text stringlengths 4 267 |
|---|
እሱም ነገሥታታቸውን በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ አንተም ስማቸውን ከሰማይ በታች ትደመስሳለህ። ድምጥማጣቸውን እስክታጠፋ ድረስ ማንም አይቋቋምህም። |
የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች በእሳት አቃጥሉ። ወጥመድ ሊሆንብህ ስለሚችል በእነሱ ላይ ያለውን ብርም ሆነ ወርቅ አትመኝ ወይም ለራስህ አትውሰድ፤ ምክንያቱም ይህ በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነገር ነው። |
አስጸያፊ ነገር ወደ ቤትህ በማምጣት ልክ እንደ እሱ ራስህን ለጥፋት አትዳርግ። ለጥፋት የተለየ ነገር ስለሆነ ፈጽመህ ጥላው፤ ሙሉ በሙሉም ተጸየፈው። |
“በሰዎች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር ሰዎቹ ዳኞች ፊት መቅረብ ይችላሉ፤ እነሱም ይዳኟቸዋል፤ ጻድቅ የሆነውን ንጹሕ፣ ጥፋተኛ የሆነውን ደግሞ በደለኛ ይሉታል። |
ጥፋተኛው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ ዳኛው መሬት ላይ እንዲያስተኙትና እሱ ባለበት እንዲገረፍ ያደርጋል። የግርፋቱም ቁጥር ከሠራው ጥፋት ጋር የሚመጣጠን ይሁን። |
እስከ 40 ግርፋት ሊገርፈው ይችላል፤ ከዚያ ማስበለጥ ግን የለበትም። ከዚህ የበለጠ ብዙ ግርፋት ከገረፈው ግን ወንድምህ በፊትህ ይዋረዳል። |
“እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር። |
“ወንድማማቾች አንድ ላይ ሲኖሩ ቆይተው ከመካከላቸው አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት የሟቹ ሚስት ከቤተሰቡ ውጭ የሆነ ሰው ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ወደ እሷ በመሄድ ሚስቱ አድርጎ ይውሰዳት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት። |
መጀመሪያ የምትወልደው ልጅ በሟች ወንድሙ ስም ይጠራል፤ ይህ የሚሆነው የሟቹ ስም ከእስራኤል መካከል እንዳይጠፋ ነው። |
“ሰውየው የሟች ወንድሙን ሚስት ለማግባት ፈቃደኛ ካልሆነ መበለት የሆነችው ሴት በከተማዋ በር ወደሚገኙት ሽማግሌዎች ሄዳ ‘የባሌ ወንድም የወንድሙ ስም ከእስራኤል መካከል እንዳይጠፋ ለማድረግ ፈቃደኛ አልሆነም። የዋርሳነት ግዴታውን ሊፈጽምልኝ አልተስማማም’ ትበላቸው። |
የከተማዋ ሽማግሌዎችም ጠርተው ያናግሩት። እሱም ‘እኔ እሷን ማግባት አልፈልግም’ ብሎ በሐሳቡ ከጸና |
የወንድሙ ሚስት በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እሱ ቀርባ ጫማውን ከእግሩ ላይ ታውልቅ፤ ከዚያም ፊቱ ላይ ትትፋበትና ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ የሚደረግበት እንዲህ ነው’ ትበል። |
ከዚያ በኋላ የዚያ ሰው ቤተሰብ ስም በእስራኤል ውስጥ ‘ጫማው የወለቀበት ሰው ቤት’ ይባላል። |
“ሁለት ሰዎች ቢደባደቡና የአንደኛው ሚስት ባሏን ከደብዳቢው እጅ ለማስጣል ስትል እጇን ዘርግታ ብልቱን ብትይዝ |
እጇን ቁረጠው። ልታዝንላት አይገባም። |
“በከረጢትህ ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት ዓይነት የሚዛን ድንጋዮች አይኑሩህ። |
በቤትህም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት ዓይነት መስፈሪያዎች አይኑሩህ። |
አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም ትክክለኛና ሐቀኛ ሚዛን እንዲሁም ትክክለኛና ሐቀኛ መስፈሪያ ይኑርህ። |
ምክንያቱም እንዲህ ያሉ ነገሮችን በማድረግ ፍትሕ የጎደለው ድርጊት የሚፈጽም ሰው ሁሉ በአምላክህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው። |
“ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ መንገድ ላይ ሳላችሁ አማሌቃውያን ያደረጉባችሁን ነገር አስታውሱ፤ |
በጉዞ ላይ ሳለህ ደክመህና ዝለህ በነበረበት ጊዜ አግኝተውህ ከኋላ ከኋላህ እያዘገሙ በነበሩት ሁሉ ላይ እንዴት ጥቃት እንደሰነዘሩ አስታውስ። አምላክንም አልፈሩም። |
አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርገህ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር ላይ አምላክህ ይሖዋ በዙሪያህ ካሉት ጠላቶችህ ሁሉ በሚያሳርፍህ ጊዜ አማሌቃውያንን ከሰማይ በታች ጨርሶ እንዳይታወሱ አድርገህ ጠራርገህ አጥፋቸው። ይህን አትርሳ። |
“አንድ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ከመካከልህ ተነስቶ ተአምራዊ ምልክት ወይም ድንቅ ነገር እንደሚያሳይ ቢነግርህና |
የነገረህ ተአምራዊ ምልክት ወይም ድንቅ ነገር ቢፈጸም፣ እሱም ‘ሌሎች አማልክትን ይኸውም አንተ የማታውቃቸውን አማልክት እንከተል፤ እናገልግላቸውም’ ቢልህ፣ |
የዚያን ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቃል እንዳትሰማ፤ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ትወዱት እንደሆነና እንዳልሆነ ለማወቅ እየፈተናችሁ ነው። |
እናንተ አምላካችሁን ይሖዋን ተከተሉ፤ እሱን ፍሩ፤ ትእዛዛቱን ጠብቁ፤ ቃሉን ስሙ፤ እሱን አገልግሉ፤ እንዲሁም እሱን አጥብቃችሁ ያዙ። |
ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ግን ይገደል፤ ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ እንድትሄዱበት ካዘዛችሁ መንገድ ዞር እንድትሉ፣ ከግብፅ ምድር ባወጣችሁና ከባርነት ቤት በታደጋችሁ በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ እንድታምፁ አበረታቷችኋል። አንተም ክፉውን ከመካከልህ አስወግድ። |
“የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ አሊያም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ጓደኛህ ‘ሌሎች አማልክትን እናምልክ’ በማለት በሚስጥር ሊያባብልህ ቢሞክርና እነዚህ አማልክት ደግሞ አንተም ሆንክ አባቶችህ የማታውቋቸው |
እንዲሁም በቅርብም ሆነ በሩቅ፣ ከአንዱ የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው የምድር ጫፍ የሚገኙ በዙሪያህ ያሉ ሕዝቦች የሚያመልኳቸው አማልክት ቢሆኑ |
እሺ አትበለው ወይም አትስማው አሊያም አትዘንለት ወይም ደግሞ አትራራለት፤ ከለላም አትሁነው፤ |
ከዚህ ይልቅ ያለማመንታት ግደለው። እሱን ለመግደል መጀመሪያ እጅህን መሰንዘር ያለብህ አንተ ነህ፤ ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ እጁን ይሰንዝርበት። |
ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣህ ከአምላክህ ከይሖዋ ዞር እንድትል ሊያደርግህ ስለሞከረ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው። |
