text stringlengths 4 267 |
|---|
ሆራውያን ቀደም ሲል በሴይር ይኖሩ ነበር፤ እስራኤላውያን ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጣቸው ምድር ላይ እንደሚያደርጉት ሁሉ የኤሳውም ዘሮች ሆራውያንን በማስለቀቅና በማጥፋት በምድራቸው ላይ መኖር ጀመሩ።) |
በሉ አሁን ተነሱና የዘረድን ሸለቆ አቋርጣችሁ ሂዱ።’ ስለዚህ የዘረድን ሸለቆ አቋርጠን ሄድን። |
ከቃዴስበርኔ ተነስተን የዘረድን ሸለቆ እስክናቋርጥ ድረስ 38 ዓመት ፈጅቶብናል፤ በዚህ ጊዜም ይሖዋ ለእነሱ በማለላቸው መሠረት ለጦርነት ብቁ የሆነው ትውልድ በሙሉ ከሕዝቡ መካከል አለቀ። |
ሙሉ በሙሉ እስኪጠፉም ድረስ የይሖዋ እጅ ከሕዝቡ መካከል ሊያጠፋቸው በእነሱ ላይ ነበር። |
“ለጦርነት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ሞተው እንዳለቁ |
ይሖዋ በድጋሚ እንዲህ አለኝ፦ |
‘ዛሬ በሞዓብ ክልል ይኸውም በኤር በኩል ታልፋለህ። |
ወደ አሞናውያን በቀረብክ ጊዜ እነሱን አታስቆጣቸው ወይም አትተናኮላቸው፤ ምክንያቱም ምድሪቱን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ስለሰጠኋቸው ከአሞን ልጆች ምድር የትኛውንም መሬት ርስት አድርጌ አልሰጥህም። |
ይህችም ምድር የረፋይማውያን ምድር ተደርጋ ትቆጠር ነበር። (ቀደም ሲል ረፋይማውያን በዚያ ይኖሩ ነበር፤ አሞናውያንም ዛምዙሚማውያን ብለው ይጠሯቸው ነበር። |
እነሱም ታላቅና ቁጥራቸው የበዛ እንዲሁም ልክ እንደ ኤናቃውያን ቁመተ ረጃጅሞች ነበሩ፤ ይሖዋ ግን ከአሞናውያን ፊት አጠፋቸው፤ እነሱም ምድራቸውን አስለቅቀው በዚያ ሰፈሩ። |
አሁን በሴይር ለሚኖሩት የኤሳው ዘሮች ሆራውያንን ከፊታቸው ባጠፋላቸው ጊዜ ያደረገላቸው ይህንኑ ነበር፤ በዚህም የተነሳ የኤሳው ዘሮች እነሱን አስለቅቀው እስከ ዛሬ ድረስ በምድራቸው ላይ እየኖሩ ነው። |
አዊማውያን ደግሞ ከካፍቶር የተገኙት ካፍቶሪማውያን እነሱን አጥፍተው በምድራቸው ላይ መኖር እስከጀመሩበት ጊዜ ድረስ እስከ ጋዛ በሚገኙት መንደሮች ይኖሩ ነበር።) |
“‘ተነሱና የአርኖንን ሸለቆ አቋርጣችሁ ሂዱ። ይኸው የሃሽቦንን ንጉሥ አሞራዊውን ሲሖንን በእጃችሁ ሰጥቻችኋለሁ። በመሆኑም ምድሩን መውረስ ጀምሩ፤ ከእሱም ጋር ጦርነት ግጠሙ። |
በዚህች ዕለት፣ ስለ እናንተ የሰሙ ከሰማይ በታች ያሉ ሕዝቦች ሁሉ እንዲሸበሩና በፍርሃት እንዲርዱ አደርጋለሁ። በእናንተም የተነሳ ይታወካሉ፤ ምጥም ይይዛቸዋል።’ |
“ከዚያም እኔ ከቀደሞት ምድረ በዳ ለሃሽቦን ንጉሥ ለሲሖን እንዲህ የሚል የሰላም መልእክት እንዲነግሩት መልእክተኞችን ላክሁበት፦ |
‘ምድርህን አቋርጬ እንዳልፍ ፍቀድልኝ። ከመንገዱ አልወጣም፤ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አልልም። |
በገንዘብ የምትሸጥልኝን ምግብ ብቻ እበላለሁ፤ በገንዘብ የምትሰጠኝንም ውኃ ብቻ እጠጣለሁ። ምድሩን ረግጬ እንዳልፍ ብቻ ፍቀድልኝ፤ |
አምላካችን ይሖዋ ወደሚሰጠን ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ በሴይር የሚኖሩት የኤሳው ዘሮችና በኤር የሚኖሩት ሞዓባውያን እንዲሁ አድርገውልኛል።’ |
የሃሽቦን ንጉሥ ሲሖን ግን በእሱ በኩል አቋርጠን እንድናልፍ አልፈቀደልንም፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሐሳበ ግትር እንዲሆንና ልቡ እንዲደነድን ፈቅዶ ነበር፤ ይህን ያደረገው ይኸው ዛሬ እንደምታዩት እጃችሁ ላይ እንዲወድቅ ነው። |
“ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እነሆ ሲሖንን እና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ። እንግዲህ ምድሩን ለመውረስ ተነስ።’ |
ሲሖንም ከመላው ሕዝቡ ጋር በመሆን ያሃጽ ላይ እኛን ለመውጋት በወጣ ጊዜ |
