text stringlengths 4 267 |
|---|
ደግሞም ወተትና ማር ወደምታፈስ ምድር አላስገባኸንም፤ ወይም እርሻና የወይን የአትክልት ቦታዎችን ርስት አድርገህ አልሰጠኸንም። ታዲያ የእነዚያን ሰዎች ዓይን ልታወጣ ነው? እኛ እንደሆነ አንመጣም!” |
ስለዚህ ሙሴ እጅግ ተቆጣ፤ ይሖዋንም እንዲህ አለው፦ “የእህል መባቸውን አትመልከት። ከእነዚህ ሰዎች አንድ አህያ እንኳ አልወሰድኩም፤ አንዳቸውንም ቢሆን አልበደልኩም።” |
ከዚያም ሙሴ ቆሬን እንዲህ አለው፦ “አንተና ግብረ አበሮችህ በሙሉ ነገ በይሖዋ ፊት ቅረቡ፤ አንተም ሆንክ እነሱ እንዲሁም አሮን መቅረብ ይኖርባችኋል። |
እያንዳንዱ ሰው የየራሱን የዕጣን ማጨሻ ይያዝ፤ በላዩም ላይ ዕጣን ያድርግበት፤ አንተንና አሮንን ጨምሮ እያንዳንዱ ሰው በይሖዋ ፊት የዕጣን ማጨሻውን ያቀርባል፤ ይህም በአጠቃላይ 250 የዕጣን ማጨሻዎች ማለት ነው፤ እያንዳንዱም የየራሱን የዕጣን ማጨሻ ይዞ ይቀርባል።” |
ስለዚህ እያንዳንዳቸው የዕጣን ማጨሻቸውን ይዘው መጡ፤ በላዩም ላይ እሳትና ዕጣን አደረጉበት፤ ከዚያም ከሙሴና ከአሮን ጋር በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆሙ። |
ቆሬ፣ ግብረ አበሮቹ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ሙሴንና አሮንን በመቃወም እንዲሰበሰቡ ባደረገ ጊዜ የይሖዋ ክብር ለመላው ማኅበረሰብ ተገለጠ። |
በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ |
“በአንዴ ጠራርጌ እንዳጠፋቸው ራሳችሁን ከዚህ ቡድን ለዩ።” |
እነሱም በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው እንዲህ አሉ፦ “አምላክ ሆይ፣ አንተ የሰው ሁሉ መንፈስ አምላክ ነህ፤ ታዲያ አንድ ሰው በሠራው ኃጢአት የተነሳ በመላው ማኅበረሰብ ላይ ትቆጣለህ?” |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“ለማኅበረሰቡ ‘ከቆሬ፣ ከዳታንና ከአቤሮን ድንኳኖች አካባቢ ራቁ!’ ብለህ ንገራቸው።” |
ሙሴም ተነስቶ ወደ ዳታንና አቤሮን ሄደ፤ የእስራኤል ሽማግሌዎችም አብረውት ሄዱ። |
ከዚያም ማኅበረሰቡን እንዲህ አላቸው፦ “በኃጢአታቸው ተጠራርጋችሁ እንዳትጠፉ እባካችሁ፣ ከእነዚህ ክፉ ሰዎች ድንኳኖች ራቁ፤ የእነሱ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትንኩ።” |
እነሱም ወዲያውኑ ከቆሬ፣ ከዳታንና ከአቤሮን ድንኳኖች፣ ከዙሪያቸውም ሁሉ ራቁ፤ ዳታንና አቤሮንም ወጥተው ከሚስቶቻቸው፣ ከልጆቻቸውና ከሕፃኖቻቸው ጋር በድንኳኖቻቸው ደጃፍ ላይ ቆሙ። |
ሙሴም እንዲህ አለ፦ “እነዚህን ነገሮች ሁሉ የማደርገው ከልቤ አመንጭቼ ሳይሆን ይሖዋ ልኮኝ መሆኑን በዚህ ታውቃላችሁ፦ |
እነዚህ ሰዎች እንደ ማንኛውም ሰው አሟሟት የሚሞቱ ከሆነና የሚደርስባቸውም ቅጣት በሌሎች ሰዎች ሁሉ ላይ የሚደርስ ዓይነት ከሆነ እኔን ይሖዋ አላከኝም ማለት ነው። |
