text stringlengths 4 267 |
|---|
የይሖዋም መልአክ ከሰማይ ለሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ጠራው፤ |
እንዲህም አለው፦ “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በራሴ እምላለሁ፤ ይህን ስላደረግክ እንዲሁም ልጅህን፣ አንድ ልጅህን ለመስጠት ስላልሳሳህ |
በእርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብትና በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ በእርግጥ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶቹን በር ይወርሳል። |
ቃሌን ስለሰማህ የምድር ብሔራት ሁሉ በዘርህ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያገኛሉ።’” |
ከዚያ በኋላ አብርሃም ወደ አገልጋዮቹ ተመለሰ፤ ተነስተውም አብረው ወደ ቤርሳቤህ ተመለሱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ መኖሩን ቀጠለ። |
ከዚህ በኋላ ለአብርሃም እንዲህ ተብሎ ተነገረው፦ “ሚልካም ለወንድምህ ለናኮር ወንዶች ልጆችን ወልዳለታለች፤ |
እነሱም የበኩር ልጁ ዑጽ፣ ወንድሙ ቡዝ፣ የአራም አባት የሆነው ቀሙኤል፣ |
ኬሰድ፣ ሃዞ፣ ፒልዳሽ፣ ይድላፍ እና ባቱኤል ናቸው።” |
ባቱኤልም ርብቃን ወለደ። ሚልካ ለአብርሃም ወንድም ለናኮር እነዚህን ስምንቱን ወለደችለት። |
ቁባቱ የሆነችው ረኡማም ተባህ፣ ጋሃም፣ ታሃሽ እና ማአካ የተባሉ ወንዶች ልጆችን ወለደች። |
ከዚህ በኋላ የይሖዋ ቃል በራእይ ወደ አብራም መጥቶ “አብራም አትፍራ። እኔ ጋሻ እሆንሃለሁ። የምታገኘውም ሽልማት እጅግ ታላቅ ይሆናል” አለው። |
አብራምም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ያለልጅ እንደቀረሁና ቤቴን የሚወርሰው የደማስቆ ሰው የሆነው ኤሊዔዘር እንደሆነ ታያለህ፤ ታዲያ ምን ትሰጠኛለህ?” |
በተጨማሪም አብራም “እንግዲህ ዘር አልሰጠኸኝም፤ ደግሞም ወራሼ የሚሆነው በቤቴ ያለው አገልጋይ ነው” አለ። |
ሆኖም እንዲህ የሚል የይሖዋ ቃል ወደ እሱ መጣ፦ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ከዚህ ይልቅ የገዛ ልጅህ ወራሽህ ይሆናል።” |
ወደ ውጭም ካወጣው በኋላ “እባክህ ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ እስቲ መቁጠር ከቻልክ ከዋክብቱን ቁጠራቸው” አለው። ከዚያም “የአንተም ዘር እንዲሁ ይሆናል” አለው። |
አብራምም በይሖዋ አመነ፤ አምላክም ይህን ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት። |
ደግሞም እንዲህ አለው፦ “ይህችን ምድር ርስት አድርጌ ልሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እኔ ይሖዋ ነኝ።” |
አብራምም “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ይህችን ምድር ርስት አድርጌ እንደምወርስ እንዴት አውቃለሁ?” አለ። |
እሱም መልሶ “አንዲት የሦስት ዓመት ጊደር፣ አንዲት የሦስት ዓመት ፍየል፣ አንድ የሦስት ዓመት አውራ በግ እንዲሁም አንድ ዋኖስና አንድ የርግብ ጫጩት ውሰድ” አለው። |
