text stringlengths 4 267 |
|---|
ከዚያም ከሪሞንጰሬጽ ተነስተው በሊብና ሰፈሩ። |
ከሊብናም ተነስተው በሪሳ ሰፈሩ። |
በመቀጠልም ከሪሳ ተነስተው በቀሄላታ ሰፈሩ። |
ከዚያም ከቀሄላታ ተነስተው በሸፈር ተራራ ሰፈሩ። |
በኋላም ከሸፈር ተራራ ተነስተው በሃራዳ ሰፈሩ። |
ከዚያም ከሃራዳ ተነስተው በማቅሄሎት ሰፈሩ። |
ቀጥሎም ከማቅሄሎት ተነስተው በታሃት ሰፈሩ። |
ከዚያ በኋላም ከታሃት ተነስተው በታራ ሰፈሩ። |
ከዚያም ከታራ ተነስተው በሚትቃ ሰፈሩ። |
በኋላም ከሚትቃ ተነስተው በሃሽሞና ሰፈሩ። |
ከሃሽሞናም ተነስተው በሞሴሮት ሰፈሩ። |
ከዚያም ከሞሴሮት ተነስተው በብኔያዕቃን ሰፈሩ። |
በኋላም ከብኔያዕቃን ተነስተው በሆርሃጊድጋድ ሰፈሩ። |
ከዚያም ከሆርሃጊድጋድ ተነስተው በዮጥባታ ሰፈሩ። |
ከዮጥባታም ተነስተው በአብሮና ሰፈሩ። |
ከዚያም ከአብሮና ተነስተው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ። |
በኋላም ከዔጽዮንጋብር ተነስተው በጺን ምድረ በዳ በምትገኘው በቃዴስ ሰፈሩ። |
ከቃዴስም ተነስተው በኤዶም ምድር ወሰን ላይ በሚገኘው በሆር ተራራ ሰፈሩ። |
እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡ በ40ኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ካህኑ አሮን ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ወደ ሆር ተራራ ወጣ፤ በዚያም ሞተ። |
አሮን በሆር ተራራ ላይ በሞተበት ጊዜ ዕድሜው 123 ዓመት ነበር። |
በከነአን ምድር በኔጌብ ይኖር የነበረው ከነአናዊው የአራድ ንጉሥ የእስራኤላውያንን መምጣት ሰማ። |
ከጊዜ በኋላም ከሆር ተራራ ተነስተው በጻልሞና ሰፈሩ። |
ከዚያም ከጻልሞና ተነስተው በጱኖን ሰፈሩ። |
በመቀጠልም ከጱኖን ተነስተው በኦቦት ሰፈሩ። |
ከኦቦትም ተነስተው በሞዓብ ድንበር ላይ በምትገኘው በኢዬዓባሪም ሰፈሩ። |
በኋላም ከኢይም ተነስተው በዲቦንጋድ ሰፈሩ። |
በመቀጠልም ከዲቦንጋድ ተነስተው በአልሞንዲብላታይም ሰፈሩ። |
ከአልሞንዲብላታይም ተነስተው ደግሞ በነቦ ፊት ለፊት በአባሪም ተራሮች ሰፈሩ። |
በመጨረሻም ከአባሪም ተራሮች ተነስተው በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ሰፈሩ። |
በሞዓብ በረሃማ ሜዳ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሺቲም በሚገኘው ስፍራ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ሰፈሩ። |
ይሖዋ በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘እንግዲህ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ወደ ከነአን ምድር ልትገቡ ነው። |
የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አባሯቸው፤ የተቀረጹ የድንጋይ ምስሎቻቸውንም ሁሉ አጥፉ፤ ከብረት የተሠሩ ሐውልቶቻቸውንም በሙሉ አስወግዱ፤ በከፍታ ቦታዎች ላይ ያሉ ቅዱስ ስፍራዎቻቸውን ሁሉ አፍርሱ። |