ከዚያም እስራኤላውያን ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ በመካከልህም እንዲህ ያለ መጥፎ ነገር ዳግመኛ አያደርጉም። |
“አምላክህ ይሖዋ እንድትኖርባቸው ከሚሰጥህ ከተሞች በአንዱ ውስጥ እንዲህ ሲባል ትሰማ ይሆናል፦ |
‘እናንተ የማታውቋቸውን “ሌሎች አማልክት ሄደን እናምልክ” እያሉ የከተማቸውን ነዋሪዎች ለማሳት የሚሞክሩ የማይረቡ ሰዎች ከመካከልህ ተነስተዋል’፤ |
በዚህ ጊዜ ጉዳዩን በጥልቀት በመመርመርና በማጣራት ስለ ሁኔታው ማወቅ ይኖርብሃል፤ ይህ አስጸያፊ ነገር በመካከልህ ተፈጽሞ ከሆነና ነገሩ እውነት መሆኑ ከተረጋገጠ |
የከተማዋን ነዋሪዎች በሰይፍ ግደላቸው። እንስሶቿን ጨምሮ ከተማዋንና በውስጧ ያለውን ነገር ሁሉ በሰይፍ ሙሉ በሙሉ አጥፋ። |
ከዚያም በከተማዋ ውስጥ የተገኘውን ምርኮ በሙሉ በአደባባይዋ ላይ ሰብስብ፤ ከተማዋን በእሳት አቃጥል፤ በውስጧ የተገኘው ምርኮ ደግሞ ለአምላክህ ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቀርብ መባ ይሆናል። እሷም ለዘላለም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች። ፈጽሞ ተመልሳ አትገነባም። |
ይሖዋ ከሚነድ ቁጣው እንዲመለስ፣ ለአባቶችህ በማለላቸው መሠረት ምሕረት እንዲያደርግልህና እንዲራራልህ እንዲሁም እንዲያበዛህ ከፈለግክ፣ እንዲጠፉ ከተለዩት ነገሮች መካከል እጅህ ምንም አይውሰድ። |
እኔ ዛሬ የምሰጥህን የእሱን ትእዛዛት በሙሉ በመጠበቅ አምላክህን ይሖዋን ታዘዝ፤ በዚህ መንገድ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ታደርጋለህ። |
“አምላክህ ይሖዋ እንድትወርሳት በሚሰጥህ ምድር አንድ ሰው ሜዳ ላይ ተገድሎ ቢገኝና ማን እንደገደለው ባይታወቅ |
ሽማግሌዎችህና ዳኞችህ ወጥተው የሞተው ሰው ከተገኘበት ስፍራ አንስቶ በዙሪያው እስከሚገኙት ከተሞች ድረስ ያለውን ርቀት ይለኩ። |
ከዚያም የሞተው ሰው ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ምንም ሥራ ያልተሠራባትንና ቀንበር ተጭኖባት የማያውቅን ጊደር ከከብቶች መካከል ይውሰዱ፤ |
የከተማዋም ሽማግሌዎች ጊደሯን ከዚህ ቀደም ታርሶ ወይም ዘር ተዘርቶበት ወደማያውቅ ወራጅ ውኃ ወዳለበት ሸለቆ ይውሰዷት፤ በሸለቆውም ውስጥ የጊደሯን አንገት ይስበሩ። |
“ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ ይቅረቡ፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ እሱን እንዲያገለግሉና በይሖዋ ስም እንዲባርኩ የመረጠው እነሱን ነው። ደግሞም የኃይል ጥቃትን በተመለከተ ለሚነሳ ለማንኛውም ክርክር እልባት የሚሰጡት እነሱ ናቸው። |
ከዚያም የሞተው ሰው ለተገኘበት ስፍራ ቅርብ የሆኑት የከተማዋ ሽማግሌዎች በሙሉ በሸለቆው ውስጥ አንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ፤ |
እንዲህ ብለውም ይናገሩ፦ ‘እጆቻችን ይህን ደም አላፈሰሱም፤ ዓይኖቻችንም ይህ ደም ሲፈስ አላዩም። |
ይሖዋ ሆይ፣ የታደግከውን ሕዝብህን እስራኤልን በዚህ ድርጊት ተጠያቂ አታድርገው፤ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የተፈጸመ በደልም በሕዝብህ በእስራኤል መካከል እንዲኖር አትፍቀድ።’ እነሱም በደም ዕዳው ተጠያቂ አይሆኑም። |
በዚህ መንገድ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የተፈጸመን በደል ከመካከልህ በማስወገድ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ። |
