text stringlengths 4 267 |
|---|
ከዚህም የተነሳ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሬ መከራ እየተቀበልኩ ነው፤ ደግሞም ታስሬአለሁ። ሆኖም የአምላክ ቃል አልታሰረም። |
ከዚህም የተነሳ የተመረጡትም በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት የሚገኘውን መዳን ከዘላለማዊ ክብር ጋር ያገኙ ዘንድ ለእነሱ ስል ሁሉንም ነገር በጽናት ተቋቁሜ እኖራለሁ። |
የሚከተለው ቃል እምነት የሚጣልበት ነው፦ አብረን ከሞትን አብረን ደግሞ በሕይወት እንደምንኖር የተረጋገጠ ነው፤ |
ጸንተን ከኖርን አብረን ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው እሱም ይክደናል፤ |
ታማኞች ሆነን ባንገኝ እሱ ምንጊዜም ታማኝ ሆኖ ይኖራል፤ እሱ ራሱን ሊክድ አይችልምና። |
ስለ ቃላት እንዳይነታረኩ በአምላክ ፊት እየመከርክ እነዚህን ነገሮች ዘወትር አሳስባቸው፤ እንዲህ ያለው ነገር በሚሰሙት ሰዎች ላይ ጉዳት ከማስከተል በስተቀር ምንም ጥቅም የለውም። |
የእውነትን ቃል በአግባቡ በመጠቀም፣ ተቀባይነት ሊያገኝ እንደሚገባውና ምንም የሚያፍርበት ነገር እንደሌለው ሠራተኛ አድርገህ ራስህን በአምላክ ፊት ለማቅረብ የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ። |
ሆኖም ቅዱስ የሆነውን ነገር ከሚጻረሩ ከንቱ ንግግሮች ራቅ፤ እንዲህ ያሉ ንግግሮች ሰዎች ይበልጥ ፈሪሃ አምላክ የሌላቸው እየሆኑ እንዲሄዱ ያደርጋሉና፤ |
እንዲህ ያሉ ንግግሮችን የሚናገሩ ሰዎች ቃላቸው እንደተመረዘ ቁስል ይሰራጫል። ከእነሱም መካከል ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ይገኙበታል። |
እነዚህ ሰዎች ‘ትንሣኤ ቀደም ብሎ ተከናውኗል’ ብለው በመናገር ከእውነት ርቀዋል፤ ደግሞም የአንዳንዶችን እምነት እያፈረሱ ነው። |
ይሁን እንጂ “ይሖዋ የእሱ የሆኑትን ያውቃል” እንዲሁም “የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት ጠንካራው የአምላክ መሠረት ጸንቶ ይኖራል። |
በአንድ ትልቅ ቤት ውስጥ የወርቅና የብር ዕቃ ብቻ ሳይሆን የእንጨትና የሸክላ ዕቃም ይኖራል፤ አንዳንዱ ክብር ላለው ዓላማ የሚያገለግል ሲሆን ሌላው ግን ክብር ለሌለው ዓላማ ያገለግላል። |
እንግዲህ ማንም ከእነዚህ ከኋለኞቹ ነገሮች ቢርቅ ክብር ላለው ዓላማ የሚያገለግል፣ የተቀደሰ፣ ለባለቤቱ የሚጠቅምና ለመልካም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ መሣሪያ ይሆናል። |
ስለዚህ ከወጣትነት ምኞቶች ሽሽ፤ ከዚህ ይልቅ በንጹሕ ልብ ጌታን ከሚጠሩት ጋር ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርንና ሰላምን ለማግኘት ተጣጣር። |