ምድሪቱን ርስት አድርጌ ስለምሰጣችሁ ምድሪቱን ወርሳችሁ በዚያ ትኖራላችሁ። |
ምድሪቱንም በየቤተሰባችሁ ውርስ አድርጋችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ተለቅ ላለው ቡድን በዛ ያለውን፣ አነስ ላለው ቡድን ደግሞ አነስ ያለውን ውርስ አድርጋችሁ ስጡት። ሁሉም በወጣለት ዕጣ መሠረት የተሰጠውን ቦታ ይወርሳል። በየአባቶቻችሁ ነገዶች ርስታችሁን ውርስ አድርጋችሁ ትቀበላላችሁ። |
“‘የምድሪቱን ነዋሪዎች ከፊታችሁ ሳታባርሩ እዚያው ከተዋችኋቸው ግን ዓይናችሁ ውስጥ እንደገባ ጉድፍ እንዲሁም ጎናችሁ ላይ እንደተሰካ እሾህ ይሆኑባችኋል፤ ደግሞም በምትኖሩበት ምድር ያንገላቷችኋል። |
እኔም በእነሱ ላይ ለማድረግ ያሰብኩትን በእናንተ ላይ አደርግባችኋለሁ።’” |
በዚህ ጊዜ ሕዝቡ፣ ስለደረሰበት ችግር በይሖዋ ፊት ክፉኛ ማጉረምረም ጀመረ። ይሖዋ ይህን ሲሰማ ቁጣው ነደደ፤ ከይሖዋም የመጣ እሳት በእነሱ ላይ ተቀጣጠለ፤ በሰፈሩ ዳርቻ ያሉትን የተወሰኑ ሰዎችም በላ። |
ሕዝቡ ወደ ሙሴ መጮኽ ሲጀምር ሙሴ ይሖዋን ተማጸነ፤ እሳቱም ከሰመ። |
ከይሖዋ የመጣ እሳት በእነሱ ላይ ስለነደደም የዚያ ቦታ ስም ታበራ ተባለ። |
እስራኤላውያንም በመካከላቸው የነበረው ድብልቅ ሕዝብ ሲስገበገብ ሲያዩ እንዲህ በማለት እንደገና ያለቅሱ ጀመር፦ “እንግዲህ አሁን የምንበላው ሥጋ ማን ይሰጠናል? |
በግብፅ እያለን በነፃ እንበላው የነበረው ዓሣ እንዲሁም ኪያሩ፣ ሐብሐቡ፣ ባሮ ሽንኩርቱ፣ ቀይ ሽንኩርቱና ነጭ ሽንኩርቱ በዓይናችን ላይ ዞሯል! |
አሁን ግን ዝለናል። ከዚህ መና በስተቀር ሌላ የምናየው ነገር የለም።” |
መናው እንደ ድንብላል ዘር ነበር፤ መልኩም ሙጫ ይመስል ነበር። |
ሕዝቡም ሜዳ ላይ ወጥቶ መናውን ከለቀመ በኋላ በወፍጮ ይፈጨው ወይም በሙቀጫ ይወቅጠው ነበር። ከዚያም በድስት ይቀቅሉት ወይም እንደ ቂጣ ይጋግሩት ነበር፤ ጣዕሙም በዘይት ተለውሶ እንደተጋገረ ጣፋጭ ቂጣ ነበር። |
ሌሊት በሰፈሩ ላይ ጤዛ በሚወርድበት ጊዜ መናውም በላዩ ላይ ይወርድ ነበር። |
ሙሴም ሕዝቡ ይኸውም እያንዳንዱ ሰው በድንኳኑ ደጃፍ ላይ ሆኖ ከቤተሰቡ ጋር ሲያለቅስ ሰማ። ይሖዋም እጅግ ተቆጣ፤ ሙሴም በጣም አዘነ። |
ከዚያም ሙሴ ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “አገልጋይህን የምታጎሳቁለው ለምንድን ነው? በፊትህ ሞገስ ያጣሁትና የዚህን ሁሉ ሕዝብ ሸክም በእኔ ላይ የጫንከው ለምንድን ነው? |
ይህን ሁሉ ሕዝብ የፀነስኩት እኔ ነኝ? ለአባቶቻቸው ለመስጠት ቃል ወደገባህላቸው ምድር እንዳስገባቸው ‘የሚጠባን ሕፃን እንደሚታቀፍ ሞግዚት በጉያህ እቀፋቸው’ የምትለኝ የወለድኳቸው እኔ ነኝ? |
ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚሆን ሥጋ ከየት ነው የማመጣው? ይኸው እነሱ ‘የምንበላው ሥጋ ስጠን!’ በማለት እያለቀሱብኝ ነው። |
ይህን ሁሉ ሕዝብ እኔ ብቻዬን ልሸከመው አልችልም፤ ከአቅሜ በላይ ነው። |
