text
stringlengths
4
267
እነሱም የቅዱሱን ድርሻ እግርና የሚወዘወዘውን መባ ፍርምባ በእሳት ከሚቀርቡት የስብ መባዎች ጋር ያመጣሉ፤ ይህን የሚያደርጉት የሚወዘወዘውን መባ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ለመወዝወዝ ነው፤ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረትም ይህ ለአንተና ከአንተ ጋር ላሉት ወንዶች ልጆችህ ዘላለማዊ ድርሻ ሆኖ ያገለግላል።”
ሙሴም ለኃጢአት መባ የሚሆነውን ፍየል በደንብ አፈላለገ፤ በኋላም ፍየሉ መቃጠሉን ተረዳ። በመሆኑም የተረፉትን የአሮን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን ተቆጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፦
“ይህ መባ እጅግ ቅዱስ ነገር ሆኖ ሳለና መባውንም የሰጣችሁ የማኅበረሰቡን ኃጢአት እንድትሸከሙ እንዲሁም በይሖዋ ፊት እንድታስተሰርዩላቸው ሆኖ ሳለ የኃጢአት መባውን በቅዱሱ ስፍራ ያልበላችሁት ለምንድን ነው?
ይኸው ደሙ ወደ ቅዱሱ ስፍራ አልገባም። ልክ እንደታዘዝኩት በቅዱሱ ስፍራ ልትበሉት ይገባችሁ ነበር።”
በዚህ ጊዜ አሮን ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ እነሱ በዛሬው ዕለት የኃጢአት መባቸውንና የሚቃጠል መባቸውን በይሖዋ ፊት ያቀረቡት እኔ እንዲህ ያለ ነገር ደርሶብኝ እያለ ነው። ታዲያ ዛሬ የኃጢአት መባውን በልቼ ቢሆን ኖሮ ይሖዋ ይደሰት ነበር?”
ሙሴም ይህን ሲሰማ ነገሩ አጥጋቢ ሆኖ አገኘው።
ሁለቱ የአሮን ወንዶች ልጆች ይሖዋ ፊት በመቅረባቸው የተነሳ ከሞቱ በኋላ ይሖዋ ሙሴን አነጋገረው።
ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “እኔ ከመክደኛው በላይ በደመና ውስጥ ስለምገለጥ በመጋረጃው ውስጥ ወዳለው ቅዱስ ስፍራ ይኸውም በታቦቱ ላይ ወዳለው መክደኛ ፊት በፈለገው ጊዜ እንዳይገባና በዚህም የተነሳ እንዳይሞት ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።
“አሮን ወደተቀደሰው ስፍራ በሚገባበት ጊዜ ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ ወይፈንና ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ አውራ በግ ይዞ ይምጣ።
ቅዱሱን የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፤ በበፍታ ቁምጣዎቹም ሰውነቱን ይሸፍን፤ የበፍታ መቀነቱንም ይታጠቅ፤ ራሱም ላይ የበፍታ ጥምጥሙን ይጠምጥም። እነዚህ ቅዱስ ልብሶች ናቸው። እሱም ገላውን በውኃ ታጥቦ ይለብሳቸዋል።
“ከእስራኤል ማኅበረሰብም ሁለት ተባዕት የፍየል ጠቦቶችን ለኃጢአት መባ፣ አንድ አውራ በግ ደግሞ ለሚቃጠል መባ ይውሰድ።
“ከዚያም አሮን ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያቅርብ፤ ለራሱም ሆነ ለቤቱ ያስተሰርያል።
“ሁለቱን ፍየሎች ወስዶ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት እንዲቆሙ ያደርጋል።
አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥላል፤ አንደኛው ዕጣ ለይሖዋ ሌላኛው ዕጣ ደግሞ ለአዛዜል ይሆናል።
አሮንም ለይሖዋ እንዲሆን ዕጣ የወጣበትን ፍየል ያቀርባል፤ የኃጢአትም መባ ያደርገዋል።
ለአዛዜል እንዲሆን ዕጣ የወጣበት ፍየል ግን በእሱ አማካኝነት ስርየት እንዲፈጸምበት ከነሕይወቱ መጥቶ በይሖዋ ፊት እንዲቆም ይደረግ፤ ከዚያም ለአዛዜል እንዲሆን ወደ ምድረ በዳ ይለቀቃል።
