text stringlengths 4 267 |
|---|
እንዲህም አሏቸው፦ “እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አናደርግም፤ እህታችንን ላልተገረዘ ሰው አንሰጥም፤ ምክንያቱም ይህ ለእኛ ውርደት ነው። |
በሐሳባችሁ የምንስማማው እኛን ከመሰላችሁና የእናንተ የሆነው ወንድ ሁሉ እንዲገረዝ ካደረጋችሁ ብቻ ነው። |
ከዚያም ሴቶች ልጆቻችንን እንድርላችኋለን፤ እኛም ሴቶች ልጆቻችሁን እናገባለን፤ አብረናችሁም እንኖራለን፤ አንድ ሕዝብም እንሆናለን። |
የምንላችሁን የማትሰሙና ለመገረዝ ፈቃደኛ የማትሆኑ ከሆነ ግን ልጃችንን ይዘን እንሄዳለን።” |
የተናገሩትም ነገር ኤሞርንና ልጁን ሴኬምን ደስ አሰኛቸው። |
ወጣቱም ያሉትን ነገር ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም፤ ምክንያቱም የያዕቆብን ልጅ ወዷት ነበር፤ ደግሞም በአባቱ ቤት ካሉት ሰዎች ሁሉ እጅግ የተከበረ ነበር። |
በመሆኑም ኤሞርና ልጁ ሴኬም ወደ ከተማዋ በር በመሄድ በከተማቸው የሚኖሩትን ወንዶች እንዲህ አሏቸው፦ |
“እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር በሰላም መኖር ይፈልጋሉ። ምድሪቱ ለእነሱም ስለምትበቃ በምድሪቱ ይኑሩ፤ እንዲሁም ይነግዱ። ሴቶች ልጆቻቸውን ማግባት፣ የእኛንም ሴቶች ልጆች ለእነሱ መዳር እንችላለን። |
ሆኖም ሰዎቹ ከእኛ ጋር አንድ ሕዝብ በመሆን አብረውን ለመኖር የሚስማሙት፣ ልክ እነሱ እንደተገረዙት የእኛ የሆኑ ወንዶች ሁሉ የሚገረዙ ከሆነ ብቻ ነው። |
እንዲህ ብናደርግ ንብረታቸው፣ ሀብታቸውና ከብቶቻቸው ሁሉ የእኛ ሆኑ ማለት አይደለም? በመሆኑም ከእኛ ጋር ለመኖር ባቀረቡት ሐሳብ እንስማማ።” |
በከተማው በር የሚወጡ ሁሉ ኤሞርና ልጁ ሴኬም ያሏቸውን ሰሙ፤ በከተማዋም በር የሚወጡ ወንዶች በሙሉ ተገረዙ። |
ሆኖም በሦስተኛው ቀን፣ ሰዎቹ ገና ቆስለው እያሉ የዲና ወንድሞች የሆኑት ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች ማለትም ስምዖንና ሌዊ ማንም ሳይጠረጥራቸው ሰይፋቸውን ይዘው ወደ ከተማዋ በመግባት ወንዶቹን ሁሉ ገደሉ። |
ኤሞርንና ልጁን ሴኬምን በሰይፍ ገደሏቸው፤ ከዚያም ዲናን ከሴኬም ቤት ይዘው ሄዱ። |
ሌሎቹ የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም በሬሳ ላይ እየተረማመዱ ከተማዋን ዘረፉ፤ ይህን ያደረጉትም እህታቸው ስለተነወረች ነው። |
እነሱም መንጎቻቸውን፣ ከብቶቻቸውን፣ አህዮቻቸውን እንዲሁም በከተማዋ ውስጥና በመስክ ያገኙትን ሁሉ ወሰዱ። |
በተጨማሪም ንብረቶቻቸውን በሙሉ ወሰዱ፤ እንዲሁም ትናንሽ ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ማረኩ፤ በየቤቱ ያገኙትን ሁሉ ዘረፉ። |
በዚህ ጊዜ ያዕቆብ፣ ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፦ “በዚህች አገር በሚኖሩት በከነአናውያንና በፈሪዛውያን ዘንድ እንደ ጥምብ እንድቆጠር በማድረግ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ከተታችሁኝ። እኔ እንግዲህ በቁጥር አነስተኛ ነኝ፤ እነሱም በእኔ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ግንባር ፈጥረው መምጣታቸው አይቀርም፤ በዚህም የተነሳ እኔም ሆንኩ ቤቴ እንጠፋለን።” |
እነሱ ግን “ታዲያ ማንም እህታችንን እንደ ዝሙት አዳሪ ቆጥሮ እንዲህ ያለ ድርጊት ይፈጽምባት?” አሉ። |
ሰዎች በምድር ላይ ቁጥራቸው እየጨመረ ሲሄድ ሴቶች ልጆችን ወለዱ፤ |
የእውነተኛው አምላክ ልጆችም የሰዎች ሴቶች ልጆች ውብ እንደሆኑ አስተዋሉ። በመሆኑም የመረጧቸውን ሁሉ ለራሳቸው ሚስቶች አድርገው ወሰዱ። |