አምላካችን ይሖዋ በእጃችን አሳልፎ ሰጠው፤ ስለዚህ እሱንም ሆነ ልጆቹን እንዲሁም ሕዝቡን በሙሉ ድል አደረግናቸው። |
በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን ጨምሮ እያንዳንዱን ከተማ ሙሉ በሙሉ አጠፋን። ማንንም በሕይወት አላስተረፍንም። |
ለራሳችን ማርከን የወሰድነው እንስሶችንና በያዝናቸው ከተሞች ውስጥ ያገኘነውን ንብረት ብቻ ነው። |
በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ካለችው ከአሮዔር (በሸለቆው ውስጥ የምትገኘውን ከተማ ጨምሮ) እስከ ጊልያድ ድረስ ከእጃችን ያመለጠ አንድም ከተማ አልነበረም። አምላካችን ይሖዋ ሁሉንም በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶን ነበር። |
ሆኖም ወደ አሞናውያን ምድር፣ ወደ ያቦቅ ሸለቆ ዳርቻ ሁሉና በተራራማው አካባቢ ወደሚገኙት ከተሞች ወይም አምላካችን ይሖዋ ወደከለከለን ወደ ሌላ ማንኛውም ቦታ አልቀረባችሁም። |
“በዚያን ጊዜ ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፤ የእንጨት ታቦትም ለራስህ ሥራ። |
እኔም በጽላቶቹ ላይ አንተ በሰበርካቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፋለሁ፤ አንተም ጽላቶቹን በታቦቱ ውስጥ አስቀምጣቸው።’ |
ስለዚህ ከግራር እንጨት ታቦት ሠራሁ፤ ከዚያም እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ የድንጋይ ጽላቶችን ከቀረጽኩ በኋላ ሁለቱን ጽላቶች ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ። |
እሱም በጽላቶቹ ላይ ቀደም ሲል ጽፏቸው የነበሩትን ቃላት ይኸውም ተሰብስባችሁ በነበረበት ቀን ይሖዋ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ለእናንተ ነግሯችሁ የነበሩትን አሥርቱን ትእዛዛት ጻፈባቸው፤ ይሖዋም ጽላቶቹን ለእኔ ሰጠኝ። |
እኔም ተመልሼ ከተራራው ወረድኩ፤ ይሖዋም ባዘዘኝ መሠረት ጽላቶቹን፣ በሠራሁት ታቦት ውስጥ አስቀመጥኳቸው። እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ ይገኛሉ። |
“ከዚያም እስራኤላውያን ከበኤሮት ብኔያዕቃን ተነስተው ወደ ሞሴራ ሄዱ። አሮንም በዚያ ቦታ ሞቶ ተቀበረ፤ ልጁ አልዓዛርም በእሱ ምትክ ካህን ሆኖ ማገልገል ጀመረ። |
ከዚያም ተነስተው ወደ ጉድጎዳ ተጓዙ፤ ከጉድጎዳም ተነስተው ጅረቶች ወደሚፈስሱባት ምድር ወደ ዮጥባታ ሄዱ። |
“በዚያን ጊዜ ይሖዋ፣ የይሖዋን የቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከም፣ ይሖዋን ለማገልገል በፊቱ እንዲቆምና እስከ ዛሬ እንደሚያደርገው በስሙ እንዲባርክ የሌዊን ነገድ ለየ። |
ሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ለዚህ ነው። አምላክህ ይሖዋ በነገረው መሠረት ይሖዋ ርስቱ ነው። |
እኔም እንደ መጀመሪያው ጊዜ ሁሉ በተራራው ላይ ለ40 ቀንና ለ40 ሌሊት ቆየሁ፤ በዚህ ጊዜም ደግሞ ይሖዋ ሰማኝ። ይሖዋ ሊያጠፋህ አልፈለገም። |
ከዚያም ይሖዋ ‘ለአባቶቻቸው ለመስጠት የማልኩላቸውን ምድር ገብተው እንዲወርሱ ተነስና ከሕዝቡ ፊት ፊት ሂድ’ አለኝ። |
“እንግዲህ እስራኤል ሆይ፣ አምላክህ ይሖዋ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን ይሖዋን እንድትፈራው፣ በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄድ፣ እንድትወደው፣ አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ እንድታገለግለው |
እንዲሁም ለገዛ ጥቅምህ ስትል እኔ ዛሬ የማዝህን የይሖዋን ትእዛዛትና ደንቦች እንድትጠብቅ ብቻ ነው። |
