text stringlengths 4 267 |
|---|
አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ ብዛታቸው 7,500 ነበር። |
የጌድሶናውያን ቤተሰቦች የሰፈሩት ከማደሪያ ድንኳኑ በስተ ኋላ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ነበር። |
የጌድሶናውያን የአባቶች ቤት አለቃ የላኤል ልጅ ኤሊያሳፍ ነበር። |
የጌድሶን ልጆች በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ ያለባቸው ኃላፊነት ከማደሪያ ድንኳኑ፣ ከድንኳኑ ጨርቅ፣ ከመደረቢያው፣ ከመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ መከለያ፣ |
ከግቢው መጋረጃዎች፣ በማደሪያ ድንኳኑ ዙሪያ በሚገኘው ግቢ መግቢያ ላይ ካለው መከለያ፣ ከመሠዊያው፣ ከድንኳኑ ገመዶችና ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ካለው አገልግሎት ሁሉ ጋር የተያያዘ ነበር። |
የአምራማውያን ቤተሰብ፣ የይጽሃራውያን ቤተሰብ፣ የኬብሮናውያን ቤተሰብና የዑዚኤላውያን ቤተሰብ የተገኘው ከቀአት ነበር። የቀአታውያን ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ። |
አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ወንዶች በሙሉ ብዛታቸው 8,600 ነበር፤ እነሱም ቅዱሱን ስፍራ የመንከባከብ ኃላፊነት ነበረባቸው። |
የቀአት ወንዶች ልጆች ቤተሰቦች ከማደሪያ ድንኳኑ በስተ ደቡብ በኩል ሰፍረው ነበር። |
የቀአታውያን ቤተሰቦች የአባቶች ቤት አለቃ የዑዚኤል ልጅ ኤሊጻፋን ነበር። |
ኃላፊነታቸውም ከታቦቱ፣ ከጠረጴዛው፣ ከመቅረዙ፣ ከመሠዊያዎቹ፣ በቅዱሱ ስፍራ ለማገልገል ከሚጠቀሙባቸው ዕቃዎች፣ ከመከለያውና ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ካለው አገልግሎት ሁሉ ጋር የተያያዘ ነበር። |
የሌዋውያኑ ዋና አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ሲሆን እሱም ከቅዱሱ ስፍራ ጋር በተያያዘ ኃላፊነት የተጣለባቸውን በበላይነት ይከታተል ነበር። |
የማህላውያን ቤተሰብና የሙሻውያን ቤተሰብ የተገኘው ከሜራሪ ነበር። የሜራሪ ቤተሰቦች እነዚህ ነበሩ። |
አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ ብዛታቸው 6,200 ነበር። |
የሜራሪ ቤተሰቦች የአባቶች ቤት አለቃ የአቢሃይል ልጅ ጹሪኤል ነበር። እነሱም ከማደሪያ ድንኳኑ በስተ ሰሜን በኩል ሰፍረው ነበር። |
የሜራሪ ወንዶች ልጆች የተጣለባቸው ኃላፊነት የማደሪያ ድንኳኑን ቋሚዎች፣ አግዳሚ እንጨቶቹን፣ ዓምዶቹን፣ መሰኪያዎቹን፣ ዕቃዎቹን በሙሉ፣ ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ያለውን አገልግሎት ሁሉ |
እንዲሁም በግቢው ዙሪያ ያሉትን ዓምዶች፣ መሰኪያዎቻቸውን፣ የድንኳን ካስማዎቻቸውንና የድንኳን ገመዶቻቸውን በበላይነት መቆጣጠር ነበር። |
በማደሪያ ድንኳኑ ፊት ለፊት በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ይኸውም በመገናኛ ድንኳኑ ፊት ፀሐይ በምትወጣበት አቅጣጫ የሰፈሩት ሙሴና አሮን እንዲሁም የአሮን ወንዶች ልጆች ነበሩ። እስራኤላውያንን ወክለው እንዲያከናውኑ የተጣለባቸው ግዴታም መቅደሱን የመንከባከብ ኃላፊነት ነበር። ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው ወደዚያ ቢቀርብ ይገደላል። |
ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ሙሴና አሮን በየቤተሰባቸው የመዘገቧቸው አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሌዋውያን ወንዶች በሙሉ 22,000 ነበሩ። |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤላውያን መካከል አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸውን በኩር የሆኑ ወንዶች በሙሉ መዝግብ፤ ከቆጠርካቸውም በኋላ ስማቸውን በዝርዝር ጻፍ። |
ከእስራኤላውያን መካከል በኩር በሆኑት ሁሉ ምትክ ሌዋውያኑን ለይልኝ፤ የሌዋውያኑን የቤት እንስሳትም ከእስራኤላውያን የቤት እንስሳት መካከል በኩር በሆኑት ሁሉ ምትክ ለይልኝ፤ እኔ ይሖዋ ነኝ።” |
ከዚያም ሙሴ ልክ ይሖዋ ባዘዘው መሠረት ከእስራኤላውያን መካከል በኩር የሆኑትን ሁሉ መዘገበ። |
አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሆኗቸው በየስማቸው የተመዘገቡት በኩር የሆኑ ወንዶች ብዛታቸው 22,273 ነበር። |
ይሖዋ እንዲህ በማለት ሙሴን ማነጋገሩን ቀጠለ፦ |
“ከእስራኤላውያን መካከል በኩር በሆኑት ሁሉ ምትክ ሌዋውያኑን ለይ፤ የሌዋውያኑን የቤት እንስሳትም በቤት እንስሶቻቸው ሁሉ ምትክ ለይ፤ ሌዋውያኑ የእኔ ይሆናሉ። እኔ ይሖዋ ነኝ። |
ቁጥራቸው ከሌዋውያኑ ቁጥር የበለጠውን 273 እስራኤላውያን በኩሮች ለመዋጀት |
ለእያንዳንዱ ግለሰብ እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት አምስት ሰቅል ውሰድ። አንድ ሰቅል 20 ጌራ ነው። |
አንተም ገንዘቡን ቁጥራቸው ከሌዋውያኑ ቁጥር የተረፈውን ሰዎች ለመዋጀት የተከፈለ ዋጋ አድርገህ ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ስጥ።” |
በመሆኑም ሙሴ ቁጥራቸው ከሌዋውያኑ ቁጥር የተረፈውን ሰዎች ለመዋጀት የመዋጃውን ገንዘብ ሰበሰበ። |
እሱም ገንዘቡን ይኸውም እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት 1,365 ሰቅል ከእስራኤላውያኑ በኩሮች ላይ ወሰደ። |
ከዚያም ሙሴ በይሖዋ ቃል መሠረት ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው የመዋጃውን ገንዘብ ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ሰጣቸው። |
ከዚያም ሙሴ የእስራኤላውያን የነገድ መሪዎችን እንዲህ አላቸው፦ “ይሖዋ የሰጠው ትእዛዝ ይህ ነው፦ |
አንድ ሰው ለይሖዋ ስእለት ቢሳል ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ ራሱን ግዴታ ውስጥ ቢያስገባ ቃሉን ማጠፍ የለበትም። አደርገዋለሁ ብሎ የማለውን ነገር ሁሉ መፈጸም አለበት። |
“በአባቷ ቤት የምትኖር አንዲት ወጣት ለይሖዋ ስእለት ብትሳል ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ ራሷን በመሐላ ግዴታ ውስጥ ብታስገባ |
