text stringlengths 4 267 |
|---|
የሥጋ ደዌው በቆዳው ሁሉ ላይ ቢወጣና የሥጋ ደዌው ካህኑ ሊያየው እስከሚችለው ድረስ ግለሰቡን ከራሱ አንስቶ እስከ እግሮቹ ድረስ ቢያለብሰው |
እንዲሁም ካህኑ ሲመረምረው የሥጋ ደዌው ቆዳውን ሁሉ አልብሶት ቢያይ ቁስሉ የወጣበት ግለሰብ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል። ቆዳው ሙሉ በሙሉ ወደ ነጭነት ተለውጧል፤ ሰውየውም ንጹሕ ነው። |
ሆኖም በቆዳው ላይ አፉን የከፈተ ቁስል በወጣበት በማንኛውም ጊዜ ሰውየው ርኩስ ይሆናል። |
ካህኑ አፉን የከፈተ ቁስል ካየ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። አፉን የከፈተው ቁስል ርኩስ ነው። ይህ የሥጋ ደዌ ነው። |
ሆኖም አፉን የከፈተው ቁስል እንደገና ወደ ነጭነት ከተለወጠ ሰውየው ወደ ካህኑ ይመጣል። |
ካህኑም ይመረምረዋል፤ ቁስሉ ወደ ነጭነት ከተለወጠ ካህኑ ቁስሉ የወጣበት ግለሰብ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል። ሰውየው ንጹሕ ነው። |
“አንድ ሰው በቆዳው ላይ እባጭ ቢወጣበትና ቢድን |
ሆኖም እባጩ በነበረበት ቦታ ላይ ነጭ እብጠት ወይም ነጣ ያለ ቀይ ቋቁቻ ቢወጣ ሰውየው ራሱን ለካህን ያሳይ። |
ካህኑም ቁስሉን ይመረምረዋል፤ ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነና በዚያ ቦታ ላይ ያለው ፀጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ በእባጩ ላይ የወጣ የሥጋ ደዌ ነው። |
ይሁንና ካህኑ ቁስሉን ሲመረምረው በላዩ ላይ ነጭ ፀጉር ከሌለና ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ እንዲሁም እየከሰመ ከሆነ ካህኑ ሰውየውን ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል። |
ቁስሉ በቆዳው ላይ እየተስፋፋ መሆኑ በግልጽ የሚታይ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ ደዌ ነው። |
ይሁን እንጂ ቋቁቻው ባለበት ከቆመና ካልተስፋፋ ይህ እባጩ ያስከተለው ቁስል ነው፤ ካህኑም ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል። |
“ወይም አንድ ሰው እሳት አቃጥሎት በሰውነቱ ቆዳ ላይ ጠባሳ ቢተውና ጠባሳው ላይ ያለው ያልሻረ ቁስል ነጣ ያለ ቀይ ወይም ነጭ ቋቁቻ ቢሆን |
ካህኑ ቁስሉን ይመረምረዋል። በቋቁቻው ላይ ያለው ፀጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠና ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነ ይህ በጠባሳው ላይ የወጣ የሥጋ ደዌ ነው፤ ካህኑም ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ የሥጋ ደዌ ነው። |
ይሁንና ካህኑ ሲመረምረው በቋቁቻው ላይ ነጭ ፀጉር ከሌለና ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ እንዲሁም እየከሰመ ከሆነ ካህኑ ሰውየውን ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል። |