“አሮንም ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያቀርባል፤ ለራሱም ሆነ ለቤቱ ያስተሰርያል፤ ከዚያም ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያርዳል።
“በይሖዋ ፊት ካለው መሠዊያ ላይ የተወሰደ ፍም የሞላበትን ዕጣን ማጨሻና ሁለት እፍኝ ሙሉ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን ይወስዳል፤ እነዚህንም ይዞ ወደ መጋረጃው ውስጥ ይገባል።
እንዳይሞትም ዕጣኑን በይሖዋ ፊት ባለው እሳት ላይ ይጨምረዋል፤ የዕጣኑም ጭስ ከምሥክሩ በላይ ያለውን የታቦቱን መክደኛ ይሸፍነዋል።
“ከወይፈኑም ደም የተወሰነውን ወስዶ ከመክደኛው ፊት ለፊት በስተ ምሥራቅ በኩል በጣቱ ይረጨዋል፤ የተወሰነውን ደም ደግሞ ከመክደኛው ፊት በጣቱ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።
“ከዚያም ለሕዝቡ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ፍየል ያርደዋል፤ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ይዞ በመግባት ልክ በወይፈኑ ደም እንዳደረገው በዚህኛውም ደም ያደርጋል፤ ደሙንም ወደ መክደኛውና በመክደኛው ፊት ይረጨዋል።
“እስራኤላውያን ስለፈጸሙት ርኩሰት፣ ስለ መተላለፋቸውና ስለ ኃጢአታቸው ለቅዱሱ ስፍራ ያስተሰርይ፤ በእነሱ ዘንድ በርኩሰታቸው መካከል ለሚገኘው ለመገናኛ ድንኳኑም ይህንኑ ያድርግ።
“ለማስተሰረይ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ገብቶ እስኪወጣ ድረስ ሌላ ማንም ሰው በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ መገኘት የለበትም። እሱም ለራሱ፣ ለቤቱና ለመላው የእስራኤል ጉባኤ ያስተሰርያል።
“ከዚያም በይሖዋ ፊት ወዳለው መሠዊያ ይወጣል፤ ለመሠዊያውም ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑ ደም የተወሰነውን እንዲሁም ከፍየሉ ደም የተወሰነውን ወስዶ በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ያሉትን ቀንዶች ይቀባል።
በተጨማሪም ከደሙ የተወሰነውን ወስዶ በመሠዊያው ላይ በጣቱ ሰባት ጊዜ በመርጨት እስራኤላውያን ከፈጸሙት ርኩሰት ያነጻዋል እንዲሁም ይቀድሰዋል።
“ለቅዱሱ ስፍራ፣ ለመገናኛ ድንኳኑና ለመሠዊያው ካስተሰረየ በኋላ በሕይወት ያለውንም ፍየል ያቀርባል።
ከዚያም አሮን ሁለቱንም እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ በመጫን እስራኤላውያን የሠሩትን ስህተት ሁሉ፣ መተላለፋቸውን ሁሉና ኃጢአታቸውን ሁሉ ይናዘዝበታል፤ እነዚህንም በፍየሉ ራስ ላይ ያደርጋል፤ ፍየሉንም ለዚህ በተመደበው ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል።
ፍየሉም ስህተቶቻቸውን በሙሉ ተሸክሞ ወደ በረሃ ይሄዳል፤ እሱም ፍየሉን ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል።
“ከዚያም አሮን ወደ መገናኛ ድንኳኑ ይገባል፤ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ሲገባ ለብሷቸው የነበሩትንም የበፍታ ልብሶች ያወልቃል፤ ልብሶቹንም እዚያው ይተዋቸዋል።
ገላውንም በቅዱስ ስፍራ በውኃ ይታጠብ፤ ልብሶቹንም ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ የራሱን የሚቃጠል መባ እንዲሁም የሕዝቡን የሚቃጠል መባ ያቀርባል፤ ለራሱና ለሕዝቡም ያስተሰርያል።