በተጨማሪም ጠብ ሊያስከትል እንደሚችል በመገንዘብ ሞኝነትና አላዋቂነት ከሚንጸባረቅበት ክርክር ራቅ። |
የጌታ ባሪያ ሊጣላ አይገባውምና፤ ከዚህ ይልቅ ለሰው ሁሉ ገር፣ ለማስተማር ብቁ የሆነና በደል ሲደርስበት ራሱን የሚገዛ፣ |
እንዲሁም ቀና አመለካከት የሌላቸውን በገርነት የሚያርም ሊሆን ይገባዋል። ምናልባትም አምላክ ትክክለኛ የእውነት እውቀት ያገኙ ዘንድ ለንስሐ ያበቃቸው ይሆናል፤ |
እነሱም ዲያብሎስ ፈቃዱን ያደርጉ ዘንድ በሕይወት እንዳሉ አጥምዶ እንደያዛቸው በመረዳት ወደ ልቦናቸው ተመልሰው ከእሱ ወጥመድ ሊወጡ ይችላሉ። |
በአምላክ ፊት እንዲሁም በሕያዋንና በሙታን ላይ በሚፈርደው በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አጥብቄ አሳስብሃለሁ፤ ደግሞም በእሱ መገለጥና በመንግሥቱ አማካኝነት አዝሃለሁ፦ |
ቃሉን ስበክ፤ አመቺ በሆነ ጊዜም ሆነ በአስቸጋሪ ጊዜ በጥድፊያ ስሜት አገልግል፤ በብዙ ትዕግሥትና በማስተማር ጥበብ ውቀስ፣ ገሥጽ እንዲሁም አጥብቀህ ምከር። |
ትክክለኛውን ትምህርት የማይታገሡበት ጊዜ ይመጣልና፤ ከዚህ ይልቅ ከራሳቸው ፍላጎት ጋር በሚስማማ ሁኔታ ጆሯቸውን እንዲኮረኩሩላቸው በዙሪያቸው አስተማሪዎችን ይሰበስባሉ። |
እውነትን ከመስማት ጆሯቸውን ይመልሳሉ፤ ለተረትም ጆሮ ይሰጣሉ። |
አንተ ግን በሁሉም ነገር የማስተዋል ስሜትህን ጠብቅ፣ መከራን በጽናት ተቋቋም፣ የወንጌላዊነትን ሥራ አከናውን እንዲሁም አገልግሎትህን በተሟላ ሁኔታ ፈጽም። |
እኔ እንደ መጠጥ መባ እየፈሰስኩ ነውና፤ ደግሞም ነፃ የምለቀቅበት ጊዜ በጣም ቀርቧል። |
መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፤ ሩጫውን ጨርሻለሁ፤ እምነትን ጠብቄአለሁ። |
ከዚህ በኋላ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ በፍርድ ቀን ይህን እንደ ሽልማት አድርጎ ይሰጠኛል፤ ይሁንና ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእሱን መገለጥ ለሚናፍቁ ሁሉ ነው። |
ወደ እኔ ቶሎ ለመምጣት የተቻለህን ሁሉ አድርግ። |
ዴማስ በአሁኑ ጊዜ ያለውን ሥርዓት ወዶ፣ ትቶኝ ወደ ተሰሎንቄ ሄዷልና፤ ቄርቂስ ወደ ገላትያ፣ ቲቶ ደግሞ ወደ ድልማጥያ ሄደዋል። |
አብሮኝ ያለው ሉቃስ ብቻ ነው። ማርቆስ በአገልግሎት ስለሚረዳኝ ከአንተ ጋር ይዘኸው ና። |
ቲኪቆስን ግን ወደ ኤፌሶን ልኬዋለሁ። |
ስትመጣ በጥሮአስ፣ ካርጶስ ጋ የተውኩትን ካባ እንዲሁም የመጽሐፍ ጥቅልሎቹን በተለይም ብራናዎቹን አምጣልኝ። |
የመዳብ አንጥረኛው እስክንድር ብዙ ጉዳት አድርሶብኛል። ይሖዋ እንደ ሥራው ይከፍለዋል። |
አንተም ከእሱ ተጠንቀቅ፤ መልእክታችንን ክፉኛ ተቃውሟልና። |
የመጀመሪያ መከላከያዬን ባቀረብኩበት ወቅት ሁሉም ትተውኝ ሄዱ እንጂ ከእኔ ጎን የቆመ ማንም አልነበረም፤ አምላክ ይህን አይቁጠርባቸው። |
