text
stringlengths
4
267
ይሖዋ በዚያው ዕለት ሙሴን እንዲህ አለው፦
“በኢያሪኮ ትይዩ በሞዓብ ምድር ወደሚገኘው ወደዚህ የአባሪም ተራራ ይኸውም ወደ ነቦ ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነአንን ምድር ተመልከት።
ወንድምህ አሮን በሆር ተራራ ላይ ሞቶ ወደ ወገኖቹ እንደተሰበሰበ ሁሉ አንተም በምትወጣበት በዚህ ተራራ ላይ ትሞታለህ፤ ወደ ወገኖችህም ትሰበሰባለህ፤
ምክንያቱም ሁለታችሁም በጺን ምድረ በዳ በሚገኘው በቃዴስ፣ በመሪባ ውኃዎች አጠገብ በእስራኤላውያን መካከል ለእኔ ታማኝ ሆናችሁ አልተገኛችሁም፤ እንዲሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት እኔን አልቀደሳችሁኝም።
ምድሪቱን ከሩቅ ታያታለህ፤ ሆኖም ለእስራኤል ሕዝብ ወደምሰጣት ምድር አትገባም።”
“አሁንም እስራኤል ሆይ፣ በሕይወት እንድትኖሩና የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ የሚሰጣችሁን ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፣ ትጠብቋቸው ዘንድ የማስተምራችሁን ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች አዳምጡ።
እኔ የማዛችሁን የአምላካችሁን የይሖዋን ትእዛዛት ጠብቁ፤ በምሰጣችሁ ትእዛዝ ላይ ምንም ነገር አትጨምሩ፤ ከዚያም ላይ ምንም አትቀንሱ።
“ይሖዋ ከፌጎር ባአል ጋር በተያያዘ ምን እንዳደረገ በገዛ ዓይናችሁ አይታችኋል፤ አምላክህ ይሖዋ የፌጎርን ባአል የተከተለውን እያንዳንዱን ሰው ከመካከልህ አጥፍቶታል።
አምላካችሁን ይሖዋን የሙጥኝ ያላችሁት እናንተ ሁላችሁ ግን ይኸው ዛሬም በሕይወት አላችሁ።
እኔም አምላኬ ይሖዋ ባዘዘኝ መሠረት ሥርዓቶችንና ድንጋጌዎችን ያስተማርኳችሁ በምትወርሷት ምድር ውስጥ እንድትጠብቋቸው ነው።
እነዚህንም በጥንቃቄ ጠብቋቸው፤ ፈጽሟቸውም፤ እንዲህ ብታደርጉ ስለ እነዚህ ሥርዓቶች ሁሉ በሚሰሙ ሕዝቦች ፊት እንደ ጥበበኞችና እንደ አስተዋዮች ትቆጠራላችሁ፤ እነሱም ‘ይህ ታላቅ ብሔር በእርግጥም ጥበበኛና አስተዋይ ሕዝብ ነው’ ይላሉ።
በምንጠራው ጊዜ ሁሉ ለእኛ ቅርብ እንደሆነው እንደ አምላካችን እንደ ይሖዋ፣ ለእሱ ቅርብ የሆኑ አማልክት ያሉት ታላቅ ብሔር የትኛው ነው?
ዛሬ በፊታችሁ እንዳስቀመጥኩት እንደዚህ ሕግ ያለ የጽድቅ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች ያሉት የትኛው ታላቅ ብሔር ነው?
