text stringlengths 4 267 |
|---|
በመሆኑም ዮሴፍ፣ አባቱና ወንድሞቹ እንዲሰፍሩ አደረገ፤ ፈርዖንም ባዘዘው መሠረት ምርጥ ከሆነው የግብፅ ምድር፣ የራምሴስን ምድር ርስት አድርጎ ሰጣቸው። |
ዮሴፍም ለአባቱ፣ ለወንድሞቹና ለመላው የአባቱ ቤተሰብ በትናንሽ ልጆቻቸው ቁጥር ልክ ቀለብ ይሰፍርላቸው ነበር። |
በዚህ ወቅት ረሃቡ እጅግ በርትቶ ስለነበር በመላው ምድር እህል አልነበረም፤ የግብፅም ምድር ሆነ የከነአን ምድር በረሃቡ የተነሳ በጣም ተጎድተው ነበር። |
ዮሴፍም ሰዎች እህል ሲገዙ የከፈሉትን በግብፅ ምድርና በከነአን ምድር የሚገኘውን ገንዘብ በሙሉ እየሰበሰበ ወደ ፈርዖን ቤት ያስገባ ነበር። |
ከጊዜ በኋላ በግብፅ ምድርና በከነአን ምድር ያለው ገንዘብ አለቀ፤ ግብፃውያንም በሙሉ ወደ ዮሴፍ በመምጣት “እህል ስጠን! ገንዘብ ስለጨረስን ብቻ እንዴት ዓይንህ እያየ እንለቅ?” ይሉት ጀመር። |
ዮሴፍም “ገንዘባችሁ ካለቀ ከብቶቻችሁን አምጡ፤ እኔም በከብቶቻችሁ ምትክ እህል እሰጣችኋለሁ” አላቸው። |
በመሆኑም ከብቶቻቸውን ወደ ዮሴፍ ያመጡ ጀመር፤ ዮሴፍም በፈረሶቻቸው፣ በመንጎቻቸው፣ በከብቶቻቸውና በአህዮቻቸው ምትክ እህል ይሰጣቸው ነበር፤ በዚያም ዓመት በከብቶቻቸው ሁሉ ምትክ እህል ሲሰጣቸው ከረመ። |
ያም ዓመት ካለቀ በኋላ በቀጣዩ ዓመት ሕዝቡ ወደ እሱ በመምጣት እንዲህ ይለው ጀመር፦ “ከጌታዬ የምንደብቀው ምንም ነገር የለም፤ ገንዘባችንንም ሆነ ከብቶቻችንን ለጌታዬ አስረክበናል። ከእኛ ከራሳችንና ከመሬታችን በስተቀር በጌታዬ ፊት ምንም የቀረን ነገር የለም። |
ዓይንህ እያየ ለምን እንለቅ? መሬታችንስ ለምን ጠፍ ሆኖ ይቅር? እኛንም ሆነ መሬታችንን በእህል ግዛን፤ እኛ ለፈርዖን ባሪያዎች እንሁን፤ መሬታችንም የእሱ ይሁን። በሕይወት እንድንኖርና እንዳንሞት እንዲሁም መሬታችን ጠፍ ሆኖ እንዳይቀር የምንዘራው እህል ስጠን።” |
በመሆኑም ዮሴፍ የግብፃውያንን መሬት በሙሉ ለፈርዖን ገዛለት፤ ምክንያቱም ረሃቡ እጅግ ስለበረታባቸው ሁሉም ግብፃውያን መሬታቸውን ሸጠው ነበር፤ ስለዚህ ምድሪቱ የፈርዖን ሆነች። |
ዮሴፍም በግብፅ ምድር ከዳር እስከ ዳር ያለው ሕዝብ ወደ ከተሞች እንዲገባ አደረገ። |
ዮሴፍ ያልገዛው የካህናቱን መሬት ብቻ ነበር፤ ምክንያቱም ፈርዖን ለካህናቱ ቀለብ ይሰፍርላቸው ነበር፤ እነሱም የሚኖሩት ፈርዖን በሚሰፍርላቸው ቀለብ ነበር። መሬታቸውን ያልሸጡትም ለዚህ ነው። |
ከዚያም ዮሴፍ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “ይኸው ዛሬ እናንተንም ሆነ መሬታችሁን ለፈርዖን ገዝቻለሁ። ዘር ይኸውላችሁ፤ እናንተም በመሬቱ ላይ ዝሩ። |
ባፈራም ጊዜ አንድ አምስተኛውን ለፈርዖን ስጡ፤ አራቱ እጅ ግን ለመሬታችሁ ዘር እንዲሁም ለራሳችሁ፣ በቤታችሁ ላሉትና ለልጆቻችሁ ምግብ እንዲሆናችሁ የእናንተ ይሆናል።” |
እነሱም “አንተ ሕይወታችንን አትርፈህልናል፤ በጌታዬ ፊት ሞገስ እናግኝ እንጂ እኛ ለፈርዖን ባሪያዎች እንሆናለን” አሉት። |