ሆኖም ይሖዋ በእነሱ ላይ እንግዳ የሆነ ነገር ቢያደርግና መሬት አፏን ከፍታ እነሱንም ሆነ የእነሱ የሆነውን ነገር ሁሉ ብትውጥ፣ በሕይወት እንዳሉም ወደ መቃብር ቢወርዱ፣ እነዚህ ሰዎች ይሖዋን እንደናቁ በእርግጥ ታውቃላችሁ።” |
እሱም ይህን ተናግሮ እንደጨረሰ፣ የቆሙባት ምድር ተሰነጠቀች። |
ምድሪቱም አፏን ከፍታ እነሱን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ የቆሬ የሆነውን ማንኛውንም ሰውና ንብረታቸውን ሁሉ ዋጠች። |
በዚህ መንገድ እነሱም ሆኑ የእነሱ የሆኑት ሁሉ በሕይወት እንዳሉ ወደ መቃብር ወረዱ፤ ምድርም ተከደነችባቸው፤ ስለዚህ ከጉባኤው መካከል ጠፉ። |
በዙሪያቸው የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ጩኸታቸውን ሲሰሙ “ኧረ ምድሪቱ እኛንም እንዳትውጠን!” በማለት መሸሽ ጀመሩ። |
ከዚያም ከይሖዋ ዘንድ እሳት መጥቶ ዕጣን ሲያጥኑ የነበሩትን 250 ሰዎች በላ። |
በዚህ ጊዜ ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“የዕጣን ማጨሻዎቹ ቅዱስ ስለሆኑ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ከእሳቱ ውስጥ እንዲያወጣቸው ንገረው። በተጨማሪም እሳቱን ራቅ አድርጎ እንዲበትነው ንገረው። |
ኃጢአት በመሥራታቸው የተነሳ ሕይወታቸውን የከፈሉት ሰዎች ይዘዋቸው የነበሩት የዕጣን ማጨሻዎች ቅዱስ ስለሆኑ ለመሠዊያው መለበጫ እንዲያገለግሉ በስሱ ይጠፍጠፉ፤ ምክንያቱም በይሖዋ ፊት ስላቀረቧቸው ቅዱስ ሆነዋል። ለእስራኤላውያንም ምልክት ሆነው ያገልግሉ።” |
ስለሆነም ካህኑ አልዓዛር በእሳት የተቃጠሉት ሰዎች ያቀረቧቸውን የመዳብ የዕጣን ማጨሻዎች ወሰደ፤ ከዚያም መሠዊያውን ለመለበጥ በስሱ ጠፈጠፋቸው፤ |
ይህን ያደረገውም ይሖዋ በሙሴ በኩል ለእሱ በነገረው መሠረት ነው። ይህም የአሮን ዘር ያልሆነ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው በይሖዋ ፊት ዕጣን ለማጨስ እንዳይቀርብ እንዲሁም ማንም ሰው እንደ ቆሬና እንደ ግብረ አበሮቹ እንዳይሆን ለእስራኤላውያን ማሳሰቢያ እንዲሆን ነው። |
በማግስቱም መላው የእስራኤል ማኅበረሰብ “እናንተ ሰዎች የይሖዋን ሕዝብ ገድላችኋል” በማለት በሙሴና በአሮን ላይ ያጉረመርም ጀመር። |
የእስራኤልም ማኅበረሰብ ሙሴንና አሮንን በመቃወም በተሰበሰበ ጊዜ ወደ መገናኛ ድንኳኑ ዞር ብሎ ሲመለከት፣ መገናኛ ድንኳኑን ደመና ሸፍኖት አየ፤ የይሖዋም ክብር ተገለጠ። |
ሙሴና አሮንም ወደ መገናኛ ድንኳኑ ፊት መጡ፤ |
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“በአንዴ እንዳጠፋቸው ራሳችሁን ከዚህ ማኅበረሰብ ለዩ።” እነሱም በዚህ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ። |
ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “የዕጣን ማጨሻ ውሰድና ከመሠዊያው ላይ እሳት አድርግበት፤ በላዩም ላይ ዕጣን ጨምርበት፤ ፈጥነህም ወደ ማኅበረሰቡ በመሄድ አስተሰርይላቸው፤ ምክንያቱም ይሖዋ ተቆጥቷል። መቅሰፍቱ ጀምሯል!” |
አሮን ልክ ሙሴ እንዳለው ወዲያውኑ የዕጣን ማጨሻውን ይዞ ወደ ጉባኤው መካከል እየሮጠ ገባ፤ መቅሰፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር። በመሆኑም ዕጣኑን በዕጣን ማጨሻው ላይ በማድረግ ለሕዝቡ ማስተሰረይ ጀመረ። |
እሱም በሞቱትና በሕይወት ባሉት መካከል ቆመ፤ መቅሰፍቱም ቀስ በቀስ ቆመ። |
በቆሬ ምክንያት የሞቱትን ሳይጨምር በመቅሰፍቱ የሞቱት ሰዎች ብዛት 14,700 ነበር። |
በመጨረሻም አሮን በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ ላይ ወደነበረው ወደ ሙሴ ሲመለስ መቅሰፍቱ ቆሞ ነበር። |
በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን የሥጋ ደዌ ያለበትን፣ ፈሳሽ የሚወጣውንና በሞተ ሰው የረከሰን ማንኛውንም ሰው ከሰፈሩ እንዲያስወጡ እዘዛቸው። |
ወንድም ሆነ ሴት አስወጧቸው። እኔ በመካከላቸው ስለምኖር ሕዝቤ የሚኖርባቸውን ሰፈሮች እንዳይበክሉ ከሰፈሩ አስወጧቸው።” |
በመሆኑም እስራኤላውያን እንደተባሉት አደረጉ፤ ሰዎቹንም ከሰፈሩ አስወጧቸው። እስራኤላውያን ልክ ይሖዋ ለሙሴ እንደነገረው አደረጉ። |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት የሰው ልጆች ከሚፈጽሟቸው ኃጢአቶች ውስጥ የትኛውንም ቢሠሩና በይሖዋ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ቢፈጽሙ ይህን ያደረገው ሰው በደለኛ ይሆናል። |
እሱም የሠራውን ኃጢአት መናዘዝና ለፈጸመው በደል ካሳ አድርጎ ሙሉ ዋጋውን መመለስ አለበት፤ የዚህን አንድ አምስተኛም ይጨምርበት፤ በደል ለፈጸመበትም ሰው ይስጠው። |
ሆኖም በደል የተፈጸመበት ሰው ቢሞትና ካሳውን የሚቀበልለት የቅርብ ዘመድ ባይኖረው ካህኑ የግለሰቡን በደል ከሚያስተሰርይበት አውራ በግ በስተቀር ካሳው ለይሖዋ ይመለስ፤ የካህኑም ይሆናል። |
“‘እስራኤላውያን ለካህኑ የሚያቀርቧቸው ቅዱስ መዋጮዎች በሙሉ የእሱ ይሆናሉ። |
እያንዳንዱ ሰው የሚያቀርባቸው ቅዱስ የሆኑ ነገሮች የእሱ ይሆናሉ። እያንዳንዱ ሰው ለካህኑ የሚሰጠው ማንኛውም ነገር የካህኑ ይሆናል።’” |
ይሖዋም ሙሴን እንዲህ አለው፦ |
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፦ ‘የአንድ ሰው ሚስት ከትክክለኛው መንገድ ዞር በማለት ለባሏ ታማኝ ሳትሆን ብትቀርና |
ሌላ ወንድ ከእሷ ጋር የፆታ ግንኙነት ቢፈጽም፣ ባሏ ግን ይህን ነገር ባያውቅና ጉዳዩ ተሰውሮ ቢቀር፣ ይህች ሴት በዚህ መንገድ ራሷን ብታረክስም የሚመሠክርባት ሰው ባይገኝና እጅ ከፍንጅ ባትያዝ፣ |
