text stringlengths 4 267 |
|---|
ከዚያም የሚቃጠል መባ ሆኖ የሚቀርበውን እንስሳ አረደው፤ ወንዶች ልጆቹም ደሙን ሰጡት፤ እሱም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው። |
እነሱም የሚቃጠለውን መባ ብልቶች ከነጭንቅላቱ ሰጡት፤ እሱም በመሠዊያው ላይ እንዲጨሱ አደረገ። |
በተጨማሪም ሆድ ዕቃውንና እግሮቹን አጠባቸው፤ በመሠዊያው ላይ ባለው በሚቃጠለው መባ ላይም እንዲጨሱ አደረገ። |
በመቀጠልም የሕዝቡን መባ አቀረበ፤ ለሕዝቡ የኃጢአት መባ ሆኖ የሚቀርበውን ፍየል ወስዶ አረደው፤ እንደ መጀመሪያው ሁሉ በዚህኛውም የኃጢአት መባ አቀረበ። |
ከዚያም የሚቃጠለውን መባ አቀረበ፤ በተለመደውም አሠራር መሠረት አቀረበው። |
በመቀጠልም የእህል መባውን አቀረበ፤ ከላዩ ላይም እፍኝ ሙሉ አንስቶ ጠዋት ላይ ከሚቀርበው የሚቃጠል መባ በተጨማሪ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አደረገ። |
በኋላም ለሕዝቡ የኅብረት መሥዋዕት የሚሆኑትን በሬውንና አውራውን በግ አረዳቸው። ወንዶች ልጆቹም ደሙን ሰጡት፤ እሱም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው። |
ከዚያም የበሬውን ስቦች፣ የአውራውን በግ ላት፣ ሆድ ዕቃውን የሸፈነውን ስብ፣ ኩላሊቶቹንና የጉበቱን ሞራ |
ማለትም ስቡን ሁሉ በፍርምባዎቹ ላይ አደረጉ፤ ስቡም ሁሉ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አደረገ። |
ሆኖም አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ እግሩን ልክ ሙሴ ባዘዘው መሠረት እንደሚወዘወዝ መባ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ወዘወዛቸው። |
ከዚያም አሮን እጆቹን ወደ ሕዝቡ በማንሳት ባረካቸው፤ የኃጢአት መባውን፣ የሚቃጠል መባውንና የኅብረት መሥዋዕቶቹን ካቀረበ በኋላ ወረደ። |
በመጨረሻም ሙሴና አሮን ወደ መገናኛ ድንኳኑ ገቡ፤ ከዚያም ወጥተው ሕዝቡን ባረኩ። በዚህ ጊዜ የይሖዋ ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ፤ |
እሳትም ከይሖዋ ፊት ወጥቶ በመሠዊያው ላይ ያለውን የሚቃጠል መባና ስብ በላ። ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያይ እልል አለ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ። |
ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“መብራቱ ያለማቋረጥ እንዲበራ ለማድረግ ለመብራቱ የሚሆን ተጨቅጭቆ የተጠለለ ንጹሕ የወይራ ዘይት እንዲያመጡልህ እስራኤላውያንን እዘዛቸው። |
ከምሽት አንስቶ እስከ ጠዋት ድረስ መብራቱ በይሖዋ ፊት ያለማቋረጥ እንዲበራ አሮን በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ካለው ከምሥክሩ መጋረጃ ውጭ ያስቀምጠው። በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላለማዊ ደንብ ነው። |
ዘወትር በይሖዋ ፊት እንዲሆኑ መብራቶቹን ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው መቅረዝ ላይ በቦታ በቦታቸው ያስቀምጣቸው። |
“አንተም የላመ ዱቄት ወስደህ የቀለበት ቅርጽ ያላቸው 12 ዳቦዎችን ጋግር። እያንዳንዱ ዳቦ ከሁለት አሥረኛ ኢፍ ዱቄት የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል። |
