text stringlengths 4 267 |
|---|
ራሔልም “አምላክ ዳኛ ሆነልኝ፤ ቃሌንም ሰማ። በመሆኑም ወንድ ልጅ ሰጠኝ” አለች። በዚህም የተነሳ ስሙን ዳን አለችው። |
የራሔል አገልጋይ ባላ በድጋሚ ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። |
ራሔልም “ከእህቴ ጋር ብርቱ ትግል ገጠምኩ፤ አሸናፊም ሆንኩ!” አለች። በመሆኑም ስሙን ንፍታሌም አለችው። |
ሊያ ልጅ መውለድ እንዳቆመች ስትረዳ አገልጋይዋን ዚልጳን ለያዕቆብ ሚስት እንድትሆነው ሰጠችው። |
የሊያም አገልጋይ ዚልጳ ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት። |
ከዚያም ሊያ “ምንኛ መታደል ነው!” አለች። በመሆኑም ስሙን ጋድ አለችው። |
ከዚያ በኋላ የሊያ አገልጋይ ዚልጳ ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። |
ከዚያም ሊያ “ምንኛ ደስተኛ ነኝ! በእርግጥም ከእንግዲህ ሴቶች ደስተኛ ይሉኛል” አለች። በመሆኑም ስሙን አሴር አለችው። |
የስንዴ መከር በሚሰበሰብበት ወቅት ሮቤል ወደ ሜዳ ወጣ፤ ከሜዳውም ላይ ፍሬ ለቀመ። ለእናቱ ለሊያም አመጣላት። ከዚያም ራሔል ሊያን “እባክሽ፣ ልጅሽ ካመጣው ፍሬ የተወሰነ ስጪኝ” አለቻት። |
በዚህ ጊዜ ሊያ “ባሌን የወሰድሽብኝ አነሰሽና አሁን ደግሞ ልጄ ያመጣውን ፍሬ መውሰድ ትፈልጊያለሽ?” አለቻት። በመሆኑም ራሔል “እሺ፣ ልጅሽ ባመጣው ፍሬ ፋንታ ዛሬ ማታ ከአንቺ ጋር ይደር” አለቻት። |
ያዕቆብ የዚያን ቀን ምሽት ከእርሻ ሲመለስ ሊያ ወጥታ ተቀበለችውና “ልጄ ባመጣው ፍሬ ስለተከራየሁህ ዛሬ የምትተኛው ከእኔ ጋር ነው” አለችው። ስለሆነም በዚያ ሌሊት ከእሷ ጋር አደረ። |
አምላክም ሊያን ሰማት፤ መልስም ሰጣት፤ እሷም ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ አምስተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። |
ሊያም “አገልጋዬን ለባሌ ስለሰጠሁ አምላክ ደሞዜን ከፈለኝ” አለች። በመሆኑም ስሙን ይሳኮር አለችው። |
ሊያም በድጋሚ ፀነሰች፤ ከዚያም ለያዕቆብ ስድስተኛ ወንድ ልጅ ወለደችለት። |
ሊያም “አምላክ አድሎኛል፤ አዎ፣ መልካም ስጦታ ሰጥቶኛል። ለባሌ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለወለድኩለት ከእንግዲህ ይታገሠኛል” አለች። በመሆኑም ስሙን ዛብሎን አለችው። |
ከዚያ በኋላ ሴት ልጅ ወለደች፤ ስሟንም ዲና አለቻት። |
በመጨረሻም አምላክ ራሔልን አሰባት፤ ልመናዋንም ሰምቶ መፀነስ እንድትችል በማድረግ ጸሎቷን መለሰላት። |
እሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። ከዚያም “አምላክ ነቀፋዬን አስወገደልኝ!” አለች። |
በመሆኑም “ይሖዋ ሌላ ወንድ ልጅ ጨመረልኝ” በማለት ስሙን ዮሴፍ አለችው። |
ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ብዙም ሳይቆይ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ስፍራዬና ወደ ምድሬ እንድመለስ አሰናብተኝ። |