ከዚያም ይሖዋ “ሰው ሥጋ ስለሆነ መንፈሴ ሰውን ለዘላለም አይታገሥም። በመሆኑም ዘመኑ 120 ዓመት ይሆናል” አለ። |
በዚያ ዘመንም ሆነ ከዚያ በኋላ ኔፍሊም በምድር ላይ ነበሩ። በዚያ ጊዜም የእውነተኛው አምላክ ልጆች ከሰዎች ሴቶች ልጆች ጋር ግንኙነት ፈጸሙ፤ ሴቶቹም ወንዶች ልጆችን ወለዱላቸው። እነሱም በጥንት ዘመን በኃያልነታቸው ዝና ያተረፉ ሰዎች ነበሩ። |
በዚህም የተነሳ ይሖዋ የሰው ልጅ ክፋት በምድር ላይ እንደበዛና የልቡም ሐሳብ ሁሉ ምንጊዜም ወደ መጥፎ ብቻ ያዘነበለ እንደሆነ ተመለከተ። |
ይሖዋም ሰዎችን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ፤ ልቡም አዘነ። |
በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “የፈጠርኳቸውን ሰዎች ከምድር ገጽ ጠራርጌ አጠፋለሁ፤ ሰውን ጨምሮ የቤት እንስሳትን እንዲሁም መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳትንና በሰማያት ላይ የሚበርሩ ፍጥረታትን አጠፋለሁ፤ ምክንያቱም እነሱን በመፍጠሬ ተጸጽቻለሁ።” |
ኖኅ ግን በይሖዋ ፊት ሞገስ አገኘ። |
የኖኅ ታሪክ ይህ ነው። ኖኅ ጻድቅ ሰው ነበር። በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች መካከል እሱ እንከን የሌለበት ሰው ነበር። ኖኅ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ይሄድ ነበር። |
ኖኅ ከጊዜ በኋላ ሴም፣ ካምና ያፌት የተባሉ ሦስት ወንዶች ልጆች ወለደ። |
ይሁንና ምድር በእውነተኛው አምላክ ፊት ተበላሽታ ነበር፤ እንዲሁም በዓመፅ ተሞልታ ነበር። |
አዎ፣ አምላክ ምድርን ተመለከተ፤ ምድርም ተበላሽታ ነበር፤ ሰው ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበር። |
ከዚህ በኋላ አምላክ ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በእነሱ የተነሳ ምድር በዓመፅ ስለተሞላች ሥጋን ሁሉ ለማጥፋት ወስኛለሁ፤ ስለሆነም እነሱን ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ። |
አንተ ከጎፈር እንጨት ለራስህ መርከብ ሥራ። በመርከቡም ውስጥ የተለያዩ ክፍሎችን ሥራ፤ እንዲሁም መርከቡን ከውስጥም ሆነ ከውጭ ቅጥራን ለቅልቀው። |
መርከቡንም የምትሠራው እንደሚከተለው ነው፦ የመርከቡ ርዝመት 300 ክንድ፣ ወርዱ 50 ክንድ እንዲሁም ከፍታው 30 ክንድ ይሁን። |
በመርከቡም ላይ ከጣሪያው ሥር አንድ ክንድ ቁመት ያለው ብርሃን ማስገቢያ የሚሆን መስኮት ሥራ፤ የመርከቡንም በር በጎኑ በኩል አድርግ፤ መርከቡም ምድር ቤት እንዲሁም አንደኛና ሁለተኛ ፎቅ ይኑረው። |
“እኔ ደግሞ ከሰማያት በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃ አመጣለሁ። በምድር ላይ ያለ ነገር ሁሉ ይጠፋል። |
እኔም ከአንተ ጋር ቃል ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ አንተም ወደ መርከቡ መግባት አለብህ፤ አንተ፣ ከአንተም ጋር ወንዶች ልጆችህ፣ ሚስትህና የልጆችህ ሚስቶች ወደ መርከቡ መግባት ይኖርባችኋል። |
ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲተርፉ ከሁሉም ዓይነት ሕያው ፍጡር ተባዕትና እንስት እያደረግክ ሁለት ሁለት ወደ መርከቡ አስገባ፤ |
በሕይወት እንዲተርፉ የሚበርሩ ፍጥረታት እንደየወገናቸው፣ የቤት እንስሳት እንደየወገናቸው እንዲሁም በምድር ላይ ያሉ መሬት ለመሬት የሚሄዱ እንስሳት ሁሉ እንደየወገናቸው ሁለት ሁለት እየሆኑ ከአንተ ጋር ይግቡ። |