ካህኑም በሰባተኛው ቀን ሰውየውን ይመረምረዋል፤ ቁስሉ በቆዳው ላይ እየተስፋፋ መሆኑ በግልጽ የሚታይ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል። ይህ የሥጋ ደዌ ነው። |
ይሁንና ቋቁቻው ባለበት ከቆመና በቆዳው ላይ ካልተስፋፋ እንዲሁም ከከሰመ ይህ ጠባሳው ያስከተለው እብጠት ነው፤ ይህ የጠባሳው ቁስል ስለሆነ ካህኑ ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል። |
“በአንድ ወንድ ወይም በአንዲት ሴት ራስ ወይም አገጭ ላይ ቁስል ቢወጣ |
ካህኑ ቁስሉን ይመረምረዋል። ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ከሆነ እንዲሁም በዚያ ቦታ ላይ ያለው ፀጉር ቢጫ ከሆነና ከሳሳ ካህኑ ያ ሰው ርኩስ መሆኑን ያስታውቃል፤ ይህ በራስ ቆዳ ወይም በጢም ላይ የሚወጣ ቁስል ነው። ይህ የራስ ወይም የአገጭ የሥጋ ደዌ ነው። |
ሆኖም ካህኑ ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ አለመሆኑንና በዚያ ቦታ ላይ ጥቁር ፀጉር አለመኖሩን ካየ ቁስሉ የወጣበትን ሰው ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያድርገው። |
ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቁስሉን ይመረምረዋል፤ ቁስሉ ካልተስፋፋና በዚያ ቦታ ላይ ቢጫ ፀጉር ካልወጣ እንዲሁም ቁስሉ ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ |
ሰውየው ፀጉሩን ይላጭ፤ ቁስሉ ያለበትን ቦታ ግን አይላጨውም። ከዚያም ካህኑ ቁስሉ የወጣበትን ሰው ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቆይ ያደርገዋል። |
“ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቁስሉ ያለበትን ቦታ እንደገና ይመረምረዋል፤ ቁስሉ በቆዳው ላይ ካልተስፋፋና ከቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ ካህኑ ሰውየው ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ፤ ሰውየውም ልብሶቹን ይጠብ፤ ንጹሕም ይሁን። |
ሆኖም ሰውየው ከነጻ በኋላ ቁስሉ በቆዳው ላይ እየተስፋፋ መሆኑ በግልጽ ከታየ |
ካህኑ ይመረምረዋል፤ ቁስሉ በቆዳው ላይ ከተስፋፋ ካህኑ ቢጫ ፀጉር መኖር አለመኖሩን ማየት አያስፈልገውም፤ ሰውየው ርኩስ ነው። |
ሆኖም ካህኑ ሲመረምረው ቁስሉ ካልተስፋፋና በዚያ ቦታ ጥቁር ፀጉር ከበቀለ ቁስሉ ድኗል ማለት ነው። ሰውየው ንጹሕ ነው፤ ካህኑም ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል። |
“አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት በቆዳቸው ላይ ቋቁቻ ቢወጣና ቋቁቻው ደግሞ ነጭ ቢሆን |
ካህኑ ይመረምራቸዋል። በቆዳው ላይ የወጣው ቋቁቻ ደብዘዝ ያለ ነጭ ከሆነ ይህ ቆዳው ላይ የወጣ ጉዳት የሌለው ሽፍታ ነው። ሰውየው ንጹሕ ነው። |
“አንድ ወንድ ራሱ ቢመለጥና ራሰ በራ ቢሆን ሰውየው ንጹሕ ነው። |
ሰውየው ከፊት በኩል ቢመለጥና ራሰ በራ ቢሆን ንጹሕ ነው። |