አባቷ ስእለት መሳሏን ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ ራሷን በመሐላ ግዴታ ውስጥ ማስገባቷን ሰምቶ ካልተቃወማት ስእለቶቿ በሙሉ ይጸናሉ፤ እንዲሁም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባችው ማንኛውም ግዴታ ይጸናል። |
ሆኖም አባቷ ስእለት መሳሏን ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ ራሷን በመሐላ ግዴታ ውስጥ ማስገባቷን ሲሰማ ቢከለክላት ስእለቱ አይጸናም። አባቷ ስለከለከላት ይሖዋ ይቅር ይላታል። |
“ይሁን እንጂ ይህች ሴት ስእለት ተስላ ወይም ሳታስብበት ራሷን ግዴታ ውስጥ የሚያስገባ ቃል ተናግራ እያለ ባል ብታገባ፣ |
ባሏም ይህን ቢሰማና በሰማበት ቀን ዝም ቢላት ስእለቶቿ ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባቻቸው ግዴታዎች ይጸናሉ። |
ሆኖም ባሏ ይህን በሰማበት ቀን ቢከለክላት የተሳለችውን ስእለት ወይም ሳታስብበት ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችበትን ቃል ያፈርሰዋል፤ ይሖዋም ይቅር ይላታል። |
“ሆኖም አንዲት መበለት ወይም ከባሏ የተፋታች አንዲት ሴት ስእለት ብትሳል ራሷን ግዴታ ውስጥ ያስገባችባቸው ነገሮች በሙሉ ይጸኑባታል። |
“ይሁን እንጂ አንዲት ሴት ስእለት የተሳለችው ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ ራሷን በመሐላ ግዴታ ውስጥ ያስገባችው በባሏ ቤት እያለች ከሆነና |
ባሏም ሰምቶ ይህን ካልተቃወማት ወይም ካልከለከላት የተሳለቻቸው ስእለቶች በሙሉ ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባቻቸው ግዴታዎች ሁሉ ይጸናሉ። |
ይሁንና ባሏ የተሳለችውን ማንኛውንም ስእለት ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባችውን የትኛውንም ግዴታ በሰማበት ቀን ሙሉ በሙሉ ቢያፈርስባት ስእለቶቹ አይጸኑም። ባሏ ስእለቶቿን አፍርሷቸዋል፤ ይሖዋም ይቅር ይላታል። |
የትኛውንም ስእለት ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባችውን ግዴታ አሊያም ራሷን ለማጎሳቆል የገባችውን ቃል ባሏ ሊያጸናው ወይም ሊያፈርሰው ይችላል። |
ሆኖም ባሏ ቀናት እያለፉ ሲሄዱ ጨርሶ ካልተቃወማት ስእለቶቿን በሙሉ ወይም ከአንድ ነገር ለመታቀብ በመሐላ የገባችውን ግዴታ ሁሉ አጽንቶታል ማለት ነው። ስእለት መሳሏን በሰማበት ቀን ስላልተቃወማት እንዳጸናቸው ይቆጠራል። |
ስእለቶቹን ሰምቶ የተወሰኑ ቀናት ካለፉ በኋላ ስእለቶቹን ካፈረሰ ግን የእሷ በደል የሚያስከትላቸውን መዘዞች እሱ ይሸከማል። |
“ከባልና ከሚስት እንዲሁም ከአባትና በቤቱ ከምትኖር ወጣት ልጁ ጋር በተያያዘ ይሖዋ ለሙሴ የሰጣቸው ደንቦች እነዚህ ናቸው።” |
ከግብፅ ምድር በወጡ በሁለተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር ይሖዋ ሙሴን በሲና ምድረ በዳ እንዲህ በማለት አነጋገረው፦ |
“እስራኤላውያን የፋሲካን መሥዋዕት በተወሰነለት ጊዜ ያዘጋጁ። |
በዚህ ወር በ14ኛው ቀን አመሻሹ ላይ በተወሰነለት ጊዜ አዘጋጁት። ደንቦቹን ሁሉና ሥርዓቱን ሁሉ ተከትላችሁ አዘጋጁት።” |
በመሆኑም ሙሴ እስራኤላውያን የፋሲካን መሥዋዕት እንዲያዘጋጁ ነገራቸው። |