ሆኖም የስብከቱ ሥራ በእኔ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ እንዲፈጸምና ብሔራት ሁሉ እንዲሰሙት ጌታ አጠገቤ ቆሞ ኃይል ሰጠኝ፤ ከአንበሳ አፍም ዳንኩ። |
ጌታ ከክፉ ሥራ ሁሉ ይታደገኛል፤ እንዲሁም አድኖኝ ለሰማያዊ መንግሥቱ ያበቃኛል። ለእሱ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን። |
ለጵርስቅላና ለአቂላ እንዲሁም ለኦኔሲፎሮስ ቤተሰብ ሰላምታ አቅርብልኝ። |
ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀርቷል፤ ጢሮፊሞስ ግን ስለታመመ በሚሊጢን ትቼዋለሁ። |
ክረምቱ ከመግባቱ በፊት ለመምጣት የተቻለህን ሁሉ አድርግ። ኤውቡሉስ ሰላም ብሎሃል፤ እንዲሁም ጱዴስ፣ ሊኖስ፣ ቅላውዲያና ወንድሞች ሁሉ ሰላምታቸውን ልከውልሃል። |
ጌታ ከምታሳየው መንፈስ ጋር ይሁን። ጸጋው ከእናንተ ጋር ይሁን። |
የአምላክ ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ። ይህ ሐዋርያ፣ አገልግሎቱ ከአምላክ ምርጦች እምነትና ከእውነት ትክክለኛ እውቀት ጋር የሚስማማ ሲሆን ይህ እውነት ለአምላክ ያደሩ ሆኖ ከመኖር ጋር የተቆራኘ ነው፤ |
ደግሞም ሊዋሽ የማይችለው አምላክ ከረጅም ዘመናት በፊት በሰጠው የዘላለም ሕይወት ተስፋ ላይ የተመሠረተ ነው፤ |
ይሁንና አዳኛችን በሆነው አምላክ ትእዛዝ በአደራ በተሰጠኝ የስብከቱ ሥራ አማካኝነት ራሱ በወሰነው ጊዜ ቃሉ እንዲታወቅ አደረገ፤ |
የጋራችን በሆነው እምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነው ለቲቶ፦ አባት ከሆነው አምላክና አዳኛችን ከሆነው ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ሰላም ለአንተ ይሁን። |
አንተን በቀርጤስ የተውኩህ ያልተስተካከሉትን ነገሮች እንድታስተካክልና በሰጠሁህ መመሪያ መሠረት በየከተማው ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው፤ |
ይኸውም ከክስ ነፃ የሆነ፣ የአንዲት ሚስት ባል እንዲሁም በስድነት ወይም በዓመፀኝነት የማይከሰሱ አማኝ የሆኑ ልጆች ያሉት ማንም ሰው ካለ እንድትሾም ነው። |
ምክንያቱም የበላይ ተመልካች በአምላክ የተሾመ መጋቢ እንደመሆኑ መጠን ከክስ ነፃ መሆን አለበት፤ በራሱ ሐሳብ የሚመራ፣ ግልፍተኛ፣ ሰካራም፣ ኃይለኛና አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚስገበገብ ሊሆን አይገባም፤ |
ከዚህ ይልቅ እንግዳ ተቀባይ፣ ጥሩ የሆነውን ነገር የሚወድ፣ ጤናማ አስተሳሰብ ያለው፣ ጻድቅ፣ ታማኝ፣ ራሱን የሚገዛ፣ |
እንዲሁም ትክክለኛ በሆነው ትምህርት ማበረታታትም ሆነ ይህን ትምህርት የሚቃወሙትን መውቀስ ይችል ዘንድ የማስተማር ጥበቡን ሲጠቀም የታመነውን ቃል በጥብቅ የሚከተል ሊሆን ይገባል። |