እነዚህንም በይሖዋ ፊት ባለው ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ ላይ ስድስት ስድስት አድርገህ በማነባበር በሁለት ረድፍ ታስቀምጣቸዋለህ። |
ተነባብሮ በተቀመጠው በእያንዳንዱ ረድፍ ላይም ንጹሕ ነጭ ዕጣን አድርግ፤ ይህም ለምግቡ መታሰቢያ እንዲሆን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ይሆናል። |
እሱም በየሰንበቱ ዘወትር በይሖዋ ፊት ይደርድረው። ይህ በእኔና በእስራኤላውያን መካከል ያለ ዘላቂ ቃል ኪዳን ነው። |
ይህም የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ይሆናል፤ ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች መካከል ለእሱ እጅግ ቅዱስ ነገር ስለሆነ ቅዱስ በሆነ ቦታ ይበሉታል፤ ይህ ዘላቂ ሥርዓት ነው።” |
በእስራኤላውያን መካከል በእናቱ እስራኤላዊ በአባቱ ግን ግብፃዊ የሆነ አንድ ሰው ነበር፤ በሰፈሩም ውስጥ በእሱና በአንድ እስራኤላዊ መካከል ጠብ ተነሳ። |
የእስራኤላዊቷም ልጅ የአምላክን ስም መሳደብና መራገም ጀመረ። በመሆኑም ወደ ሙሴ አመጡት። የእናትየውም ስም ሸሎሚት ነበር፤ እሷም ከዳን ነገድ የሆነው የዲብራይ ልጅ ነበረች። |
እነሱም የይሖዋ ውሳኔ ግልጽ እስኪሆንላቸው ድረስ በጥበቃ ሥር እንዲቆይ አደረጉት። |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“የተራገመውን ሰው ከሰፈሩ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሰዎች ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ መላው ጉባኤም በድንጋይ ይውገረው። |
ለእስራኤላውያንም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ማንኛውም ሰው አምላኩን ቢራገም ለሠራው ኃጢአት ይጠየቅበታል። |
ስለሆነም የይሖዋን ስም የተሳደበው ሰው ይገደል። መላው ጉባኤም በድንጋይ ይውገረው። የባዕድ አገሩም ሰው የአምላክን ስም ከተሳደበ ልክ እንደ አገሩ ተወላጅ ይገደል። |
“‘አንድ ሰው የሰው ሕይወት ካጠፋ ይገደል። |
የቤት እንስሳን የገደለ ሰው፣ ሕይወት ስለ ሕይወት ካሳ አድርጎ መክፈል ይኖርበታል። |
አንድ ሰው በባልንጀራው ላይ ጉዳት ቢያደርስ ልክ እሱ ያደረሰው ዓይነት ጉዳት በራሱ ላይ እንዲደርስ ይደረግ። |
ስብራት ስለ ስብራት፣ ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ ይሁን፤ በሰውየው ላይ ያደረሰው ዓይነት ጉዳት በእሱ ላይ እንዲደርስ ይደረግ። |
እንስሳን መትቶ የገደለ ስለ እንስሳው ካሳ መክፈል ይኖርበታል፤ ሰውን መትቶ የገደለ ግን መገደል አለበት። |
“‘ለባዕድ አገሩም ሰው ሆነ ለአገሬው ተወላጅ፣ ለሁላችሁም የሚሠራው አንድ ዓይነት ድንጋጌ ነው፤ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’” |
ከዚያም ሙሴ ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ እነሱም የተራገመውን ሰው ከሰፈሩ ውጭ አውጥተው በድንጋይ ወገሩት። በዚህ መንገድ እስራኤላውያን ልክ ይሖዋ ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ። |
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘አንድ ሰው የአንድን ግለሰብ የተተመነ ዋጋ ለይሖዋ ለማቅረብ ልዩ ስእለት ቢሳል |