ከዚያም ዮሴፍ አንድ አምስተኛው ለፈርዖን እንዲሰጥ የሚያዝ ሕግ አወጣ፤ ይህም ሕግ እስከ ዛሬ ድረስ በግብፅ ምድር ይሠራበታል። የፈርዖን ያልሆነው የካህናቱ መሬት ብቻ ነበር። |
እስራኤላውያንም በግብፅ አገር፣ በጎሸን ምድር መኖራቸውን ቀጠሉ። በዚያም ተደላድለው ይኖሩ ጀመር፤ ፍሬያማም ሆኑ፤ ቁጥራቸውም እጅግ እየበዛ ሄደ። |
ያዕቆብም በግብፅ ምድር ለ17 ዓመት ኖረ፤ በመሆኑም ያዕቆብ በሕይወት የኖረበት ዘመን 147 ዓመት ሆነ። |
እስራኤልም የሚሞትበት ቀን ሲቃረብ ልጁን ዮሴፍን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ እባክህ እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ፤ ለእኔም ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት አሳየኝ። እባክህ በግብፅ አትቅበረኝ። |
በምሞትበት ጊዜ ከግብፅ አውጥተህ በአባቶቼ መቃብር ቅበረኝ።” እሱም “እሺ፣ እንዳልከኝ አደርጋለሁ” አለው። |
ያዕቆብም “በል ማልልኝ” አለው፤ እሱም ማለለት። በዚህ ጊዜ እስራኤል በአልጋው ራስጌ ላይ ሰገደ። |
ይስሐቅ ባረጀና ዓይኖቹ ደክመው ማየት በተሳናቸው ጊዜ ታላቁን ልጁን ኤሳውን ወደ እሱ ጠርቶ “ልጄ ሆይ!” አለው። እሱም “አቤት!” አለው። |
ይስሐቅም እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አሁን አርጅቻለሁ። የምሞትበትንም ቀን አላውቅም። |
ስለሆነም አሁን መሣሪያዎችህን፣ የቀስት ኮሮጆህንና ደጋንህን ይዘህ ወደ ዱር ሂድ፤ አድነህም አምጣልኝ። |
እኔ የምወደው ዓይነት ጣፋጭ ምግብ ሠርተህ አቅርብልኝ። ከመሞቴም በፊት እንድባርክህ ልብላው።” |
ይሁን እንጂ ይስሐቅ፣ ልጁን ኤሳውን ሲያነጋግረው ርብቃ ታዳምጥ ነበር። ኤሳው አደን አድኖ ለማምጣት ወደ ዱር ወጣ። |
ርብቃም ልጇን ያዕቆብን እንዲህ አለችው፦ “አባትህ ወንድምህን ኤሳውን እንዲህ ሲለው ሰምቻለሁ፦ |
‘እስቲ አደን አድነህ አምጣልኝና ጣፋጭ ምግብ ሥራልኝ። እኔም ሳልሞት በይሖዋ ፊት እንድባርክህ ልብላ።’ |
እንግዲህ ልጄ፣ አሁን የምልህን በጥሞና አዳምጥ፤ የማዝህንም አድርግ። |
አባትህ የሚወደው ዓይነት ጣፋጭ ምግብ እንዳዘጋጅለት እባክህ ወደ መንጋው ሂድና ፍርጥም ያሉ ሁለት የፍየል ጠቦቶች አምጣልኝ። |
ከዚያም ከመሞቱ በፊት እንዲባርክህ ምግቡን ለአባትህ ታቀርብለትና ይበላል።” |
ያዕቆብ እናቱን ርብቃን እንዲህ አላት፦ “ወንድሜ ኤሳው ሰውነቱ ፀጉራም ነው፤ የእኔ ሰውነት ግን ለስላሳ ነው። |
አባቴ ቢዳብሰኝስ? በእሱ ላይ እያሾፍኩበት ያለሁ ሊመስል ይችላል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ በረከት ሳይሆን እርግማን አተርፋለሁ።” |
በዚህ ጊዜ እናቱ “ልጄ፣ ለአንተ የታሰበው እርግማን ለእኔ ይሁን። ብቻ እኔ የምልህን አድርግ፤ ሄደህ ጠቦቶቹን አምጣልኝ” አለችው። |
ስለዚህ ሄዶ ጠቦቶቹን አመጣ፤ ለእናቱም ሰጣት፤ እናቱም አባቱ የሚወደው ዓይነት ጣፋጭ ምግብ ሠራች። |