ዓመፀኞች፣ በከንቱ የሚለፈልፉና አታላዮች የሆኑ በተለይም ግርዘትን በጥብቅ የሚከተሉ ብዙ ሰዎች አሉና። |
እነዚህ ሰዎች አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ማስተማር የማይገባቸውን ትምህርት በማስተማር የመላውን ቤተሰብ እምነት እያፈረሱ ስለሆነ አፋቸውን ማዘጋት ያስፈልጋል። |
ከእነሱ መካከል የሆነ የገዛ ራሳቸው ነቢይ “የቀርጤስ ሰዎች ምንጊዜም ውሸታሞች፣ አደገኛ አውሬዎችና ሥራ ፈት ሆዳሞች ናቸው” ብሏል። |
ይህ የምሥክርነት ቃል እውነት ነው። ለዚህም ሲባል እነሱን አጥብቀህ መውቀስህን ቀጥል፤ ይኸውም በእምነት ጠንካሮች እንዲሆኑ |
እንዲሁም ለአይሁዳውያን ተረቶችና ከእውነት የራቁ ሰዎች ለሚሰጡት ትእዛዝ ትኩረት እንዳይሰጡ ነው። |
ንጹሕ ለሆኑ ሰዎች ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው፤ ለረከሱና እምነት ለሌላቸው ሰዎች ግን ንጹሕ የሆነ ነገር የለም፤ አእምሯቸውም ሆነ ሕሊናቸው የረከሰ ነውና። |
አምላክን እንደሚያውቁ በይፋ ይናገራሉ፤ ሆኖም በሥራቸው ይክዱታል፤ ምክንያቱም አስጸያፊና የማይታዘዙ እንዲሁም ለማንኛውም ዓይነት መልካም ሥራ የማይበቁ ናቸው። |
ለመንግሥታትና ለባለሥልጣናት እንዲገዙና እንዲታዘዙ እንዲሁም ለመልካም ሥራ ሁሉ ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስባቸው፤ |
ደግሞም ስለ ማንም ክፉ ነገር እንዳይናገሩ፣ ጠበኞች እንዳይሆኑ ከዚህ ይልቅ ምክንያታዊ እንዲሆኑና ለሰው ሁሉ ገርነትን በተሟላ ሁኔታ እንዲያንጸባርቁ አሳስባቸው። |
እኛም በአንድ ወቅት የማናመዛዝን፣ የማንታዘዝ፣ የምንስት፣ ለተለያየ ምኞትና ሥጋዊ ደስታ የምንገዛ፣ በክፋትና በቅናት የምንኖር፣ በሰዎች ዘንድ የምንጠላና እርስ በርስ የማንዋደድ ነበርን። |
ይሁን እንጂ አዳኛችን የሆነው አምላክ ደግነትና ለሰው ልጆች ያለው ፍቅር በተገለጠ ጊዜ |
(እኛ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን በምሕረቱ) እኛን አጥቦ ሕያው በማድረግና በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት በማደስ አዳነን። |
ይህን መንፈስ አዳኛችን በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በእኛ ላይ አትረፍርፎ አፈሰሰው፤ |
ይህን ያደረገው በእሱ ጸጋ አማካኝነት ከጸደቅን በኋላ ከተስፋችን ጋር በሚስማማ ሁኔታ የዘላለም ሕይወትን እንድንወርስ ነው። |
እነዚህ ቃላት እምነት የሚጣልባቸው ናቸው፤ ደግሞም በአምላክ ያመኑ ሁሉ መልካም ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንዲያተኩሩ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ ዘወትር አስረግጠህ እንድትናገር እፈልጋለሁ። እነዚህ ነገሮች መልካምና ለሰዎች ጠቃሚ ናቸው። |