የኃጢአት መባው ስብም በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል።
“ለአዛዜል ሲል ፍየሉን የለቀቀውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ ገላውንም በውኃ ይታጠብ፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል።
“ደማቸው ለማስተሰረያ እንዲሆን ወደ ቅዱሱ ስፍራ የገባው የኃጢአት መባው ወይፈንና የኃጢአት መባው ፍየል ከሰፈሩ ውጭ ይወሰዳሉ፤ ቆዳቸው፣ ሥጋቸውና ፈርሳቸውም በእሳት ይቃጠላል።
እነዚህን ያቃጠለው ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ ገላውንም በውኃ ይታጠብ፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል።
“ይህም ለእናንተ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል፦ በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን ራሳችሁን አጎሳቁሉ፤ ምንም ዓይነት ሥራም አትሥሩ፤ የአገራችሁ ሰውም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ሥራ አይሥራ።
በዚህ ቀን፣ ንጹሕ መሆናችሁን ለማሳወቅ ለእናንተ ማስተሰረያ ይቀርባል። በይሖዋም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ንጹሕ ትሆናላችሁ።
ይህ ሙሉ በሙሉ የምታርፉበት ሰንበት ነው፤ እናንተም ራሳችሁን አጎሳቁሉ። ይህም ዘላቂ ደንብ ነው።
“አባቱን ተክቶ በክህነት እንዲያገለግል የሚቀባውና የሚሾመው ካህን ያስተሰርያል፤ እንዲሁም ቅዱስ የሆኑትን የበፍታ ልብሶች ይለብሳል።
ለቅዱሱ መቅደስ፣ ለመገናኛ ድንኳኑና ለመሠዊያው ያስተሰርያል፤ እንዲሁም ለካህናቱና ለጉባኤው ሕዝብ በሙሉ ያስተሰርያል።
ይህም የእስራኤላውያንን ኃጢአት በሙሉ በዓመት አንድ ጊዜ ለማስተሰረይ የሚያገለግል ዘላቂ ደንብ ይሆናል።” እሱም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረገ።
“‘አንድ ሰው ሰዎች የምሥክርነት ቃል እንዲሰጡ ጥሪ እየቀረበ መሆኑን ቢሰማና እሱ መመሥከር እየቻለ ወይም ደግሞ ጉዳዩን አይቶ አሊያም አውቆ ሳለ ሳይናገር ቢቀር በሠራው ጥፋት ይጠየቅበታል።
“‘ወይም አንድ ሰው ርኩስ የሆነን ማንኛውንም ነገር ይኸውም ርኩስ የሆነን የዱር አውሬ ወይም ርኩስ የሆነን የቤት እንስሳ አሊያም ርኩስ የሆነን የሚርመሰመስ ፍጥረት በድን ቢነካ፣ ይህን ያደረገው ባለማወቅ ቢሆንም እንኳ ይህ ሰው ርኩስ ነው፤ በደለኛም ይሆናል።
ወይም አንድ ሰው ባለማወቅ የሰውን ርኩሰት ይኸውም እንዲረክስ ሊያደርገው የሚችለውን ማንኛውንም ርኩስ ነገር ቢነካና በኋላም ይህን ቢያውቅ በደለኛ ይሆናል።
“‘አሊያም ደግሞ አንድ ሰው ነገሩ ምንም ሆነ ምን ክፉ ወይም መልካም ለማድረግ በችኮላ ቢምልና ይህን ያደረገው ባለማወቅ ቢሆን ሆኖም የማለው በችኮላ መሆኑን በኋላ ላይ ቢገነዘብ በደለኛ ይሆናል።
“‘ከእነዚህ ነገሮች በአንዱ በደለኛ ሆኖ ቢገኝ በምን መንገድ ኃጢአት እንደሠራ መናዘዝ አለበት።
ለሠራው ኃጢአት የበደል መባ ማለትም ከመንጋው መካከል እንስት የበግ ጠቦት ወይም እንስት የፍየል ግልገል የኃጢአት መባ አድርጎ ለይሖዋ ያመጣል። ከዚያም ካህኑ ኃጢአቱን ያስተሰርይለታል።
“‘በግ ለማምጣት አቅሙ የማይፈቅድለት ከሆነ ግን ለሠራው ኃጢአት የበደል መባ እንዲሆኑ ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን ለይሖዋ ያምጣ፤ አንዱ ለኃጢአት መባ ሌላኛው ደግሞ ለሚቃጠል መባ ይሆናል።
ወደ ካህኑም ያመጣቸዋል፤ ካህኑም በቅድሚያ ለኃጢአት መባ የሚሆነውን ያቀርባል፤ አንገቱን ሙሉ በሙሉ ሳይቆርጥ ከፊት በኩል አንገቱን በመቦጨቅ ያቀርበዋል።