ከዚያም ርብቃ ቤት ውስጥ ያስቀመጠችውን የታላቁን ልጇን የኤሳውን ምርጥ ልብስ ወስዳ ታናሹን ልጇን ያዕቆብን አለበሰችው። |
በተጨማሪም የፍየል ጠቦቶቹን ቆዳ በእጆቹና ፀጉር በሌለው የአንገቱ ክፍል ላይ አደረገች። |
ከዚያም የሠራችውን ጣፋጭ ምግብና ዳቦ ለልጇ ለያዕቆብ ሰጠችው። |
እሱም ወደ አባቱ ገብቶ “አባቴ ሆይ!” አለው። እሱም መልሶ “አቤት! ለመሆኑ አንተ ማነህ ልጄ?” አለው። |
ያዕቆብም አባቱን “እኔ የበኩር ልጅህ ኤሳው ነኝ። ልክ እንዳልከኝ አድርጌአለሁ። እንድትባርከኝ እባክህ ቀና ብለህ ተቀመጥና አድኜ ካመጣሁት ብላ” አለው። |
በዚህ ጊዜ ይስሐቅ ልጁን “እንዴት እንዲህ ቶሎ ቀናህ ልጄ?” አለው። እሱም መልሶ “አምላክህ ይሖዋ አምጥቶ እጄ ላይ ስለጣለልኝ ነው” አለው። |
ከዚያም ይስሐቅ ያዕቆብን “ልጄ ሆይ፣ አንተ በእርግጥ ልጄ ኤሳው መሆንህን እንዳውቅ እስቲ ቀረብ በልና ልዳብስህ” አለው። |
በመሆኑም ያዕቆብ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ቀረበ። እሱም ዳበሰውና “ድምፁ የያዕቆብ ድምፅ ነው፤ እጆቹ ግን የኤሳው እጆች ናቸው” አለ። |
እጆቹ እንደ ወንድሙ እንደ ኤሳው እጆች ፀጉራም ስለነበሩ ማንነቱን አልለየውም። ስለዚህ ባረከው። |
ከዚያም “በእርግጥ አንተ ልጄ ኤሳው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እሱም “አዎ፣ ነኝ” አለው። |
በመቀጠልም “በል እንግዲህ ልጄ፣ አድነህ ያመጣህልኝን እንድበላ አቅርብልኝ፤ ከዚያም እባርክሃለሁ” አለው። እሱም አቀረበለትና በላ፤ እንዲሁም የወይን ጠጅ አመጣለትና ጠጣ። |
ከዚያም አባቱ ይስሐቅ “ልጄ፣ እስቲ ቀረብ በልና ሳመኝ” አለው። |
ስለዚህ ወደ እሱ ቀረበና ሳመው፤ ይስሐቅም የልጁን ልብስ ጠረን አሸተተ። ከዚያም ባረከው፤ እንዲህም አለው፦ “አቤት፣ የልጄ ጠረን ይሖዋ እንደባረከው መስክ መዓዛ ነው። |
እውነተኛው አምላክ የሰማያትን ጠል፣ የምድርን ለም አፈር እንዲሁም የተትረፈረፈ እህልና አዲስ የወይን ጠጅ ይስጥህ። |
ሕዝቦች ያገልግሉህ፤ ብሔራትም ይስገዱልህ። የወንድሞችህ ጌታ ሁን፤ የእናትህም ወንዶች ልጆች ይስገዱልህ። የሚረግሙህ ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚባርኩህም ሁሉ የተባረኩ ይሁኑ።” |
ይስሐቅ ያዕቆብን ባርኮ እንዳበቃና ያዕቆብ ከአባቱ ከይስሐቅ ፊት እግሩ እንደወጣ ወንድሙ ኤሳው ከአደን ተመለሰ። |
እሱም ደግሞ ጣፋጭ ምግብ አዘጋጅቶ ለአባቱ አቀረበለት፤ አባቱንም “እስቲ እንድትባርከኝ አባቴ ይነሳና ልጁ አድኖ ካመጣለት ይብላ” አለው። |
በዚህ ጊዜ አባቱ ይስሐቅ “አንተ ደግሞ ማን ነህ?” አለው። እሱም መልሶ “ልጅህ ነኛ! የበኩር ልጅህ ኤሳው” አለው። |
ይስሐቅም በኃይል እየተንቀጠቀጠ “አደን አድኖ ያመጣልኝና ያቀረበልኝ ታዲያ ማን ነበር? እኔ እኮ አንተ ከመምጣትህ በፊት በላሁ፤ እንዲሁም ባረክሁት፤ ደግሞም የተባረከ ይሆናል!” አለው። |