“ዓይኖቻችሁ ያዩአቸውን ነገሮች እንዳትረሱና በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ ከልባችሁ እንዳይጠፉ ተጠንቀቁ፤ ራሳችሁንም ጠብቁ። እነዚህንም ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ንገሯቸው።
በኮሬብ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት በቆማችሁበት ቀን ይሖዋ ‘በምድር ላይ በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩና ልጆቻቸውንም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን እንዲሰሙ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ’ ብሎኝ ነበር።
“በመሆኑም እናንተ መጥታችሁ በተራራው ግርጌ ቆማችሁ፤ ተራራውም እስከ ሰማያት ድረስ እየነደደ ነበር፤ ጨለማ፣ ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ሆኖ ነበር።
ይሖዋም ከእሳቱ ውስጥ ያነጋግራችሁ ጀመር። እናንተም ድምፅ ከመስማት በስተቀር መልክ አላያችሁም፤ የሰማችሁት ድምፅ ብቻ ነበር።
እሱም እንድትጠብቁት ያዘዛችሁን ቃል ኪዳኑን ይኸውም አሥርቱን ትእዛዛት ገለጸላችሁ። ከዚያም በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው።
በዚያን ጊዜ ይሖዋ፣ ገብታችሁ በምትወርሷት ምድር የምትፈጽሟቸውን ሥርዓቶችና ደንቦች እንዳስተምራችሁ አዘዘኝ።
“በመሆኑም ይሖዋ በኮሬብ በእሳቱ መካከል ሆኖ ባነጋገራችሁ ቀን ምንም መልክ ስላላያችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤
ይኸውም ምግባረ ብልሹ በመሆን በማንኛውም ነገር አምሳል የተቀረጸን የትኛውንም ዓይነት ምስል፣ የወንድ ወይም የሴት ምስል፣
በምድር ላይ ያለን የማንኛውንም እንስሳ ምስል ወይም በሰማይ ላይ የሚበርን የማንኛውንም ወፍ ምስል፣
መሬት ለመሬት የሚሄድን የማንኛውንም ነገር ምስል አሊያም ከምድር በታች በውኃ ውስጥ ያለን የማንኛውንም ዓሣ ምስል ለራሳችሁ እንዳትሠሩ ነው።
እንዲሁም ዓይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ ፀሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ይኸውም የሰማይን ሠራዊት በሙሉ በምታይበት ጊዜ ተታለህ እንዳትሰግድላቸውና እንዳታገለግላቸው። እነዚህ አምላክህ ይሖዋ ከሰማይ በታች ላሉ ሕዝቦች ሁሉ የሰጣቸው ናቸው።
እናንተን ግን ልክ እንደ ዛሬው ሁሉ ይሖዋ የእሱ የግል ንብረት እንድትሆኑ የብረት ማቅለጫ ምድጃ ከሆነችው ከግብፅ አውጥቶ አመጣችሁ።
“ይሖዋ በእናንተ የተነሳ እኔን ተቆጣኝ፤ ዮርዳኖስን እንደማልሻገርም ሆነ አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደ መልካሚቱ ምድር እንደማልገባ ማለ።
እንግዲህ እኔ የምሞተው በዚህ አገር ነው፤ ዮርዳኖስን አልሻገርም፤ እናንተ ግን ተሻግራችሁ ይህችን መልካም ምድር ትወርሳላችሁ።
አምላካችሁ ይሖዋ ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ እንዲሁም አምላካችሁ ይሖዋ የከለከላችሁን የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስል ለራሳችሁ እንዳትሠሩ ተጠንቀቁ።
ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ የሚባላ እሳት፣ እሱ ብቻ እንዲመለክ የሚፈልግ አምላክ ነው።
“ልጆችና የልጅ ልጆች ስታፈሩ፣ በምድሪቱም ላይ ረጅም ዘመን ስትኖሩ፣ የጥፋት ጎዳና ወደመከተል ዞር ብትሉና የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስል ብትሠሩ እንዲሁም በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ክፉ ነገር በመፈጸም እሱን ብታስቆጡት
ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትወርሷት ምድር ያለጥርጥር ወዲያውኑ እንደምትደመሰሱ በዚህ ቀን ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምሥክር አድርጌ እጠራባችኋለሁ። በምድሪቱ ላይ ረጅም ዘመን ከመኖር ይልቅ ሙሉ በሙሉ ትደመሰሳላችሁ።
ይሖዋም በሕዝቦች መካከል ይበትናችኋል፤ ይሖዋ በሚበትናችሁ ብሔራትም መካከል ጥቂቶቻችሁ ብቻ ትተርፋላችሁ።
እዚያም ማየትም ሆነ መስማት፣ መብላትም ሆነ ማሽተት የማይችሉ በሰው እጅ የተሠሩ የእንጨትና የድንጋይ አማልክትን ታገለግላላችሁ።
“እዚያ ሆናችሁ አምላካችሁን ይሖዋን ብትፈልጉት፣ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ነፍሳችሁ ብትሹት በእርግጥ ታገኙታላችሁ።
ከጊዜ በኋላ ከባድ ጭንቀት ውስጥ ስትገባና እነዚህ ሁሉ ነገሮች በአንተ ላይ ሲደርሱ ያኔ ወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ትመለሳለህ፤ ድምፁንም ትሰማለህ።
ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ መሐሪ አምላክ ነው። አይተውህም፣ አያጠፋህም ወይም ለአባቶችህ በመሐላ ያጸናላቸውን ቃል ኪዳን አይረሳም።
“እንግዲህ ከአንተ ዘመን በፊት ስለነበሩት ስለ ቀደሙት ጊዜያት ይኸውም አምላክ ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ቀን አንስቶ ስላለው ዘመን ጠይቅ፤ ከአንዱ የሰማይ ጥግ እስከ ሌላኛው የሰማይ ጥግ ድረስ እስቲ መርምር። እንዲህ ያለ እጅግ ታላቅ ነገር ተደርጎ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ተሰምቶ ያውቃል?