ሆኖም በራሱ ወይም በግንባሩ ላይ ባለው በራ ላይ ቀላ ያለ ነጭ ቁስል ቢወጣበት ይህ በራሱ ወይም በግንባሩ ላይ የወጣ ሥጋ ደዌ ነው። |
ካህኑም ሰውየውን ይመረምረዋል፤ በአናቱ ወይም በግንባሩ ላይ ባለው በራ ላይ የወጣው ቁስል ያስከተለው እብጠት ቀላ ያለ ነጭ ከሆነና በቆዳው ላይ ሲታይ የሥጋ ደዌ የሚመስል ከሆነ |
ሰውየው የሥጋ ደዌ በሽተኛ ነው። ርኩስ ነው፤ በራሱም ላይ ባለው ደዌ የተነሳ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ። |
የሥጋ ደዌ ያለበት ሰው ልብሶቹ የተቀዳደዱ ይሁኑ፤ ፀጉሩም ይንጨብረር፤ አፍንጫው ሥር እስካለው ጢም ድረስ ተሸፋፍኖ ‘ርኩስ ነኝ፣ ርኩስ ነኝ!’ እያለ ይጩኽ። |
ሰውየው ደዌው በላዩ ላይ ባለበት ጊዜ ሁሉ ርኩስ ይሆናል። ርኩስ ስለሆነም ከሰዎች ተገልሎ መኖር አለበት። መኖሪያውም ከሰፈሩ ውጭ ይሆናል። |
“ደዌው ከሱፍም ሆነ ከበፍታ የተሠራን ልብስ ቢበክል |
ወይም የበፍታውንም ሆነ የሱፉን ድር ወይም ማግ አሊያም ቁርበትን ወይም ደግሞ ከቆዳ የተሠራን ማንኛውንም ነገር ቢበክል |
እንዲሁም ደዌው ያስከተለው ወደ ቢጫነት ያደላ አረንጓዴ ወይም ቀላ ያለ ምልክት ልብሱን፣ ቆዳውን፣ ድሩን፣ ማጉን ወይም ደግሞ ከቆዳ የተሠራውን የትኛውንም ዕቃ ቢበክል ይህ በደዌ ምክንያት የተከሰተ ብክለት ነው፤ ካህኑ እንዲያየው መደረግ አለበት። |
ካህኑም ደዌውን ይመረምረዋል፤ ደዌው ያለበትም ነገር ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቀመጥ ያድርግ። |
በሰባተኛው ቀን ደዌውን ሲመረምረው ደዌው በልብሱ፣ በድሩ፣ በማጉ ወይም በቆዳው ላይ (ቆዳው ለማንኛውም ዓይነት አገልግሎት የሚውል ይሁን) ተስፋፍቶ ቢገኝ ደዌው አደገኛ ደዌ ነው፤ ዕቃውም ርኩስ ነው። |
እሱም ደዌው ያለበትን ልብስ ወይም የሱፍም ሆነ የበፍታ ድር ወይም ማግ አሊያም ደግሞ ከቆዳ የተሠራ ማንኛውም ዕቃ ያቃጥል፤ ምክንያቱም ይህ አደገኛ ደዌ ነው። በእሳት መቃጠል ይኖርበታል። |
“ሆኖም ካህኑ ሲመረምረው ደዌው በልብሱ ወይም በድሩ አሊያም በማጉ ወይም ደግሞ ከቆዳ በተሠራው በማንኛውም ዕቃ ላይ ካልተስፋፋ |
ካህኑ ደዌው ያለበትን ነገር እንዲያጥቡት ያዛል፤ ከዚያም እንደገና ለሰባት ቀን ተገልሎ እንዲቀመጥ ያደርጋል። |
የተበከለው ዕቃ በደንብ ከታጠበ በኋላ ካህኑ ይመረምረዋል። ደዌው ባይስፋፋም እንኳ ብክለቱ መልኩን ካልቀየረ ዕቃው ርኩስ ነው። ዕቃው ከውስጡ ወይም ከውጭው ስለተበላ በእሳት አቃጥለው። |
“ሆኖም ዕቃው በደንብ ከታጠበ በኋላ ካህኑ ሲመረምረው የተበከለው ክፍል ከደበዘዘ ያን ቦታ ከልብሱ ወይም ከቆዳው አሊያም ከድሩ ወይም ደግሞ ከማጉ ላይ ቀዶ ያወጣዋል። |
ይሁንና ደዌው በልብሱ ወይም በድሩ አሊያም በማጉ ወይም ደግሞ ከቆዳ በተሠራው በማንኛውም ዕቃ ላይ በሌላ ቦታ አሁንም ከታየ ደዌው እየተስፋፋ ነው፤ ስለዚህ በደዌው የተበከለውን ማንኛውንም ዕቃ በእሳት አቃጥለው። |
ሆኖም በልብሱ ወይም በድሩ አሊያም በማጉ ወይም ደግሞ ከቆዳ በተሠራው በማንኛውም ዕቃ ላይ የተከሰተው ብክለት ስታጥበው ከለቀቀ ዕቃው ለሁለተኛ ጊዜ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል። |
