኑም ከሕዝቡ ማለትም ከገዛ ወንድሞቻቸው አሥራት እንዲሰበስቡ ሕጉ ያዛል። |
ሆኖም ከእነሱ የትውልድ ሐረግ ያልመጣው ይህ ሰው ከአብርሃም አሥራት የተቀበለ ሲሆን የተስፋ ቃል የተሰጠውን ሰው ባርኮታል። |
እንግዲህ አነስተኛ የሆነው ከእሱ በሚበልጠው እንደተባረከ ምንም ጥርጥር የለውም። |
በአንድ በኩል አሥራት የሚቀበሉት ሟች የሆኑ ሰዎች ሲሆኑ በሌላ በኩል ግን አሥራት የሚቀበለው ሕያው ሆኖ እንደሚኖር የተመሠከረለት ሰው ነው። |
እንግዲህ አሥራት የሚቀበለው ሌዊ እንኳ በአብርሃም በኩል አሥራት ከፍሏል ማለት ይቻላል፤ |
መልከጼዴቅ አብርሃምን ባገኘው ጊዜ ሌዊ ገና በአባቱ በአብርሃም አብራክ ውስጥ ነበርና። |
እንግዲህ ፍጽምና ሊገኝ የሚችለው በሌዊ ክህነት አማካኝነት ቢሆን ኖሮ (ክህነቱ ለሕዝቡ የተሰጠው ሕግ አንዱ ገጽታ ስለሆነ)፣ እንደ አሮን ሥርዓት ሳይሆን እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት ያለ ተብሎ የተነገረለት ሌላ ካህን መነሳቱ ምን ያስፈልግ ነበር? |
ክህነቱ ስለሚለወጥ ሕጉም የግድ መለወጥ ያስፈልገዋልና። |
ይህ ሁሉ ነገር የተነገረለት ሰው ከሌላ ነገድ የመጣ ነውና፤ ከዚህ ነገድ ማንም ወደ መሠዊያው ቀርቦ ያገለገለ የለም። |
ጌታችን ከይሁዳ ነገድ እንደወጣ የታወቀ ነውና፤ ይሁንና ሙሴ ከዚህ ነገድ ካህናት እንደሚገኙ የተናገረው ነገር የለም። |
ደግሞም እንደ መልከጼዴቅ ያለ ሌላ ካህን ሲነሳ ይህ ጉዳይ ይበልጥ ግልጽ ይሆናል፤ |
እሱ ካህን የሆነው በሥጋዊ ትውልድ ላይ በተመካውና ሕጉ በያዘው መሥፈርት ሳይሆን የማይጠፋ ሕይወት እንዲኖረው ባስቻለው ኃይል ነው። |
“እንደ መልከጼዴቅ፣ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ተብሎ ተመሥክሮለታልና። |
እንግዲህ የቀድሞው ትእዛዝ ደካማና ፍሬ ቢስ በመሆኑ ተሽሯል። |
ሕጉ የትኛውንም ነገር ወደ ፍጽምና አላደረሰምና፤ ወደ አምላክ የምንቀርብበት የተሻለ ተስፋ መሰጠቱ ግን ይህን ማድረግ ችሏል። |
በተጨማሪም ይህ ያለመሐላ እንዳልሆነ ሁሉ |
(ያለመሐላ ካህናት የሆኑ ሰዎች አሉና፤ እሱ ግን በመሐላ ካህን ሆኗል፤ ይህም የሆነው “ይሖዋ ‘አንተ ለዘላለም ካህን ነህ’ ብሎ ምሏል፤ ደግሞም ሐሳቡን አይለውጥም” በማለት ስለ እሱ የተናገረው አምላክ በማለው መሐላ መሠረት ነው፤) |
እንደዚሁም ኢየሱስ ለተሻለ ቃል ኪዳን ዋስትና ሆኗል። |
ከዚህም በተጨማሪ ካህናት አገልግሎታቸውን እንዳይቀጥሉ ሞት ስለሚያግዳቸው አንዱ ሌላውን እየተካ እንዲያገለግል ብዙዎች ካህናት መሆን ነበረባቸው፤ |
እሱ ግን ለዘላለም ሕያው ሆኖ ስለሚኖር ክህነቱ ተተኪ የለውም። |
ስለሆነም ለእነሱ ለመማለድ ሁልጊዜ ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእሱ አማካኝነት ወደ አምላክ የሚቀርቡትን ፈጽሞ ሊያድናቸውም ይችላል። |
እኛ የሚያስፈልገን ታማኝ፣ ቅን የሆነ፣ ያልረከሰ፣ ከኃጢአተኞች የተለየና ከሰማያት በላይ ከፍ ያለ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ነው። |
እነዚያ ሊቃነ ካህናት ያደርጉ እንደነበረው፣ በመጀመሪያ ለራሱ ኃጢአት ከዚያም ለሕዝቡ ኃጢአት በየዕለቱ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ምክንያቱም ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ ይህን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ፈጽሞታል። |
ሕጉ ድክመት ያለባቸውን ሰዎች ሊቃነ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕጉ በኋላ የመጣው የመሐላ ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የተደረገውን ልጅ ይሾማል። |
እርስ በርሳችሁ እንደ ወንድማማች መዋደዳችሁን ቀጥሉ። |
እንግዳ መቀበልን አትርሱ፤ አንዳንዶች ይህን ሲያደርጉ ሳያውቁት መላእክትን አስተናግደዋልና። |
በእስር ላይ ያሉትን ከእነሱ ጋር ታስራችሁ እንዳላችሁ አድርጋችሁ በማሰብ ሁልጊዜ አስታውሷቸው፤ እናንተም ራሳችሁ ገና በሥጋ ያላችሁ በመሆናችሁ እንግልት እየደረሰባቸው ያሉትን አስቡ። |
ጋብቻ በሁሉ ዘንድ ክቡር፣ መኝታውም ከርኩሰት የጸዳ ይሁን፤ አምላክ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ይፈርድባቸዋልና። |
አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር ነፃ ይሁን፤ ባሏችሁ ነገሮች ረክታችሁ ኑሩ። እሱ “ፈጽሞ አልተውህም፤ በምንም ዓይነት አልጥልህም” ብሏልና። |
ስለዚህ በሙሉ ልብ “ይሖዋ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም። ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን። |
የአምላክን ቃል የነገሯችሁን በመካከላችሁ ሆነው አመራር የሚሰጡትን አስቡ፤ ደግሞም ምግባራቸው ያስገኘውን ውጤት በሚገባ በማጤን በእምነታቸው ምሰሏቸው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.