ልክ እንደ አንተ፣ አምላክ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሰማና በሕይወት የኖረ ሌላ ሕዝብ አለ?
ወይስ አምላካችሁ ይሖዋ የገዛ ዓይኖቻችሁ እያዩ ለእናንተ በግብፅ እንዳደረገው ሁሉ በፍርድ እርምጃዎች፣ ድንቅ በሆኑ ምልክቶች፣ በተአምራት፣ በጦርነት፣ በብርቱ እጅ፣ በተዘረጋ ክንድና አስፈሪ በሆኑ ሥራዎች ከሌላ ብሔር መካከል ለራሱ ብሔር ለመውሰድ ሞክሯል?
እውነተኛው አምላክ፣ ይሖዋ መሆኑን ታውቅ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እንድታይ ተደርገሃል፤ ከእሱ ሌላ ማንም የለም።
አንተን ለማረም ከሰማያት ድምፁን እንድትሰማ አደረገህ፤ በምድርም ላይ የእሱን ታላቅ እሳት እንድታይ አደረገህ፤ ድምፁንም ከእሳቱ ውስጥ ሰማህ።
“እሱ አባቶችህን ስለወደደና ከእነሱ በኋላ የሚመጣውን ዘራቸውን ስለመረጠ ከአንተ ጋር በመሆን በታላቅ ኃይሉ ከግብፅ አወጣህ።
እንዲሁም ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ወደ ምድራቸው ሊያስገባህና ምድራቸውን ርስት አድርጎ ሊሰጥህ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ኃያል የሆኑትን ብሔራት ከፊትህ አባረራቸው።
እንግዲህ በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር እውነተኛው አምላክ፣ ይሖዋ እንደሆነ ዛሬ እወቅ፤ እንዲሁም ልብ በል። ሌላ ማንም የለም።
ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁና አምላክህ ይሖዋ በሚሰጥህ ምድር ላይ ለረጅም ዘመን እንድትኖር እኔ ዛሬ የማዝህን የእሱን ሥርዓትና ትእዛዛት ጠብቅ።”
በዚያን ጊዜ ሙሴ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ሦስት ከተሞችን ለየ።
ነፍስ ያጠፋ ማንኛውም ግለሰብ ባልንጀራውን የገደለው ሆን ብሎ ካልሆነና የቆየ ጥላቻ ካልነበረው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ በዚያ መኖር ይችላል።
ከተሞቹም ለሮቤላውያን በአምባው ላይ ባለው ምድረ በዳ የምትገኘው ቤጼር፣ ለጋዳውያን በጊልያድ የምትገኘው ራሞት እንዲሁም ለምናሴያውያን በባሳን ያለችው ጎላን ናቸው።
ሙሴ በእስራኤል ሕዝብ ፊት ያስቀመጠው ሕግ ይህ ነው።
እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ሙሴ የሰጣቸው ማሳሰቢያዎች፣ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤
ይህን የነገራቸው በዮርዳኖስ ክልል ከቤትጰኦር ባሻገር በሚገኘው ሸለቆ ይኸውም ሙሴና እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ ድል ባደረጉት በሃሽቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ምድር ነበር።
እነሱም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ባለው ክልል የነበሩትን የሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት ምድር ማለትም የሲሖንን ምድርና የባሳንን ንጉሥ የኦግን ምድር ወረሱ፤
ይህም ምድር በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከሚገኘው ከአሮዔር አንስቶ እስከ ሲዎን ተራራ ይኸውም እስከ ሄርሞን ድረስ ያለውን አካባቢ ይሸፍናል፤
እንዲሁም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን የአረባን ምድርና በጲስጋ ሸንተረር ግርጌ እስከሚገኘው እስከ አረባ ባሕር ድረስ ያለውን አካባቢ ይጨምራል።
