text stringlengths 4 267 |
|---|
እንዲሁም ለኃጢአት መባ እንዲሆን ከፍየሎች መካከል አንድ ግልገል፣ ለኅብረት መሥዋዕት እንዲሆኑ ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ዓመት የሆናቸው ሁለት ተባዕት የበግ ጠቦቶችን አቅርቡ። |
ካህኑም መጀመሪያ ከደረሱ ፍሬዎች ከተዘጋጁት ቂጣዎችና ከሁለቱ ተባዕት ጠቦቶች ጋር በይሖዋ ፊት የሚወዘወዝ መባ አድርጎ ወዲያና ወዲህ ይወዝውዛቸው። እነዚህም ለይሖዋ የተቀደሱ ነገሮች ናቸው፤ የካህኑም ድርሻ ይሆናሉ። |
በዚህ ቀን ለእናንተ ቅዱስ ጉባኤ ታውጃላችሁ። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ። በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላቂ ደንብ ነው። |
“‘የምድራችሁን አዝመራ በምታጭዱበት ጊዜ የእርሻችሁን ዳርና ዳር ሙልጭ አድርጋችሁ አትጨዱት፤ የእርሻችሁን ቃርሚያም አትልቀሙ። እነዚህን ለድሃውና ለባዕድ አገሩ ሰው ተዉለት። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’” |
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘በሰባተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን መለከት በመንፋት የሚታሰብ ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ቅዱስ ጉባኤ ታከብራላችሁ። |
ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ፤ ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ታቀርባላችሁ።’” |
በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“ሆኖም የዚህ የሰባተኛው ወር አሥረኛ ቀን የስርየት ቀን ነው። ቅዱስ ጉባኤ አክብሩ፣ ራሳችሁን አጎሳቁሉ እንዲሁም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ አቅርቡ። |
ይህ ቀን በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ለእናንተ ማስተሰረያ የሚቀርብበት የስርየት ቀን ስለሆነ በዚህ ቀን ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። |
በዚህ ቀን ራሱን የማያጎሳቁል ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረጋል። |
በዚህ ቀን ምንም ዓይነት ሥራ የሚሠራን ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። |
ምንም ዓይነት ሥራ መሥራት የለባችሁም። በምትኖሩበት በየትኛውም ቦታ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህ ዘላቂ ደንብ ነው። |
ይህ እናንተ ሙሉ በሙሉ የምታርፉበት ሰንበት ነው፤ በወሩም ዘጠነኛ ቀን ምሽት ላይ ራሳችሁን ታጎሳቁላላችሁ። ሰንበታችሁንም ከዚያ ዕለት ምሽት አንስቶ እስከ ቀጣዩ ቀን ምሽት ድረስ አክብሩ።” |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘በዚህ በሰባተኛው ወር ከ15ኛው ቀን ጀምሮ ለሰባት ቀን ያህል ለይሖዋ የዳስ በዓል ይከበራል። |
በመጀመሪያው ቀን ላይ ቅዱስ ጉባኤ ይሆናል፤ እናንተም ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ መሥራት የለባችሁም። |