ለእነሱ ስል ያገለገልኩህን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፤ ምን ያህል እንዳገለገልኩህ በሚገባ ታውቃለህ።” |
ከዚያም ላባ “በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ ከእኔ ጋር ተቀመጥ፤ ይሖዋ እየባረከኝ ያለው በአንተ የተነሳ መሆኑን በንግርት ተረድቻለሁ” አለው። |
ከዚያም “ደሞዝህን አሳውቀኝና እሰጥሃለሁ” አለው። |
በመሆኑም ያዕቆብ እንዲህ አለው፦ “እንዴት እንዳገለገልኩህና መንጋህም ምን ያህል እየበዛልህ እንዳለ ታውቃለህ፤ |
እኔ ከመምጣቴ በፊት የነበረህ ነገር ጥቂት እንደሆነና እኔ ከመጣሁ በኋላ ግን ከብቶችህ በጣም እየበዙ እንደሄዱ፣ ይሖዋም እንደባረከህ ታውቃለህ። ታዲያ ለራሴ ቤት አንድ ነገር የማደርገው መቼ ነው?” |
ከዚያም ላባ “ምን እንድሰጥህ ትፈልጋለህ?” አለው። ያዕቆብም እንዲህ አለ፦ “እኔ ምንም ነገር እንድትሰጠኝ አልፈልግም! የምጠይቅህን አንድ ነገር ብቻ የምታደርግልኝ ከሆነ መንጋህን መጠበቄንና መንከባከቤን እቀጥላለሁ። |
ዛሬ በመንጎችህ ሁሉ መካከል እዘዋወራለሁ። አንተም ከመንጋው መካከል ጠቃጠቆ ያለባቸውንና ዥጉርጉር የሆኑትን በጎች ሁሉ፣ ከጠቦቶቹም መካከል ጥቁር ቡናማ የሆኑትን በጎች ሁሉ እንዲሁም ዥጉርጉር የሆኑትንና ጠቃጠቆ ያለባቸውን እንስት ፍየሎች ሁሉ ለይ። ከዚህ በኋላ እንዲህ ዓይነቶቹ የእኔ ደሞዝ ይሆናሉ። |
ወደፊት ደሞዜን ለመመልከት በምትመጣበት ጊዜ ጽድቄ ስለ እኔ ይናገራል፤ ከእንስት ፍየሎቹ መካከል ጠቃጠቆ የሌለበትና ዥጉርጉር ያልሆነ እንዲሁም ከጠቦቶቹ መካከል ጥቁር ቡናማ ያልሆነ በእኔ ዘንድ ከተገኘ ያ የተሰረቀ እንደሆነ ይቆጠራል።” |
በዚህ ጊዜ ላባ “ይሄማ ጥሩ ነው! እንዳልከው ይሁን” አለው። |
ከዚያም በዚያኑ ቀን ሽንትር ያለባቸውንና ዥጉርጉር የሆኑትን ተባዕት ፍየሎች ሁሉ፣ ጠቃጠቆ ያለባቸውንና ዥጉርጉር የሆኑትን እንስት ፍየሎች ሁሉ፣ ነጭ የሚባል ነገር ያለበትን ሁሉ እንዲሁም ከጠቦቶቹ መካከል ጥቁር ቡናማ የሆኑትን ሁሉ ለየ፤ እነዚህንም ወንዶች ልጆቹ እንዲጠብቋቸው ሰጣቸው። |
ከዚህ በኋላ በእሱና በያዕቆብ መካከል የሦስት ቀን መንገድ ያህል ርቀት እንዲኖር አደረገ፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን መንጎች ይጠብቅ ጀመር። |
ከዚያም ያዕቆብ ከሊብነህ፣ ከአልሞንድና ከአርሞን ዛፎች ላይ የተቆረጡ እርጥብ በትሮችን ወሰደ፤ በመቀጠልም በትሮቹን አለፍ አለፍ ብሎ በመላጥና ነጩ እንዲታይ በማድረግ ዥጉርጉር እንዲሆኑ አደረገ። |
ከዚያም የላጣቸውን በትሮች ወስዶ መንጎቹ ውኃ ለመጠጣት ሲመጡ እንዲያዩአቸው በመንጎቹ ፊት ለፊት በቦዮቹ ማለትም ውኃ በሚጠጡባቸው ገንዳዎች ውስጥ አስቀመጣቸው፤ ይህን ያደረገውም መንጎቹ ውኃ ለመጠጣት ሲመጡ በበትሮቹ ፊት ለስሪያ እንዲነሳሱ ለማድረግ ነው። |