ከኃጢአት መባው ደም ላይ የተወሰነውን በመሠዊያው ጎን ላይ ይረጨዋል፤ የተረፈው ደም ግን በመሠዊያው ሥር ይንጠፈጠፋል። ይህ የኃጢአት መባ ነው።
ሌላኛውን ደግሞ በተለመደው አሠራር መሠረት የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤ ካህኑም ለሠራው ኃጢአት ማስተሰረያ ያቀርብለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
“‘ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ለማምጣት አቅሙ የማይፈቅድለት ከሆነ ደግሞ ለሠራው ኃጢአት፣ የኃጢአት መባ እንዲሆን አንድ አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄት መባ አድርጎ ያምጣ። የኃጢአት መባ ስለሆነ ዘይት አይጨምርበት ወይም ነጭ ዕጣን አያድርግበት።
ወደ ካህኑም ያመጣዋል፤ ካህኑም አምላክ መላውን መባ እንዲያስበው ለማድረግ ከላዩ ላይ አንድ እፍኝ አንስቶ በመሠዊያው ላይ ባሉት ለይሖዋ በእሳት በሚቀርቡት መባዎች ላይ እንዲጨስ ያደርጋል። ይህ የኃጢአት መባ ነው።
ካህኑም ሰውየው ከእነዚህ ኃጢአቶች ውስጥ ለሠራው ለየትኛውም ኃጢአት ማስተሰረያ ያቀርብለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል። እንደ እህል መባው ሁሉ ከመባው የተረፈውም የካህኑ ይሆናል።’”
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦
“አንድ ሰው ለይሖዋ በተቀደሱት ነገሮች ላይ ባለማወቅ ኃጢአት በመሥራት ታማኝነቱን ቢያጎድል ከመንጋው መካከል እንከን የሌለበትን አውራ በግ የበደል መባ አድርጎ ለይሖዋ ያመጣል፤ ዋጋው በብር ሰቅል የሚተመነው እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት ነው።
በቅዱሱ ስፍራ ላይ ለፈጸመው ኃጢአት ካሳ ይከፍላል፤ የዋጋውንም አንድ አምስተኛ ይጨምርበታል። ካህኑ ለበደል መባ በቀረበው አውራ በግ አማካኝነት እንዲያስተሰርይለትም ለካህኑ ይሰጠዋል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
“አንድ ሰው ይሖዋ እንዳይደረጉ ብሎ ካዘዛቸው ነገሮች መካከል አንዱን በመፈጸም ኃጢአት ቢሠራ፣ እንዲህ ያደረገው ባለማወቅ ቢሆንም እንኳ በደለኛ ይሆናል፤ በሠራውም ጥፋት ይጠየቅበታል።
የበደል መባ እንዲሆንም የተተመነለትን ዋጋ ያህል የሚያወጣ እንከን የሌለበት አውራ በግ ከመንጋው መካከል ወስዶ ለካህኑ ያምጣ። ከዚያም ካህኑ፣ ሰውየው ባለማወቅ ለፈጸመው ስህተት ያስተሰርይለታል፤ ኃጢአቱም ይቅር ይባልለታል።
ይህ የበደል መባ ነው። በይሖዋ ላይ ኃጢአት ስለፈጸመ በእርግጥ በደለኛ ይሆናል።”
ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
“የሥጋ ደዌ ያለበት አንድ ሰው መንጻቱን ለማረጋገጥ ካህኑ ፊት እንዲቀርብ በሚደረግበት ዕለት የሚኖረው ሕግ ይህ ነው።
ካህኑ ከሰፈሩ ውጭ ወጥቶ ሰውየውን ይመረምረዋል። የሥጋ ደዌ ይዞት የነበረው ሰው ከሥጋ ደዌው ከዳነ
ካህኑ ሰውየው ራሱን ለማንጻት በሕይወት ያሉ ሁለት ንጹሕ ወፎችን፣ የአርዘ ሊባኖስ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ማግና ሂሶጵ እንዲያመጣ ያዘዋል።
እንዲሁም ካህኑ አንደኛዋ ወፍ ከወራጅ ውኃ የተቀዳ ውኃ ባለበት የሸክላ ዕቃ ውስጥ እንድትታረድ ትእዛዝ ይሰጣል።
በሕይወት ያለችውን ወፍ ደግሞ ከአርዘ ሊባኖስ እንጨቱ፣ ከደማቁ ቀይ ማግና ከሂሶጱ ጋር ወስዶ ከወራጅ ውኃ በተቀዳው ውኃ ላይ በታረደችው ወፍ ደም ውስጥ ይንከራቸው።