ለሰባት ቀን ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ማቅረብ ይኖርባችኋል። በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ታከብራላችሁ፤ ለይሖዋም በእሳት የሚቀርብ መባ ማቅረብ አለባችሁ። ይህ የተቀደሰ ጉባኤ ነው። ምንም ዓይነት ከባድ ሥራ አትሥሩ። |
“‘ለይሖዋ በእሳት የሚቀርበውን መባ ማለትም የሚቃጠለውን መባ፣ ከመሥዋዕቱ ጋር የሚቀርበውን የእህል መባና በየዕለቱ እንዲቀርቡ የተመደቡትን የመጠጥ መባዎች ለማቅረብ ቅዱስ ጉባኤዎች እንደሆኑ አድርጋችሁ የምታውጇቸው በየወቅቱ የሚከበሩት የይሖዋ በዓላት እነዚህ ናቸው። |
እነዚህ ለይሖዋ ልትሰጧቸው ከሚገቡት በይሖዋ ሰንበቶች ላይ ከሚቀርቡት፣ ከስጦታዎቻችሁ፣ ስእለት ለመፈጸም ከምታቀርቧቸው መባዎችና ከፈቃደኝነት መባዎቻችሁ በተጨማሪ የምታቀርቧቸው ናቸው። |
ይሁን እንጂ የምድራችሁን ፍሬ በምትሰበስቡበት ጊዜ በሰባተኛው ወር ላይ ከ15ኛው ቀን ጀምሮ የይሖዋን በዓል ለሰባት ቀን ታከብራላችሁ። የመጀመሪያው ቀን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይሆናል፤ ስምንተኛውም ቀን ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይሆናል። |
በመጀመሪያውም ቀን የተንዠረገጉ ዛፎችን ፍሬ፣ የዘንባባ ዝንጣፊዎችን፣ የለመለሙ ዛፎችን ቅርንጫፎችና በሸለቆ የሚበቅሉ የአኻያ ዛፎችን ውሰዱ፤ በአምላካችሁም በይሖዋ ፊት ለሰባት ቀን ተደሰቱ። |
ይህን በዓል በየዓመቱ ለሰባት ቀን ለይሖዋ የሚከበር በዓል አድርጋችሁ ታከብሩታላችሁ። በትውልዶቻችሁም ሁሉ ዘላቂ ደንብ አድርጋችሁ በሰባተኛው ወር አክብሩት። |
ለሰባት ቀን በዳስ ውስጥ ተቀመጡ። በእስራኤል የሚኖሩ የአገሩ ተወላጆች በሙሉ በዳስ ውስጥ ይቀመጡ፤ |
ይህን የሚያደርጉት እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር ባወጣኋቸው ጊዜ በዳስ ውስጥ እንዲቀመጡ እንዳደረግኩ መጪዎቹ ትውልዶቻችሁ እንዲያውቁ ነው። እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝ።’” |
ስለዚህ ሙሴ በየወቅቱ የሚከበሩትን የይሖዋን በዓላት ለእስራኤላውያን አስታወቀ። |
ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“አንድ ሰው በአደራ እንዲይዝ ወይም እንዲያስቀምጥ ከተሰጠው ነገር ጋር በተያያዘ ባልንጀራውን በማታለል ኃጢአት ቢሠራና በይሖዋ ላይ ታማኝነት የማጉደል ተግባር ቢፈጽም አሊያም ባልንጀራውን ቢሰርቅ ወይም ቢያጭበረብር |
አሊያም ደግሞ የጠፋ ነገር አግኝቶ አላየሁም ብሎ ቢዋሽና ሰውየው ከእነዚህ ኃጢአቶች መካከል አንዱንም እንዳልሠራ አድርጎ በሐሰት ቢምል እንዲህ ማድረግ አለበት፦ |
ኃጢአት ቢሠራና በደለኛ ሆኖ ቢገኝ የሰረቀውን፣ ቀምቶ ወይም አጭበርብሮ የወሰደውን አሊያም በአደራ ተሰጥቶት የነበረውን ወይም ደግሞ ጠፍቶ ያገኘውን ነገር ይመልስ፤ |
አሊያም በሐሰት የማለበትን ማንኛውንም ነገር ይመልስ፤ ሙሉ ካሳ ይክፈል፤ የዋጋውንም አንድ አምስተኛ ይጨምርበት። በደለኛ መሆኑ በተረጋገጠበትም ዕለት ለባለቤቱ ይሰጠዋል። |
በተተመነውም ዋጋ መሠረት እንከን የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው መካከል በመውሰድ የበደል መባው አድርጎ ለይሖዋ ለማቅረብ ወደ ካህኑ ያመጣዋል። |
ካህኑም በይሖዋ ፊት ያስተሰርይለታል፤ እሱም በደለኛ እንዲሆን ያደረገው ማንኛውም ነገር ይቅር ይባልለታል።” |