ከ20 ዓመት እስከ 60 ዓመት ድረስ ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኝ ወንድ የሚተመነው ዋጋ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል 50 የብር ሰቅል ይሆናል። |
ሴት ከሆነች ግን የሚተመንላት ዋጋ 30 ሰቅል ይሆናል። |
ከ5 ዓመት እስከ 20 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወንድ ከሆነ የሚተመንለት ዋጋ 20 ሰቅል ይሆናል፤ ሴት ከሆነች ደግሞ 10 ሰቅል ይሆናል። |
ከአንድ ወር እስከ አምስት ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ወንድ ከሆነ የሚተመንለት ዋጋ አምስት የብር ሰቅል ይሆናል፤ ሴት ከሆነች ደግሞ ሦስት የብር ሰቅል ይሆናል። |
“‘ዕድሜው ከ60 ዓመት በላይ ለሆነ ወንድ ደግሞ የሚተመንለት ዋጋ 15 ሰቅል ይሆናል፤ ሴት ከሆነች 10 ሰቅል ይሆናል። |
ሆኖም ሰውየው በጣም ድሃ ቢሆንና የተተመነውን ዋጋ መስጠት ባይችል ግለሰቡ ካህኑ ፊት ይቆማል፤ ካህኑም ለሰውየው ዋጋ ይተምንለታል። ካህኑ ስእለት የተሳለውን ሰው አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ለሰውየው ዋጋ ይተምንለታል። |
“‘ስእለቱ ለይሖዋ መባ ሆኖ መቅረብ የሚችል እንስሳ ከሆነ ለይሖዋ የሚሰጠው ማንኛውም ነገር የተቀደሰ ይሆናል። |
እንስሳውን በሌላ መተካትም ሆነ መጥፎውን በጥሩ፣ ጥሩውን በመጥፎ መለወጥ አይችልም። እንስሳውን በሌላ እንስሳ መለወጥ ካለበት ግን የመጀመሪያው እንስሳም ሆነ ተለዋጭ ሆኖ የቀረበው እንስሳ የተቀደሱ ይሆናሉ። |
ሰውየው ያቀረበው እንስሳ ለይሖዋ መባ ሆኖ ሊቀርብ የማይችል ርኩስ እንስሳ ከሆነ እንስሳውን ካህኑ ፊት ያቁመው። |
ካህኑ እንስሳው ጥሩ ወይም መጥፎ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ ይተምንለት። ካህኑ የተመነውም ዋጋ ይጸናል። |
ሆኖም ሰውየው እንስሳውን መልሶ መግዛት ከፈለገ በተተመነው ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ መስጠት አለበት። |
“‘አንድ ሰው ቤቱን ቅዱስ አድርጎ ለይሖዋ ቢሰጥ ካህኑ ቤቱ ጥሩ ወይም መጥፎ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋ ይተምንለት። የቤቱ ዋጋ ካህኑ የተመነው ዋጋ ይሆናል። |
ሆኖም ቤቱን ቅዱስ አድርጎ የሰጠው ሰው ቤቱን መልሶ መግዛት ከፈለገ በተተመነው ዋጋ ላይ የገንዘቡን አንድ አምስተኛ ጨምሮ መስጠት አለበት፤ ቤቱም የእሱ ይሆናል። |
“‘አንድ ሰው ርስት አድርጎ ከያዘው እርሻ ላይ የተወሰነውን ለይሖዋ ቅዱስ አድርጎ ቢሰጥ ዋጋው መተመን ያለበት የሚዘራበትን ዘር መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት ይሆናል፤ ለአንድ ሆሜር የገብስ ዘር 50 የብር ሰቅል ይሆናል። |
ሰውየው እርሻውን ከኢዮቤልዩ ዓመት አንስቶ ቅዱስ አድርጎ ከሰጠ የተተመነለት ዋጋ ይጸናል። |
ሰውየው እርሻውን ቅዱስ አድርጎ የሰጠው ኢዮቤልዩ ካለፈ በኋላ ከሆነ ካህኑ እስከ ቀጣዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የቀሩትን ዓመታት ግምት ውስጥ በማስገባት ዋጋውን ያስላለት፤ ከተተመነውም ዋጋ ላይ መቀነስ አለበት። |
ሆኖም እርሻውን ቅዱስ አድርጎ የሰጠው ሰው እርሻውን መልሶ መግዛት ከፈለገ በተተመነው ዋጋ ላይ የገንዘቡን አንድ አምስተኛ ጨምሮ መስጠት አለበት፤ ከዚያም እርሻው የእሱ ንብረት እንደሆነ ይጸናል። |