እነሱም በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ14ኛው ቀን አመሻሹ ላይ የፋሲካን መሥዋዕት በሲና ምድረ በዳ አዘጋጁ። እስራኤላውያንም ሁሉንም ነገር ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረጉ። |
የሞተ ሰው ነክተው በመርከሳቸው የተነሳ በዚያ ቀን የፋሲካን መሥዋዕት ማዘጋጀት ያልቻሉ ሰዎች ነበሩ። በመሆኑም እነዚህ ሰዎች በዚያ ቀን ሙሴና አሮን ፊት ቀረቡ፤ |
እንዲህም አሉት፦ “እኛ የሞተ ሰው በመንካታችን የተነሳ ረክሰናል። ይሁንና ከእስራኤላውያን ጋር መባውን በተወሰነለት ጊዜ ለይሖዋ እንዳናቀርብ የምንከለከለው ለምንድን ነው?” |
በዚህ ጊዜ ሙሴ “ይሖዋ እናንተን በተመለከተ የሚሰጠውን ትእዛዝ እስክሰማ ድረስ እዚያ ጠብቁ” አላቸው። |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘ከእናንተ ወይም ከመጪዎቹ ትውልዶቻችሁ መካከል ማንኛውም ሰው የሞተ ሰው በመንካቱ ቢረክስ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ ለይሖዋ የፋሲካን መሥዋዕት ማዘጋጀት ይጠበቅበታል። |
እነሱም በሁለተኛው ወር በ14ኛው ቀን አመሻሹ ላይ ያዘጋጁት። ይህንም ከቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት። |
ከእሱም ላይ እስከ ጠዋት ድረስ ምንም ማስተረፍ ወይም ከአጥንቱ ውስጥ አንዱንም መስበር የለባቸውም። ፋሲካን በተመለከተ የወጣውን ደንብ ሁሉ ተከትለው ያዘጋጁት። |
ይሁንና አንድ ሰው ንጹሕ ሆኖ ሳለ ወይም ሩቅ መንገድ ሳይሄድ በቸልተኝነት የፋሲካን መሥዋዕት ሳያዘጋጅ ቢቀር፣ ያ ሰው የይሖዋን መባ በተወሰነለት ጊዜ ስላላቀረበ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ እንዲጠፋ ይደረግ። ይህ ሰው ለሠራው ኃጢአት ይጠየቅበታል። |
“‘በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ካለ እሱም ለይሖዋ የፋሲካን መሥዋዕት ማዘጋጀት አለበት። ይህን በፋሲካው ደንብና በወጣለት ሥርዓት መሠረት ማድረግ አለበት። ለሁላችሁም ማለትም ለባዕድ አገሩም ሰው ሆነ ለአገሬው ተወላጅ አንድ ዓይነት ደንብ ይኑር።’” |
የማደሪያ ድንኳኑ በተተከለበት ቀን ደመናው የማደሪያ ድንኳኑን ይኸውም የምሥክሩን ድንኳን ሸፈነው፤ ሆኖም ከምሽት ጀምሮ እስከ ጠዋት ድረስ በማደሪያ ድንኳኑ ላይ እሳት የሚመስል ነገር ታየ። |
ሁልጊዜም እንዲህ ይሆን ነበር፦ ቀን ቀን ደመናው ድንኳኑን ይሸፍነው ነበር፤ ሌሊት ሌሊት ደግሞ እሳት የሚመስል ነገር ይታይ ነበር። |
ደመናው ከድንኳኑ ላይ በሚነሳበት ጊዜ ሁሉ እስራኤላውያን ወዲያውኑ ተነስተው ይጓዙ ነበር፤ ደመናው በሚቆምበት ቦታ ደግሞ እስራኤላውያን ይሰፍሩ ነበር። |
እስራኤላውያን ተነስተው የሚጓዙት በይሖዋ ትእዛዝ ነበር፤ የሚሰፍሩትም በይሖዋ ትእዛዝ ነበር። ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ በሚቆይባቸው ቀናት ሁሉ እነሱም በሰፈሩበት ቦታ ይቆዩ ነበር። |
ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ ረዘም ላሉ ቀናት በሚቆይበትም ጊዜ እስራኤላውያን ይሖዋን በመታዘዝ ባሉበት ይቆዩ ነበር። |