እንዲህስ ከምታደርገኝ እባክህ አሁኑኑ ግደለኝ። በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ ከእንግዲህ መከራ እንዳይ አታድርገኝ።” |
ይሖዋም መልሶ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች መካከል የሕዝቡ ሽማግሌዎችና አለቆች የመሆን ብቃት አላቸው የምትላቸውን 70 ሰዎች ሰብስብልኝ፤ እነሱንም ወደ መገናኛ ድንኳኑ ውሰዳቸውና በዚያ ከአንተ ጋር ይቁሙ። |
እኔም ወርጄ በዚያ ከአንተ ጋር እነጋገራለሁ፤ በአንተ ላይ ካለው መንፈስ ወስጄ በእነሱ ላይ አደርጋለሁ፤ እነሱም የሕዝቡን ሸክም ብቻህን እንዳትሸከም ይረዱሃል። |
ሕዝቡንም እንዲህ በለው፦ ‘ሥጋ ስለምትበሉ ለነገ ራሳችሁን ቀድሱ፤ ምክንያቱም በይሖዋ ፊት አልቅሳችኋል፤ ደግሞም “የምንበላው ሥጋ ማን ይሰጠናል? በግብፅ የነበርንበት ሁኔታ የተሻለ ነበር” ብላችኋል። ይሖዋ በእርግጥ ሥጋ ይሰጣችኋል፤ እናንተም ትበላላችሁ። |
የምትበሉትም ለአንድ ቀን ወይም ለ2 ቀን ወይም ለ5 ቀን ወይም ለ10 ቀን ወይም ለ20 ቀን አይደለም፤ |
ከዚህ ይልቅ በአፍንጫችሁ እስኪወጣና እስኪያንገፈግፋችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበላላችሁ፤ ምክንያቱም በመካከላችሁ ያለውን ይሖዋን ትታችኋል፤ እንዲሁም “ከግብፅ የወጣነው ለምንድን ነው?” በማለት በፊቱ አልቅሳችኋል።’” |
ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፦ “እኔ በመካከሉ የምገኘው ሕዝብ 600,000 እግረኛ ወንዶች ያሉበት ነው፤ አንተ ደግሞ ‘ሥጋ እሰጣቸዋለሁ፤ ወር ሙሉ እስኪጠግቡ ይበላሉ’ ትላለህ። |
በጎቹና ከብቶቹ ሁሉ ቢታረዱ እንኳ ይበቃቸዋል? የባሕር ዓሣዎች ሁሉ ቢያዙስ ሊበቃቸው ይችላል?” |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን “ለመሆኑ የይሖዋ እጅ አጭር ነው? እንግዲህ ያልኩት ነገር ይፈጸምልህ እንደሆነና እንዳልሆነ ታያለህ” አለው። |
ሙሴም ወጥቶ የይሖዋን ቃል ለሕዝቡ ተናገረ። እንዲሁም ከሕዝቡ ሽማግሌዎች መካከል 70 ሰዎችን ሰብስቦ በድንኳኑ ዙሪያ እንዲቆሙ አደረገ። |
ከዚያም ይሖዋ በደመና ወርዶ አነጋገረው፤ በሙሴ ላይ ከነበረውም መንፈስ ወስዶ በ70ዎቹ ሽማግሌዎች ላይ አደረገ። እነሱም ወዲያው መንፈሱ እንዳረፈባቸው እንደ ነቢያት አደረጋቸው፤ ሆኖም ዳግመኛ እንደዚያ አልሆኑም። |
በዚህ ጊዜ ከሰዎቹ መካከል ሁለቱ በሰፈሩ ውስጥ ቀርተው ነበር። ስማቸውም ኤልዳድና ሞዳድ ነበር። እነዚህ ሰዎች ምንም እንኳ ወደ ድንኳኑ ባይሄዱም ስማቸው ከተመዘገቡት ሰዎች መካከል ስለነበሩ መንፈሱ በእነሱም ላይ ወረደ። በመሆኑም እነሱም በሰፈሩ ውስጥ እንደ ነቢያት ሆኑ። |
አንድ ወጣትም እየሮጠ በመሄድ “ኤልዳድና ሞዳድ በሰፈሩ ውስጥ እንደ ነቢያት እየሆኑ ነው!” ሲል ለሙሴ ነገረው። |
በዚህ ጊዜ ከወጣትነቱ ጀምሮ የሙሴ አገልጋይ የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ “ጌታዬ ሙሴ ሆይ፣ እነዚህን ሰዎች ከልክላቸው እንጂ!” ሲል ተናገረ። |