እነሆ ሰማያት፣ ሌላው ቀርቶ ሰማየ ሰማያት እንዲሁም ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ የአምላክህ የይሖዋ ናቸው። |
ይሁንና ይሖዋ የቀረበውና ፍቅሩን የገለጸው ለአባቶችህ ብቻ ነው፤ ስለሆነም ይኸው ዛሬ እንደሆነው የእነሱ ዘር የሆናችሁትን እናንተን ከሕዝቦች ሁሉ መካከል መረጠ። |
ስለዚህ ልባችሁን አንጹ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ግትር መሆናችሁን ተዉ። |
ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ የአማልክት አምላክና የጌቶች ጌታ እንዲሁም ታላቅ፣ ኃያል፣ የሚያስፈራ፣ ለማንም የማያዳላና ጉቦ የማይቀበል አምላክ ነው። |
አባት ለሌለው ልጅና ለመበለት ይፈርዳል፤ እንዲሁም የባዕድ አገሩን ሰው ይወደዋል፤ ምግብና ልብስም ይሰጠዋል። |
እናንተም የባዕድ አገሩን ሰው ውደዱ፤ ምክንያቱም በግብፅ ምድር ሳላችሁ የባዕድ አገር ሰው ነበራችሁ። |
“አምላክህን ይሖዋን ፍራ፤ አገልግለው፤ ከእሱም ጋር ተጣበቅ፤ በስሙም ማል። |
ልታወድሰው የሚገባህ እሱን ነው። እሱ በዓይኖችህ ያየሃቸውን እነዚያን ታላላቅና አስፈሪ ነገሮች ሁሉ ያደረገልህ አምላክህ ነው። |
አባቶችህ ወደ ግብፅ ሲወርዱ 70 ነበሩ፤ አሁን ግን አምላክህ ይሖዋ በሰማያት ላይ እንዳሉ ከዋክብት ቁጥርህን አብዝቶታል። |
“አምላክህ ይሖዋ ከግብፅ በሌሊት ያወጣህ በአቢብ ወር ስለሆነ የአቢብን ወር አስብ፤ እንዲሁም ለአምላክህ ለይሖዋ ፋሲካን አክብር። |
ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በመረጠው ስፍራ ከመንጋህና ከከብትህ ለአምላክህ ለይሖዋ የፋሲካን መባ ሠዋ። |
ከእሱም ጋር እርሾ የገባበት ምንም ነገር አትብላ፤ ከግብፅ ምድር የወጣኸው በጥድፊያ ስለነበር ለሰባት ቀን ቂጣ ይኸውም የመከራ ቂጣ ብላ። ይህን የምታደርገው ከግብፅ ምድር የወጣህበትን ዕለት በሕይወት ዘመንህ ሁሉ እንድታስታውስ ነው። |
ለሰባት ቀን በግዛትህ ሁሉ እርሾ አይገኝ፤ በመጀመሪያው ቀን ምሽት ላይ ከምታቀርበው መሥዋዕት ላይም ቢሆን ምንም ሥጋ ማደር የለበትም። |
የፋሲካውን መባ አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ከተሞች አንተ በፈለግከው በአንዱ ውስጥ መሠዋት አይገባህም። |
ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ መቅረብ ይኖርበታል። የፋሲካውን መባ ምሽት ላይ ፀሐይ እንደጠለቀች፣ ከግብፅ በወጣህበት በዚያው ጊዜ ሠዋው። |
አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ቦታ አብስለህ ብላው፤ ሲነጋም ተመልሰህ ወደ ድንኳንህ መሄድ ትችላለህ። |
ለስድስት ቀን ቂጣ ብላ፤ በሰባተኛውም ቀን ለአምላክህ ለይሖዋ የተቀደሰ ጉባኤ ይሆናል። ምንም ሥራ አትሥራ። |
“ሰባት ሳምንት ቁጠር። በማሳህ ላይ ያለውን እህል ለማጨድ ማጭድህን ካነሳህበት ጊዜ አንስቶ ሰባት ሳምንት ቁጠር። |
ከዚያም አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን በምታቀርበው የፈቃደኝነት መባ አማካኝነት ለአምላክህ ለይሖዋ የሳምንታት በዓልን ታከብራለህ። |
በአምላክህ በይሖዋ ፊት ደስ ይበልህ፤ አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖር ሌዋዊ፣ በመካከልህ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው፣ አባት የሌለው ልጅና መበለቲቱ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በመረጠው ስፍራ ደስ ይበላችሁ። |
አንተም በግብፅ ባሪያ እንደነበርክ አስታውስ፤ እነዚህንም ሥርዓቶች ጠብቅ እንዲሁም ፈጽም። |
“እህልህን ከአውድማህ፣ ዘይትህንና የወይን ጠጅህን ከመጭመቂያህ በምታስገባበት ጊዜ የዳስ በዓልን ለሰባት ቀን አክብር። |