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ ‘የሚቃጠል መባ ሕግ ይህ ነው፦ የሚቃጠለው መባ ሌሊቱን ሙሉ እስኪነጋ ድረስ በመሠዊያው ላይ ባለው ማንደጃ ላይ ይቀመጣል፤ እሳቱም በመሠዊያው ላይ ሲነድ ያድራል። |
ካህኑ ከበፍታ የተሠራውን የክህነት ልብሱን ይለብሳል፤ እርቃኑንም ለመሸፈን ከበፍታ የተሠራውን ቁምጣ ያደርጋል። ከዚያም በመሠዊያው ላይ ከነበረው በእሳት ከነደደው የሚቃጠል መባ የወጣውን አመድ ያነሳል፤ በመሠዊያውም ጎን ያደርገዋል። |
ከዚያም ልብሱን አውልቆ ሌላ ልብስ ይለብሳል፤ አመዱንም ከሰፈሩ ውጭ ወደሚገኝ ንጹሕ የሆነ ቦታ ይወስደዋል። |
እሳቱ በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል። መጥፋትም የለበትም። ካህኑም በየማለዳው እንጨት ይማግድበት፤ በላዩም ላይ የሚቃጠለውን መባ ይረብርብበት፤ የኅብረት መሥዋዕቶቹንም ስብ በላዩ ላይ ያጨስበታል። |
በመሠዊያውም ላይ ያለማቋረጥ እሳት ይነድዳል። መጥፋትም የለበትም። |
“‘የእህል መባ ሕግ ደግሞ ይህ ነው፦ እናንተ የአሮን ወንዶች ልጆች በመሠዊያው ፊት ለፊት በይሖዋ ፊት ታቀርቡታላችሁ። |
ከመካከላቸው አንዱ ለእህል መባ ከቀረበው የላመ ዱቄት ላይ ከነዘይቱ አንድ እፍኝ ያነሳል፤ እንዲሁም በእህል መባው ላይ ያለውን ነጭ ዕጣን በሙሉ ይወስዳል። አምላክ መላውን መባ እንዲያስበውም ለይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጨሰዋል። |
ከዚያ የተረፈውን አሮንና ወንዶች ልጆቹ ይበሉታል፤ እንደ ቂጣ ተጋግሮ በቅዱስ ስፍራ ይበላል። በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ይበሉታል። |
ያለእርሾ መጋገር አለበት። ለእኔ በእሳት ከሚቀርቡልኝ መባዎች ውስጥ ይህን ድርሻቸው አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። እንደ ኃጢአት መባና እንደ በደል መባ ሁሉ ይህም እጅግ ቅዱስ ነገር ነው። |
የአሮን ዘር የሆኑ ወንዶች ሁሉ ይበሉታል። ይህ ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡ መባዎች ውስጥ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእነሱ የሚሰጥ ዘላለማዊ ድርሻ ነው። የሚነካቸውም ነገር ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።’” |
ይሖዋም በድጋሚ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“አሮን በሚቀባበት ቀን እሱና ወንዶች ልጆቹ ለይሖዋ የሚያቀርቡት መባ ይህ ነው፦ የኢፍ አንድ አሥረኛ የላመ ዱቄት በቋሚነት የሚቀርብ የእህል መባ አድርገው ያቅርቡ፤ ግማሹን ጠዋት፣ ግማሹን ደግሞ ምሽት ላይ ያቅርቡ። |
በዘይት ከተለወሰ በኋላም በምጣድ ላይ ይጋገራል። ከዚያም በደንብ በዘይት ለውሰህ ታመጣዋለህ፤ የተጋገረውንም የእህል መባ ቆራርሰህ ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ይሆን ዘንድ ለይሖዋ ታቀርበዋለህ። |
ከወንዶች ልጆቹ መካከል እሱን የሚተካው የተቀባው ካህንም ያቀርበዋል። ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ መባም ሆኖ ለይሖዋ እንዲጨስ ይደረጋል፤ ይህም ዘላቂ ሥርዓት ነው። |
አንድ ካህን የሚያቀርበው እያንዳንዱ የእህል መባ ሙሉ በሙሉ መቃጠል ይኖርበታል። መበላት የለበትም።” |