ስለዚህ መንጎቹ በበትሮቹ ፊት ለስሪያ ይነሳሱ ነበር፤ መንጎቹም ሽንትርና ጠቃጠቆ ያለባቸውን እንዲሁም ዥጉርጉር የሆኑ ግልገሎችን ይወልዱ ነበር። |
ከዚያም ያዕቆብ ጠቦቶቹን ለየ፤ ከዚያም መንጎቹ በላባ መንጎች መካከል ወዳሉት ሽንትር ወዳለባቸውና ጥቁር ቡናማ ወደሆኑት ሁሉ እንዲመለከቱ አደረገ። ከዚያም የራሱን መንጎች ለየ፤ ከላባ መንጎች ጋር አልቀላቀላቸውም። |
ያዕቆብም ብርቱ የሆኑት እንስሳት ለስሪያ በተነሳሱ ቁጥር በትሮቹን በመንጎቹ ፊት ለፊት ገንዳዎቹ ውስጥ ያስቀምጣቸው ነበር፤ እንዲህ የሚያደርገው መንጎቹ በበትሮቹ አማካኝነት ለስሪያ እንዲነሳሱ ለማድረግ ነበር። |
እንስሶቹ ደካማ ሲሆኑ ግን በትሮቹን ገንዳዎቹ ውስጥ አያስቀምጥም ነበር። ስለሆነም ደካማ ደካማዎቹ ለላባ ሲሆኑ ብርቱ ብርቱዎቹ ግን ለያዕቆብ ሆኑ። |
በዚህ መንገድ ይህ ሰው እጅግ ባለጸጋ እየሆነ ሄደ፤ የብዙ መንጎች፣ የወንድና የሴት አገልጋዮች፣ የግመሎች እንዲሁም የአህዮች ባለቤት ሆነ። |
አምላክም ኖኅንና ወንዶች ልጆቹን ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት። |
አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በምድር ላይ ባለ በእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር፣ በሰማያት ላይ በሚበር በእያንዳንዱ ፍጡር እንዲሁም በመሬት ላይ በሚንቀሳቀስ ማንኛውም ፍጡርና በባሕር ውስጥ ባለ ዓሣ ሁሉ ላይ ይሁን። ይኸው ሁሉም በእጃችሁ ውስጥ እንዲሆኑ ተሰጥተዋል። |
በሕይወት የሚንቀሳቀስ እያንዳንዱ እንስሳ ምግብ ይሁናችሁ። የለመለመውን ተክል እንደሰጠኋችሁ ሁሉ እነዚህን በሙሉ ሰጥቻችኋለሁ። |
ሕይወቱ ማለትም ደሙ በውስጡ ያለበትን ሥጋ ብቻ አትብሉ። |
ከዚህም በተጨማሪ ሕይወታችሁ የሆነውን ደማችሁን የሚያፈሰውን ሁሉ ተጠያቂ አደርገዋለሁ። እያንዳንዱን ሕያው ፍጡር ተጠያቂ አደርገዋለሁ፤ እያንዳንዱንም ሰው ለወንድሙ ሕይወት ተጠያቂ አደርገዋለሁ። |
አምላክ ሰውን በአምሳሉ ስለሠራው የሰውን ደም የሚያፈስ ማንም ሰው የእሱም ደም በሰው እጅ ይፈስሳል። |
እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፤ ቁጥራችሁም በምድር ላይ እጅግ ይጨምር፤ ደግሞም ተባዙ።” |
አምላክም ኖኅንና ከእሱ ጋር ያሉትን ወንዶች ልጆቹን እንዲህ አላቸው፦ |
“እኔም አሁን፣ ከእናንተና ከእናንተ በኋላ ከሚመጡት ዘሮቻችሁ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ |
እንዲሁም ከእናንተ ጋር ካለው ከእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር ማለትም ከወፎች፣ ከእንስሳት፣ አብረዋችሁ በምድር ላይ ከሚኖሩት ሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ እንዲሁም ከመርከቡ ከወጡት ሁሉ ጋር ይኸውም በምድር ላይ ከሚገኝ ከእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ። |