ኤሳው አባቱ የተናገረውን ሲሰማ ከፍ ባለ ድምፅ ምርር ብሎ እያለቀሰ አባቱን “አባቴ ባርከኝ፤ እኔንም ባርከኝ እንጂ!” አለው። |
ይስሐቅ ግን “ወንድምህ ለአንተ የታሰበውን በረከት ለማግኘት አንድ ተንኮል ሠርቷል” አለው። |
ኤሳውም እንዲህ አለ፦ “ስሙ ያዕቆብ የተባለው መቼ ያለምክንያት ሆነ! የኔ የሆነውን ሲወስድብኝ ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው። የብኩርና መብቴን መውሰዱ ሳያንሰው አሁን ደግሞ በረከቴን ቀማኝ!” ከዚያም “ለእኔ ምንም በረከት አላስቀረህልኝም?” አለው። |
ይስሐቅ ግን ኤሳውን እንዲህ አለው፦ “በአንተ ላይ ጌታ አድርጌ ሾሜዋለሁ፤ እንዲሁም ወንድሞቹን ሁሉ አገልጋዮቹ እንዲሆኑ ሰጥቼዋለሁ። እህልና አዲስ የወይን ጠጅ እንዲበዛለት ባርኬዋለሁ፤ ታዲያ ለአንተ ላደርግልህ የምችለው ምን የቀረ ነገር አለ ልጄ?” |
ኤሳውም አባቱን “አባቴ ሆይ፣ ለእኔ የምትሆን አንዲት በረከት እንኳ የለችህም? አባቴ ባርከኝ። እኔንም ባርከኝ እንጂ!” አለው። ኤሳውም ከፍ ባለ ድምፅ ምርር ብሎ አለቀሰ። |
ስለዚህ አባቱ ይስሐቅ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ መኖሪያህ ለም ከሆነው የምድር አፈር እንዲሁም በላይ ካሉት ሰማያት ጠል የራቀ ይሆናል። |
በሰይፍህ ትኖራለህ፤ ወንድምህንም ታገለግላለህ። ይሁንና እየተቅበጠበጥክ ባስቸገርክ ጊዜ ቀንበሩን ከጫንቃህ ላይ ሰብረህ ትጥላለህ።” |
ይሁን እንጂ ኤሳው አባቱ ያዕቆብን ስለባረከው ለያዕቆብ ከፍተኛ ጥላቻ አደረበት። ኤሳውም በልቡ “ለአባቴ ሐዘን የምንቀመጥበት ቀን ሩቅ አይደለም። ከዚያ በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ” ይል ነበር። |
ርብቃ ታላቁ ልጇ ኤሳው ያለው ነገር ሲነገራት ወዲያውኑ ለታናሹ ልጇ ለያዕቆብ እንዲህ የሚል መልእክት ላከችበት፦ “ወንድምህ ኤሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ እያሰበ ነው። |
እንግዲህ ልጄ እኔ የምልህን አድርግ። ተነስተህ በካራን ወደሚገኘው ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሽሽ። |
የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ ለተወሰነ ጊዜ እሱ ጋ ተቀመጥ፤ |
ወንድምህ ንዴቱ እስኪበርድለትና ያደረግክበትን እስኪረሳ ድረስ እዚያ ቆይ። እኔም እልክብህና አስጠራሃለሁ። ሁለታችሁንም በአንድ ቀን ለምን ልጣ?” |
ከዚያ በኋላ ርብቃ ይስሐቅን እንዲህ ትለው ጀመር፦ “በሄት ሴቶች ልጆች የተነሳ ሕይወቴን ጠልቻለሁ። ያዕቆብም በዚህ አገር የሚገኙትን እንደነዚህ ያሉትን የሄት ሴቶች ልጆች የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለእኔ ምን ያደርግልኛል?” |
በዚህ መንገድ ሰማያትንና ምድርን እንዲሁም በውስጣቸው ያለውን ነገር ሁሉ የመፍጠሩ ሥራ ተጠናቀቀ። |