ይሖዋ በድጋሚ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፦ ‘የኃጢአት መባ ሕግ ይህ ነው፦ ለኃጢአት መባ የሚሆነውም እንስሳ፣ ለሚቃጠል መባ የሚሆነው እንስሳ በሚታረድበት ቦታ በይሖዋ ፊት ይታረዳል። ይህ እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው። |
ይህን ለኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው ካህን ይበላዋል። በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ይበላል። |
“‘ሥጋውን የሚነካ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ይሆናል፤ ማንም ሰው የእንስሳውን ደም በልብሱ ላይ ቢረጭ ደም የተረጨበትን ልብስ በቅዱስ ስፍራ እጠበው። |
ሥጋው የተቀቀለበት የሸክላ ዕቃም መሰባበር አለበት። የተቀቀለው ከመዳብ በተሠራ ዕቃ ከሆነ ግን ዕቃው ፍትግ ተደርጎ በውኃ መታጠብ አለበት። |
“‘ካህን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበላዋል። እጅግ ቅዱስ የሆነ ነገር ነው። |
ይሁን እንጂ በቅዱሱ ስፍራ ለማስተሰረያ እንዲሆን ደሙ ወደ መገናኛ ድንኳኑ የገባ የኃጢአት መባ መበላት የለበትም። በእሳት መቃጠል አለበት። |
ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“አሮንን፣ ከእሱም ጋር ወንዶች ልጆቹን እንዲሁም ልብሶቹን፣ የቅብዓት ዘይቱን፣ ለኃጢአት መባ የሚሆነውን በሬ፣ ሁለቱን አውራ በጎችና ቂጣ ያለበትን ቅርጫት ውሰድ፤ |
መላው ማኅበረሰብም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ እንዲሰበሰብ አድርግ።” |
ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበረሰቡም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ተሰበሰበ። |
ሙሴም ለማኅበረሰቡ “ይሖዋ እንድናደርግ ያዘዘን ነገር ይህ ነው” አላቸው። |
በመሆኑም ሙሴ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን አቀረባቸው፤ በውኃም አጠባቸው። |
ከዚያም ለአሮን ረጅሙን ቀሚስ አጠለቀለት፤ መቀነቱንም አሰረለት፤ እጅጌ የሌለውን ቀሚስም አለበሰው፤ ኤፉዱንም አደረገለት፤ ኤፉዱንም ተሸምኖ በተሠራው የኤፉዱ መቀነት ጠበቅ አድርጎ አሰረው። |
በመቀጠልም የደረት ኪሱን አደረገለት፤ በደረት ኪሱም ውስጥ ኡሪሙንና ቱሚሙን አስቀመጠ። |
ከዚያም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ጥምጥሙን በራሱ ላይ አደረገለት፤ በጥምጥሙም ከፊት በኩል፣ የሚያብረቀርቀውን ጠፍጣፋ ወርቅ ይኸውም ለአምላክ የተወሰኑ መሆንን የሚያሳየውን ቅዱስ ምልክት አደረገለት። |
ሙሴም የቅብዓት ዘይቱን ወስዶ የማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያሉትን ነገሮች በሙሉ ቀባቸው፤ እንዲሁም ቀደሳቸው። |
ከዚያም ይቀድሳቸው ዘንድ ከዘይቱ የተወሰነውን ወስዶ በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ በመርጨት መሠዊያውንና ዕቃዎቹን በሙሉ እንዲሁም የውኃ ገንዳውንና ማስቀመጫውን ቀባቸው። |
በመጨረሻም ከቅብዓት ዘይቱ የተወሰነውን ወስዶ በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰው፤ የተቀደሰም ይሆን ዘንድ ቀባው። |
ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት የአሮንን ወንዶች ልጆች አቀረባቸው፤ ረጅሞቹን ቀሚሶችም አለበሳቸው፤ መቀነቶቹንም አሰረላቸው፤ የራስ ቆቡንም ደፋላቸው። |
ከዚያም ለኃጢአት መባ የሚሆነውን በሬ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጆቻቸውን ለኃጢአት መባ በሚሆነው በሬ ራስ ላይ ጫኑ። |
ሙሴም በሬውን አረደው፤ ደሙንም በጣቱ ወስዶ በሁሉም የመሠዊያው ጎኖች ላይ ያሉትን ቀንዶች ቀባ፤ መሠዊያውንም ከኃጢአት አነጻው፤ የቀረውንም ደም መሠዊያው ማስተሰረያ ይቀርብበት ዘንድ መሠዊያውን ለመቀደስ በሥሩ አፈሰሰው። |
ከዚያም ሙሴ አንጀቱን የሸፈነውን ስብ ሁሉ፣ በጉበቱ ላይ ያለውን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ ወስዶ በመሠዊያው ላይ እንዲጨሱ አደረገ። |
ሙሴም ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ከበሬው የቀረውን፣ ቆዳውን፣ ሥጋውንና ፈርሱን ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለው። |
እሱም ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን አውራ በግ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጆቻቸውን በአውራው በግ ራስ ላይ ጫኑ። |
ከዚያም ሙሴ አውራውን በግ አረደው፤ ደሙንም በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው። |
አውራውንም በግ በየብልቱ ቆራረጠው፤ ቀጥሎም ጭንቅላቱን፣ ብልቶቹንና ሞራውን አጨሰው። |
ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠባቸው፤ ሙሴም አውራው በግ በሙሉ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አደረገ። ይህም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ ነበር። ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነበር። |
ከዚያም ሁለተኛውን አውራ በግ ይኸውም ለክህነት ሹመት ሥርዓት የሚቀርበውን አውራ በግ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ። |
ከዚያም ሙሴ አውራውን በግ አረደው፤ ከደሙም የተወሰነውን ወስዶ የአሮንን የቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ የቀኝ እጁን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግሩን አውራ ጣት ቀባ። |
በመቀጠልም ሙሴ የአሮንን ወንዶች ልጆች ወደ ፊት አቀረባቸው፤ ከደሙም የተወሰነውን ወስዶ የቀኝ ጆሯቸውን ጫፍ፣ የቀኝ እጃቸውን አውራ ጣት እንዲሁም የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ቀባ፤ የቀረውን ደም ግን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው። |
ከዚያም ስቡን፣ ላቱን፣ አንጀቱን የሚሸፍነውን ስብ በሙሉ፣ የጉበቱን ሞራ፣ ሁለቱን ኩላሊቶችና በእነሱ ላይ ያለውን ስብ እንዲሁም ቀኝ እግሩን ወሰደ። |
በይሖዋ ፊት ካለው ቂጣዎች ከተቀመጡበት ቅርጫት ውስጥም እርሾ ያልገባበት የቀለበት ቅርጽ ያለው አንድ ዳቦ፣ ዘይት የተቀባ የቀለበት ቅርጽ ያለው አንድ ዳቦና አንድ ስስ ቂጣ ወሰደ። ከዚያም በስቦቹና በቀኝ እግሩ ላይ አደረጋቸው። |
በመቀጠልም ሁሉንም በአሮን መዳፍና በወንዶች ልጆቹ መዳፍ ላይ አስቀመጣቸው፤ በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባም ወዲያና ወዲህ ወዘወዛቸው። |