አዎ፣ ከእንግዲህ ሥጋ ሁሉ በጥፋት ውኃ እንደማይጠፋ እንዲሁም የጥፋት ውኃ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን ፈጽሞ እንደማያጠፋት ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ።” |
በተጨማሪም አምላክ እንዲህ አለ፦ “በእኔና በእናንተ እንዲሁም ከእናንተ ጋር ባለው በእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር መካከል ለመሠረትኩት ቃል ኪዳን ምልክቱ ይህ ነው፤ ይህም ቃል ኪዳን በመጪዎቹ ትውልዶች ሁሉ ጸንቶ ይኖራል። |
ቀስተ ደመናዬን በደመናው ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምልክት ሆኖ ያገለግላል። |
ምድርን በደመና በጋረድኩ ጊዜ ሁሉ ቀስተ ደመናው በደመናው ላይ ይታያል። |
እኔም ከእናንተ እንዲሁም ከማንኛውም ዓይነት ሕያው ፍጡር ሁሉ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሥጋን ሁሉ ለማጥፋት የጥፋት ውኃ ፈጽሞ አይወርድም። |
ቀስተ ደመናው በደመናው ላይ ይታያል፤ እኔም እሱን በማይበት ጊዜ በአምላክና በምድር ላይ በሚኖር በማንኛውም ዓይነት ሕያው ፍጡር መካከል ያለውን ዘላለማዊ ቃል ኪዳን አስታውሳለሁ።” |
አምላክም “በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ሁሉ መካከል ለመሠረትኩት ቃል ኪዳን ምልክቱ ይህ ነው” በማለት ለኖኅ በድጋሚ ነገረው። |
ከመርከቡ የወጡት የኖኅ ወንዶች ልጆች ሴም፣ ካምና ያፌት ናቸው። ከጊዜ በኋላ ካም፣ ከነአንን ወለደ። |
የኖኅ ወንዶች ልጆች እነዚህ ሦስቱ ነበሩ፤ የምድር ሕዝብ ሁሉ የተገኘው ከእነሱ ሲሆን በኋላም ወደተለያየ አካባቢ ተሰራጨ። |
ኖኅም ገበሬ ሆነ፤ የወይን እርሻም አለማ። |
አንድ ቀን ኖኅ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰከረ፤ በድንኳኑም ውስጥ ራቁቱን ሆነ። |
የከነአን አባት ካምም የአባቱን እርቃን አየ፤ ውጭ ላሉት ሁለት ወንድሞቹም ነገራቸው። |
ስለዚህ ሴምና ያፌት ልብስ ወስደው ትከሻቸው ላይ በማድረግ የኋሊት እየተራመዱ ገቡ። በዚህ መንገድም ፊታቸውን ወደ አባታቸው ሳያዞሩ እርቃኑን ሸፈኑ፤ በመሆኑም የአባታቸውን እርቃን አላዩም። |
ኖኅ ከወይን ጠጅ ስካሩ ሲነቃ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን አወቀ፤ |
እንዲህም አለ፦ “ከነአን የተረገመ ይሁን። ለወንድሞቹም የባሪያ ባሪያ ይሁን።” |
በተጨማሪም እንዲህ አለ፦ “የሴም አምላክ ይሖዋ ይወደስ፤ከነአንም የእሱ ባሪያ ይሁን። |
አምላክ ለያፌት ሰፊ መሬት ይስጠው፤በሴም ድንኳኖች ውስጥም ይኑር። ከነአን ለእሱም ጭምር ባሪያ ይሁን።” |
ኖኅ ከጥፋት ውኃው በኋላ 350 ዓመት ኖረ። |
በመሆኑም ኖኅ በአጠቃላይ 950 ዓመት ኖረ፤ ከዚያም ሞተ። |
በዚሁ ጊዜ አካባቢ ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ በመውረድ ሂራ በሚባል አዱላማዊ ሰው አቅራቢያ ድንኳኑን ተከለ። |