ሙሴ ግን እንዲህ አለው፦ “ስለ እኔ ተቆርቁረህ ነው? አትቆርቆር፤ የይሖዋ ሕዝቦች በሙሉ ነቢያት ቢሆኑና ይሖዋ መንፈሱን ቢሰጣቸው እንዴት ደስ ባለኝ!” |
በኋላም ሙሴ ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር ወደ ሰፈሩ ተመለሰ። |
ከዚያም ነፋስ ከይሖዋ ዘንድ ወጥቶ ድርጭቶችን ከባሕሩ እየነዳ በማምጣት በሰፈሩ ዙሪያ በተናቸው፤ ድርጭቶቹም የአንድ ቀን መንገድ ያህል በአንድ በኩል፣ የአንድ ቀን መንገድ ያህል ደግሞ በሌላ በኩል በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ ተበትነው ነበር፤ መሬት ላይም ሁለት ክንድ ከፍታ ያህል ተቆልለው ነበር። |
ሕዝቡም በዚያን ዕለት ቀኑን ሙሉና ሌሊቱን ሙሉ እንዲሁም በማግስቱ ቀኑን ሙሉ ድርጭቶቹን ሲሰበስብ ዋለ። ከአሥር ሆሜር ያነሰ የሰበሰበ አልነበረም፤ የሰበሰቧቸውንም በሰፈሩ ዙሪያ አሰጧቸው። |
ሆኖም ሥጋውን ገና ሳያኝኩት፣ በጥርሳቸው መካከል እያለ የይሖዋ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነደደ፤ ይሖዋም ሕዝቡን ክፉኛ ፈጀ። |
እነሱም ሲስገበገቡ የነበሩትን ሰዎች በዚያ ስለቀበሯቸው የቦታውን ስም ቂብሮትሃታባ አሉት። |
ሕዝቡም ከቂብሮትሃታባ ተነስቶ ወደ ሃጼሮት ተጓዘ፤ በሃጼሮትም ተቀመጠ። |
ከመቅሰፍቱ በኋላ ይሖዋ ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፦ |
“ከመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ መካከል ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን በየአባቶቻቸው ቤት ቁጠሩ፤ በእስራኤል የጦር ሠራዊት ውስጥ ገብተው ማገልገል የሚችሉትን ሁሉ ቁጠሩ።” |
በመሆኑም ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ በሚገኘው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፦ |
“ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው 20 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን ቁጠሩ።” ከግብፅ ምድር የወጡት የእስራኤል ልጆች የሚከተሉት ነበሩ፦ |
የእስራኤል የበኩር ልጅ ሮቤል፤ የሮቤል ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ከሃኖክ የሃኖካውያን ቤተሰብ፣ ከፓሉ የፓላውያን ቤተሰብ፣ |
ከኤስሮን የኤስሮናውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከካርሚ የካርማውያን ቤተሰብ። |
የሮቤላውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 43,730 ነበሩ። |
የፓሉ ልጅ ኤልያብ ነበር። |
የኤልያብ ልጆች ደግሞ ነሙኤል፣ ዳታን እና አቤሮን ነበሩ። እዚህ ላይ የተጠቀሱት ዳታን እና አቤሮን ቆሬና ግብረ አበሮቹ በይሖዋ ላይ ባመፁበት ወቅት ከእነሱ ጋር በማበር በሙሴና በአሮን ላይ የተነሱ የማኅበረሰቡ ተወካዮች ነበሩ። |
