text
stringlengths
4
267
ከዚያም እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ በመግባት ሁለቱንም ወጋቸው፤ እስራኤላዊውን ወጋው፤ እሷንም ሆዷ ላይ ወጋት። በዚህ ጊዜ መቅሰፍቱ ከእስራኤል ልጆች ላይ ተወገደ።
በመቅሰፍቱ የሞቱት ሰዎች 24,000 ነበሩ።
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
“የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ በመካከላቸው እኔን የሚቀናቀነኝን ማንኛውንም ነገር በቸልታ ባለማለፉ ቁጣዬ ከእስራኤል ሕዝብ ላይ እንዲመለስ አድርጓል። ስለዚህ እስራኤላውያንን እኔን ብቻ ለምን አላመለካችሁም ብዬ ጠራርጌ አላጠፋኋቸውም።
በዚህም የተነሳ ከእሱ ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እንደምገባ ንገረው።
ይህም አምላኩን የሚቀናቀነውን ማንኛውንም ነገር በቸልታ ባለማለፉ እንዲሁም ለእስራኤል ሕዝብ በማስተሰረዩ ለእሱና ከእሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ ዘላቂ የክህነት ቃል ኪዳን ሆኖ ያገለግላል።”
ከምድያማዊቷ ሴት ጋር የተገደለው ሟቹ እስራኤላዊ የስምዖናውያን አባቶች ቤት አለቃ የሆነው የሳሉ ልጅ ዚምሪ ነበር።
የተገደለችውም ምድያማዊት ሴት የጹር ልጅ ኮዝቢ ነበረች፤ ጹር በምድያም ካሉት የአባቶች ቤት ጎሳዎች የአንዱ መሪ ነበር።
በኋላም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
“ምድያማውያንን አንገላቷቸው፤ እንዲሁም ፍጇቸው፤
ምክንያቱም እነሱ ከፌጎርና ከእህታቸው ከኮዝቢ ጋር በተያያዘ በፈጸሙባችሁ ተንኮል የተነሳ አንገላተዋችኋል፤ ኮዝቢ ከፌጎር ጋር በተያያዘ የተከሰተው መቅሰፍት በመጣበት ዕለት የተገደለች የምድያማዊው አለቃ ልጅ ነች።”
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦
“ለእስራኤላውያን የምሰጠውን የከነአንን ምድር እንዲሰልሉ ሰዎችን ላክ። ከእያንዳንዱ የአባቶች ነገድ አንድ አንድ ሰው ይኸውም ከመካከላቸው አለቃ የሆነውን ሰው ትልካለህ።”
በመሆኑም ሙሴ ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው። ሰዎቹ በሙሉ የእስራኤላውያን መሪዎች ነበሩ።
ስማቸውም የሚከተለው ነው፦ ከሮቤል ነገድ የዛኩር ልጅ ሻሙአ፣
ከስምዖን ነገድ የሆሪ ልጅ ሻፋጥ፣
ከይሁዳ ነገድ የየፎኒ ልጅ ካሌብ፣
ከይሳኮር ነገድ የዮሴፍ ልጅ ይግዓል፣
ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ ሆሺአ፣
ከቢንያም ነገድ የራፉ ልጅ ፓልጢ፣
ከዛብሎን ነገድ የሶዲ ልጅ ጋዲኤል፣
ከዮሴፍ ነገድ መካከል ለምናሴ ነገድ የሱሲ ልጅ ጋዲ፣
ከዳን ነገድ የገማሊ ልጅ አሚዔል፣
ከአሴር ነገድ የሚካኤል ልጅ ሰቱር፣
ከንፍታሌም ነገድ የዎፍሲ ልጅ ናህቢ
እንዲሁም ከጋድ ነገድ የማኪ ልጅ ጌኡዔል።
ሙሴ ምድሪቱን እንዲሰልሉ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴም ለነዌ ልጅ ለሆሺአ፣ ኢያሱ የሚል ስም አወጣለት።