ለአንተም ሆነ ለእንስሳቱ ምግብ እንዲሆን ማንኛውንም ዓይነት ምግብ ሰብስበህ ይዘህ ትገባለህ።” |
ኖኅም አምላክ ያዘዘውን ሁሉ በተባለው መሠረት አከናወነ። ልክ እንደዚሁ አደረገ። |
ይህ ከሆነ በኋላ የግብፁ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የዳቦ ጋጋሪዎች አለቃ ጌታቸውን የግብፁን ንጉሥ በደሉ። |
በመሆኑም ፈርዖን በሁለቱ ሹማምንቱ ማለትም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በዳቦ ጋጋሪዎቹ አለቃ ላይ እጅግ ተቆጣ፤ |
እሱም በዘቦች አለቃ ቤት በሚገኘው ወህኒ ቤት ይኸውም ዮሴፍ በታሰረበት እስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩ አደረገ። |
ከዚያም የዘቦቹ አለቃ፣ ዮሴፍ ከእነሱ ጋር እንዲሆንና እንዲረዳቸው መደበው፤ እነሱም ለተወሰነ ጊዜ ወህኒ ቤት ውስጥ ቆዩ። |
እስር ቤት ውስጥ ታስረው የነበሩት የግብፁ ንጉሥ መጠጥ አሳላፊና ዳቦ ጋጋሪ በአንድ ሌሊት ሕልም አለሙ፤ የእያንዳንዳቸውም ሕልም የተለያየ ፍቺ ነበረው። |
በማግስቱ ጠዋት ዮሴፍ ገብቶ ሲያያቸው ተክዘው አገኛቸው። |
በመሆኑም በጌታው ቤት ከእሱ ጋር የታሰሩትን የፈርዖንን ሹማምንት “ምነው ዛሬ ፊታችሁ በሐዘን ጠቆረ?” ሲል ጠየቃቸው። |
እነሱም “ሁለታችንም ሕልም አልመን ነበር፤ ሕልማችንን የሚፈታልን ሰው ግን አላገኘንም” አሉት። ዮሴፍም “ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም? እስቲ ያያችሁትን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው። |
በመሆኑም የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ እንዲህ ሲል ሕልሙን ለዮሴፍ ነገረው፦ “በሕልሜ ከፊት ለፊቴ አንድ የወይን ተክል አየሁ። |
በወይኑም ተክል ላይ ሦስት ቀንበጦች ነበሩ፤ ተክሉም በማቆጥቆጥ ላይ እያለ አበባ አወጣ፤ በዘለላዎቹም ላይ ያሉት ፍሬዎች በሰሉ። |
እኔም የፈርዖንን ጽዋ በእጄ ይዤ ነበር፤ የወይን ፍሬዎቹንም ወስጄ በፈርዖን ጽዋ ውስጥ ጨመቅኳቸው። ከዚያም ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ሰጠሁት።” |
በዚህ ጊዜ ዮሴፍ እንዲህ አለው፦ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፦ ሦስቱ ቀንበጦች ሦስት ቀናት ናቸው። |
ከሦስት ቀን በኋላ ፈርዖን ከእስር ቤት ያስወጣሃል፤ ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል። አንተም የመጠጥ አሳላፊው በነበርክበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ሁሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ። |
ይሁንና ሁኔታዎች ሲስተካከሉልህ እኔን እንዳትረሳኝ። እባክህ ታማኝ ፍቅር አሳየኝ፤ ከዚህ እስር ቤት እንዲያስፈታኝም ስለ እኔ ለፈርዖን ንገረው። |
በመሠረቱ እኔ ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት ተገድጄ ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት ውስጥ የጣሉኝ ያለምንም ጥፋት ነው።” |
የዳቦ ጋጋሪዎቹ አለቃም ዮሴፍ የተናገረው የሕልሙ ፍቺ መልካም መሆኑን ሲያይ እሱም እንዲህ አለው፦ “እኔም ሕልም አይቼ ነበር፤ በሕልሜም ነጭ ዳቦዎች የያዙ ሦስት ቅርጫቶች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤ |
ከላይ ባለው ቅርጫት ውስጥ ለፈርዖን የሚቀርቡ የተለያዩ የተጋገሩ ምግቦች ነበሩ፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከተሸከምኩት ቅርጫት ውስጥ ይበሉ ነበር።” |
ከዚያም ዮሴፍ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፦ ሦስቱ ቅርጫቶች ሦስት ቀናት ናቸው። |
ከሦስት ቀን በኋላ ፈርዖን ከእስር ቤት ያስወጣሃል፤ ራስህንም ቆርጦ በእንጨት ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበላሉ።” |
ሦስተኛው ቀን ደግሞ ፈርዖን የልደት በዓሉን የሚያከብርበት ዕለት ነበር፤ እሱም ለአገልጋዮቹ በሙሉ ግብዣ አዘጋጀ። አገልጋዮቹ ባሉበትም የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃና የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ ከእስር ቤት አስወጣቸው። |
የመጠጥ አሳላፊዎቹንም አለቃ ወደ መጠጥ አሳላፊነት ሹመቱ መለሰው፤ እሱም እንደቀድሞው ለፈርዖን ጽዋውን ይሰጠው ጀመር። |
የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃ ግን ዮሴፍ ሕልማቸውን በፈታላቸው መሠረት ሰቀለው። |
ይሁንና የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ጨርሶም ረሳው። |
ከዚያ በኋላ ያዕቆብ ጉዞውን ቀጠለ፤ ወደ ምሥራቅ ሰዎች ምድርም ሄደ። |
እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውኃ ጉድጓድ ተመለከተ፤ እረኞች የበግ መንጎቻቸውን ሁልጊዜ የሚያጠጡት ከዚያ የውኃ ጉድጓድ ስለነበር በአቅራቢያው ሦስት የበግ መንጎች ተኝተው አየ። በጉድጓዱም አፍ ላይ ትልቅ ድንጋይ ነበር። |
መንጎቹ በሙሉ እዚያ ከተሰበሰቡ በኋላ እረኞቹ በውኃ ጉድጓዱ አፍ ላይ ያለውን ድንጋይ ያንከባልሉና መንጎቹን ያጠጣሉ፤ ከዚያም ድንጋዩን ወደ ቦታው በመመለስ የጉድጓዱን አፍ ይገጥሙታል። |
ያዕቆብም “ወንድሞቼ፣ ከየት ነው የመጣችሁት?” ብሎ ጠየቃቸው፤ እነሱም “ከካራን ነው የመጣነው” አሉት። |
እሱም “የናኮርን የልጅ ልጅ ላባን ታውቁታላችሁ?” አላቸው፤ እነሱም “አዎ፣ እናውቀዋለን” አሉት። |
እሱም “ለመሆኑ ደህና ነው?” አላቸው። እነሱም “አዎ፣ ደህና ነው። እንዲያውም ልጁ ራሔል ይኸው በጎች ይዛ እየመጣች ነው!” አሉት። |
ከዚያም እሱ “እንደምታዩት ገና እኩለ ቀን ነው። አሁን እኮ መንጎች የሚገቡበት ሰዓት አይደለም፤ በጎቹን አጠጧቸውና ወደ ግጦሽ አሰማሯቸው” አላቸው። |
እነሱም “መንጎቹ ሁሉ ካልተሰባሰቡና እረኞቹ ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ ላይ ካላንከባለሉት እንዲህ ማድረግ አንችልም፤ በጎቹን ማጠጣት የምንችለው ከዚያ በኋላ ነው” አሉት። |
እሱም ገና ከእነሱ ጋር እየተነጋገረ ሳለ ራሔል እረኛ ስለነበረች የአባቷን በጎች እየነዳች መጣች። |
ያዕቆብ የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የላባን በጎች ሲያይ ወዲያውኑ ወደ ጉድጓዱ ሄዶ ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ ላይ አንከባለለ፤ የእናቱን ወንድም የላባን በጎችም አጠጣ። |
ከዚያም ያዕቆብ ራሔልን ሳማት፤ ጮክ ብሎም አለቀሰ። |
ያዕቆብም ለራሔል የአባቷ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ነገራት። እሷም እየሮጠች ሄዳ ለአባቷ ነገረችው። |
ላባም የእህቱ ልጅ ስለሆነው ስለ ያዕቆብ ሲሰማ ወደ እሱ እየሮጠ ሄዶ አቅፎ ሳመው፤ ወደ ቤቱም አስገባው። ያዕቆብም ሁኔታውን ሁሉ ለላባ ነገረው። |
ላባም “በእርግጥም አንተ የአጥንቴ ፍላጭ የሥጋዬ ቁራጭ ነህ” አለው። በመሆኑም ያዕቆብ ከእሱ ጋር አንድ ወር ሙሉ ተቀመጠ። |