በዓልህን በምታከብርበት ወቅት ደስ ይበልህ፤ አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህ፣ ሴት ባሪያህ እንዲሁም በከተሞችህ ውስጥ የሚኖር ሌዋዊ፣ የባዕድ አገር ሰው፣ አባት የሌለው ልጅና መበለቲቱ ደስ ይበላችሁ። |
አምላክህ ይሖዋ ምርትህንና የእጅህን ሥራ ሁሉ ስለሚባርክልህ ይሖዋ በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለይሖዋ ሰባት ቀን በዓሉን ታከብራለህ፤ አንተም እጅግ ትደሰታለህ። |
“በመካከልህ ያሉ ወንዶች ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ ይኸውም በቂጣ በዓል ቀን፣ በሳምንታት በዓል ቀን እንዲሁም በዳስ በዓል ቀን አምላክህ ይሖዋ በመረጠው ስፍራ ፊቱ ይቅረቡ፤ ማናቸውም ባዶ እጃቸውን ይሖዋ ፊት አይቅረቡ። |
እያንዳንዱ ሰው የሚያመጣው ስጦታ አምላክህ ይሖዋ በባረከህ መጠን መሆን አለበት። |
“አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለእያንዳንዱ ነገድ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነሱም ለሕዝቡ የጽድቅ ፍርድ ይፍረዱ። |
ፍርድን አታዛባ፤ አድልዎ አትፈጽም ወይም ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ የጥበበኞችን ዓይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማል። |
በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ ይሖዋ የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ ፍትሕን፣ አዎ ፍትሕን ተከታተል። |
“ለአምላክህ ለይሖዋ በምትሠራው መሠዊያ አጠገብ የማምለኪያ ግንድ እንዲሆን ማንኛውንም ዓይነት ዛፍ አትትከል። |
“አምላክህ ይሖዋ አጥብቆ የሚጠላውን የማምለኪያ ዓምድ ለራስህ አታቁም። |
ከዚያም ሙሴ እስራኤላውያንን በሙሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እስራኤላውያን፣ በዛሬው ዕለት የምነግራችሁን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ስሙ፤ እወቋቸው፤ በጥንቃቄም ፈጽሟቸው። |
አምላካችን ይሖዋ በኮሬብ ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን ገብቷል። |
ይሖዋ ይህን ቃል ኪዳን የገባው ከአባቶቻችን ጋር ሳይሆን ዛሬ በሕይወት እዚህ ካለነው ከእኛ ከሁላችን ጋር ነው። |
ይሖዋ በተራራው ላይ በእሳት ውስጥ ሆኖ ከእናንተ ጋር ፊት ለፊት ተነጋገረ። |
በዚያ ወቅት እኔ የይሖዋን ቃል ለእናንተ ለመንገር በይሖዋና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር፤ ምክንያቱም እናንተ ከእሳቱ የተነሳ ፈርታችሁ ወደ ተራራው አልወጣችሁም። እሱም እንዲህ አለ፦ |
“‘ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እኔ አምላክህ ይሖዋ ነኝ። |
ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ። |
“‘በላይ በሰማያት ወይም በታች በምድር አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ባለ በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸ ቅርጽም ሆነ የተሠራ ምስል ለራስህ አታብጅ። |
ለእነሱ አትስገድ፤ አታገልግላቸውም፤ ምክንያቱም እኔ አምላክህ ይሖዋ እኔ ብቻ እንድመለክ የምፈልግና በሚጠሉኝ ሁሉ ላይ በአባቶች ስህተት የተነሳ በልጆቻቸው እንዲሁም በሦስተኛና በአራተኛ ትውልዶቻቸው ላይ ቅጣት የማመጣ አምላክ ነኝ፤ |
ሆኖም ለሚወዱኝና ትእዛዛቴን ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ታማኝ ፍቅር የማሳይ አምላክ ነኝ። |
“‘የአምላክህን የይሖዋን ስም በከንቱ አታንሳ፤ ምክንያቱም ይሖዋ ስሙን በከንቱ የሚያነሳውን ሳይቀጣ አይተወውም። |