ከዚያም ራሱን ከሥጋ ደዌ በሚያነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፤ ሰውየውም ንጹሕ መሆኑን ያስታውቃል፤ በሕይወት ያለችውንም ወፍ ሜዳ ላይ ይለቃታል።
“ራሱን የሚያነጻውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ ፀጉሩንም በሙሉ ይላጭ፤ ገላውንም በውኃ ይታጠብ፤ ንጹሕም ይሆናል። ይህን ካደረገ በኋላ ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል፤ ሆኖም ለሰባት ቀን ከድንኳኑ ውጭ ይቀመጣል።
በሰባተኛው ቀን በራሱ ላይ ያለውን ፀጉር፣ ጺሙንና ቅንድቡን በሙሉ ይላጭ። ፀጉሩን በሙሉ ከተላጨ በኋላ ልብሶቹን ያጥባል እንዲሁም ገላውን በውኃ ይታጠባል፤ ከዚያም ንጹሕ ይሆናል።
“በስምንተኛው ቀን እንከን የሌለባቸውን ሁለት የበግ ጠቦቶች፣ አንድ ዓመት ገደማ የሆናትን እንከን የሌለባት አንዲት እንስት የበግ ጠቦት፣ የእህል መባ እንዲሆን በዘይት የተለወሰ ሦስት አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄትና አንድ የሎግ መስፈሪያ ዘይት ያመጣል፤
ሰውየው ንጹሕ መሆኑን የሚያስታውቀው ካህንም ራሱን የሚያነጻውን ሰው ከመባዎቹ ጋር በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት ያቀርበዋል።
ካህኑም አንደኛውን የበግ ጠቦት ወስዶ ከአንዱ የሎግ መስፈሪያ ዘይት ጋር በማድረግ የበደል መባ እንዲሆን ያቀርበዋል፤ እነዚህንም የሚወዘወዝ መባ አድርጎ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዘውዛቸዋል።
ከዚያም የበግ ጠቦቱን የኃጢአት መባውና የሚቃጠል መባው ዘወትር በሚታረዱበት ቦታ ይኸውም ቅዱስ በሆነ ስፍራ ያርደዋል፤ ምክንያቱም እንደ ኃጢአት መባው ሁሉ የበደል መባውም የካህኑ ድርሻ ነው። ይህ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው።
“ካህኑም ከበደል መባው ደም ላይ የተወሰነውን ይወስዳል፤ ከዚያም ራሱን የሚያነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ይቀባል።
ካህኑም ከአንዱ የሎግ መስፈሪያ ዘይት ላይ የተወሰነውን በራሱ የግራ እጅ መዳፍ ላይ ያንቆረቁረዋል።
ከዚያም የቀኝ እጁን ጣት በግራ እጁ መዳፍ ላይ ባለው ዘይት ውስጥ ይነክራል፤ ከዘይቱም የተወሰነውን በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ በጣቱ ይረጨዋል።
በእጁም መዳፍ ላይ ከቀረው ዘይት ላይ የተወሰነውን ወስዶ ራሱን የሚያነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ይቀባል፤ በበደል መባው ደም ላይ ደርቦ ይቀባዋል።
ካህኑም በእጁ መዳፍ ላይ የቀረውን ዘይት ራሱን በሚያነጻው ሰው ራስ ላይ ያፈሰዋል፤ ለሰውየውም በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል።
“ካህኑ ለኃጢአት መባ የሚሆነውን እንስሳ ይሠዋል፤ ራሱን ከርኩሰቱ ለሚያነጻውም ሰው ያስተሰርይለታል፤ ከዚያም ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን እንስሳ ያርዳል።
ካህኑም የሚቃጠለውን መባና የእህሉን መባ በመሠዊያው ላይ ያቀርባል፤ ለሰውየውም ያስተሰርይለታል፤ እሱም ንጹሕ ይሆናል።
“ሆኖም ሰውየው ድሃ ከሆነና ይህን ለማቅረብ አቅሙ ካልፈቀደለት ለራሱ ማስተሰረያ እንዲሆንለት ለሚወዘወዝ መባ አንድ የበግ ጠቦት የበደል መባ አድርጎ ያመጣል፤ በተጨማሪም ለእህል መባ እንዲሆን በዘይት የተለወሰ አንድ አሥረኛ ኢፍ የላመ ዱቄት፣ አንድ የሎግ መስፈሪያ ዘይት