“ከጠላቶችህ ጋር ብትዋጋ፣ አምላክህ ይሖዋም እነሱን በእጅህ አሳልፎ ቢሰጥህ፣ አንተም ምርኮኛ አድርገህ ብትወስዳቸውና |
ከምርኮኞቹ መካከል አንዲት የምታምር ሴት አይተህ ብትወዳት፣ ሚስትህም ልታደርጋት ብትፈልግ |
ወደ ቤትህ ልትወስዳት ትችላለህ። እሷም ፀጉሯን ትላጭ፤ ጥፍሯንም ትቁረጥ፤ |
የምርኮኛነት ልብሷን ታውልቅ፤ በቤትህም ትቀመጥ። ለአባቷና ለእናቷ አንድ ወር ሙሉ ታልቅስ፤ ከዚህ በኋላ ከእሷ ጋር ግንኙነት መፈጸም ትችላለህ፤ አንተ ባሏ ትሆናለህ፤ እሷም ሚስትህ ትሆናለች። |
በእሷ ካልተደሰትክ ግን ወደፈለገችበት እንድትሄድ አሰናብታት። ሆኖም ለውርደት ስለዳረግካት በገንዘብ ልትሸጣት ወይም ግፍ ልትፈጽምባት አይገባም። |
“አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩትና አንደኛዋን ከሌላኛዋ አስበልጦ የሚወዳት ቢሆን፣ ሁለቱም ወንዶች ልጆች ቢወልዱለትና በኩሩ የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን |
ውርሱን ለወንዶች ልጆቹ በሚያስተላልፍበት ቀን ከማይወዳት ሚስቱ የተወለደውን በኩር የሆነውን ወንድ ልጅ ትቶ ከሚወዳት ሚስቱ የተወለደውን ወንድ ልጅ እንደ በኩር ልጁ አድርጎ መቁጠር የለበትም። |
ከዚህ ይልቅ ከማይወዳት ሚስቱ ለተወለደው ወንድ ልጅ፣ ካለው ከማንኛውም ነገር ላይ ሁለት እጥፍ በመስጠት የልጁን ብኩርና መቀበል ይኖርበታል፤ ምክንያቱም የጎልማሳነቱ ብርታት መጀመሪያ ይህ ልጅ ነው። የብኩርና መብቱ የእሱ ነው። |
“አንድ ሰው እልኸኛና ዓመፀኛ ልጅ ቢኖረው ልጁም አባቱንም ሆነ እናቱን ለመታዘዝ አሻፈረኝ ቢል፣ እነሱም እርማት ሊሰጡት ቢሞክሩና እሱ ግን ሊሰማቸው ፈቃደኛ ባይሆን |
አባትና እናቱ እሱ ባለበት ከተማ በር ላይ ወዳሉት ሽማግሌዎች ያምጡት፤ |
ሽማግሌዎቹንም ‘ይህ ልጃችን እልኸኛና ዓመፀኛ ነው፤ ሊታዘዘንም ፈቃደኛ አይደለም። ሆዳምና ሰካራም ነው’ ይበሏቸው። |
ከዚያም የከተማዋ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት። በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ይህን ሰምተው ይፈራሉ። |
“አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ሠርቶ ቢገደልና በእንጨት ላይ ብትሰቅለው |
በድኑ በእንጨቱ ላይ አይደር። ከዚህ ይልቅ በዚያው ዕለት ቅበረው፤ ምክንያቱም እንጨት ላይ የሚሰቀለው፣ አምላክ የረገመው ነው፤ አንተም አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር አታርክስ። |
“ከዚያም ተመልሰን ወደ ባሳን የሚወስደውን መንገድ ይዘን ወጣን። የባሳን ንጉሥ ኦግም ከሕዝቡ ሁሉ ጋር በመሆን ኤድራይ ላይ ጦርነት ሊገጥመን ወጣ። |
በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እሱንም ሆነ ሕዝቡን ሁሉ እንዲሁም ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥህ አትፍራው፤ አንተም በሃሽቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግከው ሁሉ በእሱም ላይ ታደርግበታለህ።’ |
ስለዚህ አምላካችን ይሖዋ የባሳንን ንጉሥ ኦግንና ሕዝቡን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጠን፤ እኛም ከሕዝቡ መካከል አንድም ሰው ሳናስቀር ሁሉንም ደመሰስን። |