ሙሴ የከነአንን ምድር እንዲሰልሉ ሰዎቹን ሲልካቸው እንዲህ አላቸው፦ “በዚህ አድርጋችሁ ወደ ኔጌብ አቅኑ፤ ከዚያም ወደ ተራራማው አካባቢ ሂዱ።
ምድሪቱ ምን እንደምትመስል፣ ነዋሪዎቿም ብርቱ ወይም ደካማ፣ ጥቂት ወይም ብዙ መሆናቸውን እዩ፤
እንዲሁም ምድሪቱ መልካም ወይም መጥፎ መሆኗን ከተሞቹም በግንብ የታጠሩ ወይም ያልታጠሩ መሆናቸውን ተመልከቱ።
ምድሪቱም ለም ወይም ደረቅ መሆኗን፣ በዚያም ዛፎች መኖር አለመኖራቸውን አጣሩ። እንዲሁም በድፍረት ከምድሪቱ ፍሬ ጥቂት ይዛችሁ ኑ።” ደግሞም ጊዜው የመጀመሪያው የወይን ፍሬ የሚደርስበት ወቅት ነበር።
ስለዚህ ሰዎቹ ወጥተው ምድሪቱን ከጺን ምድረ በዳ አንስተው በሌቦሃማት እስከምትገኘው እስከ ሬሆብ ድረስ ሰለሉ።
በኔጌብ በኩል ሽቅብ ሲወጡም ኤናቃውያኑ አሂማን፣ ሸሻይ እና ታልማይ ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን ደረሱ። ኬብሮን የተቆረቆረችው በግብፅ ያለችው ጾዓን ከመቆርቆሯ ከሰባት ዓመት በፊት ነበር።
ወደ ኤሽኮል ሸለቆ በደረሱ ጊዜ የወይን ዘለላዎችን ያንዠረገገ አንድ ቅርንጫፍ ከዚያ ቆረጡ፤ ከሰዎቹም መካከል ሁለቱ በዱላ ተሸከሙት፤ በተጨማሪም ጥቂት የሮማን ፍሬዎችንና የበለስ ፍሬዎችን ያዙ።
እስራኤላውያን ከዚያ በቆረጡት ዘለላ የተነሳ ያን ቦታ የኤሽኮል ሸለቆ ብለው ጠሩት።
ምድሪቱንም ሰልለው ከ40 ቀን በኋላ ተመለሱ።
በቃዴስ ባለው በፋራን ምድረ በዳ ወደሚገኙት ወደ ሙሴ፣ ወደ አሮንና ወደ መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ተመልሰው መጡ። ያዩትንም ሁሉ ለመላው ማኅበረሰብ ተናገሩ፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።
ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “ወደላክኸን ምድር ገብተን ነበር፤ በእርግጥም ምድሪቱ ወተትና ማር የምታፈስ ናት፤ የምድሪቱም ፍሬ ይህን ይመስላል።
ይሁንና በምድሪቱ የሚኖሩት ሰዎች ብርቱዎች ናቸው፤ በግንብ የታጠሩት ከተሞችም ቢሆኑ በጣም ታላላቅ ናቸው። ደግሞም ኤናቃውያንን በዚያ አይተናል።
አማሌቃውያን በኔጌብ ምድር ይኖራሉ፤ ሂታውያን፣ ኢያቡሳውያንና አሞራውያን ደግሞ በተራራማው አካባቢ ይኖራሉ፤ በባሕሩ አካባቢና በዮርዳኖስ ዳርቻ ደግሞ ከነአናውያን ይኖራሉ።”
ከዚያም ካሌብ “በድፍረት እንውጣ፤ ድል እንደምናደርግ ምንም ጥርጥር ስለሌለው ምድሪቱን እንወርሳለን” በማለት በሙሴ ፊት የቆመውን ሕዝብ ሊያረጋጋ ሞከረ።
ከእሱ ጋር የወጡት ሰዎች ግን “ሰዎቹ ከእኛ ይልቅ ብርቱዎች ስለሆኑ ወጥተን ልንዋጋቸው አንችልም” አሉ።
እንዲሁም የሰለሏትን ምድር በተመለከተ ለእስራኤላውያን እንዲህ የሚል መጥፎ ወሬ አወሩ፦ “በውስጧ ተዘዋውረን የሰለልናት ምድር ነዋሪዎቿን የምትበላ ምድር ናት፤ እዚያ ያየናቸውም ሰዎች በሙሉ እጅግ ግዙፎች ናቸው።
በዚያም ኔፍሊሞችን ይኸውም የኔፍሊም ዝርያ የሆኑትን የኤናቅን ልጆች አይተናል፤ እኛ ከእነሱ ጋር ስንነጻጸር በእኛም ሆነ በእነሱ ዓይን ልክ እንደ ፌንጣ ነበርን።”