“ከጠላቶችህ ጋር ጦርነት ለመግጠም ብትሄድና ፈረሶቻቸው፣ ሠረገሎቻቸውና ሠራዊታቸው ከአንተ ይልቅ እጅግ ብዙ መሆናቸውን ብታይ አትፍራቸው፤ ምክንያቱም ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ነው።
ወደ ውጊያው ለመግባት በምትቀርቡበትም ጊዜ ካህኑ መጥቶ ሕዝቡን ማነጋገር አለበት።
እንዲህም ይበላቸው፦ ‘እስራኤላውያን ሆይ፣ ስሙ፤ እንግዲህ ዛሬ ከጠላቶቻችሁ ጋር ጦርነት ልትገጥሙ ነው። ልባችሁ አይራድ። በእነሱ ምክንያት አትፍሩ፣ አትሸበሩ ወይም አትንቀጥቀጡ፤
ምክንያቱም አምላካችሁ ይሖዋ ጠላቶቻችሁን ሊዋጋላችሁና ሊያድናችሁ አብሯችሁ ይወጣል።’
“አለቆቹም ሕዝቡን እንዲህ ይበሉ፦ ‘ከመካከላችሁ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለ? ወደ ቤቱ ይመለስ። አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ቤቱን ሌላ ሰው ሊያስመርቀው ይችላል።
ወይን ተክሎ ገና ከዚያ ያልበላ አለ? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ሌላ ሰው ሊበላው ይችላል።
አንዲት ሴት አጭቶ ገና ያላገባት ሰው አለ? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ። አለዚያ በጦርነቱ ላይ ሊሞትና ሌላ ሰው ሊያገባት ይችላል።’
በተጨማሪም አለቆቹ ለሕዝቡ እንዲህ በማለት ይናገሩ፦ ‘ከመካከላችሁ የፈራና ልቡ የራደ አለ? ልክ እንደ ራሱ ልብ የወንድሞቹንም ልብ እንዳያቀልጥ ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ።’
አለቆቹም ለሕዝቡ ተናግረው ሲጨርሱ ሕዝቡን እንዲመሩ የሠራዊቱን አለቆች ይሹሙ።
“አንዲትን ከተማ ለመውጋት ወደ እሷ ስትቀርብ ለከተማዋ የሰላም ጥሪ አስተላልፍ።
ከተማዋ የሰላም ጥሪህን ከተቀበለችና በሯን ከከፈተችልህ ነዋሪዎቿ ሁሉ የግዳጅ ሥራ የሚሠሩ ሕዝቦች ይሆኑልሃል፤ አንተንም ያገለግሉሃል።
ይሁን እንጂ የሰላም ጥሪህን ካልተቀበለችና ከአንተ ጋር ውጊያ ለመግጠም ከተነሳች ከተማዋን ክበባት፤
አምላክህ ይሖዋ ከተማዋን በእጅህ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ አንተም በውስጧ የሚኖሩትን ወንዶች ሁሉ በሰይፍ ግደላቸው።
ሆኖም ሴቶቹን፣ ትናንሽ ልጆቹን፣ እንስሳቱንና በከተማዋ ውስጥ የተገኘውን ነገር ሁሉ ማርከህ ለራስህ መውሰድ ትችላለህ፤ አምላክህ ይሖዋ በእጅህ አሳልፎ የሰጠህን ከጠላቶችህ ያገኘኸውን ምርኮም ትበላለህ።
“በአቅራቢያህ የሚገኙት ብሔራት ከተሞች ባልሆኑ ከአንተ ርቀው በሚገኙ ከተሞች ሁሉ ላይ የምታደርገው ይህንኑ ነው።
አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ እነዚህ ሕዝቦች በሚኖሩባቸው ከተሞች ውስጥ ግን እስትንፋስ ያለውን ማንኛውንም ነገር በሕይወት አታስቀር።
ከዚህ ይልቅ አምላክህ ይሖዋ ባዘዘህ መሠረት ሂታውያንን፣ አሞራውያንን፣ ከነአናውያንን፣ ፈሪዛውያንን፣ ሂዋውያንንና ኢያቡሳውያንን ሙሉ በሙሉ አጥፋ፤
ይህን የምታደርጉት ለአማልክታቸው የሚያደርጓቸውን አስጸያፊ ነገሮች በሙሉ እንዳያስተምሯችሁና በአምላካችሁ በይሖዋ ላይ ኃጢአት እንድትሠሩ እንዳያደርጓችሁ ነው።
“አንዲትን ከተማ ከበህ ከብዙ ቀናት ውጊያ በኋላ በቁጥጥርህ ሥር ብታውላት ዛፎቿን በመጥረቢያ አትጨፍጭፍ። ፍሬያቸውን ልትበላ ትችላለህ፤ ሆኖም አትቁረጣቸው። ደግሞስ ሰው ይመስል የሜዳን ዛፍ ከበህ ማጥፋት አለብህ?