ሆኖም ሞኝነት ከሚንጸባረቅበት ክርክር፣ ከትውልድ ሐረግ ቆጠራ፣ ከጭቅጭቅና ሕጉን በተመለከተ ከሚነሳ ጠብ ራቅ፤ እነዚህ ነገሮች ምንም የማይጠቅሙና ከንቱ ናቸው። |
ኑፋቄ የሚያስፋፋን ሰው ከአንዴም ሁለቴ አጥብቀህ ምከረው። ካልሰማህ ግን ከእሱ ራቅ፤ |
እንዲህ ዓይነቱ ሰው ከትክክለኛው መንገድ የወጣና ኃጢአት እየሠራ ያለ ከመሆኑም ሌላ በራሱ ላይ እንደፈረደ እወቅ። |
አርጤማስን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፣ እኔ ወዳለሁበት ወደ ኒቆጶሊስ ለመምጣት የተቻለህን ሁሉ አድርግ፤ ክረምቱን በዚያ ለማሳለፍ ወስኛለሁና። |
ሕጉን ጠንቅቆ የሚያውቀው ዜናስም ሆነ አጵሎስ ለጉዟቸው የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ እንዲሟላላቸው የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ። |
ይሁን እንጂ አሳሳቢ ችግር ሲፈጠር መርዳት እንዲችሉና ፍሬ ቢሶች እንዳይሆኑ የእኛም ሰዎች በመልካም ሥራ መጠመድን ይማሩ። |
አብረውኝ ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል። ለሚወዱን የእምነት ባልንጀሮቻችን ሰላምታ አቅርብልኝ። የአምላክ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን። |
አንተ ግን ምንጊዜም ከትክክለኛ ትምህርት ጋር የሚስማማ ነገር ተናገር። |
አረጋውያን ወንዶች በልማዶቻቸው ረገድ ልከኞች፣ ቁም ነገረኞች፣ ጤናማ አስተሳሰብ ያላቸው እንዲሁም በእምነት፣ በፍቅርና በጽናት ጤናሞች ይሁኑ። |
በተመሳሳይም አረጋውያን ሴቶች ለቅዱሳን ሰዎች የሚገባ ባሕርይ ያላቸው፣ ስም የማያጠፉ፣ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይገዙ እንዲሁም ጥሩ የሆነውን ነገር የሚያስተምሩ ይሁኑ፤ |
ይህም ወጣት ሴቶችን በመምከር ባሎቻቸውን የሚወዱ፣ ልጆቻቸውን የሚወዱ፣ |
ጤናማ አስተሳሰብ ያላቸው፣ ንጹሐን፣ በቤት ውስጥ የሚሠሩ፣ ጥሩዎችና ለባሎቻቸው የሚገዙ እንዲሆኑ ለማድረግ ያስችላቸዋል፤ ይህም የአምላክ ቃል እንዳይሰደብ ነው። |
በተመሳሳይም ወጣት ወንዶች ጤናማ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው አሳስባቸው፤ |
በማንኛውም ሁኔታ መልካም ሥራ በመሥራት አርዓያ መሆንህን አሳይ። ንጹሕ የሆነውን ነገር በቁም ነገር አስተምር፤ |
ደግሞም ሊነቀፍ የማይችል ጤናማ አነጋገር በመጠቀም አስተምር፤ ይኸውም ተቃዋሚዎች ስለ እኛ የሚናገሩት መጥፎ ነገር አጥተው እንዲያፍሩ ነው። |
ባሪያዎች ጌቶቻቸውን ለማስደሰት ጥረት በማድረግ በሁሉም ነገር ይገዙላቸው፤ የአጸፋ ቃልም አይመልሱላቸው፤ |