ከዚያም ሙሴ ከእጃቸው ላይ ወስዶ በመሠዊያው ላይ ባለው በሚቃጠለው መባ ላይ እንዲጨሱ አደረገ። እነዚህም ደስ የሚያሰኝ መዓዛ የሚሰጡ የክህነት ሹመት መሥዋዕት ናቸው። ይህም ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነበር። |
ሙሴም ፍርምባውን ወስዶ በይሖዋ ፊት እንደሚወዘወዝ መባ ወዲያና ወዲህ ወዘወዘው። ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረትም ለክህነት ሹመት ሥርዓት ከሚቀርበው አውራ በግ ላይ ይህ የእሱ ድርሻ ሆነ። |
ሙሴም ከቅብዓት ዘይቱና በመሠዊያው ላይ ካለው ደም የተወሰነውን ወስዶ በአሮንና በልብሶቹ እንዲሁም ከእሱ ጋር በነበሩት ወንዶች ልጆቹና በወንዶች ልጆቹ ልብሶች ላይ ረጨው። በዚህ መንገድ አሮንንና ልብሶቹን እንዲሁም ወንዶች ልጆቹንና ልብሶቻቸውን ቀደሰ። |
ከዚያም ሙሴ አሮንንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ አላቸው፦ “ሥጋውን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ቀቅሉት፤ ‘አሮንና ወንዶች ልጆቹ ይበሉታል’ ተብዬ በታዘዝኩት መሠረት ሥጋውንም ሆነ በክህነት ሹመት ሥርዓቱ ቅርጫት ውስጥ ያለውን ቂጣ እዚያ ትበሉታላችሁ። |
ከሥጋውም ሆነ ከቂጣው የተረፈውን በእሳት ታቃጥሉታላችሁ። |
ለክህነት ሹመታችሁ ሥርዓት የተመደቡት ቀናት እስከሚያበቁ ድረስ ይኸውም ለሰባት ቀን ያህል በመገናኛ ድንኳኑ ደጃፍ ቆዩ፤ ምክንያቱም እናንተን ካህን አድርጎ መሾም ሰባት ቀን ይፈጃል። |
ለእናንተ ለማስተሰረይ ዛሬ ያደረግነውን ነገር እንድናደርግ ይሖዋ አዟል። |
በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ቀንና ሌሊት ለሰባት ቀን ያህል ትቆያላችሁ፤ እንዳትሞቱም ለይሖዋ የገባችሁትን ግዴታ ፈጽሙ፤ ምክንያቱም እንዲህ እንዳደርግ ታዝዣለሁ።” |
አሮንና ወንዶች ልጆቹም ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት ያዘዛቸውን ነገሮች በሙሉ አደረጉ። |
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን አናግራቸው፤ ለእያንዳንዱ የአባቶች ቤት ከእያንዳንዱ የአባቶች ቤት አለቃ ላይ አንድ አንድ በትር ይኸውም በአጠቃላይ 12 በትሮችን ከእነሱ ላይ ውሰድ። የእያንዳንዳቸውንም ስም በየበትራቸው ላይ ጻፍ። |
ለእያንዳንዱ የአባቶች ቤት መሪ የሚኖረው አንድ በትር ስለሆነ የአሮንን ስም በሌዊ በትር ላይ ጻፍ። |
በትሮቹን ራሴን ዘወትር ለእናንተ በምገልጥበት በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ በምሥክሩ ፊት ለፊት አስቀምጣቸው። |
ከዚያም እኔ የምመርጠው ሰው በትር ያቆጠቁጣል፤ እኔም እስራኤላውያን በእናንተ ላይ በማጉረምረም በእኔ ላይ እያሰሙ ያሉት ማጉረምረም እንዲያበቃ አደርጋለሁ።” |
በመሆኑም ሙሴ እስራኤላውያንን አነጋገራቸው፤ አለቆቻቸውም በሙሉ በትሮቹን ይኸውም ለእያንዳንዱ የአባቶች ቤት አለቃ አንድ በትር ማለትም 12 በትሮችን ሰጡት፤ የአሮንም በትር ከእነሱ በትሮች ጋር ነበር። |
ከዚያም ሙሴ በትሮቹን በምሥክሩ ድንኳን ውስጥ በይሖዋ ፊት አስቀመጣቸው። |
በማግስቱም ሙሴ ወደ ምሥክሩ ድንኳን ሲገባ የሌዊን ቤት የሚወክለውን የአሮንን በትር አቆጥቁጦ፣ እንቡጥ አውጥቶ፣ አበባ አብቦና የደረሰ የአልሞንድ ፍሬ አፍርቶ አገኘው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.