አንዳንድ ጊዜ ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ የሚቆየው ለጥቂት ቀናት ነበር። እነሱም የሚሰፍሩት በይሖዋ ትእዛዝ ነበር፤ ተነስተው የሚጓዙትም በይሖዋ ትእዛዝ ነበር። |
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ደመናው የሚቆየው ከምሽት እስከ ጠዋት ድረስ ብቻ ነበር፤ ጠዋት ላይ ደመናው ሲነሳ እነሱም ተነስተው ይጓዛሉ። ቀንም ሆነ ሌሊት ደመናው በሚነሳበት ጊዜ እነሱም ተነስተው ይጓዛሉ። |
እስራኤላውያን ደመናው በማደሪያ ድንኳኑ ላይ እስካለ ድረስ ለሁለት ቀንም ይሁን ለአንድ ወር ወይም ረዘም ላለ ጊዜ በሰፈሩበት ይቆያሉ እንጂ ተነስተው አይጓዙም። ደመናው በሚነሳበት ጊዜ ግን ተነስተው ይጓዛሉ። |
እነሱም የሚሰፍሩት በይሖዋ ትእዛዝ ነበር፤ ተነስተውም የሚጓዙት በይሖዋ ትእዛዝ ነበር። ይሖዋ በሙሴ አማካኝነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይሖዋ የጣለባቸውን ግዴታ ይወጡ ነበር። |
በለዓምም ይሖዋ እስራኤልን መባረክ እንደወደደ ሲያይ ዳግመኛ ድግምት ፍለጋ አልሄደም፤ ከዚህ ይልቅ ፊቱን ወደ ምድረ በዳ አቀና። |
በለዓም አሻግሮ ሲመለከት እስራኤል በየነገዱ እንደሰፈረ አየ፤ ከዚያም የአምላክ መንፈስ በእሱ ላይ ወረደ። |
በመሆኑም ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦ “የቢዖር ልጅ የበለዓም ቃል፣ዓይኑ የተከፈተው የዚያ ሰው ቃል፣ |
የአምላክን ቃል የሰማው፣ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራእይ ያየውዓይኖቹ ሳይከደኑ የሰገደው ሰው ቃል ይህ ነው፦ |
ያዕቆብ ሆይ፣ ድንኳኖችህ፣እስራኤል ሆይ፣ የማደሪያ ድንኳኖችህ እንዴት ያማሩ ናቸው! |
እንደ ሸለቆዎች፣በወንዝም ዳር እንዳሉ የአትክልት ስፍራዎች በረጅሙ ተዘርግተዋል።ይሖዋ እንደተከላቸው እሬቶች፣በውኃም ዳር እንዳሉ አርዘ ሊባኖሶች ሆነዋል። |
ከሁለቱም አቁማዳዎቹ ውኃ ይንጠባጠባል፤ዘሩም በብዙ ውኃዎች አጠገብ ተዘርቷል። ንጉሡም ከአጋግ የላቀ ይሆናል፤መንግሥቱም ከፍ ከፍ ይላል። |
አምላክ ከግብፅ አወጣው፤ለእነሱ ልክ እንደ ጎሽ ቀንዶች ነው። የሚጨቁኑትን ብሔራት ይበላል፤አጥንቶቻቸውንም ይቆረጣጥማል፤ በፍላጻዎቹም ያደቃቸዋል። |
አድብቷል፤ እንደ አንበሳም ተጋድሟል፤እንደ አንበሳስ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል? አንተን የሚባርኩህ የተባረኩ ናቸው፤የሚረግሙህም የተረገሙ ናቸው።” |
በዚህ ጊዜ ባላቅ በበለዓም ላይ በጣም ተቆጣ። ባላቅም በንቀት እጆቹን አጨብጭቦ በለዓምን እንዲህ አለው፦ “የጠራሁህ ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ነበር፤ አንተ ግን ይኸው ሦስቱንም ጊዜ ባረክሃቸው እንጂ ምንም የፈየድከው ነገር የለም። |
በል አሁን ቶሎ ብለህ ወደ ቤትህ ሂድ። እኔ እንኳ ታላቅ ክብር ላጎናጽፍህ አስቤ ነበር፤ ይሖዋ ግን ክብር ነፈገህ።” |
በለዓምም ለባላቅ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ወደ እኔ ለላክሃቸው መልእክተኞች እንዲህ ብዬ ነገሬአቸው አልነበረም? |
‘ባላቅ በብርና በወርቅ የተሞላውን ቤቱን ቢሰጠኝ እንኳ ከይሖዋ ትእዛዝ ውጭ በገዛ ፈቃዴ መልካምም ሆነ መጥፎ ነገር ማድረግ አልችልም። እኔ የምናገረው ይሖዋ የሚነግረኝን ብቻ ነው።’ |