ባሏም ሚስቱ ራሷን አርክሳ ሳለ የቅናት መንፈስ ቢያድርበትና የሚስቱን ታማኝነት ቢጠራጠር ወይም ደግሞ ራሷን ሳታረክስ የቅናት መንፈስ ቢያድርበትና ታማኝነቷን ቢጠራጠር |
ሰውየው ሚስቱን ለእሷ ከሚቀርበው መባ ይኸውም ከአንድ አሥረኛ ኢፍ የገብስ ዱቄት ጋር ወደ ካህኑ ያምጣ። ይህ የቅናት የእህል መባ ይኸውም በደል እንዲታወስ የሚያደርግ የእህል መባ ስለሆነ በላዩ ላይ ዘይት አያፍስበት ወይም ነጭ ዕጣን አያድርግበት። |
“‘ካህኑ ሴትየዋን አምጥቶ ይሖዋ ፊት እንድትቆም ያደርጋል። |
ከዚያም ካህኑ የተቀደሰ ውኃ በሸክላ ዕቃ ይወስዳል፤ ከማደሪያ ድንኳኑም ወለል ላይ ጥቂት አፈር ወስዶ ውኃው ውስጥ ይጨምረዋል። |
ካህኑም ሴትየዋ በይሖዋ ፊት እንድትቆም ያደርጋል፤ ፀጉሯንም ይፈታል፤ ለመታሰቢያ የሚሆነውን የእህል መባ ይኸውም የቅናት የእህል መባውን በእጆቿ ላይ ያደርጋል፤ ካህኑም እርግማን የሚያመጣውን መራራ ውኃ በእጁ ይይዛል። |
“‘ካህኑም ሴትየዋን እንዲህ በማለት ያስምላታል፦ “በባልሽ ሥልጣን ሥር ሆነሽ ሳለ ሌላ ወንድ ከአንቺ ጋር የፆታ ግንኙነት ካልፈጸመ አንቺም ከትክክለኛው መንገድ ዞር ካላልሽና ካልረከስሽ እርግማን የሚያስከትለው ይህ ውኃ ምንም ጉዳት አያድርስብሽ። |
ይሁንና በባልሽ ሥልጣን ሥር ሆነሽ ሳለ ራስሽን በማርከስ ከትክክለኛው መንገድ ዞር ብለሽ ከሆነና ከሌላ ወንድ ጋር የፆታ ግንኙነት ፈጽመሽ ከሆነ . . . ” |
ካህኑም ሴትየዋን እርግማን ያለበት መሐላ ያስምላታል፤ እንዲህም ይላታል፦ “ይሖዋ ጭንሽ እንዲሰልና ሆድሽ እንዲያብጥ በማድረግ፣ ይሖዋ በሕዝብሽ መካከል የእርግማንና የመሐላ ምሳሌ ያድርግሽ። |
እርግማን የሚያመጣው ይህ ውኃ ወደ አንጀትሽ ገብቶ ሆድሽን ያሳብጠው፤ መሃንም ያድርግሽ።” በዚህ ጊዜ ሴትየዋ “አሜን! አሜን!” ትበል። |
“‘ከዚያም ካህኑ እነዚህን እርግማኖች በመጽሐፍ ይጻፋቸው፤ በመራራውም ውኃ አጥቦ ያጥፋቸው። |
እርግማን የሚያመጣውን መራራ ውኃም እንድትጠጣ ያድርግ፤ ውኃውም ወደ ሰውነቷ ገብቶ መራራ ሥቃይ ያስከትልባት። |
ካህኑም የቅናት የእህል መባውን ከሴትየዋ እጅ ላይ ወስዶ በይሖዋ ፊት ወዲያና ወዲህ ይወዝውዘው፤ ወደ መሠዊያውም ያምጣው። |
ካህኑም ከእህል መባው ላይ አንድ እፍኝ በመውሰድ የመባው መታሰቢያ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያጭሰው፤ ከዚያ በኋላ ሴትየዋ ውኃውን እንድትጠጣ ያድርግ። |
ውኃውን እንድትጠጣ በሚያደርግበትም ጊዜ ሴትየዋ ራሷን አርክሳና በባሏ ላይ ታማኝነት የጎደለው ድርጊት ፈጽማ ከሆነ እርግማን የሚያመጣው ውኃ ወደ ሰውነቷ ገብቶ መራራ ሥቃይ ያስከትልባታል፤ ሆዷም ያብጣል፤ ጭኗም ይሰልላል፤ እሷም በሕዝቧ መካከል የእርግማን ምሳሌ ትሆናለች። |
ይሁንና ሴትየዋ ራሷን ካላረከሰችና ንጹሕ ከሆነች እንዲህ ካለው ቅጣት ነፃ ትሆናለች፤ እንዲሁም መጸነስና ልጆች ማፍራት ትችላለች። |
“‘እንግዲህ ቅናትን በተመለከተ ሕጉ ይህ ነው፤ አንዲት ሴት በባሏ ሥልጣን ሥር ሆና ሳለ ከትክክለኛው መንገድ ዞር ብትልና ራሷን ብታረክስ |