በኔጌብ የሚኖረው ከነአናዊው የአራድ ንጉሥ እስራኤላውያን በአታሪም መንገድ እየመጡ መሆናቸውን በሰማ ጊዜ በእነሱ ላይ ጥቃት ሰነዘረ፤ ከመካከላቸውም የተወሰኑትን በምርኮ ወሰደ።
ስለዚህ እስራኤል “ይህን ሕዝብ በእጄ አሳልፈህ የምትሰጠኝ ከሆነ ከተሞቻቸውን ጠራርጌ አጠፋለሁ” በማለት ለይሖዋ ስእለት ተሳለ።
በመሆኑም ይሖዋ የእስራኤልን ጩኸት ሰማ፤ ከነአናውያንንም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነሱም ሕዝቡንና ከተሞቻቸውን ጠራርገው አጠፉ። ስለሆነም የቦታውን ስም ሆርማ አሉት።
እስራኤላውያን ከሆር ተራራ በመነሳት በኤዶም ምድር ዞረው ለመሄድ ስላሰቡ የቀይ ባሕርን መንገድ ይዘው ተጓዙ፤ ከጉዞውም የተነሳ ሕዝቡ ዛለ።
ሕዝቡም እንዲህ በማለት በአምላክና በሙሴ ላይ ያማርር ጀመር፦ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብፅ ያወጣችሁን ለምንድን ነው? ምግብ የለ፣ ውኃ የለ፤ ደግሞም ይህን የማይረባ ምግብ ጠልተነዋል።”
በመሆኑም ይሖዋ በሕዝቡ ላይ መርዘኛ እባቦችን ሰደደባቸው፤ እባቦቹም ሰዎቹን ስለነደፏቸው ብዙ እስራኤላውያን ሞቱ።
ስለሆነም ሕዝቡ ወደ ሙሴ መጥቶ “በይሖዋና በአንተ ላይ በማማረራችን ኃጢአት ሠርተናል። እባቦቹን ከመካከላችን እንዲያስወግድልን ይሖዋን ተማጸንልን” አለ። ሙሴም ስለ ሕዝቡ ተማጸነ።
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የመርዛማ እባብ ምስል ሠርተህ እንጨት ላይ ስቀለው። ማንኛውም ሰው በሚነደፍበት ጊዜ በሕይወት እንዲኖር ምስሉን ማየት አለበት።”
ሙሴም ወዲያው የመዳብ እባብ ሠርቶ እንጨት ላይ ሰቀለው፤ አንድ ሰው እባብ ሲነድፈው ከመዳብ ወደተሠራው እባብ ከተመለከተ ይድን ነበር።
ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ከነበሩበት ተነስተው በመጓዝ በኦቦት ሰፈሩ።
ከዚያም ከኦቦት ተነስተው በምሥራቅ አቅጣጫ በሞዓብ ፊት ለፊት በሚገኘው ምድረ በዳ በኢዬዓባሪም ሰፈሩ።
ከዚያ ተነስተው ደግሞ በዘረድ ሸለቆ ሰፈሩ።
ከዘረድ ሸለቆ ተነስተው ከአሞራውያን ድንበር ጀምሮ ባለው ምድረ በዳ ውስጥ በሚገኘው በአርኖን ክልል ሰፈሩ፤ ምክንያቱም አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል የሚገኝ የሞዓብ ድንበር ነው።
የይሖዋ የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ በማለት የሚናገረው ለዚህ ነው፦ “በሱፋ የሚገኘው ዋሄብ፣ የአርኖን ሸለቆዎች
እንዲሁም ኤር ወደሚገኝበት አቅጣጫ የሚዘረጋውና የሞዓብን ድንበር የሚያዋስነው የሸለቆዎች ቁልቁለት።”
ከዚያም ወደ በኤር ተጓዙ። ይሖዋ ሙሴን “ሕዝቡን ሰብስብ፤ እኔም ውኃ እሰጣቸዋለሁ” ያለው ይህን የውኃ ጉድጓድ አስመልክቶ ነው።
በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ዘመሩ፦ “አንተ ጉድጓድ፣ ውኃ አፍልቅ! እናንተም መልሱለት!