እንግዲህ አሁን ወደ ሕዝቤ ልሄድ ነው። ይልቅስ መጥተህ ወደፊት ይህ ሕዝብ በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን ልንገርህ።” |
ስለዚህ ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦ “የቢዖር ልጅ የበለዓም ቃል፣ዓይኑ የተከፈተው የዚያ ሰው ቃል፣ |
የአምላክን ቃል የሰማው፣የልዑሉን አምላክ እውቀት የሚያውቀው ሰው ቃል ይህ ነው፤ዓይኖቹ ሳይከደኑ እየሰገደ ሳለሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ራእይ አየ፦ |
አየዋለሁ፣ አሁን ግን አይደለም፤እመለከተዋለሁ፣ በቅርቡ ግን አይደለም። ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል፤በትረ መንግሥትም ከእስራኤል ይነሳል። የሞዓብን ግንባር፣የሁከት ልጆችንም ሁሉ ራስ ቅል ይፈረካክሳል። |
እስራኤል ጀግንነቱን ሲያሳይኤዶም ርስቱ ይሆናል፤ሴይርም የጠላቶቹ ርስት ይሆናል። |
ከያዕቆብም አንዱ ድል እያደረገ ይወጣል፤የተረፉትንም የከተማዋን ነዋሪዎች ሁሉ ያጠፋል።” |
አማሌቅንም ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦ “አማሌቅ ከብሔራት መካከል የመጀመሪያ ነበር፤ሆኖም በመጨረሻ ይጠፋል።” |
ቄናውያንንም ባየ ጊዜ እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦ “መኖሪያህ አስተማማኝ ነው፤ ጎጆህም በቋጥኝ ላይ የተሠራ ነው። |
ሆኖም አንድ ሰው ቄይንን ያቃጥላታል። አሦር ማርኮ እስኪወስዳችሁ ድረስ ምን ያህል ትቆዩ ይሆን?” |
እሱም እንዲህ ሲል ምሳሌያዊ አባባሉን መናገሩን ቀጠለ፦ “አቤት! አምላክ ይህን በሚያደርግበት ጊዜ ማን ይተርፍ ይሆን? |
ከኪቲም የባሕር ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፤አሦርንም ያጠቃሉ፤ደግሞም ኤቤርን ያሠቃያሉ። ሆኖም እሱም ፈጽሞ ይጠፋል።” |
ከዚያም በለዓም ተነስቶ ወደ ስፍራው ተመለሰ። ባላቅም መንገዱን ቀጠለ። |
ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ቤተሰቦች የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የጊልያድ ልጅ፣ የሄፌር ልጅ የሆነው የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች ቀረቡ። የሴት ልጆቹም ስም ማህላ፣ ኖኅ፣ ሆግላ፣ ሚልካ እና ቲርጻ ነበር። |
እነሱም በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በሙሴ፣ በካህኑ በአልዓዛር፣ በአለቆቹ እንዲሁም በመላው ማኅበረሰብ ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፦ |
“አባታችን በምድረ በዳ ሞተ፤ ይሁንና እሱ በይሖዋ ላይ ለማመፅ ከተባበሩት ከቆሬ ግብረ አበሮች አንዱ አልነበረም፤ እሱ የሞተው በራሱ ኃጢአት ነው፤ ወንዶች ልጆችም አልነበሩትም። |
ታዲያ አባታችን ወንድ ልጅ ስለሌለው ብቻ ስሙ ከቤተሰቡ መካከል ለምን ይጥፋ? በአባታችን ወንድሞች መካከል ርስት ስጡን።” |
ስለዚህ ሙሴ ጉዳያቸውን በይሖዋ ፊት አቀረበ። |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.