ከዚያም ላባ ያዕቆብን “ዘመዴ ስለሆንክ ብቻ እኔን በነፃ ልታገለግለኝ ይገባል? ንገረኝ፣ ደሞዝህ ምንድን ነው?” አለው። |
ላባ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት። የታላቋ ስም ሊያ ሲሆን የታናሿ ስም ደግሞ ራሔል ነበር። |
ሊያ ዓይነ ልም ነበረች፤ ራሔል ግን ዓይን የምትማርክ ውብ ሴት ነበረች። |
ያዕቆብ ራሔልን ይወዳት ስለነበር “ለታናሿ ልጅህ ለራሔል ስል ሰባት ዓመት ላገለግልህ ፈቃደኛ ነኝ” አለው። |
ላባም “ለሌላ ሰው ከምሰጣት ለአንተ ብሰጥህ ይሻለኛል፤ አብረኸኝ ተቀመጥ” አለው። |
ያዕቆብም ለራሔል ሲል ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁንና ራሔልን ይወዳት ስለነበር ሰባቱ ዓመታት ለእሱ እንደ ጥቂት ቀናት ነበሩ። |
ከዚያም ያዕቆብ ላባን “እንግዲህ የተባባልነው ጊዜ ስላበቃ ሚስቴን ስጠኝ፤ ከእሷም ጋር ልተኛ” አለው። |
ስለዚህ ላባ የአካባቢውን ሰዎች በሙሉ ጠራ፤ ግብዣም አደረገ። |
ሆኖም ሲመሽ ላባ ልጁን ሊያን ወስዶ ከእሷ ጋር እንዲተኛ ለያዕቆብ ሰጠው። |
በተጨማሪም ላባ የእሱ አገልጋይ የሆነችውን ዚልጳን አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለሊያ ሰጣት። |
በማግስቱ ጠዋት ያዕቆብ አብራው ያደረችው ሊያ መሆኗን አወቀ! በመሆኑም ያዕቆብ ላባን “ያደረግክብኝ ነገር ምንድን ነው? ያገለገልኩህ ለራሔል ስል አልነበረም? ታዲያ ለምን አታለልከኝ?” አለው። |
ላባም እንዲህ አለው፦ “በአካባቢያችን በኩሯ እያለች ታናሺቱን መዳር የተለመደ አይደለም። |
ሳምንቱን ከዚህችኛዋ ጋር ተሞሸር። ከዚያም ለምታገለግለኝ ተጨማሪ ሰባት ዓመታት ሌላኛዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።” |
ያዕቆብም እንደተባለው አደረገ፤ ሳምንቱን ከዚህችኛዋ ጋር ተሞሸረ። ከዚያም ላባ ልጁን ራሔልን ሚስት እንድትሆነው ሰጠው። |
በተጨማሪም ላባ አገልጋዩ የሆነችውን ባላን አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለራሔል ሰጣት። |
ከዚያም ያዕቆብ ከራሔል ጋር ተኛ፤ ራሔልንም ከሊያ ይልቅ ወደዳት። ላባንም ሌላ ሰባት ዓመት አገለገለው። |
ይሖዋም ሊያ እንዳልተወደደች ሲመለከት መፀነስ እንድትችል አደረጋት፤ ራሔል ግን መሃን ነበረች። |
ሊያም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ይህ የሆነው ይሖዋ መከራዬን ስላየልኝ ነው፤ ከእንግዲህ ባሌ ይወደኛል” ስትል ስሙን ሮቤል አለችው። |
ዳግመኛም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ይሖዋ እንዳልተወደድኩ ስለሰማ ይሄኛውንም ልጅ ሰጠኝ” አለች። ስሙንም ስምዖን አለችው። |
አሁንም ደግሞ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “ሦስት ወንዶች ልጆች ስለወለድኩለት አሁን ባሌ ይቀርበኛል” አለች። በዚህም የተነሳ ሌዊ ተባለ። |
አሁንም እንደገና ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች። እሷም “አሁን ይሖዋን አወድሰዋለሁ” አለች። ስለሆነም ይሁዳ አለችው። ከዚያ በኋላ መውለድ አቆመች። |
ሆኖም አምላክ ኖኅን እንዲሁም ከእሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን የዱር እንስሳትና የቤት እንስሳት ሁሉ አሰበ። አምላክም ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውኃውም መጉደል ጀመረ። |
የጥልቁ ውኃ ምንጮችና የሰማያት የውኃ በሮች ተደፈኑ፤ በመሆኑም ከሰማያት የሚወርደው ዝናብ መዝነቡን አቆመ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.