ለምግብነት እንደማይሆን የምታውቀውን ዛፍ ብቻ ማጥፋት ትችላለህ። ዛፉንም ቆርጠህ ከአንተ ጋር ውጊያ የገጠመችው ከተማ እስክትወድቅ ድረስ ዙሪያዋን ልታጥርበት ትችላለህ።
“የአባቶቻችሁ አምላክ ይሖዋ እንድትወርሷት በሚሰጣችሁ ምድር ላይ በሕይወት በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ በጥንቃቄ ልትፈጽሟቸው የሚገቡ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው።
ከምድራቸው የምታስለቅቋቸው ብሔራት አማልክታቸውን ያመልኩባቸው የነበሩትን ቦታዎች በሙሉ፣ በረጃጅም ተራሮችም ሆነ በኮረብቶች ላይ ወይም በተንዠረገጉ ዛፎች ሥር ያሉትን ስፍራዎች ሙሉ በሙሉ አጥፉ።
መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን አድቅቁ፤ የማምለኪያ ግንዶቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች ሰባብራችሁ ጣሉ፤ ስማቸውንም ከዚያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ ደምስሱ።
“እነሱ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት መንገድ አምላካችሁን ይሖዋን አታምልኩ።
ከዚህ ይልቅ በነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ስሙን ሊያጸናበትና ማደሪያ ስፍራው ሊያደርገው በሚመርጠው በማንኛውም ቦታ አምላካችሁን ይሖዋን ፈልጉ፤ ወደዚያም ስፍራ ሂዱ።
የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን፣ መሥዋዕቶቻችሁን፣ አሥራቶቻችሁን፣ ከእጃችሁ የሚዋጣውን መዋጮ፣ የስእለት መባዎቻችሁን፣ የፈቃደኝነት መባዎቻችሁን እንዲሁም የከብታችሁንና የመንጋችሁን በኩራት የምትወስዱት ወደዚያ ስፍራ ነው።
እናንተም ሆናችሁ ቤተሰቦቻችሁ በዚያ በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ብሉ፤ አምላካችሁ ይሖዋ ስለባረካችሁ በሥራችሁ ሁሉ ተደሰቱ።
“ዛሬ እዚህ እያደረግን እንዳለነው እያንዳንዳችሁ በራሳችሁ አመለካከት ትክክል መስሎ የታያችሁን ማድረግ የለባችሁም፤
ምክንያቱም አሁን ይህን የምታደርጉት ወደምታርፉበት ቦታና አምላካችሁ ይሖዋ ወደሚሰጣችሁ ርስት ገና ስላልገባችሁ ነው።
ዮርዳኖስን በምትሻገሩበትና አምላካችሁ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ላይ በምትኖሩበት ጊዜ በዙሪያችሁ ካሉ ጠላቶቻችሁ ሁሉ ያሳርፋችኋል፤ እናንተም ያለስጋት ትቀመጣላችሁ።
የማዛችሁንም ነገር በሙሉ ይኸውም የሚቃጠሉ መባዎቻችሁን፣ መሥዋዕቶቻችሁን፣ አሥራቶቻችሁን፣ የእጃችሁን መዋጮና ለይሖዋ የተሳላችሁትን ማንኛውንም የስእለት መባ አምላካችሁ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ታመጣላችሁ።