መኳንንት ለቆፈሩት፣ በሕዝቡ መካከል ያሉ ታላላቅ ሰዎች ለማሱት፣በገዢ ዘንግና በራሳቸው በትሮች ላዘጋጁት የውኃ ጉድጓድ ዘምሩለት።” ከዚያም ከምድረ በዳው ተነስተው ወደ ማታናህ ተጓዙ፤
ከማታናህ ተነስተው ደግሞ ወደ ናሃሊኤል፣ ከናሃሊኤልም ተነስተው ወደ ባሞት ተጓዙ።
ከባሞትም ተነስተው የሺሞንን ቁልቁል ማየት ወደሚቻልበት በጲስጋ አናት ላይ ወደሚገኘውና በሞዓብ ክልል ወዳለው ሸለቆ ተጓዙ።
እስራኤላውያን የአሞራውያን ንጉሥ ወደሆነው ወደ ሲሖን እንዲህ በማለት መልእክተኞችን ላኩ፦
“ምድርህን አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን። ወደ የትኛውም እርሻ ወይም ወደ የትኛውም የወይን ቦታ አንገባም። ከየትኛውም ጉድጓድ ውኃ አንጠጣም። ክልልህን አቋርጠን እስክናልፍ ድረስ በንጉሡ መንገድ ቀጥ ብለን እንሄዳለን።”
ሲሖን ግን እስራኤላውያን ክልሉን አቋርጠው እንዲያልፉ አልፈቀደላቸውም። ከዚህ ይልቅ ሲሖን ሕዝቡን ሁሉ ሰብስቦ እስራኤልን ለመውጋት ወደ ምድረ በዳው ሄደ፤ ያሃጽ በደረሰ ጊዜም ከእስራኤላውያን ጋር ውጊያ ገጠመ።
እስራኤላውያን ግን በሰይፍ ድል አደረጉት፤ ምድሩንም ከአርኖን አንስቶ በአሞናውያን አቅራቢያ እስከሚገኘው እስከ ያቦቅ ድረስ ያዙ፤ ሆኖም ያዜር የአሞናውያን ወሰን ስለሆነ ከዚያ አላለፉም።
በመሆኑም እስራኤላውያን እነዚህን ከተሞች ሁሉ ያዙ፤ ከዚያም በአሞራውያን ከተሞች ይኸውም በሃሽቦንና በሥሯ ባሉት ከተሞች ሁሉ መኖር ጀመሩ።
ምክንያቱም ሃሽቦን የአሞራውያን ንጉሥ የሲሖን ከተማ ነበረች፤ እሱም ከሞዓብ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ እስከ አርኖን ድረስ ያለውን ምድር ከእጁ ወስዶበት ነበር።
እንዲህ የሚለውን ቅኔ በመቀኘት የተሳለቁበት በዚህ የተነሳ ነው፦ “ወደ ሃሽቦን ኑ። የሲሖን ከተማ ትገንባ፤ ጸንታም ትቁም።
እሳት ከሃሽቦን፣ ነበልባልም ከሲሖን ከተማ ወጥቷልና። የሞዓብን ኤር፣ የአርኖንን ኮረብቶች ጌቶች በላ።
ሞዓብ ሆይ፣ ወዮልህ! እናንተ የከሞሽ ሕዝቦች ሆይ፣ ድምጥማጣችሁ ይጠፋል። ወንዶች ልጆቹን ለስደት ይዳርጋል፤ ሴቶች ልጆቹንም ለአሞራውያን ንጉሥ ለሲሖን ምርኮኛ አድርጎ ይሰጣል።
በመሆኑም ጥቃት እንሰንዝርባቸው፤ሃሽቦን እስከ ዲቦን ድረስ ይደመሰሳል፤እስከ ኖፋ ድረስ እንደምስሰው፤እስከ መደባም ድረስ እሳት ይዛመታል።”
ስለዚህ እስራኤላውያን በአሞራውያን ምድር መኖር ጀመሩ።
ከዚያም ሙሴ ያዜርን እንዲሰልሉ የተወሰኑ ሰዎችን ላከ። እነሱም በሥሯ ያሉትን ከተሞች ተቆጣጠሩ፤ በዚያ የነበሩትንም አሞራውያን አባረሩ።
ከዚህ በኋላ ተመልሰው ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ ይዘው ወጡ። የባሳን ንጉሥ ኦግም ከሕዝቡ ሁሉ ጋር በመሆን ኤድራይ ላይ ጦርነት ሊገጥማቸው ወጣ።
ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እሱንም ሆነ ሕዝቡን ሁሉ እንዲሁም ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥህ አትፍራው፤ አንተም በሃሽቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግከው በእሱም ላይ ታደርግበታለህ።”
በመሆኑም ኦግን ከወንዶች ልጆቹና ከሕዝቡ ሁሉ ጋር አንድም ሰው ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ፤ ምድሩንም ወረሱ።