ሰውየው እርሻውን መልሶ ባይገዛውና እርሻው ለሌላ ሰው ቢሸጥ ሰውየው መልሶ ሊገዛው አይችልም። |
እርሻው በኢዮቤልዩ ነፃ በሚለቀቅበት ጊዜ ለይሖዋ እንደተሰጠ እርሻ ተቆጥሮ ለእሱ የተቀደሰ ይሆናል። የካህናቱም ንብረት ይሆናል። |
“‘አንድ ሰው በውርስ ያገኘው ንብረት ክፍል ያልሆነውን በገንዘቡ የገዛውን እርሻ ለይሖዋ ቅዱስ አድርጎ ቢሰጥ |
ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የሚያወጣውን ዋጋ ይተምንለት፤ እሱም የተተመነውን ዋጋ በዚያው ቀን ይስጥ። ይህ ለይሖዋ የተቀደሰ ነው። |
በኢዮቤልዩ ዓመት እርሻው ለሻጩ ይኸውም ለመሬቱ ባለቤት ይመለሳል። |
“‘እያንዳንዱ ዋጋ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት መተመን አለበት። አንዱ ሰቅል 20 ጌራ መሆን ይኖርበታል። |
“‘ይሁንና ማንም ሰው ከእንስሳት መካከል በኩር የሆነውን ቅዱስ አድርጎ መስጠት የለበትም፤ ምክንያቱም በኩሩ የይሖዋ ነው። በሬም ሆነ በግ ቀድሞውንም የይሖዋ ነው። |
በኩሩ ርኩስ ከሆኑት እንስሳት መካከል ከሆነና በተተመነለት ዋጋ መሠረት ከዋጀው በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ መስጠት አለበት። ሰውየው መልሶ የማይገዛው ከሆነ ግን በተተመነው ዋጋ መሠረት ይሸጥ። |
“‘አንድ ሰው የራሱ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ ያለምንም ገደብ ለይሖዋ የሰጠው ማንኛውም ተለይቶ የተሰጠ ነገር ይኸውም የእሱ ንብረት የሆነ ሰውም ሆነ እንስሳ አሊያም እርሻ ሊሸጥም ሆነ ተመልሶ ሊገዛ አይችልም። ተለይቶ የተሰጠ ማንኛውም ነገር ለይሖዋ እጅግ የተቀደሰ ነው። |
በተጨማሪም እንዲጠፋ የተበየነበት ማንኛውም ለጥፋት የተለየ ሰው አይዋጅም፤ ከዚህ ይልቅ መገደል አለበት። |
“‘እርሻው ከሚሰጠው ምርትም ሆነ ዛፉ ከሚያፈራው ፍሬ ውስጥ የምድሩ አንድ አሥረኛ ሁሉ የይሖዋ ነው። ይህ ለይሖዋ የተቀደሰ ነው። |
አንድ ሰው አንድ አሥረኛ አድርጎ የሰጠውን ማንኛውንም ነገር መልሶ መግዛት ቢፈልግ በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ መስጠት አለበት። |
ከከብቶቹና ከመንጋው መካከል አንድ አሥረኛው ማለትም በበትሩ ሥር ከሚያልፉት መካከል አሥረኛው እንስሳ ለይሖዋ የተቀደሰ መሆን አለበት። |
ከዚህ በኋላ እንስሳው ጥሩ ይሁን መጥፎ መመርመር የለበትም፤ በሌላ ሊለውጠውም አይገባም። እንስሳውን በሌላ መለወጥ ካሰበ ግን የመጀመሪያው እንስሳም ሆነ ተለዋጭ ሆኖ የቀረበው እንስሳ የተቀደሱ ይሆናሉ። ተመልሶ ሊገዛ አይችልም።’” |
ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ትእዛዛት እነዚህ ናቸው። |
“‘አንድ ሰው ለይሖዋ የእህል መባ የሚያቀርብ ከሆነ መባው የላመ ዱቄት መሆን አለበት፤ በላዩም ላይ ዘይት ያፍስበት፤ ነጭ ዕጣንም ያስቀምጥበት። |
ከዚያም ካህናት ወደሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች ያመጣዋል፤ ካህኑም ከላዩ ላይ አንድ እፍኝ የላመ ዱቄትና ዘይት፣ ነጭ ዕጣኑንም በሙሉ ይወስዳል፤ ይህንም አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ ይኸውም ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል። |