በሰባተኛውም ቀን አምላክ ይሠራው የነበረውን ሥራ አጠናቀቀ፤ በሰባተኛውም ቀን ይሠራው ከነበረው ሥራ ሁሉ ማረፍ ጀመረ። |
አምላክም ሰባተኛውን ቀን ባረከው እንዲሁም ቀደሰው፤ ምክንያቱም አምላክ ከመፍጠር ሥራው ሁሉ፣ ሊሠራ ካሰበው ነገር ሁሉ ያረፈው ከዚያ ቀን አንስቶ ነው። |
ሰማያትና ምድር በተፈጠሩበት ጊዜ፣ ይሖዋ አምላክ ምድርንና ሰማይን በሠራበት ቀን የተከናወነው ነገር ይህ ነው። |
በዚህ ጊዜ በምድር ላይ ምንም ዓይነት የሜዳ ቁጥቋጦ አልነበረም፤ እንዲሁም በሜዳ ላይ ምንም ዓይነት ተክል አልበቀለም፤ ምክንያቱም ይሖዋ አምላክ በምድር ላይ ዝናብ እንዲዘንብ አላደረገም ነበር፤ መሬቱን የሚያለማም ሰው አልነበረም። |
ይሁንና ተን ከምድር እየተነሳ መላውን መሬት ያጠጣ ነበር። |
ይሖዋ አምላክም ሰውን ከምድር አፈር ሠራው፤ በአፍንጫውም የሕይወትን እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውየውም ሕያው ሰው ሆነ። |
በተጨማሪም ይሖዋ አምላክ በስተ ምሥራቅ፣ በኤደን የአትክልት ስፍራ ተከለ፤ የሠራውንም ሰው በዚያ አስቀመጠው። |
ከዚያም ይሖዋ አምላክ ለማየት የሚያስደስተውንና ለምግብነት መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከመሬት አበቀለ። በተጨማሪም በአትክልቱ ስፍራ መካከል የሕይወት ዛፍ እንዲሁም የመልካምና ክፉ እውቀት ዛፍ አበቀለ። |
የአትክልቱን ስፍራ የሚያጠጣ ወንዝ ከኤደን ወጥቶ ይፈስ ነበር፤ ከዚያም ተከፋፍሎ አራት ወንዝ ሆነ። |
የመጀመሪያው ወንዝ ስም ፊሶን ነው፤ ይህ ወንዝ ወርቅ የሚገኝበትን መላውን የሃዊላ ምድር የሚከብ ነው። |
የዚያ አገር ወርቅ ምርጥ ነው። በተጨማሪም በዚያ ጥሩ መዓዛ ያለው ሙጫና የኦኒክስ ድንጋዮች ይገኛሉ። |
የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ ይህ ወንዝ መላውን የኢትዮጵያ ምድር የሚከብ ነው። |
የሦስተኛው ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ ይህ ወንዝ ከአሦር በስተ ምሥራቅ የሚፈስ ነው። አራተኛው ወንዝ ደግሞ ኤፍራጥስ ነው። |
ይሖዋ አምላክ ሰውየውን ወስዶ እንዲያለማውና እንዲንከባከበው በኤደን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው። |
በተጨማሪም ይሖዋ አምላክ ለሰውየው ይህን ትእዛዝ ሰጠው፦ “በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ ከሚገኘው ዛፍ ሁሉ እስክትረካ ድረስ መብላት ትችላለህ። |
ከመልካምና ክፉ እውቀት ዛፍ ግን አትብላ፤ ምክንያቱም ከዚህ ዛፍ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ።” |
ከዚያም ይሖዋ አምላክ “ሰውየው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለም። ማሟያ የምትሆነውን ረዳት እሠራለታለሁ” አለ። |