እሱም እነዚህን እንስሳት ሁሉ ወስዶ ለሁለት ሰነጠቃቸው፤ ከዚያም አንዱን ግማሽ ከሌላኛው ግማሽ ትይዩ አድርጎ አስቀመጠ። ወፎቹን ግን አልሰነጠቃቸውም። |
አሞሮችም በበድኖቹ ላይ መውረድ ጀመሩ፤ አብራም ግን ያባርራቸው ነበር። |
ፀሐይ ልትጠልቅ ስትቃረብም አብራም ከባድ እንቅልፍ ወሰደው፤ ታላቅና የሚያስፈራ ጨለማም ወረደበት። |
አምላክም አብራምን እንዲህ አለው፦ “ዘሮችህ በባዕድ አገር ባዕዳን ሆነው እንደሚኖሩ እንዲሁም በዚያ ያሉት ሰዎች ለ400 ዓመት በባርነት እንደሚገዟቸውና እንደሚያጎሳቁሏቸው በእርግጥ እወቅ። |
ይሁንና በባርነት በሚገዛቸው ብሔር ላይ እፈርዳለሁ፤ እነሱም ብዙ ንብረት ይዘው ይወጣሉ። |
አንተ ግን ወደ አባቶችህ በሰላም ትሄዳለህ፤ ዕድሜ ጠግበህም ወደ መቃብር ትወርዳለህ። |
ሆኖም በአራተኛው ትውልድ ወደዚህ ይመለሳሉ፤ ምክንያቱም የአሞራውያን በደል ጽዋው ገና አልሞላም።” |
ፀሐይዋ ከጠለቀችና ድቅድቅ ጨለማ አካባቢውን ከዋጠው በኋላ የሚጨስ ምድጃ ታየ፤ ለሁለት በተከፈለውም ሥጋ መካከል የሚንቦገቦግ ችቦ አለፈ። |
በዚያ ቀን ይሖዋ እንዲህ ሲል ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገባ፦ “ከግብፅ ወንዝ አንስቶ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ይህን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤ |
የቄናውያንን፣ የቀኒዛውያንን፣ የቃድሞናውያንን፣ |
የሂታውያንን፣ የፈሪዛውያንን፣ የረፋይምን፣ |
የአሞራውያንን፣ የከነአናውያንን፣ የገርጌሻውያንንና የኢያቡሳውያንን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ።” |
ያዕቆብም ወንዶች ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “በኋለኞቹ ቀናት ምን እንደሚያጋጥማችሁ እንድነግራችሁ ተሰብሰቡ። |
እናንተ የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ተሰብሰቡና ስሙ፤ አዎ፣ አባታችሁን እስራኤልን አዳምጡ። |
“ሮቤል፣ አንተ የበኩር ልጄ ነህ፤ ኃይሌና የብርታቴ የመጀመሪያ ፍሬ ነህ፤ የላቀ ክብርና የላቀ ኃይል ነበረህ። |
እንደሚናወጥ ውኃ ስለምትዋልል የበላይ አትሆንም፤ ምክንያቱም አባትህ አልጋ ላይ ወጥተሃል። በዚያን ወቅት መኝታዬን አርክሰሃል። በእርግጥም አልጋዬ ላይ ወጥቷል! |
“ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች ናቸው። ሰይፎቻቸው የዓመፅ መሣሪያዎች ናቸው። |
ነፍሴ ሆይ፣ ከእነሱ ጋር አትወዳጂ። ክብሬ ሆይ፣ ከእነሱ ማኅበር ጋር አትተባበር፤ ምክንያቱም በቁጣ ተነሳስተው ሰዎችን ገድለዋል፤ ደስ ስላላቸውም ብቻ የበሬዎችን ቋንጃ ቆርጠዋል። |
ቁጣቸው ጨካኝ፣ ንዴታቸውም ምሕረት የለሽ ስለሆነ የተረገመ ይሁን። በያዕቆብ ልበትናቸው፤ በእስራኤልም ላሰራጫቸው። |
“ይሁዳ ሆይ፣ ወንድሞችህ ያወድሱሃል። እጅህ የጠላቶችህን አንገት ያንቃል። የአባትህ ወንዶች ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ። |
ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው። ልጄ፣ በእርግጥም ያደንከውን በልተህ ትነሳለህ። እንደ አንበሳ ያደፍጣል፤ እንደ አንበሳ ይንጠራራል፤ ማንስ ሊያስነሳው ይደፍራል? |
ሴሎ እስኪመጣ ድረስ በትረ መንግሥት ከይሁዳ፣ የአዛዥም በትር ከእግሮቹ መካከል አይወጣም፤ ለእሱም ሕዝቦች ይታዘዙለታል። |