በዚያም ሹአ የሚባል የአንድ ከነአናዊ ሰው ሴት ልጅ አየ። እሷንም አገባትና ከእሷ ጋር ግንኙነት ፈጸመ፤ |
እሷም ፀነሰች። ወንድ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ኤር አለው። |
ዳግመኛም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ ስሙንም ኦናን አለችው። |
በድጋሚም ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም አለችው። እሱም ልጅ በወለደችለት ጊዜ አክዚብ በሚባል ቦታ ነበር። |
ከጊዜ በኋላ ይሁዳ ለበኩር ልጁ ለኤር ሚስት አመጣለት፤ ስሟም ትዕማር ይባል ነበር። |
ይሁንና የይሁዳ የበኩር ልጅ ኤር ይሖዋ ያዘነበት ሰው ነበር፤ በመሆኑም ይሖዋ በሞት ቀሰፈው። |
በዚህ የተነሳ ይሁዳ ኦናንን “ከወንድምህ ሚስት ጋር ግንኙነት በመፈጸም የዋርሳነት ግዴታህን ተወጣ፤ ለወንድምህም ዘር ተካለት” አለው። |
ኦናን ግን የሚወለደው ልጅ የእሱ ልጅ እንደሆነ ተደርጎ እንደማይቆጠር ያውቅ ነበር። በመሆኑም ለወንድሙ ዘር ላለመተካት ሲል ከወንድሙ ሚስት ጋር ግንኙነት በሚፈጽምበት ጊዜ ዘሩን መሬት ላይ ያፈስ ነበር። |
እሱም ያደረገው ነገር በይሖዋ ፊት መጥፎ ስለነበር አምላክ በሞት ቀሰፈው። |
ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን “ልጄ ሴሎም እስኪያድግ ድረስ በአባትሽ ቤት መበለት ሆነሽ ተቀመጪ” አላት፤ ይህን ያላት ‘እሱም እንደ ወንድሞቹ ሊሞትብኝ ይችላል’ ብሎ ስላሰበ ነው። ስለዚህ ትዕማር ሄዳ በአባቷ ቤት መኖር ጀመረች። |
የተወሰነ ጊዜ ካለፈ በኋላም የሹአ ልጅ የሆነችው የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳም ሐዘን ተቀምጦ ተነሳ፤ ከዚያም ከአዱላማዊው ወዳጁ ከሂራ ጋር በመሆን በጎቹን የሚሸልቱለት ሰዎች ወዳሉበት ወደ ቲምና ሄደ። |
ትዕማርም “አማትሽ በጎቹን ለመሸለት ወደ ቲምና እየወጣ ነው” ተብሎ ተነገራት። |
በዚህ ጊዜ የመበለትነት ልብሷን በማውለቅ የአንገት ልብስ ተከናንባና ፊቷን ተሸፍና ወደ ቲምና በሚወስደው መንገድ ላይ በምትገኘው በኤናይም መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው ሴሎም ቢያድግም ለእሱ እንዳልተዳረች ስላየች ነው። |
ይሁዳም ባያት ጊዜ ዝሙት አዳሪ መሰለችው፤ ምክንያቱም ፊቷን ሸፍና ነበር። |
ስለሆነም ከመንገዱ ወጣ በማለት ወደ እሷ ጠጋ ብሎ “እባክሽ አብሬሽ እንድተኛ ፍቀጂልኝ” አላት፤ ይህን ያደረገውም ምራቱ መሆኗን ስላላወቀ ነው። ሆኖም እሷ “አብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ?” አለችው። |
እሱም “ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እሷ ግን “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ መያዣ ትሰጠኛለህ?” አለችው። |