ደግሞም ሊሰርቋቸው አይገባም፤ ከዚህ ይልቅ አዳኛችን የሆነው አምላክ ትምህርት በሁሉም መንገድ ውበት እንዲጎናጸፍ ያደርጉ ዘንድ ሙሉ በሙሉ እምነት የሚጣልባቸው ይሁኑ። |
የአምላክ ጸጋ ተገልጧልና፤ ጸጋው ለሁሉም ዓይነት ሰዎች መዳን ያስገኛል። |
ይህም ጸጋ ፈሪሃ አምላክ በጎደለው መንገድ መኖርና ዓለማዊ ምኞቶችን መከተል ትተን አሁን ባለው በዚህ ሥርዓት ውስጥ ጤናማ አስተሳሰብ በመያዝ፣ በጽድቅና ለአምላክ በማደር እንድንኖር ያሠለጥነናል፤ |
በዚህ ሁኔታ አስደሳች የሆነውን ተስፋ እንዲሁም የታላቁን አምላክና የአዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በክብር መገለጥ እንጠባበቃለን፤ |
ክርስቶስ ከማንኛውም ዓይነት የዓመፅ ሕይወት እኛን ነፃ ለማውጣትና ለመልካም ሥራ የሚቀና ልዩ ንብረቱ የሆነ ሕዝብ ለራሱ ለማንጻት ሕይወቱን ለእኛ ሰጥቷል። |
እነዚህን ነገሮች፣ በሙሉ ሥልጣን መናገርህን፣ አጥብቀህ መምከርህንና መውቀስህን ቀጥል። ማንም ሰው ፈጽሞ አይናቅህ። |
ለክርስቶስ ኢየሱስ ሲል እስረኛ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፣ ለተወደደው የሥራ ባልደረባችን ለፊልሞና፣ |
ለእህታችን ለአፍብያና አብሮን የክርስቶስ ወታደር ለሆነው ለአርክጳ እንዲሁም በቤትህ ላለው ጉባኤ፦ |
አባታችን ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። |
አንተን በጸሎቴ በጠቀስኩ ቁጥር ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ፤ |
ስለ እምነትህ እንዲሁም ለጌታ ኢየሱስና ለቅዱሳን ሁሉ ስላለህ ፍቅር እሰማለሁና። |
ከሌሎች ጋር የምትጋራው እምነት በክርስቶስ አማካኝነት መልካም ነገሮችን ሁሉ እንደተቀበልን እንድትገነዘብ ይረዳህ ዘንድ እጸልያለሁ። |
ወንድሜ ሆይ፣ ስለምታሳየው ፍቅር በመስማቴ እጅግ ተደስቻለሁ እንዲሁም ተጽናንቻለሁ፤ ምክንያቱም የቅዱሳን ልብ በአንተ አማካኝነት ታድሷል። |
ስለዚህ ተገቢ የሆነውን ነገር እንድታደርግ አንተን ለማዘዝ ከክርስቶስ ጋር በተያያዘ ሙሉ ነፃነት ቢኖረኝም፣ |
እኔ ጳውሎስ አረጋዊና አሁን ደግሞ ለክርስቶስ ኢየሱስ ስል እስረኛ እንደመሆኔ መጠን ፍቅርን መሠረት በማድረግ እለምንሃለሁ። |
በእስር ላይ እያለሁ እንደ አባት የሆንኩለትን ልጄን አናሲሞስን በተመለከተ እለምንሃለሁ። |
እሱ ቀደም ሲል ምንም አይጠቅምህም ነበር፤ አሁን ግን ለአንተም ሆነ ለእኔ የሚጠቅም ሰው ሆኗል። |
እሱን፣ አዎ ከልቤ የምወደውን እሱን ወደ አንተ መልሼ ልኬዋለሁ። |
ለምሥራቹ ስል እዚህ ታስሬ ሳለሁ በአንተ ፋንታ እኔን እንዲያገለግል ለራሴ እዚሁ ባስቀረው ደስ ይለኝ ነበር። |
ነገር ግን የምታደርገው መልካም ነገር በራስህ ፈቃድ እንጂ በግዴታ እንዳይሆን አንተ ሳትስማማ ምንም ነገር ማድረግ አልፈልግም። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.