ወይም አንድ ሰው የቅናት መንፈስ ቢያድርበትና የሚስቱን ታማኝነት ቢጠራጠር ሕጉ ይህ ነው፤ እሱም ሚስቱ በይሖዋ ፊት እንድትቆም ያድርግ፤ ካህኑም ይህ ሕግ በሙሉ በእሷ ላይ እንዲፈጸም ያድርግ። |
ሰውየው ከበደል ነፃ ይሆናል፤ ሚስቱ ግን ስለ በደሏ ትጠየቃለች።’” |
ከዚያም ማኅበረሰቡ ሁሉ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ፤ ሕዝቡም ሌሊቱን ሙሉ ሲጮኽና ሲያለቅስ አደረ። |
እስራኤላውያንም በሙሉ በሙሴና በአሮን ላይ ያጉረመርሙ ጀመር፤ መላው ማኅበረሰብ እንዲህ አላቸው፦ “ምነው በግብፅ ምድር ሳለን ሞተን ባረፍነው፤ ወይም ምናለ በዚህ ምድረ በዳ በሞትን! |
ይሖዋ በሰይፍ እንድንሞት ወደዚህ ምድር ያመጣን ለምንድን ነው? እንግዲህ ሚስቶቻችንና ልጆቻችን ይማረካሉ። ታዲያ ወደ ግብፅ ብንመለስ አይሻለንም?” |
እንዲያውም እርስ በርሳቸው “መሪ እንሹምና ወደ ግብፅ እንመለስ” ይባባሉ ጀመር። |
በዚህ ጊዜ ሙሴና አሮን በተሰበሰበው በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ። |
ምድሩን ከሰለሉት ሰዎች መካከል የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የየፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤ |
ለመላው የእስራኤል ማኅበረሰብም እንዲህ አሉ፦ “ተዘዋውረን የሰለልናት ምድር እጅግ በጣም ጥሩ ምድር ናት። |
ይሖዋ በእኛ ከተደሰተ ወተትና ማር ወደምታፈሰው ወደዚህች ምድር በእርግጥ ያስገባናል፤ ደግሞም ይህችን ምድር ይሰጠናል። |
ብቻ እናንተ በይሖዋ ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ ስለምንጎርሳቸው የምድሪቱን ሕዝቦች አትፍሯቸው። ጥላቸው ተገፏል፤ ደግሞም ይሖዋ ከእኛ ጋር ነው። ፈጽሞ አትፍሯቸው።” |
ይሁን እንጂ መላው ማኅበረሰብ በድንጋይ ሊወግራቸው ተማከረ። ሆኖም የይሖዋ ክብር በመገናኛ ድንኳኑ ላይ ለመላው የእስራኤል ሕዝብ ተገለጠ። |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ የሚንቀኝ እስከ መቼ ነው? በመካከላቸው ይህን ሁሉ ተአምራዊ ምልክት እያሳየሁ የማያምኑብኝስ እስከ መቼ ነው? |
እንግዲህ በቸነፈር እመታቸዋለሁ፤ ደግሞም እደመስሳቸዋለሁ፤ አንተን ግን ከእነሱ ይልቅ ታላቅና ኃያል ብሔር አደርግሃለሁ።” |
ሙሴ ግን ይሖዋን እንዲህ አለው፦ “እንዲህ ካደረግክ ይህን ሕዝብ በኃይልህ ከመካከላቸው ስታወጣ ያዩ ግብፃውያን መስማታቸው አይቀርም፤ |
እነሱ ደግሞ የሰሙትን ነገር ለዚህ ምድር ነዋሪዎች ይናገራሉ። እነሱም ቢሆኑ አንተ ይሖዋ በዚህ ሕዝብ መካከል እንዳለህና ፊት ለፊት እንደተገለጥክላቸው ሰምተዋል። አንተ ይሖዋ ነህ፤ ደመናህም በላያቸው ላይ ቆሟል፤ ቀን ቀን በደመና ዓምድ፣ ሌሊት ሌሊት ደግሞ በእሳት ዓምድ ከፊት ከፊታቸው ትሄዳለህ። |
እንግዲህ ይህን ሕዝብ በሙሉ በአንዴ ብትፈጀው የአንተን ዝና የሰሙ ብሔራት እንዲህ ማለታቸው አይቀርም፦ |
‘ይሖዋ ይህን ሕዝብ፣ ሊሰጠው ወደማለለት ምድር ሊያስገባው ስላልቻለ በምድረ በዳ ፈጀው።’ |
አሁንም እባክህ ይሖዋ እንዲህ በማለት ቃል በገባኸው መሠረት ኃይልህ ታላቅ ይሁን፦ |
‘ይሖዋ ለቁጣ የዘገየ፣ ታማኝ ፍቅሩ የበዛ፣ ስህተትንና መተላለፍን ይቅር የሚል፣ በደለኛውን ግን በምንም ዓይነት ሳይቀጣ የማያልፍ እንዲሁም አባቶች ለሠሩት ስህተት በልጆች፣ በሦስተኛና በአራተኛ ትውልድ ላይ ቅጣትን የሚያመጣ ነው።’ |
ይህን ሕዝብ ከግብፅ አንስቶ እስካሁን ድረስ ይቅር ስትለው እንደቆየህ ሁሉ አሁንም እባክህ፣ የዚህን ሕዝብ ስህተት ታላቅ በሆነው ታማኝ ፍቅርህ ይቅር በል።” |
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለ፦ “ባልከኝ መሠረት ይቅር እላቸዋለሁ። |
በሌላ በኩል ግን በሕያውነቴ እምላለሁ፣ መላዋ ምድር በይሖዋ ክብር ትሞላለች። |
ይሁን እንጂ ክብሬንና በግብፅም ሆነ በምድረ በዳ የፈጸምኳቸውን ተአምራዊ ምልክቶች የተመለከቱት ሆኖም አሥር ጊዜ የተፈታተኑኝና ቃሌን ያልሰሙት ሰዎች አንዳቸውም ቢሆኑ |
ለአባቶቻቸው የማልኩላቸውን ምድር ፈጽሞ አያዩም። አዎ፣ የናቁኝ ሰዎች አንዳቸውም ቢሆኑ ያን ምድር አያዩም። |
አገልጋዬ ካሌብ ግን የተለየ መንፈስ እንዳለው ስላሳየና በሙሉ ልቡ ስለተከተለኝ ሄዶባት ወደነበረው ምድር በእርግጥ አስገባዋለሁ፤ ዘሮቹም ያቺን ምድር ይወርሳሉ። |
አማሌቃውያንና ከነአናውያን በሸለቆው ውስጥ ስለሚኖሩ በነገው ዕለት ተመልሳችሁ በቀይ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳው ሂዱ።” |
ከዚያም ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ |
“ይህ ክፉ ማኅበረሰብ በእኔ ላይ እንዲህ የሚያጉረመርመው እስከ መቼ ነው? እስራኤላውያን በእኔ ላይ የሚያጉረመርሙትን ሰምቻለሁ። |
እንዲህ በሏቸው፦ ‘“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ይሖዋ፤ “እናንተው ራሳችሁ ስትናገሩ የሰማሁትን ነገር አደርግባችኋለሁ! |
ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኗችሁ የተመዘገባችሁትና የተቆጠራችሁት ሁሉ አዎ፣ በእኔ ላይ ያጉረመረማችሁት ሁሉ ሬሳችሁ በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል። |
ከየፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በስተቀር አንዳችሁም ብትሆኑ በዚያ እንደማኖራችሁ ወደማልኩላችሁ ምድር አትገቡም። |
“‘“ለምርኮ ይዳረጋሉ ያላችኋቸውን ልጆቻችሁን ግን አስገባቸዋለሁ፤ እናንተ የናቃችኋትንም ምድር በሚገባ ያውቋታል። |
የእናንተ ሬሳ ግን በዚህ ምድረ በዳ ይወድቃል። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.