እንዲሁም ከሁለት ዋኖሶች ወይም ከሁለት የርግብ ጫጩቶች አቅሙ የቻለውን ያቀርባል፤ አንደኛው ለኃጢአት መባ ሌላኛው ደግሞ ለሚቃጠል መባ ይሆናል።
መንጻቱን ለማረጋገጥም በስምንተኛው ቀን እነዚህን ይዞ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት ወዳለው ወደ ካህኑ ይመጣል።
“ካህኑም ለበደል መባ እንዲሆን የቀረበውን የበግ ጠቦትና አንዱን የሎግ መስፈሪያ ዘይት ይወስዳል፤ እነዚህንም የሚወዘወዝ መባ አድርጎ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዘውዛቸዋል።
ከዚያም ለበደል መባ እንዲሆን የቀረበውን የበግ ጠቦት ያርዳል፤ ከበደል መባው ደም ላይ የተወሰነውን ወስዶ ራሱን የሚያነጻውን ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ይቀባል።
ካህኑም ከዘይቱ የተወሰነውን በራሱ የግራ እጅ መዳፍ ላይ ያንቆረቁረዋል።
በግራ እጁ መዳፍ ላይ ካለው ዘይት የተወሰነውን በቀኝ እጁ ጣት በይሖዋ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።
በእጁ መዳፍ ላይ ካለው ዘይት የተወሰነውን ወስዶ የበደል መባውን ደም በቀባበት ቦታ ላይ ማለትም ራሱን በሚያነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት እንዲሁም በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል።
ከዚያም በእጁ መዳፍ ላይ የቀረውን ዘይት ራሱን በሚያነጻው ሰው ራስ ላይ ያፈሰዋል፤ ይህን የሚያደርገው በይሖዋ ፊት እንዲያስተሰርይለት ነው።
“ካህኑም ሰውየው አቅሙ ፈቅዶ ካመጣቸው ዋኖሶች ወይም የርግብ ጫጩቶች መካከል አንዱን ያቀርባል፤
አቅሙ ፈቅዶ ካመጣቸውም መካከል አንዱን የኃጢአት መባ ሌላኛውን ደግሞ የሚቃጠል መባ አድርጎ ከእህል መባው ጋር ያቀርባል፤ ካህኑም ራሱን ለሚያነጻው ሰው በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል።
“የሥጋ ደዌ የነበረበትን ሆኖም መንጻቱን ለማረጋገጥ የሚያስፈልገውን ነገር ለማቅረብ አቅሙ የማይፈቅድለትን ሰው በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው።”
ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦
“ርስት አድርጌ ወደምሰጣችሁ ወደ ከነአን ምድር በምትገቡበት ጊዜ በምድራችሁ ውስጥ የሚገኝን አንድ ቤት በደዌ ብበክለው
የቤቱ ባለቤት ወደ ካህኑ መጥቶ ‘አንድ የሚበክል ነገር ቤቴ ውስጥ ታይቷል’ በማለት ይንገረው።
ካህኑም ቤቱ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ርኩስ ነው እንዳይል የሚበክለውን ነገር ለመመርመር ወደ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ቤቱ ውስጥ ያለውን ዕቃ በሙሉ እንዲያወጡ ትእዛዝ ይሰጣል፤ ከዚያም ካህኑ ቤቱን ለመመርመር ወደ ውስጥ ይገባል።
እሱም ብክለቱ የታየበትን ቦታ ይመረምራል፤ በቤቱም ግድግዳ ላይ ወደ ቢጫነት ያደላ አረንጓዴ ወይም ቀላ ያለ የተቦረቦረ ምልክት ቢታይና ይህም ከላይ ወደ ውስጥ ዘልቆ የገባ ከሆነ
ካህኑ ከቤቱ ውስጥ ወደ ደጃፉ ወጥቶ ቤቱን ለሰባት ቀን ያሽገዋል።
“ከዚያም ካህኑ በሰባተኛው ቀን ተመልሶ በመምጣት ቤቱን ይመረምረዋል። ቤቱን የበከለው ነገር በግድግዳው ላይ ተስፋፍቶ ከሆነ
ካህኑ ትእዛዝ ይሰጣል፤ የተበከሉትም ድንጋዮች ተሰርስረው መውጣትና ከከተማዋ ውጭ ወዳለ ርኩስ የሆነ ስፍራ መጣል አለባቸው።
ከዚያም ቤቱ ከውስጥ በኩል በደንብ እንዲፈቀፈቅ ያደርጋል፤ ተፈቅፍቆ የተነሳው ልስንና ምርጊትም ከከተማዋ ውጭ በሚገኝ ርኩስ የሆነ ስፍራ ይደፋ።