እናንተ፣ ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ሴቶች ልጆቻችሁ፣ ወንድ ባሪያዎቻችሁ፣ ሴት ባሪያዎቻችሁ እንዲሁም በከተሞቻችሁ ውስጥ የሚኖሩ ሌዋውያን በአምላካችሁ በይሖዋ ፊት ትደሰታላችሁ፤ ምክንያቱም ሌዋውያኑ በእናንተ መካከል ድርሻም ሆነ ውርሻ የላቸውም።
የሚቃጠሉ መባዎችህን በፈለግከው በየትኛውም ቦታ እንዳታቀርብ ተጠንቀቅ።
ከዚህ ይልቅ የሚቃጠሉ መባዎችህን ይሖዋ በሚመርጠው የነገዶችህ ይዞታ በሆነው ቦታ ብቻ አቅርብ፤ በዚያም እኔ የማዝህን ነገር ሁሉ አድርግ።
“አምላክህ ይሖዋ በሰጠህ በረከት መጠን በከተሞችህ ሁሉ አንተን ባሰኘህ በማንኛውም ጊዜ እንስሳትን አርደህ ሥጋ መብላት ትችላለህ። የሜዳ ፍየልና ርኤም እንደምትበላ ሁሉ ንጹሕ ያልሆነውም ሆነ ንጹሕ የሆነው ሰው ሊበላው ይችላል።
ደሙን ግን እንዳትበሉ፤ ከዚህ ይልቅ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍሱት።
የእህልህን፣ የአዲሱን የወይን ጠጅህንና የዘይትህን አንድ አሥረኛ፣ የከብትህንና የመንጋህን በኩር፣ የምትሳለውን ማንኛውንም የስእለት መባ፣ የፈቃደኝነት መባዎችህን ወይም የእጅህን መዋጮ በከተሞችህ ውስጥ እንድትበላ አይፈቀድልህም።
እነዚህንም አንተ፣ ወንድ ልጅህ፣ ሴት ልጅህ፣ ወንድ አገልጋይህ፣ ሴት አገልጋይህ እንዲሁም በከተሞችህ የሚኖሩ ሌዋውያን አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ትበሏቸዋላችሁ፤ አንተም በሥራህ ሁሉ በአምላክህ በይሖዋ ፊት ትደሰታለህ።
በምድርህ ላይ በሕይወት እስካለህ ድረስ ሌዋውያንን ቸል እንዳትል ተጠንቀቅ።
“አምላክህ ይሖዋ ቃል በገባልህ መሠረት ግዛትህን በሚያሰፋልህ ጊዜ ሥጋ መብላት ፈልገህ ‘ሥጋ አማረኝ’ ብትል ባሰኘህ ጊዜ ሁሉ ሥጋ ብላ።
አምላክህ ይሖዋ ስሙ እንዲኖርበት የሚመርጠው ስፍራ አንተ ካለህበት የራቀ ከሆነ ይሖዋ ከሰጠህ ከከብትህ ወይም ከመንጋህ መካከል እኔ ባዘዝኩህ መሠረት አርደህ ባሰኘህ ጊዜ ሁሉ በከተሞችህ ውስጥ ብላ።
የሜዳ ፍየልንና ርኤምን እንደምትበላው ሁሉ ይህንም ልትበላው ትችላለህ፤ ንጹሕ ያልሆነውም ሆነ ንጹሕ የሆነው ሰው ሊበላው ይችላል።
ብቻ ደሙን እንዳትበሉ ተጠንቀቁ፤ ምክንያቱም ደም ሕይወት ነው፤ ሕይወትን ደግሞ ከሥጋ ጋር መብላት የለብህም።
ደሙን ፈጽሞ እንዳትበላ። ከዚህ ይልቅ እንደ ውኃ መሬት ላይ አፍስሰው።
ደሙን አትብላ፤ ምክንያቱም እንዲህ ስታደርግ በይሖዋ ፊት ትክክል የሆነውን ነገር ትፈጽማለህ፤ ይህን የምታደርገው ለአንተም ሆነ ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችህ መልካም እንዲሆንላችሁ ነው።
ይሖዋ ወደሚመርጠው ስፍራ ስትመጣ የአንተ የሆኑትን ቅዱስ ነገሮችና የስእለት መባዎችህን ብቻ መያዝ ይኖርብሃል።