“‘አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት ቅዱስ አድርገህ ትጠብቀው ዘንድ የሰንበትን ቀን አክብር። |
ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀን ትሠራለህ፤ |
ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው። በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ በሬህም ሆነ አህያህ ወይም ማንኛውም የቤት እንስሳህ አሊያም በከተሞችህ ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው ምንም ሥራ አትሥሩ፤ ይህም አንተ እንደምታርፈው ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ እንዲያርፉ ነው። |
አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ በብርቱ እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ እንዳወጣህ አስታውስ። አምላክህ ይሖዋ የሰንበትን ቀን እንድታከብር ያዘዘህ ለዚህ ነው። |
“‘አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንልህ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት አባትህንና እናትህን አክብር። |
“‘አትግደል። |
“‘አታመንዝር። |
“‘አትስረቅ። |
“‘በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመሥክር። |
“‘የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ። የባልንጀራህን ቤት፣ እርሻውን፣ ወንድ ባሪያውን፣ ሴት ባሪያውን፣ በሬውን፣ አህያውን ወይም የባልንጀራህ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትመኝ።’ |
“ይሖዋ በተራራው ላይ በእሳቱ መካከል በደመናውና በድቅድቅ ጨለማው ውስጥ ሆኖ እነዚህን ትእዛዛት ከፍ ባለ ድምፅ ለመላው ጉባኤያችሁ ተናገረ፤ ከእነዚህም ሌላ ምንም አልጨመረም፤ ከዚያም እነዚህን በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጽፎ ሰጠኝ። |
“ይሁን እንጂ ተራራው በእሳት እየነደደ ሳለ ከጨለማው ውስጥ ድምፅ ሲወጣ ስትሰሙ የነገድ መሪዎቻችሁና ሽማግሌዎቹ በሙሉ ወደ እኔ መጡ። |
ከዚያም እንዲህ አላችሁ፦ ‘ይኸው አምላካችን ይሖዋ ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፤ ድምፁንም ከእሳቱ ውስጥ ሰምተናል። አምላክ ከሰው ጋር መነጋገር እንደሚችልና ያም ሰው በሕይወት ሊኖር እንደሚችል በዛሬው ቀን አይተናል። |
ታዲያ አሁን ለምን እንሙት? ምክንያቱም ይህ ታላቅ እሳት ሊበላን ይችላል። የአምላካችንን የይሖዋን ድምፅ መስማት ከቀጠልን እንደምንሞት የተረጋገጠ ነው። |
ለመሆኑ ከሥጋ ሁሉ መካከል ልክ እኛ እንደሰማነው ሕያው የሆነው አምላክ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር ሰምቶ በሕይወት የኖረ ማን አለ? |
አንተው ራስህ ቀርበህ አምላካችን ይሖዋ የሚናገረውን ሁሉ ስማ፤ ከዚያም አምላካችን ይሖዋ የነገረህን ሁሉ ትነግረናለህ፤ እኛም እንሰማለን፤ ደግሞም የተባልነውን እናደርጋለን።’ |
“ከዚያም ይሖዋ ያላችሁኝን ነገር ሰማ፤ ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ ‘ይህ ሕዝብ ምን እንዳለህ ሰምቻለሁ። የተናገሩት ነገር ሁሉ መልካም ነው። |
ምንጊዜም እኔን የሚፈራና ትእዛዛቴን ሁሉ የሚጠብቅ ልብ ቢኖራቸው ምናለ፤ እንዲህ ቢሆን ለእነሱም ሆነ ለልጆቻቸው ለዘላለም መልካም ይሆንላቸው ነበር! |
ሂድና “ወደየድንኳናችሁ ተመለሱ” በላቸው። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.