ከዚያም ምድር አፏን ከፍታ ዋጠቻቸው። ቆሬም እሳት ወርዶ 250 ሰዎችን በበላ ጊዜ ከነግብረ አበሮቹ ሞተ። እነሱም የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ሆኑ። |
ይሁንና የቆሬ ልጆች አልሞቱም። |
የስምዖን ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከነሙኤል የነሙኤላውያን ቤተሰብ፣ ከያሚን የያሚናውያን ቤተሰብ፣ ከያኪን የያኪናውያን ቤተሰብ፣ |
ከዛራ የዛራውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሻኡል የሻኡላውያን ቤተሰብ። |
የስምዖናውያን ቤተሰቦች እነዚህ ሲሆኑ እነሱም 22,200 ነበሩ። |
የጋድ ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከጸፎን የጸፎናውያን ቤተሰብ፣ ከሃጊ የሃጋውያን ቤተሰብ፣ ከሹኒ የሹናውያን ቤተሰብ፣ |
ከኦዝኒ የኦዝናውያን ቤተሰብ፣ ከኤሪ የኤራውያን ቤተሰብ፣ |
ከአሮድ የአሮዳውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከአርዔላይ የአርዔላውያን ቤተሰብ። |
የጋድ ልጆች ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 40,500 ነበሩ። |
የይሁዳ ልጆች ኤር እና ኦናን ነበሩ። ሆኖም ኤር እና ኦናን በከነአን ምድር ሞቱ። |
የይሁዳ ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከሴሎም የሴሎማውያን ቤተሰብ፣ ከፋሬስ የፋሬሳውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከዛራ የዛራውያን ቤተሰብ። |
የፋሬስ ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ከኤስሮን የኤስሮናውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሃሙል የሃሙላውያን ቤተሰብ። |
የይሁዳ ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 76,500 ነበሩ። |
የይሳኮር ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከቶላ የቶላውያን ቤተሰብ፣ ከፑዋ የፑዋውያን ቤተሰብ፣ |
ከያሹብ የያሹባውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከሺምሮን የሺምሮናውያን ቤተሰብ። |
የይሳኮር ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 64,300 ነበሩ። |
የዛብሎን ልጆች በየቤተሰባቸው እነዚህ ነበሩ፦ ከሰሬድ የሰሬዳውያን ቤተሰብ፣ ከኤሎን የኤሎናውያን ቤተሰብ እንዲሁም ከያህልኤል የያህልኤላውያን ቤተሰብ። |
የዛብሎናውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ፤ ከእነሱም መካከል የተመዘገቡት 60,500 ነበሩ። |
የዮሴፍ ልጆች በየቤተሰባቸው ምናሴና ኤፍሬም ነበሩ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.