“ከሱፍ ወይም ከበፍታ በተሠራ ልብስ አሊያም በድር ወይም በማግ አሊያም ደግሞ ከቆዳ በተሠራ በማንኛውም ዕቃ ላይ የወጣን ደዌ በተመለከተ ዕቃው ንጹሕ ነው ብሎ ለማስታወቅም ሆነ ርኩስ ነው ለማለት ሕጉ ይህ ነው።” |
ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለካህናቱ ማለትም ለአሮን ወንዶች ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ማንም ሰው ከሕዝቦቹ መካከል ለሞተ ሰው ራሱን አያርክስ። |
ይሁንና ለቅርብ የሥጋ ዘመዱ ይኸውም ለእናቱ፣ ለአባቱ፣ ለወንድ ልጁ፣ ለሴት ልጁ፣ ለወንድሙ እንዲህ ማድረግ ይችላል፤ |
እንዲሁም ድንግል ለሆነች፣ ለምትቀርበውና ላላገባች እህቱ ሲል ራሱን ማርከስ ይችላል። |
ከሕዝቡ መካከል ባል ላገባች ሴት ሲል ራሱን ማርከስና ማዋረድ የለበትም። |
ራሳቸውን መላጨት ወይም የጢማቸውን ዳር ዳር መላጨት አሊያም ሰውነታቸውን መተልተል የለባቸውም። |
የአምላካቸው ምግብ የሆኑትን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርቡትን መባዎች የሚያቀርቡት እነሱ ስለሆኑ ለአምላካቸው ቅዱሳን መሆንና የአምላካቸውን ስም ከማርከስ መራቅ አለባቸው፤ ቅዱሳን መሆን ይኖርባቸዋል። |
ዝሙት አዳሪ የሆነችን ይኸውም የረከሰችን ሴት ወይም ከባሏ የተፋታችን ሴት አያግቡ፤ ምክንያቱም ካህኑ ለአምላኩ ቅዱስ ነው። |
የአምላክህን ምግብ የሚያቀርበው እሱ ስለሆነ ቀድሰው። እናንተን የምቀድሳችሁ እኔ ይሖዋ ቅዱስ ስለሆንኩ እሱም በአንተ ፊት ቅዱስ ሆኖ መገኘት አለበት። |
“‘የአንድ ካህን ሴት ልጅ ዝሙት አዳሪ በመሆን ራሷን ብታረክስ አባቷን ታረክሳለች። ስለዚህ በእሳት መቃጠል አለባት። |
“‘ከወንድሞቹ መካከል ሊቀ ካህናት በመሆን በራሱ ላይ የቅብዓት ዘይት የሚፈስበትና የክህነት ልብሶቹን እንዲለብስ የተሾመው ካህን ፀጉሩን ማንጨብረር ወይም ልብሶቹን መቅደድ የለበትም። |
ወደ ሞተ ሰው አይጠጋ። ሌላው ቀርቶ ለአባቱ ወይም ለእናቱ ሲል ራሱን አያርክስ። |
ለአምላክ የተወሰኑ መሆንን የሚያሳየው ምልክት ይኸውም የአምላኩ የቅብዓት ዘይት በላዩ ላይ ስላለ ከመቅደሱ መውጣትም ሆነ የአምላኩን መቅደስ ማርከስ የለበትም። እኔ ይሖዋ ነኝ። |
“‘የሚያገባው ድንግል የሆነችን ሴት መሆን ይኖርበታል። |
ባል የሞተባትን፣ ከባሏ የተፋታችን፣ የረከሰችን ወይም ዝሙት አዳሪ የሆነችን ሴት አያግባ፤ ሆኖም ከሕዝቡ መካከል ድንግል የሆነችውን ያግባ። |
እሱን የምቀድሰው እኔ ይሖዋ ስለሆንኩ በሕዝቡ መካከል ዘሩን ማርከስ የለበትም።’” |
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“አሮንን እንዲህ በለው፦ ‘ከዘርህ መካከል በትውልዶቹ ሁሉ በሰውነቱ ላይ እንከን ያለበት ማንም ሰው የአምላኩን ምግብ ለማቅረብ አይምጣ። |
እንደሚከተሉት ያሉ እንከኖች ያሉበት ማንም ሰው መቅረብ የለበትም፦ ዓይነ ስውር ወይም አንካሳ አሊያም የፊቱ ገጽታ የተበላሸ ወይም አንዱ እግሩ ወይም አንዱ እጁ የረዘመ |
አሊያም እግሩ የተሰበረ ወይም እጁ የተሰበረ ሰው |
አሊያም ጀርባው ላይ ጉብር ያለበት ወይም ድንክ የሆነ አሊያም የዓይን ችግር ያለበት ወይም ችፌ የያዘው አሊያም ጭርት ያለበት ወይም የዘር ፍሬው የተጎዳ አይቅረብ። |
ከካህኑ ከአሮን ዘር እንከን ያለበት ማንኛውም ሰው በእሳት የሚቀርቡትን የይሖዋን መባዎች ለማቅረብ አይምጣ። ይህ ሰው እንከን ስላለበት የአምላኩን ምግብ ለማቅረብ መምጣት አይችልም። |