ይሖዋ በሲና ተራራ ላይ ከሙሴ ጋር በተነጋገረ ጊዜ የአሮንና የሙሴ የቤተሰብ ሐረግ ይህ ነበር።
የአሮን ወንዶች ልጆች ስም ይህ ነው፦ የበኩር ልጁ ናዳብ፣ አቢሁ፣ አልዓዛርና ኢታምር።
የአሮን ወንዶች ልጆች ስም ይኸውም ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ የተሾሙት ቅቡዕ የሆኑት ካህናት ስም ይህ ነበር።
ይሁንና ናዳብና አቢሁ በሲና ምድረ በዳ በይሖዋ ፊት ያልተፈቀደ እሳት ባቀረቡ ጊዜ በይሖዋ ፊት ሞቱ፤ እነሱም ወንዶች ልጆች አልነበሯቸውም። አልዓዛርና ኢታምር ግን ከአባታቸው ከአሮን ጋር በክህነት ማገልገላቸውን ቀጠሉ።
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
“የሌዊን ነገድ አምጥተህ በካህኑ በአሮን ፊት አቁመው፤ እነሱም ያገልግሉት።
ከመገናኛ ድንኳኑ ጋር በተያያዘ የሚያከናውኑትን አገልግሎት በመፈጸም ለእሱም ሆነ ለመላው ማኅበረሰብ ያለባቸውን ኃላፊነት በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ይወጡ።
የመገናኛ ድንኳኑን ዕቃዎች በሙሉ በኃላፊነት መቆጣጠርና ከማደሪያ ድንኳኑ ጋር የተያያዘውን አገልግሎት በማከናወን ለእስራኤል ልጆች ያለባቸውን ኃላፊነት መወጣት ይኖርባቸዋል።
ሌዋውያኑን ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ስጣቸው። እነሱ የተሰጡ ናቸው፤ ከእስራኤላውያን መካከል ለእሱ የተሰጡ ናቸው።
አሮንንና ወንዶች ልጆቹን ሹማቸው፤ እነሱም የክህነት ኃላፊነታቸውን ይወጡ፤ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው ወደ መቅደሱ ቢቀርብ ይገደል።”
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦
“በእስራኤላውያን በኩሮች ሁሉ ምትክ ሌዋውያኑን ከእስራኤላውያን መካከል እወስዳለሁ፤ ሌዋውያኑም የእኔ ይሆናሉ።
ምክንያቱም በኩር ሁሉ የእኔ ነው። በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ በመታሁበት ቀን በእስራኤላውያን መካከል ያለውን የሰውም ሆነ የእንስሳ በኩር ለራሴ ቀድሻለሁ። እነሱ የእኔ ይሆናሉ። እኔ ይሖዋ ነኝ።”
በተጨማሪም ይሖዋ በሲና ምድረ በዳ ሙሴን እንዲህ አለው፦
“የሌዊን ወንዶች ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶችና በየቤተሰባቸው መዝግብ። አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆነውን ወንድ ሁሉ መዝግብ።”
በመሆኑም ሙሴ ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ልክ እንደታዘዘው መዘገባቸው።
የሌዊ ወንዶች ልጆች ስም ይህ ነው፦ ጌድሶን፣ ቀአትና ሜራሪ።
የጌድሶን ወንዶች ልጆች ስም በየቤተሰባቸው ይህ ነበር፦ ሊብኒ እና ሺምአይ።
የቀአት ወንዶች ልጆች በየቤተሰባቸው አምራም፣ ይጽሃር፣ ኬብሮንና ዑዚኤል ነበሩ።
የሜራሪ ወንዶች ልጆች በየቤተሰባቸው ማህሊ እና ሙሺ ነበሩ። የሌዋውያኑ ቤተሰቦች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ነበሩ።
የሊብናውያን ቤተሰብና የሺምአያውያን ቤተሰብ የተገኘው ከጌድሶን ነበር። የጌድሶናውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ።