text stringlengths 4 267 |
|---|
አምላክህ ይሖዋ በአባቶችህ ደስ እንደተሰኘ ሁሉ ይሖዋ አንተንም በማበልጸግ ስለሚደሰት የሆድህን ፍሬ፣ እንስሶችህንና የምድርህን ፍሬ በማብዛት በእጅህ ሥራ ሁሉ እጅግ እንድትበለጽግ ያደርግሃል። |
ይህም የሚሆነው የአምላክህን የይሖዋን ቃል ስለምትሰማ፣ በዚህ የሕግ መጽሐፍ የተጻፉትን ትእዛዛቱንና ደንቦቹን ስለምትጠብቅ እንዲሁም በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ስለምትመለስ ነው። |
“እኔ ዛሬ የማዝህ ይህ ትእዛዝ ለአንተ ያን ያህል ከባድ አይደለም፤ ከአንተም የራቀ አይደለም። |
‘ሰምተን እንድንፈጽመው ወደ ሰማይ ወጥቶ ማን ያምጣልን?’ እንዳትል ትእዛዙ ያለው በሰማይ አይደለም። |
ደግሞም ‘ሰምተን እንድንፈጽመው ባሕሩን ተሻግሮ ማን ያምጣልን?’ እንዳትል ትእዛዙ ያለው ከባሕሩ ማዶ አይደለም። |
ቃሉ ትፈጽመው ዘንድ ለአንተ በጣም ቅርብ ነውና፤ ደግሞም በአፍህና በልብህ ውስጥ ነው። |
“እንግዲህ እኔ ዛሬ ሕይወትንና መልካም ነገርን እንዲሁም ሞትንና መጥፎ ነገርን በፊትህ አስቀምጫለሁ። |
አምላክህን ይሖዋን በመውደድ፣ በመንገዶቹ በመሄድ እንዲሁም ትእዛዛቱን፣ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን በመጠበቅ እኔ ዛሬ የማዝህን የአምላክህን የይሖዋን ትእዛዛት ብትሰማ በሕይወት ትኖራለህ፤ ደግሞም ትበዛለህ፤ አምላክህ ይሖዋም በምትወርሳት ምድር ውስጥ ይባርክሃል። |
“ሆኖም ልብህ ቢሸፍትና ለመስማት ፈቃደኛ ባትሆን እንዲሁም ተታለህ ለሌሎች አማልክት ብትሰግድና ብታገለግላቸው |
በእርግጥ እንደምትጠፉ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ። ደግሞም ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር ላይ ዕድሜያችሁ ያጥራል። |
ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና እርግማንን በፊታችሁ እንዳስቀመጥኩ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምሥክሮች አድርጌ እጠራባችኋለሁ፤ እንግዲህ አንተም ሆንክ ዘሮችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤ |
ይህን የምታደርገው አምላክህን ይሖዋን በመውደድ፣ ቃሉን በመስማትና ከእሱ ጋር በመጣበቅ ነው፤ ምክንያቱም እሱ ሕይወትህ ነው፤ ይሖዋ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በማለላቸው ምድር ረጅም ዕድሜ የምትኖረውም በእሱ ነው።” |
“እስራኤል ሆይ፣ ስማ፤ እንግዲህ ዛሬ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ኃያል የሆኑ ብሔራትን እንዲሁም ታላላቅና እስከ ሰማያት የሚደርስ ቅጥር ያላቸውን ከተሞች በማስለቀቅ ወደ ምድሪቱ ለመግባት ዮርዳኖስን ልትሻገር ነው፤ |
‘የኤናቅን ልጆች ማን ሊቋቋማቸው ይችላል?’ ሲባልላቸው የሰማኸውን፣ አንተ ራስህ የምታውቃቸውን ታላቅ ሕዝብና ቁመተ ረጃጅም የሆኑትን የኤናቅን ልጆችም ልታስለቅቅ ነው። |
ስለሆነም አምላክህ ይሖዋ ዛሬ ከአንተ ቀድሞ እንደሚሻገር እወቅ። እሱ የሚባላ እሳት ነው፤ ደግሞም ያጠፋቸዋል። ልክ ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት በፍጥነት ታባርራቸውና ታጠፋቸው ዘንድ ዓይንህ እያየ ድል ያደርጋቸዋል። |
“አምላክህ ይሖዋ እነሱን ከፊትህ በሚያባርራቸው ጊዜ በልብህ ‘ይሖዋ ይህችን ምድር እንድወርስ ወደዚህ ያመጣኝ እኮ በራሴ ጽድቅ ነው’ አትበል፤ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት ከፊትህ የሚያባርራቸው በራሳቸው ክፋት የተነሳ ነው። |
የእነሱን ምድር ገብተህ የምትወርሰው ከጽድቅህ ወይም ከልብህ ቅንነት የተነሳ አይደለም። ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ እነዚህን ብሔራት ከፊትህ የሚያባርራቸው ከራሳቸው ክፋት የተነሳ ነው፤ እንዲሁም ይሖዋ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የማለላቸውን ቃል ለመፈጸም ሲል ነው። |
ስለዚህ አምላክህ ይሖዋ ይህችን መልካም ምድር እንድትወርሳት የሚሰጥህ ከጽድቅህ የተነሳ እንዳልሆነ እወቅ፤ ምክንያቱም አንተ ግትር ሕዝብ ነህ። |
“በምድረ በዳ አምላክህን ይሖዋን እንዴት እንዳስቆጣኸው አስታውስ፤ ፈጽሞም አትርሳ። ከግብፅ ምድር ከወጣችሁበት ጊዜ አንስቶ እዚህ ቦታ እስክትደርሱ ድረስ በይሖዋ ላይ ዓምፃችኋል። |
በኮሬብም እንኳ ይሖዋን አስቆጥታችሁት ነበር፤ ይሖዋም በእናንተ ላይ እጅግ ከመቆጣቱ የተነሳ እናንተን ለማጥፋት አስቦ ነበር። |
እኔም የድንጋይ ጽላቶቹን ይኸውም ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን የተጻፈባቸውን ጽላቶች ለመቀበል ወደ ተራራው በወጣሁ ጊዜ እህል ሳልበላና ውኃ ሳልጠጣ በተራራው ላይ 40 ቀንና 40 ሌሊት ቆይቼ ነበር። |
ከዚያም ይሖዋ በአምላክ ጣት የተጻፈባቸውን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች ሰጠኝ፤ በእነሱም ላይ ይሖዋ እዚያ ተሰብስባችሁ በነበረበት ቀን በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ የነገራችሁ ነገር ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር። |
ከ40 ቀንና ከ40 ሌሊት በኋላ ይሖዋ ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች ይኸውም የቃል ኪዳኑን ጽላቶች ሰጠኝ፤ |
ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ ‘ተነስ፤ ቶሎ ብለህ ውረድ፤ ምክንያቱም ከግብፅ ያወጣኸው ሕዝብህ የጥፋት ጎዳና እየተከተለ ነው። እንዲከተሉት ካዘዝኳቸው መንገድ ፈጥነው ዞር ብለዋል። ከብረት የተሠራ ምስልም ለራሳቸው አበጅተዋል።’ |
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ይህን ሕዝብ አይቼዋለሁ፤ በእርግጥም ግትር ሕዝብ ነው። |
አጠፋቸውና ስማቸውን ከሰማይ በታች እደመስሰው ዘንድ ተወኝ፤ አንተን ግን ከእነሱ ይልቅ ኃያልና ብዙ ሕዝብ ያቀፈ ብሔር አደርግሃለሁ።’ |
“እኔም ተራራው በእሳት እየተቀጣጠለ እያለ ተመልሼ ከተራራው ወረድኩ፤ ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶችም በእጆቼ ይዤ ነበር። |
ከዚያም ስመለከት በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እንደፈጸማችሁ አየሁ! ለራሳችሁም የብረት ጥጃ ሠርታችሁ ነበር። ይሖዋ እንድትከተሉት ካዘዛችሁ መንገድ ፈጥናችሁ ዞር ብላችሁ ነበር። |
ስለዚህ ሁለቱን ጽላቶች አሽቀንጥሬ በመወርወር ዓይናችሁ እያየ ሰባበርኳቸው። |
ከዚያም እንደ መጀመሪያው ጊዜ ሁሉ ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት በይሖዋ ፊት ተደፋሁ። በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር በማድረግና እሱን በማስቆጣት በፈጸማችሁት ኃጢአት ሁሉ የተነሳ እህል አልቀመስኩም፤ ውኃም አልጠጣሁም። |
ምክንያቱም ይሖዋ በእናንተ ላይ እጅግ ከመቆጣቱ የተነሳ ሊያጠፋችሁ ስለተዘጋጀ ፈርቼ ነበር። ይሁንና ይሖዋ በዚያን ጊዜም ሰማኝ። |
“ይሖዋ አሮንን ለማጥፋት እስኪያስብ ድረስ በእሱ ላይ ተቆጥቶ ነበር፤ ሆኖም በዚያን ጊዜ ስለ አሮንም ምልጃ አቀረብኩ። |
ከዚያም የኃጢአት ሥራችሁን ይኸውም ጥጃውን ወስጄ በእሳት አቃጠልኩት፤ ሰባበርኩት፤ እንደ አቧራ ብናኝ እስኪሆንም ድረስ ፈጨሁት፤ ብናኙንም ከተራራው በሚወርደው ጅረት ውስጥ በተንኩት። |
“በተጨማሪም በታበራ፣ በማሳህ እና በቂብሮትሃታባ ይሖዋን አስቆጣችሁት። |
ይሖዋ ከቃዴስበርኔ በላካችሁና ‘ውጡ፤ የምሰጣችሁንም ምድር ውረሱ!’ ባላችሁ ጊዜ በአምላካችሁ በይሖዋ ትእዛዝ ላይ በድጋሚ ዓመፃችሁ፤ በእሱ አልታመናችሁም፤ እንዲሁም አልታዘዛችሁትም። |
እኔ እናንተን ካወቅኩበት ጊዜ አንስቶ በይሖዋ ላይ እንዳመፃችሁ ነው። |
“በመሆኑም 40 ቀንና 40 ሌሊት በይሖዋ ፊት ተደፋሁ፤ እንዲህ በፊቱ የተደፋሁት፣ ይሖዋ እንደሚያጠፋችሁ ተናግሮ ስለነበር ነው። |
ከዚያም እንዲህ በማለት ይሖዋን መማጸን ጀመርኩ፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ሕዝብህን አታጥፋ። እነሱ በታላቅነትህ የታደግካቸውና በኃያል ክንድህ ከግብፅ ያወጣሃቸው የግል ንብረቶችህ ናቸው። |
አገልጋዮችህን አብርሃምን፣ ይስሐቅንና ያዕቆብን አስብ። የዚህን ሕዝብ ግትርነት፣ ክፋትና ኃጢአት አትመልከት። |
አለዚያ እኛን ባወጣህበት ምድር የሚገኙ ሰዎች “ይሖዋ ቃል ወደገባላቸው ምድር ሊያስገባቸው ስላልቻለና ስለጠላቸው በምድረ በዳ ሊገድላቸው አወጣቸው” ሊሉ ይችላሉ። |
እነሱ በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋ ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዝቦችህና የግል ንብረቶችህ ናቸው።’ |
“አንድ ሰው አንዲት ሴት ቢያገባ ሆኖም ነውር የሆነ ነገር አግኝቶባት ቅር ቢሰኝ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ያሰናብታት። |
እሷም ከእሱ ቤት ከወጣች በኋላ የሌላ ሰው ሚስት መሆን ትችላለች። |
በኋላ ያገባትም ሰው ቢጠላትና የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ቢያሰናብታት ወይም አግብቷት የነበረው ሁለተኛው ሰው ቢሞት |
ከቤቱ አሰናብቷት የነበረው የመጀመሪያው ባለቤቷ ከረከሰች በኋላ እንደገና ሚስቱ አድርጎ እንዲወስዳት አይፈቀድለትም፤ ምክንያቱም ይህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው። አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጣ። |
“አንድ ሰው አዲስ ሙሽራ ከሆነ በሠራዊቱ ውስጥ ማገልገል የለበትም፤ ወይም ምንም ዓይነት ሌላ ሥራ ሊሰጠው አይገባም። ለአንድ ዓመት ያህል ከምንም ነገር ነፃ ሆኖ ይቆይ፤ በቤቱም ተቀምጦ ሚስቱን ያስደስታት። |
“ማንም ሰው ወፍጮን ወይም መጅን የብድር መያዣ አድርጎ መውሰድ የለበትም፤ ምክንያቱም የሰውየውን መተዳደሪያ መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆንበታል። |
“አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ መካከል አንዱን አፍኖ በመውሰድ በደል ሲፈጽምበትና ሲሸጠው ቢገኝ አፍኖ የወሰደው ሰው ይገደል። ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ። |
“የሥጋ ደዌ ቢከሰት ሌዋውያን ካህናት የሚሰጧችሁን መመሪያዎች ሁሉ በጥንቃቄ ተከተሉ። እኔ የሰጠኋቸውንም ትእዛዝ በጥንቃቄ ፈጽሙ። |
ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ መንገድ ላይ ሳላችሁ አምላካችሁ ይሖዋ በሚርያም ላይ ያደረገውን አስታውሱ። |
“ለባልንጀራህ ማንኛውንም ነገር ብታበድር መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ነገር ለመውሰድ ወደ ቤቱ አትግባ። |
ውጭ ቆመህ ጠብቅ፤ ያበደርከውም ሰው መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ነገር ውጭ ድረስ ያምጣልህ። |
ሰውየው ከተቸገረ መያዣ አድርጎ የሰጠህን ነገር አንተ ጋ አታሳድር። |
ልክ ፀሐይ ስትጠልቅ መያዣውን ልትመልስለት ይገባል፤ እሱም ለብሶት ይተኛል፤ ደግሞም ይባርክሃል፤ በአምላክህም በይሖዋ ፊት እንደ ጽድቅ ይቆጠርልሃል። |
“ከወንድሞችህም ሆነ በምድርህ ይኸውም በከተሞችህ ውስጥ ከሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች መካከል የተቸገረውንና ድሃ የሆነውን ቅጥር ሠራተኛ አታታል። |
ደሞዙን በዕለቱ ስጠው፤ ችግረኛ በመሆኑና ሕይወቱ የተመካው በደሞዙ ላይ ስለሆነ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ስጠው። አለዚያ በአንተ የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻል፤ አንተም በኃጢአት ትጠየቃለህ። |
“አባቶች ልጆቻቸው በሠሩት ነገር መገደል የለባቸውም፤ ልጆችም አባቶቻቸው በሠሩት ነገር መገደል የለባቸውም። አንድ ሰው መገደል ያለበት በገዛ ኃጢአቱ ብቻ ነው። |
“የባዕድ አገሩን ሰው ወይም አባት የሌለውን ልጅ ፍርድ አታዛባ፤ የመበለቲቱን ልብስ የብድር መያዣ አድርገህ አትውሰድ። |
አንተም በግብፅ ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ ከዚያ እንደተቤዠህ አስታውስ። እኔም ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው። |
“በማሳህ ላይ ያለውን እህል በምታጭድበት ጊዜ በማሳው ላይ ነዶ ብትረሳ ያን ለመውሰድ አትመለስ። አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ እንዲሆን እዚያው ተወው። |
“የወይራ ዛፍህን በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉ ላይ የቀረውን ሙልጭ አድርገህ አታራግፈው። የቀረው ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ ይሁን። |
“ከወይን እርሻህ ላይ የወይን ፍሬህን በምትሰበስብበት ጊዜ ተመልሰህ ቃርሚያውን አትልቀም። ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ መተው አለበት። |
አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክ አስታውስ። እኔም ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው። |
ከዚያም ሙሴ ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር በመሆን ሕዝቡን እንዲህ ሲል አዘዘ፦ “እኔ ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዛት በሙሉ ጠብቁ። |
አምላካችሁ ይሖዋ ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በምትሻገሩበት ቀን ትላልቅ ድንጋዮችን አቁማችሁ ለስኗቸው። |
ከዚያም የአባቶችህ አምላክ ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት አምላክህ ይሖዋ ወደሚሰጥህ ምድር ይኸውም ወተትና ማር ወደምታፈሰው ምድር ለመግባት በምትሻገርበት ጊዜ የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ ጻፍባቸው። |
ዮርዳኖስን ስትሻገሩ ዛሬ በሰጠኋችሁ ትእዛዝ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በኤባል ተራራ ላይ አቁሟቸው፤ ደግሞም ለስኗቸው። |
በዚያም ለአምላክህ ለይሖዋ መሠዊያ ይኸውም የድንጋይ መሠዊያ ሥራ። ድንጋዮቹንም የብረት መሣሪያ አታስነካቸው። |
የአምላክህን የይሖዋን መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ ሥራ፤ በላዩም ላይ ለአምላክህ ለይሖዋ የሚቃጠሉ መባዎችን አቅርብ። |
የኅብረት መሥዋዕቶችንም አቅርብ፤ መሥዋዕቶቹንም እዚያው ብላቸው፤ አንተም በአምላክህ በይሖዋ ፊት ደስ ይልሃል። |
በድንጋዮቹም ላይ የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በግልጽ ጻፍባቸው።” |
ከዚያም ሙሴና ሌዋውያኑ ካህናት እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ አሏቸው፦ “እስራኤል ሆይ፣ ጸጥ ብለህ አዳምጥ። በዛሬው ቀን አንተ የአምላክህ የይሖዋ ሕዝብ ሆነሃል። |
የአምላክህን የይሖዋን ቃል ስማ፤ እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ትእዛዛትና ሥርዓቶች ፈጽም።” |
ሙሴም በዚያ ቀን ሕዝቡን እንዲህ ሲል አዘዘ፦ |
“ዮርዳኖስን በምትሻገሩበት ጊዜ በገሪዛን ተራራ ላይ ቆመው ሕዝቡን የሚባርኩት ነገዶች ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዮሴፍ እና ቢንያም ናቸው። |
እርግማኑን ለማሰማት በኤባል ተራራ ላይ የሚቆሙት ደግሞ ሮቤል፣ ጋድ፣ አሴር፣ ዛብሎን፣ ዳን እና ንፍታሌም ናቸው። |
ሌዋውያኑም ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ለእያንዳንዱ እስራኤላዊ እንዲህ ብለው ይናገራሉ፦ |
“‘ይሖዋ የሚጠላውን አስጸያፊ ነገር ይኸውም የአንድ የእጅ ጥበብ ባለሙያ የእጅ ሥራ ውጤት የሆነውን የተቀረጸ ምስል ወይም ከብረት የተሠራ ሐውልት የሚሠራና በስውር የሚያስቀምጥ ሰው የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ብሎ ይመልሳል።) |
“‘አባቱን ወይም እናቱን የሚንቅ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) |
“‘የጎረቤቱን የወሰን ምልክት የሚገፋ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) |
“‘ዓይነ ስውሩን መንገድ የሚያሳስት የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) |
“‘የባዕድ አገሩን ሰው፣ አባት የሌለውን ልጅ ወይም የመበለቲቱን ፍርድ የሚያዛባ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) |
“‘ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ አባቱን ስላዋረደ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) |
“‘ከማንኛውም ዓይነት እንስሳ ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) |
“‘የአባቱ ልጅ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው ከእህቱ ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) |
“‘ከሚስቱ እናት ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) |
“‘ጎረቤቱን አድብቶ በመጠበቅ የሚገድል የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) |
“‘ንጹሑን ሰው ለመግደል ሲል ጉቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) |
“‘የዚህን ሕግ ቃል ተግባራዊ በማድረግ የማይጠብቅ ሰው የተረገመ ይሁን።’ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) |
ከዚያም ልክ ይሖዋ በነገረኝ መሠረት ተመልሰን ወደ ቀይ ባሕር የሚወስደውን መንገድ በመከተል ወደ ምድረ በዳው ተጓዝን፤ በሴይር ተራራ አካባቢም ለብዙ ቀናት ተንከራተትን። |
በመጨረሻም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ |
‘እንግዲህ በዚህ ተራራ አካባቢ ብዙ ተንከራታችኋል። አሁን ወደ ሰሜን አቅኑ። |
ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዝ፦ “እንግዲህ በሴይር በሚኖሩት በወንድሞቻችሁ በኤሳው ዘሮች ድንበር አልፋችሁ ልትሄዱ ነው፤ እነሱም ይፈሯችኋል፤ ቢሆንም ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ። |
ከምድራቸው ላይ የእግር መርገጫ የምታክል መሬት እንኳ ስለማልሰጣችሁ ከእነሱ ጋር እንዳትጣሉ፤ ምክንያቱም የሴይርን ተራራ ለኤሳው ርስት አድርጌ ሰጥቼዋለሁ። |
ለምትበሉት ምግብም ሆነ ለምትጠጡት ውኃ ገንዘብ ክፈሏቸው። |
አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና። በዚህ ጭልጥ ያለ ምድረ በዳ እንደተጓዝክ በሚገባ ያውቃል። በእነዚህ 40 ዓመታት አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ስለነበር ምንም የጎደለብህ ነገር የለም።”’ |
ስለዚህ በሴይር በሚኖሩት ወንድሞቻችን በኤሳው ዘሮች በኩል አልፈን ሄድን፤ ወደ አረባ ከሚወስደው መንገድ፣ ከኤላት እና ከዔጽዮንጋብር ርቀን ተጓዝን። “በመቀጠልም ተነስተን ወደ ሞዓብ ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ተጓዝን። |
ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ከሞዓብ ምድር የትኛውንም መሬት ርስት አድርጌ ስለማልሰጥህ ከእሱ ጋር አትጣላ ወይም ጦርነት አትግጠም፤ ምክንያቱም ኤርን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ። |
(ታላቅና ብዙ እንዲሁም ልክ እንደ ኤናቃውያን ቁመተ ረጃጅም የሆኑት ኤሚማውያን ቀደም ሲል በዚያ ይኖሩ ነበር። |
ረፋይማውያንም ልክ እንደ ኤናቃውያን ይቆጠሩ ነበር፤ ሞዓባውያንም ኤሚማውያን ብለው ይጠሯቸው ነበር። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.