እጅግ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮችና ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች የአምላኩን ምግብ መብላት ይችላል። |
ሆኖም እንከን ስላለበት ወደ መጋረጃው አይቅረብ፤ ወደ መሠዊያውም አይጠጋ፤ የምቀድሳቸው እኔ ይሖዋ ስለሆንኩ መቅደሴን አያርክስ።’” |
ስለዚህ ሙሴ ይህን ለአሮን፣ ለወንዶች ልጆቹና ለእስራኤላውያን በሙሉ ነገራቸው። |
“‘አንድ ሰው የሚያቀርበው መባ የኅብረት መሥዋዕት ቢሆንና ከከብቶች መካከል ወስዶ የሚያቀርብ ከሆነ እንስሳው ተባዕትም ሆነ እንስት እንከን የሌለበትን በይሖዋ ፊት ማቅረብ ይኖርበታል። |
እሱም መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ እንስሳውም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ይታረዳል፤ ካህናት የሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይረጩታል። |
እሱም ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤ ይኸውም አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ፣ |
ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያቀርባል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳዋል። |
የአሮን ወንዶች ልጆችም በመሠዊያው ላይ ይኸውም በእሳቱ ላይ ባለው እንጨት ላይ በሚገኘው የሚቃጠል መባ ላይ ያጨሱታል፤ ይህም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ ነው። |
“‘ለይሖዋ የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው መባ ከመንጋው መካከል የተወሰደ ከሆነ እንስሳው ተባዕትም ሆነ እንስት እንከን የሌለበትን ያቀርባል። |
የበግ ጠቦት መባ አድርጎ የሚያቀርብ ከሆነ ይሖዋ ፊት ያቀርበዋል። |
እሱም መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ይጭናል፤ እንስሳውም በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ለፊት ይታረዳል። የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይረጩታል። |
ከኅብረት መሥዋዕቱ ላይም ስቡን ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባል። ከጀርባ አጥንቱ አጠገብ ያለውን ላት በሙሉ፣ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ ያነሳዋል፤ |
ደግሞም ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያነሳዋል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል። |
ካህኑም እንደ ምግብ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት እንደሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል። |
“‘ፍየል መባ አድርጎ የሚያቀርብ ከሆነ ይሖዋ ፊት ያቀርበዋል። |
እጁንም በራሱ ላይ ይጭንበታል፤ በመገናኛ ድንኳኑም ፊት ይታረዳል፤ የአሮን ወንዶች ልጆችም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ይርጩት። |
ለይሖዋ በእሳት የሚቃጠል መባ አድርጎ የሚያቀርበውም እነዚህን ነው፦ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ፣ በአንጀቱ ዙሪያ ያለውን ስብ በሙሉ፣ |
ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ማለትም በሽንጡ አካባቢ ያለውን ስብ ያቀርባል። በጉበቱ ላይ ያለውንም ሞራ ከኩላሊቶቹ ጋር አብሮ ያነሳል። |
ካህኑም እንደ ምግብ ይኸውም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ እንዳለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሳቸዋል። ስቡ ሁሉ የይሖዋ ነው። |
“‘ስብም ሆነ ደም ፈጽሞ አትብሉ። ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተም ሆነ ለትውልዶቻችሁ ዘላቂ ደንብ ነው።’” |
በስምንተኛውም ቀን ሙሴ አሮንን፣ ወንዶች ልጆቹንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠራ። |
አሮንንም እንዲህ አለው፦ “ለኃጢአት መባ አንድ ጥጃ፣ ለሚቃጠል መባ ደግሞ አንድ አውራ በግ ለራስህ ውሰድ፤ እንከን የሌለባቸው ይሁኑ፤ በይሖዋም ፊት አቅርባቸው። |
እስራኤላውያንን ግን እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘ለኃጢአት መባ አንድ ተባዕት ፍየል፣ ለሚቃጠል መባ ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸውና እንከን የሌለባቸው አንድ ጥጃና አንድ የበግ ጠቦት ውሰዱ፤ |
የኅብረት መሥዋዕት ሆነው በይሖዋ ፊት እንዲሠዉም አንድ በሬና አንድ አውራ በግ ውሰዱ፤ እንዲሁም በዘይት የተለወሰ የእህል መባ አቅርቡ፤ ምክንያቱም ይሖዋ ዛሬ ለእናንተ ይገለጣል።’” |
ስለዚህ ሙሴ ያዘዛቸውን ነገሮች በሙሉ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ፊት አመጡ። ከዚያም መላው ማኅበረሰብ መጥቶ በይሖዋ ፊት ቆመ። |
ሙሴም “የይሖዋ ክብር ይገለጥላችሁ ዘንድ ይሖዋ እንድታደርጉት ያዘዛችሁ ነገር ይህ ነው” አለ። |
ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኃጢአት መባህንና የሚቃጠል መባህን አቅርብ፤ ለራስህና ለቤትህም አስተሰርይ፤ ይሖዋ ባዘዘውም መሠረት የሕዝቡን መባ አቅርብ፤ እንዲሁም ለእነሱ አስተሰርይ።” |
አሮንም ወዲያው ወደ መሠዊያው ቀርቦ ስለ ራሱ የኃጢአት መባ ሆኖ የሚቀርበውን ጥጃ አረደ። |
ከዚያም ወንዶች ልጆቹ ደሙን አቀረቡለት፤ እሱም ጣቱን ደሙ ውስጥ በመንከር የመሠዊያውን ቀንዶች ቀባ፤ የቀረውንም ደም በመሠዊያው ሥር አፈሰሰው። |
ይሖዋ ሙሴን ባዘዘውም መሠረት ከኃጢአት መባው ላይ ስቡን፣ ኩላሊቶቹንና በጉበቱ ላይ ያለውን ሞራ ወስዶ በመሠዊያው ላይ እንዲጨሱ አደረገ። |
ሥጋውንና ቆዳውንም ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.