አህያውን በወይን ተክል ላይ፣ ውርንጭላውንም ምርጥ በሆነ የወይን ተክል ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጎናጸፊያውንም በወይን ፍሬ ጭማቂ ያጥባል። |
ዓይኖቹ ከወይን ጠጅ የተነሳ የቀሉ፣ ጥርሶቹም ከወተት የተነሳ የነጡ ናቸው። |
“የዛብሎን መኖሪያ በባሕር ዳርቻ፣ መርከቦች መልሕቅ ጥለው በሚቆሙበት ዳርቻ ይሆናል፤ የወሰኑም ጫፍ በሲዶና አቅጣጫ ይሆናል። |
“ይሳኮር በመንታ ጭነት መካከል የሚተኛ አጥንተ ብርቱ አህያ ነው። |
ማረፊያ ቦታው መልካም፣ ምድሩም አስደሳች መሆኑን ያያል። ሸክሙን ለመሸከም ትከሻውን ዝቅ ያደርጋል፤ ለግዳጅ ሥራ ይንበረከካል። |
“ከእስራኤል ነገዶች አንዱ የሆነው ዳን በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል። |
ዳን፣ ጋላቢው ወደ ኋላ እንዲወድቅ የፈረሱን ሰኮና የሚነክስ በመንገድ ዳር ያለ እባብ፣ በመተላለፊያ ላይ ያለ ቀንዳም እባብ ይሁን። |
ይሖዋ ሆይ፣ የአንተን ማዳን እጠባበቃለሁ። |
“ጋድ ደግሞ የወራሪዎች ቡድን አደጋ ይጥልበታል፤ እሱ ግን ዱካውን ተከታትሎ ይመታዋል። |
“የአሴር ምግብ የተትረፈረፈ ይሆናል፤ በንጉሥ ፊት የሚቀርብ ምግብ ያዘጋጃል። |
“ንፍታሌም ሸንቃጣ የሜዳ ፍየል ነው። ከአፉም ያማሩ ቃላት ይወጣሉ። |
“ዮሴፍ ፍሬያማ የሆነ ዛፍ ቀንበጥ ነው፤ ቅርንጫፎቹን በግንብ ላይ የሚሰድ በምንጭ ዳር ያለ ፍሬያማ የሆነ ዛፍ ቀንበጥ ነው። |
ቀስተኞች ግን እረፍት ነሱት፤ ቀስታቸውንም ወረወሩበት፤ ለእሱም ጥላቻ አደረባቸው። |
ሆኖም ቀስቱ ከቦታው ንቅንቅ አላለም፤ እጆቹም ብርቱና ቀልጣፋ ናቸው። ይህም ከያዕቆብ ኃያል አምላክ እጆች፣ ከእረኛው፣ ከእስራኤል ዓለት የተገኘ ነው። |
እሱ ከአባትህ አምላክ የተገኘ ነው፤ አምላክም ይረዳሃል፤ እሱም ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ ጋር ይሆናል። አምላክም ከላይ ከሰማያት በሚገኙ በረከቶች፣ ከታች ከጥልቁ በሚገኙ በረከቶች እንዲሁም ከጡትና ከማህፀን በሚገኙ በረከቶች ይባርክሃል። |
የአባትህ በረከቶች ከዘላለማዊ ተራሮች ከሚመጡት በረከቶችና ጸንተው ከሚኖሩት ኮረብቶች ከሚገኙት መልካም ነገሮች የላቁ ይሆናሉ። በረከቶቹም በዮሴፍ ራስ ላይ፣ ከወንድሞቹ መካከል ተነጥሎ በወጣው በእሱ አናት ላይ ይሆናሉ። |
“ቢንያም እንደ ተኩላ ይቦጫጭቃል። ያደነውን ጠዋት ላይ ይበላል፤ ምሽት ላይ ደግሞ ምርኮ ያከፋፍላል።” |
እነዚህ ሁሉ 12ቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፤ አባታቸው በባረካቸው ጊዜ የነገራቸው ነገር ይህ ነው። ለእያንዳንዳቸውም የሚገባቸውን በረከት ሰጣቸው። |
ከዚህ በኋላ የሚከተሉትን ትእዛዛት ሰጣቸው፦ “እንግዲህ እኔ ወደ ወገኖቼ ልሰበሰብ ነው። በሂታዊው በኤፍሮን እርሻ ውስጥ በሚገኘው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ፤ |
አብርሃም ለመቃብር ስፍራ ብሎ ከሂታዊው ከኤፍሮን በገዛው እርሻ ይኸውም በከነአን ምድር በማምሬ ፊት ለፊት በሚገኘው በማክፈላ እርሻ ውስጥ ባለው ዋሻ ቅበሩኝ። |
አብርሃምንና ሚስቱን ሣራን የቀበሯቸው እዚያ ነው። ይስሐቅንና ሚስቱን ርብቃንም የቀበሯቸው እዚያ ነው፤ እኔም ብሆን ሊያን የቀበርኳት እዚያው ነው። |
እርሻውም ሆነ በውስጡ ያለው ዋሻ የተገዛው ከሄት ወንዶች ልጆች ነው።” |