ይሖዋ አምላክም እያንዳንዱን የዱር እንስሳ እንዲሁም በሰማያት ላይ የሚበረውን እያንዳንዱን ፍጥረት ከአፈር ሠርቶ ነበር፤ ከዚያም ሰውየው እያንዳንዳቸውን ምን ብሎ እንደሚጠራቸው ለማየት ሁሉንም ወደ እሱ አመጣቸው፤ ሰውየው ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር የሰጠው መጠሪያም የዚያ ፍጡር ስም ሆነ። |
በመሆኑም ሰውየው ለቤት እንስሳት በሙሉ፣ በሰማያት ላይ ለሚበርሩ ፍጥረታት እንዲሁም ለዱር እንስሳት ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ለሰው ግን ማሟያ የሚሆን ረዳት አልነበረውም። |
ስለሆነም ይሖዋ አምላክ በሰውየው ላይ ከባድ እንቅልፍ ጣለበት፤ እንቅልፍ ወስዶት ሳለም ከጎድን አጥንቶቹ አንዷን ወሰደ፤ ቦታውንም በሥጋ ደፈነው። |
ይሖዋ አምላክም ከሰውየው የወሰዳትን የጎድን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ሴቲቱንም ወደ ሰውየው አመጣት። |
በዚህ ጊዜ ሰውየው እንዲህ አለ፦ “እንግዲህ እሷ የአጥንቶቼ አጥንት፣የሥጋዬም ሥጋ ናት። እሷ ከወንድ ስለተገኘች‘ሴት’ ትባላለች።” |
በዚህም ምክንያት ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል። ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። |
ሰውየውም ሆነ ሚስቱ ራቁታቸውን ነበሩ፤ እንደዚያም ሆኖ ኀፍረት አይሰማቸውም ነበር። |
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ የቤቱ ኃላፊ የሆነውን ሰው እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “የቻሉትን ያህል እህል በየከረጢቶቻቸው ሙላላቸው፤ የእያንዳንዳቸውንም ገንዘብ በየከረጢቶቻቸው አፍ ላይ አድርገው። |
ሆኖም የእኔን ጽዋ ይኸውም የብር ጽዋዬን ውሰድና እህል ለመግዛት ካመጣው ገንዘብ ጋር አድርገህ በትንሹ ወንድማቸው ከረጢት አፍ ላይ አድርገው።” እሱም ልክ ዮሴፍ እንዳዘዘው አደረገ። |
ሰዎቹም ማለዳ ላይ ጎህ ሲቀድ ከነአህዮቻቸው ተሸኙ። |
እነሱም ከከተማዋ ብዙም ርቀው ሳይሄዱ ዮሴፍ የቤቱ ኃላፊ የሆነውን ሰው እንዲህ አለው፦ “ተነስ! ሰዎቹን ተከታተላቸው! ስትደርስባቸውም እንዲህ በላቸው፦ ‘ለተደረገላችሁ መልካም ነገር ክፉ የመለሳችሁት ለምንድን ነው? |
ይህ ጌታዬ የሚጠጣበትና የሚጠነቁልበት ጽዋ አይደለም? የፈጸማችሁት ድርጊት በጣም አሳፋሪ ነው።’” |
እሱም ተከታትሎ ደረሰባቸውና ልክ እንደተባለው አላቸው። |
እነሱ ግን እንዲህ አሉት፦ “ጌታዬ እንዲህ ያለ ነገር የሚናገረው ለምንድን ነው? አገልጋዮችህ እንዲህ ያለ ነገር ያደርጋሉ ማለት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። |
በከረጢቶቻችን አፍ ላይ ያገኘነውን ገንዘብ እንኳ ከከነአን ምድር ድረስ ይዘን ወደ አንተ መጥተን የለም? ታዲያ ከጌታህ ቤት ብር ወይም ወርቅ እንዴት እንሰርቃለን? |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.