እሱም “ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እሷም “የማኅተም ቀለበትህን ከነማንጠልጠያ ክሩ እንዲሁም በእጅህ የያዝከውን በትርህን ስጠኝ” አለችው። ከዚያም እነዚህን ነገሮች ሰጣት፤ ከእሷም ጋር ተኛ፤ ከእሱም ፀነሰች። |
ከዚያ በኋላ ተነስታ ሄደች፤ የአንገት ልብሷንም አውልቃ የመበለትነት ልብሷን ለበሰች። |
ይሁዳም መያዣውን ከሴቲቱ እጅ ለማስመለስ አዱላማዊ ወዳጁን የፍየል ጠቦት አስይዞ ወደ እሷ ላከው፤ እሱ ግን ፈጽሞ ሊያገኛት አልቻለም። |
እሱም የአካባቢውን ሰዎች “ያቺ መንገድ ዳር የምትቀመጠው በኤናይም ያለች የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ የት አለች?” በማለት ጠየቀ። እነሱ ግን “ኧረ በዚህ አካባቢ የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ ታይታ አትታወቅም” አሉት። |
በመጨረሻም ወደ ይሁዳ ተመልሶ እንዲህ አለው፦ “ሴቲቱን በፍጹም ላገኛት አልቻልኩም፤ ደግሞም የአካባቢው ሰዎች ‘በዚህ አካባቢ የቤተ መቅደስ ዝሙት አዳሪ ታይታ አትታወቅም’ አሉኝ።” |
በመሆኑም ይሁዳ “በኋላ እኛ መሳለቂያ እንዳንሆን መያዣውን ትውሰደው። እኔ እንደሆነ ይህን ጠቦት ልኬላት ነበር፤ አንተ ግን ፈጽሞ ልታገኛት አልቻልክም” አለው። |
ይሁን እንጂ ከሦስት ወር በኋላ ለይሁዳ “ምራትህ ትዕማር ዝሙት አዳሪ ሆናለች፤ ዝሙት በመፈጸሟም ፀንሳለች” ተብሎ ተነገረው። በዚህ ጊዜ ይሁዳ “አውጧትና በእሳት ትቃጠል” አለ። |
እሷም ይዘዋት እየሄዱ ሳሉ ለአማቷ “የፀነስኩት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው” የሚል መልእክት ላከችበት። በተጨማሪም “ይህ የማኅተም ቀለበትና ማንጠልጠያ ክሩ እንዲሁም ይህ በትር የማን እንደሆነ እስቲ አጣራ” አለችው። |
ይሁዳም ዕቃዎቹን ከተመለከተ በኋላ “እሷ ከእኔ ይልቅ ጻድቅ ናት፤ ምክንያቱም ለልጄ ለሴሎም ልድራት ይገባኝ ነበር” አለ። ከእሷም ጋር ዳግመኛ የፆታ ግንኙነት አልፈጸመም። |
የመውለጃዋም ጊዜ ሲደርስ በሆዷ ውስጥ መንታ ልጆች እንዳሉ ታወቀ። |
በምትወልድበት ጊዜም አንደኛው ልጅ እጁን አወጣ፤ አዋላጇም “መጀመሪያ የወጣው ይህ ነው” በማለት ወዲያውኑ በእጁ ላይ ቀይ ክር አሰረችለት። |
ይሁን እንጂ ልጁ እጁን በመለሰ ጊዜ ወንድሙ ቀድሞት ወጣ፤ በመሆኑም አዋላጇ “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ?” አለች። በመሆኑም ስሙ ፋሬስ ተባለ። |
በኋላም እጁ ላይ ቀይ ክር የታሰረለት ወንድሙ ወጣ፤ ስሙም ዛራ ተባለ። |
ከዚያም ዮሴፍ አባቱ ላይ ተደፍቶ አለቀሰ፤ አባቱንም ሳመው። |
በኋላም ዮሴፍ መድኃኒት ቀማሚ የሆኑ አገልጋዮቹን የአባቱን አስከሬን መድኃኒት እንዲቀቡ አዘዛቸው። መድኃኒት ቀማሚዎቹም እስራኤልን መድኃኒት ቀቡት፤ |
ይህም 40 ቀን ሙሉ ፈጀባቸው፤ ምክንያቱም አስከሬን መድኃኒት መቀባት ይህን ያህል ጊዜ ይወስድ ነበር፤ ግብፃውያንም 70 ቀን አለቀሱለት። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.