ከዚያም ከተሞቹን በሙሉ ያዝን። ከእነሱ ያልወሰድነው አንድም ከተማ አልነበረም፤ በባሳን ባለው በኦግ መንግሥት ሥር የሚገኘውን የአርጎብን ክልል በሙሉ ይኸውም 60 ከተሞችን ወሰድን። |
እነዚህ ከተሞች በሙሉ በረጃጅም ቅጥሮች የታጠሩ እንዲሁም በሮችና መቀርቀሪያዎች ያሏቸው ነበሩ፤ ከእነዚህም በተጨማሪ በጣም ብዙ የገጠር ከተሞች ነበሩ። |
ሆኖም እያንዳንዱን ከተማ እንዲሁም ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን በማጥፋት በሃሽቦን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግነው ሁሉ እነዚህንም ሙሉ በሙሉ ደመሰስናቸው። |
ከብቶቹንና ከየከተማው የማረክናቸውን ነገሮች ሁሉ ለራሳችን ወሰድን። |
“በዚያን ጊዜም ከአርኖን ሸለቆ አንስቶ እስከ ሄርሞን ተራራ ድረስ ባለው በዮርዳኖስ ክልል ከነበሩት ከሁለቱ የአሞራውያን ነገሥታት እጅ ምድራቸውን ወሰድን፤ |
(ሲዶናውያን የሄርሞንን ተራራ ሲሪዮን ብለው ሲጠሩት አሞራውያን ደግሞ ሰኒር ብለው ይጠሩት ነበር፤) |
በባሳን ባለው በኦግ መንግሥት ሥር የሚገኙትን ከተሞች ይኸውም በአምባው ላይ የሚገኙትን ከተሞች በሙሉ፣ ጊልያድን በሙሉ፣ ባሳንን በሙሉ እስከ ሳልካ ድረስ እንዲሁም ኤድራይን ወሰድን። |
ከረፋይም ወገን የተረፈው የባሳን ንጉሥ ኦግ ብቻ ነበር። ቃሬዛው እንኳ የብረት ቃሬዛ ነበር፤ አሁንም የአሞናውያን ከተማ በሆነችው በራባ ይገኛል። በሰው ክንድ ሲለካ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ስፋቱ ደግሞ አራት ክንድ ነበር። |
በዚያን ጊዜ ይህችን ምድር ወረስን፤ በአርኖን ሸለቆ አጠገብ ከምትገኘው ከአሮዔር አንስቶ ያለውን ምድር እንዲሁም የጊልያድን ተራራማ አካባቢ እኩሌታ ከነከተሞቹ ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን ሰጠኋቸው። |
የቀረውን የጊልያድን ክፍልና በኦግ ግዛት ሥር ያለውን ባሳንን በሙሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ። የባሳን ይዞታ የሆነው የአርጎብ አካባቢ በሙሉ የረፋይም ምድር ተብሎ ይጠራ ነበር። |
“የምናሴ ልጅ ያኢር የአርጎብን ክልል በሙሉ እስከ ገሹራውያን እና እስከ ማአካታውያን ወሰን ድረስ ያለውን ወሰደ፤ በባሳን የሚገኙትን እነዚህን መንደሮች በራሱ ስም ሃዎትያኢር ብሎ ሰየማቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ የሚጠሩት በዚህ ስም ነው። |
ጊልያድን ደግሞ ለማኪር ሰጠሁት። |
ለሮቤላውያንና ለጋዳውያን የአርኖንን ሸለቆ መሃል ወሰን በማድረግ ከጊልያድ አንስቶ እስከ አርኖን ሸለቆ ድረስ እንዲሁም የአሞናውያን ወሰን እስከሆነው ሸለቆ ማለትም እስከ ያቦቅ ድረስ ሰጠኋቸው፤ |
እንዲሁም ከኪኔሬት አንስቶ በአረባ እስከሚገኘው ባሕር ይኸውም በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ በጲስጋ ሸንተረር ግርጌ እስከሚገኘው እስከ ጨው ባሕር ድረስ ያለውን አረባን፣ ዮርዳኖስንና ወሰኑን ሰጠኋቸው። |
“ከዚያም ይህን ትእዛዝ ሰጠኋችሁ፦ ‘አምላካችሁ ይሖዋ ይህችን ምድር ርስት አድርጋችሁ እንድትወርሷት ሰጥቷችኋል። ብርቱ የሆናችሁት ወንዶች ሁሉ የጦር መሣሪያችሁን ታጥቃችሁ በወንድሞቻችሁ በእስራኤላውያን ፊት ትሻገራላችሁ። |
ሚስቶቻችሁ፣ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ ብቻ (መቼም ብዙ ከብቶች እንዳሏችሁ አውቃለሁ) በሰጠኋችሁ ከተሞች ውስጥ ይቀራሉ፤ |