በዚህ መንገድ ያዕቆብ ለወንዶች ልጆቹ እነዚህን መመሪያዎች ሰጥቶ ጨረሰ። ከዚያም እግሮቹን ወደ አልጋው አውጥቶ የመጨረሻ እስትንፋሱን ተነፈሰ፤ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ። |
ከዚያም ያዕቆብ ጉዞውን ቀጠለ፤ የአምላክ መላእክትም አገኙት። |
ያዕቆብም ልክ እንዳያቸው “ይህ የአምላክ ሰፈር ነው!” አለ። በመሆኑም የቦታውን ስም ማሃናይም አለው። |
ከዚያም ያዕቆብ በኤዶም ክልል ሴይር በተባለው ምድር ወደሚኖረው ወንድሙ ወደ ኤሳው መልእክተኞችን አስቀድሞ ላከ፤ |
እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “ጌታዬን ኤሳውን እንዲህ በሉት፦ ‘አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ይላል፦ “ከላባ ጋር እስካሁን ድረስ ለረጅም ጊዜ ኖሬአለሁ። |
አሁን በሬዎች፣ አህዮች፣ በጎች እንዲሁም ወንድና ሴት አገልጋዮች አሉኝ፤ ይህን መልእክት ለጌታዬ የላክሁት በፊትህ ሞገስ እንዳገኝ ለመጠየቅ ነው።”’” |
ከተወሰነ ጊዜ በኋላም መልእክተኞቹ ወደ ያዕቆብ ተመልሰው በመምጣት እንዲህ አሉት፦ “ወንድምህን ኤሳውን አግኝተነው ነበር፤ እሱም ከአንተ ጋር ለመገናኘት ወደዚህ እየመጣ ነው፤ ከእሱም ጋር 400 ሰዎች አሉ።” |
ያዕቆብም እጅግ ፈራ፤ በጭንቀትም ተዋጠ። በመሆኑም አብረውት ያሉትን ሰዎች፣ መንጎቹን፣ ከብቶቹንና ግመሎቹን በሁለት ቡድን ከፈላቸው። |
እሱም “ምናልባት ኤሳው በአንደኛው ቡድን ላይ ጥቃት ቢሰነዝር፣ ሌላኛው ቡድን ሊያመልጥ ይችላል” አለ። |
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ አለ፦ “‘ወደ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እኔም መልካም ነገር አደርግልሃለሁ’ ያልከኝ የአባቴ የአብርሃም አምላክና የአባቴ የይስሐቅ አምላክ የሆንከው ይሖዋ ሆይ፣ |
እኔ ባሪያህ ይህን ያህል ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ ሰው አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር ከበትር ሌላ ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ቡድን ሆኛለሁ። |
ከወንድሜ ከኤሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ ምክንያቱም መጥቶ በእኔም ሆነ በእነዚህ እናቶችና በልጆቻቸው ላይ ጥቃት እንዳይሰነዝር ፈርቻለሁ። |
አንተው ራስህ ‘በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፤ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሳ ሊቆጠር እንደማይችል የባሕር አሸዋ አደርገዋለሁ’ ብለኸኛል።” |
እሱም በዚያ ሌሊት እዚያው አደረ። ከንብረቱም መካከል የተወሰነውን ወስዶ ለወንድሙ ለኤሳው ስጦታ አዘጋጀ፤ |
ስጦታውም የሚከተለው ነበር፦ 200 እንስት ፍየሎች፣ 20 ተባዕት ፍየሎች፣ 200 እንስት በጎች፣ 20 አውራ በጎች |
እንዲሁም 30 የሚያጠቡ ግመሎች፣ 40 ላሞች፣ 10 በሬዎች፣ 20 እንስት አህዮችና 10 ተባዕት አህዮች። |
እሱም በመንጋ በመንጋ ለይቶ ለአገልጋዮቹ ሰጣቸው። አገልጋዮቹንም “ቀድማችሁኝ ተሻገሩ፤ አንዱን መንጋ ከሌላው መንጋ አራርቁት” አላቸው። |