ከእህል መባው የተረፈው ማንኛውም ነገር የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ነው፤ ይህም ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈ ስለሆነ እጅግ ቅዱስ ነው። |
“‘በመጋገሪያ ምድጃ የተጋገረ የእህል መባ የምታቀርብ ከሆነ ከላመ ዱቄት በዘይት ተለውሶ የተጋገረ እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው ዳቦ ወይም ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ መሆን ይኖርበታል። |
“‘መባህ በምጣድ የተጋገረ የእህል መባ ከሆነ በዘይት ከተለወሰ እርሾ ያልገባበት የላመ ዱቄት የተጋገረ መሆን ይኖርበታል። |
መቆራረስ አለበት፤ ዘይትም አፍስበት። ይህ የእህል መባ ነው። |
“‘መባህ በድስት የተዘጋጀ የእህል መባ ከሆነ ከላመ ዱቄትና ከዘይት የተሠራ መሆን ይኖርበታል። |
ከእነዚህ ነገሮች የተዘጋጀውን የእህል መባ ወደ ይሖዋ ማምጣት ይኖርብሃል፤ ወደ መሠዊያው ለሚያቀርበውም ካህን ይሰጠው። |
ካህኑም አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ እንዲሆን ከእህል መባው ላይ የተወሰነውን በማንሳት ይሖዋን ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል። |
ከእህል መባው የተረፈው የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ነው፤ ይህም ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈ ስለሆነ እጅግ ቅዱስ ነው። |
“‘እርሾ ወይም ማር ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጋችሁ ማጨስ ስለሌለባችሁ ለይሖዋ ከምታቀርቡት የእህል መባ ውስጥ እርሾ የገባበት ምንም ነገር አይኑር። |
“‘እነዚህንም የፍሬ በኩራት መባ አድርጋችሁ ለይሖዋ ልታቀርቧቸው ትችላላችሁ፤ ሆኖም ደስ እንደሚያሰኝ መዓዛ ሆነው ወደ መሠዊያው መምጣት የለባቸውም። |
“‘የምታቀርበው የእህል መባ በሙሉ በጨው መቀመም አለበት፤ የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨውም ከእህል መባህ ላይ አይጥፋ። ከማንኛውም መባህ ጋር ጨው አብረህ ታቀርባለህ። |
“‘መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬ የእህል መባ አድርገህ ለይሖዋ የምታቀርብ ከሆነ የደረሰውን ሆኖም ገና እሸት የሆነውን በእሳት የተጠበሰና የተከካ እህል መጀመሪያ ላይ እንደደረሰው ፍሬህ የእህል መባ አድርገህ አቅርብ። |
በላዩም ላይ ዘይት ትጨምርበታለህ፤ ነጭ ዕጣንም ታስቀምጥበታለህ። ይህ የእህል መባ ነው። |
ካህኑም ከተከካው እህልና ከዘይቱ የተወሰነውን፣ ነጭ ዕጣኑንም በሙሉ ወስዶ አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው የሚያደርግ መባ ይኸውም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አድርጎ ያጨሰዋል። |
በኋላም የአሮን ወንዶች ልጆች ናዳብና አቢሁ እያንዳንዳቸው የዕጣን ማጨሻቸውን አምጥተው በላዩ ላይ እሳት አደረጉበት፤ በእሳቱም ላይ ዕጣን ጨመሩበት። ከዚያም ይሖዋ እንዲያደርጉ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደ እሳት በፊቱ አቀረቡ። |
በዚህ ጊዜ እሳት ከይሖዋ ፊት ወጥቶ በላቸው፤ እነሱም በይሖዋ ፊት ሞቱ። |
ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “ይሖዋ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ ሰዎች መካከል እቀደሳለሁ፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከበራለሁ’ ብሏል።” አሮንም ዝም አለ። |
ሙሴም የአሮን አጎት የዑዚኤል ልጆች የሆኑትን ሚሳኤልንና ኤሊጻፋንን ጠርቶ “ኑ፣ ወንድሞቻችሁን ከቅዱሱ ስፍራ ፊት ለፊት አንስታችሁ ከሰፈሩ ውጭ ወዳለው ቦታ አውጧቸው” አላቸው። |
ስለዚህ መጥተው ልክ ሙሴ በነገራቸው መሠረት ሟቾቹን ከነቀሚሳቸው ተሸክመው ከሰፈሩ ውጭ አወጧቸው። |
ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲሁም ሌሎቹን የአሮን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “እንዳትሞቱ እንዲሁም አምላክ በመላው ማኅበረሰብ ላይ እንዳይቆጣ ፀጉራችሁን አታንጨብርሩ ወይም ልብሶቻችሁን አትቅደዱ። ሆኖም ወንድሞቻችሁ ይኸውም መላው የእስራኤል ቤት ይሖዋ በእሳት ለገደላቸው ያለቅሱላቸዋል። |
የይሖዋ የቅብዓት ዘይት በላያችሁ ላይ ስላለ ከመገናኛ ድንኳኑ ደጃፍ መራቅ የለባችሁም፤ አለዚያ ትሞታላችሁ።” እነሱም ሙሴ እንዳላቸው አደረጉ። |
ከዚያም ይሖዋ አሮንን እንዲህ አለው፦ |
“እንዳትሞቱ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ስትገቡ አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶች ልጆችህ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ። ይህ ትእዛዝ ለትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘላለማዊ ደንብ ነው። |
ይህም ቅዱስ የሆነውን ከረከሰው ነገር እንዲሁም ንጹሕ ያልሆነውን ንጹሕ ከሆነው ነገር ለመለየት |
እንዲሁም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት የሰጣቸውን ሥርዓቶች በሙሉ ለእስራኤላውያን ለማስተማር ነው።” |
ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲሁም የተረፉትን የአሮን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ አላቸው፦ “ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈውን የእህል መባ ወስዳችሁ ያለእርሾ በማዘጋጀት በመሠዊያው አጠገብ ብሉት፤ ምክንያቱም ይህ እጅግ ቅዱስ ነገር ነው። |
ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች ላይ ይህ የአንተ ድርሻና የወንዶች ልጆችህ ድርሻ ስለሆነ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ብሉት፤ ምክንያቱም እንዲህ እንዳደርግ ታዝዣለሁ። |
እንዲሁም የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባና የቅዱሱን ድርሻ እግር አንተም ሆንክ ከአንተ ጋር ያሉት ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ንጹሕ በሆነ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች እስራኤላውያን ከሚያቀርቧቸው የኅብረት መሥዋዕቶች ላይ የአንተ ድርሻና የወንዶች ልጆችህ ድርሻ ሆነው የተሰጡ ናቸው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.