ይህም ይሖዋ ልክ ለእናንተ እንዳደረገላችሁ ሁሉ ለወንድሞቻችሁም እረፍት እስኪሰጣቸው እንዲሁም አምላካችሁ ይሖዋ ከዮርዳኖስ ማዶ የሚሰጣቸውን ምድር ርስት አድርገው እስኪወርሱ ድረስ ነው። ከዚያ በኋላ እያንዳንዳችሁ ወደሰጠኋችሁ ወደየራሳችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።’ |
“በዚያን ጊዜ ለኢያሱ ይህን ትእዛዝ ሰጠሁት፦ ‘አምላክህ ይሖዋ በእነዚህ ሁለት ነገሥታት ላይ ያደረገውን ሁሉ በገዛ ዓይንህ አይተሃል። ይሖዋ አልፈሃቸው በምትሄደው መንግሥታት ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጋል። |
ስለ እናንተ የሚዋጋው አምላካችሁ ይሖዋ ስለሆነ አትፍሯቸው።’ |
“እኔም በዚያን ጊዜ ይሖዋን እንዲህ በማለት ተማጸንኩት፦ |
‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አገልጋይህ ታላቅነትህንና ብርቱ ክንድህን እንዲያይ አድርገሃል፤ አንተ እንደምታደርጋቸው ያሉ ታላላቅ ነገሮችን መፈጸም የሚችለው በሰማይም ሆነ በምድር ያለ የትኛው አምላክ ነው? |
እባክህ ከዮርዳኖስ ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር፣ አዎ ውብ የሆነችውን ይህችን ተራራማ አካባቢና ሊባኖስን ተሻግሬ እንዳይ ፍቀድልኝ።’ |
ይሖዋ ግን በእናንተ የተነሳ በጣም ተቆጥቶኝ ስለነበር አልሰማኝም። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘በቃ! ዳግመኛ ስለዚህ ጉዳይ እንዳታነሳብኝ። |
ይህን ዮርዳኖስን ስለማትሻገር ወደ ጲስጋ አናት ውጣና ዓይንህን አቅንተህ ወደ ምዕራብ፣ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ ተመልከት። |
በዚህ ሕዝብ ፊት የሚሻገረውም ሆነ አንተ ያየሃትን ምድር እንዲወርሱ የሚያደርገው ኢያሱ ስለሆነ እሱን መሪ አድርገህ ሹመው፤ አደፋፍረው፤ አበረታታውም።’ |
ይህ ሁሉ የሆነው በቤትጰኦር ፊት ለፊት በሚገኘው ሸለቆ ውስጥ በነበርንበት ጊዜ ነው። |
“ይህ ቃል ሁሉ ይኸውም በፊትህ ያስቀመጥኩት በረከትና እርግማን በአንተ ላይ በሚመጣበትና አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ባደረገህ ብሔራት ምድር ሆነህ ይህን ቃል ሁሉ በምታስታውስበት ጊዜ |
እንዲሁም አንተም ሆንክ ልጆችህ እኔ ዛሬ በማዝህ ትእዛዝ ሁሉ መሠረት በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ ይሖዋ በምትመለሱበትና ቃሉን በምትሰሙበት ጊዜ |
አምላክህ ይሖዋ ተማርከው የተወሰዱብህን ይመልስልሃል፤ ምሕረትም ያሳይሃል፤ እንዲሁም አምላክህ ይሖዋ በመካከላቸው እንድትበተን ካደረገህ ሕዝቦች ምድር ሁሉ መልሶ ይሰበስብሃል። |
ሕዝብህ እስከ ሰማያት ዳርቻ ድረስ ቢበተን እንኳ አምላክህ ይሖዋ ከዚያ ይሰበስብሃል፤ ከዚያም መልሶ ያመጣሃል። |
አምላክህ ይሖዋ አባቶችህ ወርሰዋት ወደነበሩት ምድር ያስገባሃል፤ አንተም ትወርሳታለህ፤ እሱም ከአባቶችህ ይበልጥ ያበለጽግሃል፤ እንዲሁም ያበዛሃል። |
በሕይወትም ትኖር ዘንድ አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህና በሙሉ ነፍስህ እንድትወደው አምላክህ ይሖዋ ልብህን እንዲሁም የልጆችህን ልብ ያነጻል። |
ከዚያም አምላክህ ይሖዋ እነዚህን እርግማኖች ሁሉ በሚጠሉህና በሚያሳድዱህ ጠላቶችህ ላይ ያመጣል። |
“አንተም ተመልሰህ የይሖዋን ቃል ትሰማለህ፤ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዛቱን ሁሉ ትፈጽማለህ። |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.