በተጨማሪም የመጀመሪያውን እንዲህ ሲል አዘዘው፦ “ወንድሜ ኤሳው ቢያገኝህና ‘ለመሆኑ አንተ የማን ነህ? የምትሄደው ወዴት ነው? እነዚህ የምትነዳቸው እንስሳትስ የማን ናቸው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፣ |
‘የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው። ይህ ለጌታዬ ለኤሳው የተላከ ስጦታ ነው፤ እንዲያውም እሱ ራሱ ከኋላችን እየመጣ ነው’ በለው።” |
እንዲሁም ሁለተኛውን፣ ሦስተኛውንና መንጎቹን የሚነዱትን በሙሉ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ኤሳውን ስታገኙት ይህንኑ ንገሩት። |
‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ ማለት እንዳለባችሁም አትዘንጉ።” ይህን ያላቸው ‘ስጦታውን አስቀድሜ በመላክ ቁጣው እንዲበርድለት ካደረግኩ ከእሱ ጋር ስገናኝ በጥሩ ሁኔታ ይቀበለኝ ይሆናል’ ብሎ ስላሰበ ነው። |
በመሆኑም ስጦታው ከእሱ ቀድሞ ተሻገረ፤ እሱ ግን እዚያው የሰፈረበት ቦታ አደረ። |
በኋላም በዚያው ሌሊት ተነሳ፤ ሁለቱን ሚስቶቹን፣ ሁለቱን ሴት አገልጋዮቹንና 11ዱን ወንዶች ልጆቹን ይዞ በያቦቅ መልካ ተሻገረ። |
እነሱንም ወስዶ ወንዙን አሻገራቸው፤ ያለውንም ነገር ሁሉ አሻገረ። |
በመጨረሻም ያዕቆብ ብቻውን ቀረ። ከዚያም አንድ ሰው ጎህ እስኪቀድ ድረስ ሲታገለው ቆየ። |
ሰውየውም ሊያሸንፈው እንዳልቻለ ሲያይ የጭኑን መጋጠሚያ ነካው፤ ያዕቆብም ከእሱ ጋር በሚታገልበት ጊዜ የጭኑ መጋጠሚያ ከቦታው ተናጋ። |
በኋላም ሰውየው “ጎህ እየቀደደ ስለሆነ ልቀቀኝና ልሂድ” አለው። እሱም “ካልባረክኸኝ አለቅህም” አለው። |
በመሆኑም ሰውየው “ስምህ ማን ነው?” አለው፤ እሱም “ያዕቆብ” ሲል መለሰለት። |
ሰውየውም “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል እንጂ ያዕቆብ አይባልም፤ ምክንያቱም ከአምላክም ሆነ ከሰዎች ጋር ታግለህ በመጨረሻ አሸንፈሃል” አለው። |
ያዕቆብም መልሶ “እባክህ ስምህን ንገረኝ” አለው። እሱ ግን “ስሜን የምትጠይቀኝ ለምንድን ነው?” አለው። እንዲህ ካለው በኋላም በዚያ ስፍራ ባረከው። |
በመሆኑም ያዕቆብ “አምላክን ፊት ለፊት አይቼ እንኳ ሕይወቴ ተርፏል” በማለት የቦታውን ስም ጰኒኤል አለው። |
ያዕቆብ ጰኑኤልን እንዳለፈ ፀሐይ ወጣችበት፤ እሱም ጭኑ በመጎዳቱ ምክንያት ያነክስ ነበር። |
የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን ጅማት የማይበሉት ለዚህ ነው፤ ምክንያቱም ሰውየው በያዕቆብ ጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን ጅማት ነክቶ ነበር። |
አዳምም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ፀነሰች። ቃየንንም በወለደች ጊዜ “በይሖዋ እርዳታ ወንድ ልጅ አፈራሁ” አለች። |
በኋላም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤል የበግ እረኛ ሆነ፤ ቃየን ግን አራሽ ሆነ። |
ከጊዜ በኋላም ቃየን የተወሰኑ የምድር ፍሬዎችን ለይሖዋ መባ አድርጎ አቀረበ። |
አቤል ግን ከመንጋው በኩራት መካከል የተወሰኑትን ከነስባቸው አቀረበ። ይሖዋ አቤልንና ያቀረበውን መባ በጥሩ ፊት ሲመለከት |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.